በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት/Hulbarag wereda Justice Office

በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት/Hulbarag wereda Justice Office ፍትህ የሠላማችን መሠረት ነው!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ6ኛው የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በመዝገብ ቁጥር 150 በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የ...
05/08/2026

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ6ኛው የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በመዝገብ ቁጥር 150 በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ሰው፣ የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
​አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ (ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢሆን) ቤት ቢሠራ፣ የመሬቱ ባለይዞታነት ወይም የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም።
​የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው ሰው እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት አይደለም።
​ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ መብት ለቤቱ/ለግንባታው ያወጣውን ወጪ (ግምት) ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ ነው።
​በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት የሰጣቸውን የቀደሙ አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ናቸው በማለት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።

ሐምሌ 28/2018የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የተቋሙ ሰራተኞችን የዕውቅና ሰርተፍኬትና ማበረታቻ ሽልማት በመስጠት አትግቷል...
04/08/2026

ሐምሌ 28/2018
የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የተቋሙ ሰራተኞችን የዕውቅና ሰርተፍኬትና ማበረታቻ ሽልማት በመስጠት አትግቷል።

በመርሐግብሩ የተገኙት የተቋሙ ኃላፊና የወረዳው ም/ል አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አወል፥ የተቋም ውጤት በቅንጅትና በቲም መንፈስ በመስራት የሁሉም ሰራተኛ ውጤት እንደሆነ በመግለፅ በዚህ ሂደት ላይ በሁለት ግማሽ ዓመት አማካይ ውጤት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡና በሌሎችም መስፈርቶች ከ1ኛ-3ኛ ደረጃ ላስመዘገቡ እንዲሁም 01 በልዩ ተሸላሚ ሆነው እንዲተጉ ጽ/ቤቱ መወሰኑን ተናግረዋል።

የማትግያው ዋና ዓላማ የተሻለ ለፈጸሙት ሠራተኞች ዕውቅና መስጠትና ሌሎች ያልተሸለሙ ሰራተኞች በቀጣይ ቁጭት ተፈጥሮባቸው የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ተሸላሚ እንዲሆኑ ከማነሳሳትም ባሻገር ለተቋም ግንባታ የጎላ ሚና አንዳለው አስረድተዋል።

በፕሮግራሙ በክብር እንግድነት ተገኝተው ማትግያውን ለተሸላሚዎች ያበረከቱት የሁልባራግ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ባለሙያ አቶ ያየህራድ አሻግሬ በበኩላቸው ማትጊያ ፕሮግራሙ በወቅቱ መደረጉ ያለፈውን ዓመት ተግባራትን በጊዜ ዘግቶ ወደቀጣዩ ምዕራፍ ለመሸጋገር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

01/08/2026
የሴቶችንና የህጻናት መብት ለማስከበርና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።ሐምሌ 14 /2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴበስልጤ ዞን የ...
21/07/2026

የሴቶችንና የህጻናት መብት ለማስከበርና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።

ሐምሌ 14 /2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ሴቶችና የፍትህ አካላት የጋራ ፎረም የ2018 ዓ.ም የ12ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።

በመድረኩ የፎረሙ አባል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ12 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም የሴቶችና ህጻናት ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማስከበርና የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት ባሻገር ፣ የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ እና የሴቶች ንጽሕና መጠበቅያ ቁሳቁሶች ተደራሽነት አንጻር የተሠሩ ስራዎች አበረታች እንደሆኑ ተገምግሟል።

የሴቶችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለማስከበር በፍርድ ቤትና በፍትህ ጽ/ቤት በተደረገላቸው የህግ ድጋፍ በወንጀልና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ለ66 አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንብረት ባለቤትነት፣ የጉዳት ካሳ፣ የልጅ ቀለብ መብትና ሌሎች ተጨባጭ የሴቶችን መብት የማስከበር ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።

በሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት በኩልም 22 ለጋብቻ ፍቺ የተካሰሱ ሴቶች ጉዳያቸው በእርቅ እንድያልቅ መደረጉ አና ሁለንተናዊ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
ከጤና ጋር ተያይዞ ከቅድመ ወሊድ ክትትል አንፃር በአራቱም ጤና ጣቢያዎች 3348 እናቶች በቅርበት በአልትራሳውንድ የተደገፈ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ እና ከማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ጋር የተጀመሩ ስራዎችና በከተማው የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አምራች ግለሰቦችን ማበረታታቱ በጥንካሬ ተገምግሟል።

ከትምህርት ተቋማት ጋር ተያይዞም የንጽህና መጠበቂያ ክፍሎችን ማዘጋትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ማቅረብ:የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፎች መደረጋቸውንና ለሴት ተማሪዎች 5321 ሰዓት ልዩ ድጋፍ ትምህርት እንደተሰጠተም በመድረኩ ተወስቷል።

ፍትህ ተቋማትን በተመለከተም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከማስከበር አንጻር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተቀምጧል።

መድረኩን የመሩት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ አወል በበኩላቸው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት በመሰራቱ ወጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው ይህ ስራ በቀጣይ ዓመት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም የ2019 ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ውይይቱ ተጠናቋል።

መረጃው የሁልባራግ ወ/መ/ኮሙኒኬሽን ነው!

ይህ ፅሁፍ ስለፍትህ እመቤት/madam justice / በቀድሞ የፌደራል ሰበር ዳኛ እና አሁን ታዋቂ ጠበቃ Almaw Wolie  የተሰጠ ግሩ ም ማብራሪያ ነው።ይነበብ👇ቀደም ባሉት ጊዜያት ትኩረ...
18/07/2026

ይህ ፅሁፍ ስለፍትህ እመቤት/madam justice / በቀድሞ የፌደራል ሰበር ዳኛ እና አሁን ታዋቂ ጠበቃ Almaw Wolie የተሰጠ ግሩ ም ማብራሪያ ነው።ይነበብ👇

ቀደም ባሉት ጊዜያት ትኩረቴን ረጅም እና ውስብስብ በሆኑ የህግ ትንተናዎች ላይ አድርጌ ከቆየሁ በኋላ፣ አንዳንድ ጊዜ ቀለል ያሉ፣ አጫጭር እና ማራኪ ወደሆኑ መሰረታዊ የህግ ጥያቄዎች መመለስ መልካም እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ። በዚህም መሰረት፣ ይህ አጭር ጽሑፍ በፍትህ እመቤት ሰይፍ ተምሳሌትነት ዙሪያ ያለውን ፍልስፍናዊ ይዘት በአጭሩ እና በግልጽ ለመዳሰስ የቀረበ ነው።

የፍትህ እመቤት ሰይፍ ድርብ ስለት

በአልማው ወሌ
11/11/2018
1. መግቢያ

የፍትህ እመቤት (Madam Justice) ምስላዊ መግለጫዎች በህግ ፍልስፍና እና በዳኝነት ታሪክ ውስጥ ስር የሰደዱ ተምሳሌቶች ናቸው። ዓይኖቿን የሸፈነው ጨርቅ የገለልተኝነትን እና ከማዳላት የጸዳ መሆንን ሲያመለክት፣ በእጇ የያዘችው ሚዛን ደግሞ የእውነታዎችን እና የክርክሮችን ሚዛናዊ ምርመራ ያሳያል። ሆኖም ግን፣ በሦስተኛው መሣሪያዋ፤ በሰይፉ፣ ላይ የሚነሱት ፍልስፍናዊ ጥያቄዎች እና ትንተናዎች በታዋቂ የህግ ሊቃውንት እና ንድፈ-ሀሳቦች መካከል ሰፊ የክርክር መድረክ ፈጥረዋል። ይህ አጭር ጽሑፍ በታዋቂ ባለስልጣናት እይታዎች እና በማሻሻያ ፍትህ (Ameliorative Justice) እሳቤዎች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጥናት የሰይፉን ተምሳሌትነት በአካዳሚያዊ እና በሙያዊ ትንተና መልሶ ይገነባል።

2. የመንግስት አስገዳጅነት እና የአምባገንነት ተምሳሌት፡- ባህላዊ እና ታዋቂ የህግ ምሁራን እይታ

በታሪክ እና በህግ ፍልስፍና ረገድ የፍትህ ሰይፍ የመንግስት ሉዓላዊነት፣ አስገዳጅ ሀይል እና የቅጣት ስልጣን ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቷል። ይህ እይታ በበርካታ ታዋቂ የህግ ምሁራን ስራዎች ውስጥ ይንጸባረቃል። ለምሳሌ፣ ጀርመናዊው የህግ ንድፈ-ሀሳብ ምሁር ሩዶልፍ ፎን ጄሪንግ “The Struggle for Law” በተሰኘው ታዋቂ ስራው የሰይፉን እና የሚዛኑን የማይነጣጠል ትስስር ሲገልጽ፣ ሚዛን የሌለው ሰይፍ ጥሬ ሀይል ሲሆን፣ ሰይፍ የሌለው ሚዛን ደግሞ የህግ አቅም-ቢስነትን እንደሚያሳይ ያስረዳል። ለጄሪንግ ህግ በባህሪው የትግል ውጤት ነው፤ ህግ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው አስገዳጅ ሀይል (ሰይፉ) ሲታከልበት ብቻ በመሆኑ ሰይፉ የህግ አስፈጻሚነት ህያው ምስክር ነው።

በተመሳሳይ መልኩ፣ በእንግሊዛዊው ፈላስፋ ቶማስ ሆብስ የፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ፣ የመንግስት አስገዳጅ ሀይል የህግ ህልውና መሰረት ነው። ሆብስ “Leviathan” በተሰኘው ስራው ሰይፍ የሌላቸው ቃል-ኪዳኖች ባዶ ቃላት እንደሆኑና ሰውን የመጠበቅ ምንም ዓይነት አቅም እንደሌላቸው ይገልጻል። ይህ እሳቤ የህግን አስገዳጅነት ከሰይፍ ተምሳሌት ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ሲሆን፣ ህጋዊ ውሎች እና ግዴታዎች ዋጋ የሚኖራቸው ከበስተጀርባው የመንግስት አስገዳጅ ሀይል ሲኖር ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል።

ይህንን የሆብስ እና የጄሪንግን እይታ በመከተል፣ ታዋቂው እንግሊዛዊ ዳኛ ሎርድ ዴኒንግ “The Closing Chapter” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ሰይፉ ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎቻቸውን ለማስፈጸም የሚጠቀሙበት የመንግስት አስገዳጅ ስልጣን ተምሳሌት መሆኑን ገልጿል ። በእሱ እይታ፣ የትኛውም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከበስተጀርባው የመንግስት አስገዳጅ ሀይል ከሌለ ዋጋ-ቢስ ነው። በጥንታዊው የሮማውያን ህግ አውድ ውስጥ የሰይፍ መብት/ስልጣን ተብሎ የሚታወቀው እሳቤም፣ ገዢዎች ወይም ዳኞች በወንጀለኞች ላይ የሞት ፍርድን ጨምሮ የማስገደድ እና የመቅጣት የበላ

03/07/2026

ዜና ችሎት

በሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ወንጀል የተከሰሰው ረዳት ኢንስፔክተር ቃሲም ሀደም የእስር ቅጣት ተወሰነበት።

ሰኔ 26/10/2018 ዓ/ም
የዳሎቻ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን

በዳሎቻ ወረዳ ዳሎቻ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ነዋሪ በሆኑዉ ረዳት ኢንስፔክተር ቃሲም አደም ላለምዳ ላይ የቀረበውን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ወንጀል ክስ ሲመለከት የቆየው የዳሎቻ ወረዳ ፍርድ ቤት በተከሳሹ ላይ የአንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) እስራት ውሳኔ አስተላለፈ።

ተከሳሹ ረዳት ኢንስፔክተር ቃሲም አደም በ2012 ዓ.ም የወጣውን የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል መፈጸሙ ተገልጿል። በተለይም በአዋጁ አንቀጽ 4፣ አንቀጽ 5 እንዲሁም አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (3) ስር የተመለከቱትን ክልከላዎች በመጣስ፣ በዳሎቻ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ ያነጣጠረ የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ሲያሰራጭ እንደነበር በወረዳው ዐቃቤ ህግ የቀረበው ክስ ያስረዳል።

የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን ማስረጃዎች ሲመረምር የቆየው የዳሎቻ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ ተከሳሹ የቀረበበትን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በማረጋገጥ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ቅጣት ተከሳሹን ያርማል፣ ሌሎችንም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ላይ እንዳይሰማሩ ያስተምራል በማለት ተከሳሹ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!!

የዳሎቻ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ የመንግሥት ሀብት ማስመለሱንና በምርመራ መዛግብት ላይ የ100% ውሳኔ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አስታወቀ   ሰኔ 24/2018 : ወ...
01/07/2026

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ የመንግሥት ሀብት ማስመለሱንና በምርመራ መዛግብት ላይ የ100% ውሳኔ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አስታወቀ

ሰኔ 24/2018 : ወራቤ

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ባጠናቀቀው የ 2018 የበጀት ዓመት 12 ባከናወነው የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ሥራ፣ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ የመንግሥት ገንዘብ ማስመለሱን እና በምርመራ መዛግብት አፈጻጸም ታይቶ የማይታወቅ የ100 በመቶ ስኬት ማስመዝገቡን አስታወቀ።

መምሪያው የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት የውይይት መድረክ እንደተገለጸው፤ እስከ ስር መዋቅር ያሉ የተቋሙ ዓቃቤያን ህግ እና ሌሎች ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብ የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ምዝበራን በመከላከል ረገድ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሬድዋን ኑሪ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘበረ ሀብትና ንብረት አመላለስ ላይ የተሠራው ሥራ በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ትልቅ አሻራ የጣለ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት በተለያዩበፍትሐ ብሔር የሙስና እና በታክስ እና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ተመዝብሮ የነበረ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ገንዘብ በሕግ አግባብ ተጣርቶ ወደ መንግሥት ካዝና እንዲመለስ ተደርጓል።
ሌላው በሪፖርቱ በልዩ ስኬትነት የተነሳው የወንጀል ምርመራ መዝገቦች አፈጻጸም ነው። በዓመቱ ለዐቃቤ ሕግ የቀረቡ የወንጀል ምርመራ መዛግብትን በማጥራትና ውሳኔ በመስጠት ሂደት፣ ተቋሙ ከምግዜውም ግዜ በተሻለ መልኩ በሁሉም (100 በመቶ) መዛግብት ላይ ፈጣንና ሕጋዊ ውሳኔ መስጠት መቻሉ ተገልጿል።

ይህ አፈጻጸም የተገልጋዮችን እንግልት በእጅጉ የቀነሰና የፍትህ ሥርዓቱን ተአማኒነት ያሳደገ እርምጃ መሆኑ ተብራርቷል።

እነዚህ አመርቂ ስኬቶች ሊመዘገቡ የቻሉት በዋናነት "በቅንጅታዊ አሠራር" መሆኑን ኃላፊው አጽንዖት ሰጥተው አንስተዋል። የፍትህ መምሪያው ከፖሊስ፣ ከፍርድ ቤቶች፣ ከተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እና ከማኅበረሰቡ ጋር በፈጠረው ጠንካራ የሥራ ትስስርና የመግባቢያ ሰነድ፣ ሌብነትን ለመከላከልና ወንጀልን በፍጥነት ለማጣራት መቻሉ ተጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪም በንቃተ ህግ ሥራ ዘርፍ ላይ በዓመቱ ውስጥ በሁሉም የማስተማሪያ ዘዴዎች ከ 730ሺ በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መሰራቱ ተመልክቷል::

ከሰነድ ማረጋገጥ እና የጠበቆች ክትትል ሥራ : ከሕገ ወጥ የሠዎች ዝውውር ወንጀል መከላከል እና ከሴቶች እና ሕፃናት ጥቃት ጋር ተያይዞ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ለውጦች መምጣታቸውን ኃላፊው አንስተዋል::

በመጨረሻም መምሪያው ይህንን በበጀት ዓመቱ የተገኘውን ትልቅ ስኬት እንደ ጠንካራ መሠረት (እርሾ) በመውሰድ፣ በቀጣይም የሕግ የበላይነትን ይበልጥ ለማረጋገጥና ማኅበረሰቡን በላቀ ደረጃ ለማገልገል መጠነ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት በእቅድ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል::

{ በአብደላ ከድር }

ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር አበረታች ስራ ማከናወን ተችሏል- የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አወል።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ...
25/06/2026

ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር አበረታች ስራ ማከናወን ተችሏል- የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አወል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የሁልባራግ ፍትህ ጽ/ቤት ዛሬ በ2018 አፈጻጸም እና በ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ ከህዝብ ክንፍና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የሁልባራግ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አወል፥ በ2018 በጀት ዓመት በፍትህ ጽ/ቤት ከባለድርሻ ተቋማት ከፓሊስ፣ ከፀጥታ:ከማዘጋጃ ቤቶችና ከሌሎችም ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር አበረታች ስራ ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በበጀቱ ዓመቱ ለክስ የቀረቡ 124 መዝገቦችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እንዲያገኙ በማድረግና የመመላለስ ምጣኔ ዜሮ በማድረግ በእጅ ያለና ወደ ተያዘው በጀት ዓመት የሚሸጋገር መዝገብ አለመኖሩንም ጠቅሰዋል።

ከዚህም የሦስቲዮሽ በመወያየት በተለይ 38/ሐ/ የሚመለሱ መዝገቦችን የተገልጋይ ዕንግልት ለመቀነስ ሲባል ከመርማሪ ፓሊስና ከዓቃቤ ህግ ጋር በመሆን ማስረጃዎችን እስከ ቀበሌ ድረስ ወርዶ በጋራ የማጣራትና የመመርመር ስራ እንደተሰራ የተናገሩት ምክትል አስተዳዳሪው ይህም በአንዳንድ ጉድለት ከአቃቤ ህግ ተመላሽ የሚሆኑ መዝገቦችን ያስቀራል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ከብድርና ከኦዲት ጉድለት ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ገንዘብ ማስመለስ መቻሉን አውስተው ፤2 ሺህ 793 ካሬ የከተማ መሬት፣ 18.8 ሄ/ር በገጠር የወል መሬት በክስና ድርድር ለመንግስት ገቢ እንደሆነ፣ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ለ 21 ወገኖች በጠበቃ እና በዐቃቢያነ ህጎች ነፃ የጥብቅና አገልግሎት እንደተሰጠ፣ ከፋይናንስ ጋር በመወያየት መንግስታዊ ውሎች በፍትህ እየተከናወኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የፍትህ ስራ የቅብብሎሽና ቅንጅታዊ ስራን የሚጠይቅ እንደመሆኑ የባለድርሻ ተቋማት ዕገዛና ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበው የተነሱ ነጥቦችን የቀጣይ የዕቅድ አካል እንደሚሆኑ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፍዎች ተቋሙ ከህዝብ ክንፍና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያደርገው እንቅስቃሴና የቀረበው አፈጻጸምና ዕቅድ እጅግ ግልጽና ጥሩ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የንቃተ ህግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለወጣቶች፣ ለሀገር ሽማግሎዎች መሰጠት አለበት ያሉት ተሳታፊዎች አንዳንድ ተቋማት ላይ የሚታዩ ተቀናጅቶ የመስራት ችግሮች በቀጣይ መቀረፍ እንዳለበትም ተወስቷል።

በመጨረሻም ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የ2019 የስራ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።

ዜና ችሎት!ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በጽኑ  እስራት ተቀጡ!         ቀን 08/11/2018 ዓ.ም ኬራቴ                 1ኛ ተከሳሽ ዘካሪያስ መንግስቱ እና 2ኛ ...
15/06/2026

ዜና ችሎት!

ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ!

ቀን 08/11/2018 ዓ.ም ኬራቴ

1ኛ ተከሳሽ ዘካሪያስ መንግስቱ እና 2ኛ ተከሳሽ አንዱዓለም ገላዬ ማይገባቸውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ በዚሁ በሁልባረግ ወረዳ ኬራቴ ከተማ ልዩ ስሙ መንደር 5 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 9፡30 ሰዓት ገደማ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ የአቶ ቶፊቅ ዴተሞ የሆነውንና የዋጋ ግምቱ 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር ) የሚያወጣውን ባለሁለት እግር ዲስከቨር ሞተር ሳይክል አጥር ዘለው ከገቡ በኋላ የግቢውን በር በመክፈት ገፍተው ከግቢ አውጥተው ይዘው ሊሰወሩ ሲሉ የግል ተበዳይ ሲደርስባቸው ጥለው ሲያመልጡ የግል ተበዳይ ባሰማው የድረሱልኝ ጥሪ እና ብርቱ ክትትል በወራበት ሻማ የተያዙ ሲሆን የሁልባራግ ወረዳ ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሲሆን በዚህም መሰረት:-

የወረዳው ዓቃቤ-ሕግም የቀረበውን መዝገብ በጥልቀት በመመርመር በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ/ቁ 19 መሠረት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕጉ አንቀፅ 32(1ሀ) እና 669(3ለ) ስር ክስ በመመስረትና ማስረጃ በማደራጀት ለወረዳው ፍርድ ቤት ለችሎት አቅርቧል።

የሁልባራግ ወረዳ ፍርድ ቤትም ክሱን ተቀብሎ ካከራከረና የግራ እና ቀኝ ማስረጃዎችን ከመመረመረ በኃላ ተከሳሾችን በእጅ ከፍንጅ ከባድ ስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው በማለት በዛሬው ቀን ሰኔ 08/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት 1ኛ ተከሳሽ 5 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ 6 ዓመት ጽኑ እንዲቀጡ ሲል ወስኗል፡፡ በተያያዘ የችሎት ዜና እንዲሁ ሸረፋ ኢዶ እና አባተ አይሶ የተባሉ ተከሳሾችም 2 smart ስልኮችን በመስረቅ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው 1ኛ ተከሳሽ 5 ዓመት ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ 2 ዓመት ከ 3 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ሲል ፍ/ቤቱ ወስኗል። መረጃው የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ነው።

ለህግ፣ለፍትህ፣ለርዕትህ!!

ቸር ያሰማን!!!

ህጉ ምን ይላል?በቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ስለሚነሱ ቅሬታ ዎችና አፈታታቸው ህጉ ምን ይላል ? እስከ ፍ/ቤት የሚደርስ መፍትሔ አለው።የምርጫ ጉዳዮች ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች መመሪያ ቁጥር 10/...
30/05/2026

ህጉ ምን ይላል?

በቆጠራ ሂደትና በውጤት ላይ ስለሚነሱ ቅሬታ ዎችና አፈታታቸው ህጉ ምን ይላል ?

እስከ ፍ/ቤት የሚደርስ መፍትሔ አለው።

የምርጫ ጉዳዮች ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች መመሪያ ቁጥር 10/2013

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት/Hulbarag wereda Justice Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share