Ethiopian Biodiversity Institute - EBI

Ethiopian Biodiversity Institute - EBI Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Biodiversity Institute - EBI, Government Organization, Addis Ababa, Ababa.

We ensure that the country’s biodiversity and the associated community knowledge are properly conserved and sustainably utilized, and the country and its communities get fair and equitable share of the benefits arising from their utilization.

የጣና ባዮስፌር ሪዘርቭ አሁናዊ ሁኔታ /Periodic Review / ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ተካሄደየጣና ባዮስፌር ሪዘርቭ አሁናዊ ሁኔታ /Periodic Review / ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ነሀሴ ...
24/08/2026

የጣና ባዮስፌር ሪዘርቭ አሁናዊ ሁኔታ /Periodic Review / ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ተካሄደ
የጣና ባዮስፌር ሪዘርቭ አሁናዊ ሁኔታ /Periodic Review / ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ተካሄደ፡፡
ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተወካይ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቀ ስነምህዳራዊ ፣ ከባቢያዊ እና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለውን የጣና ሀይቅና አካባቢውን በሚመለከት አጀንዳ ላይ ለመምከር በመምጣታችሁ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ካሉ በኋላ በምርምር የተደገፈ አሳማኝ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባ አስታውሰዋል፡፡
ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የጣና ባዮስፌር ሪዘርቭ አሁናዊ ሁኔታ /Periodic Review / ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት እና የምክክሩን አስፈላጊነትን አስታውሰው ጣናን መሰል ጥብቅ ስፍራዎች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በቀጣይ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ ሊያስመዘግባቸው የተዘጋጁትን ጥብቅ ስፍራዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ጥብቅ ስፍራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ጠቁመው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ታዋቂነት እንድታጎሉ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር እንየው አድጎ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት ባስተላለፉት መልዕክት የጣናን ጤንነት መጠበቅ ግዴታችን ነው ካሉ በኋላ በጣና ሀይቅ ዙሪያ ባለድርሻ አካላት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
አቶ አበራ ስዩም በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የደንና ግጦሽ መሬት እጽዋት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ Ethiopian Biosphere Reserves: Concept & Practices እንዲሁም Periodic Review of Tana Biosphere Reserve (TOR) የተሰኙ ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ Tana Biosphere Reserve: Challenges and Opportunities የተሰኘ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
በወርክሾፑ ማጠናቀቂያ ላይ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተወካይ እና ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ለቴክኒክ ቡድን አባላት የስራ መመሪያ ሰጥተው መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተከናወነበኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የደም ልገሳ መርሀ ግብር ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተከናወነ፡፡በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ...
20/08/2026

የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተከናወነ
በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የደም ልገሳ መርሀ ግብር ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተከናወነ፡፡
በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት አርአያነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል በሆነው የደም ልገሳ መርሀ ግብር ላይ የተሳተፉ አመራሮችና ሰራተኞች ደም በመለገስ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሚናቸውን በመወጣታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የማኔጅመንት አባላት ሦስተኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በቢሾፍቱ አከናወኑ። በኢንስቲትዩቱ በዓመቱ ከታቀደው አሥራ አምስት ሺህ ችግኝ ተከላ ውስጥ...
17/08/2026

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የማኔጅመንት አባላት ሦስተኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በቢሾፍቱ አከናወኑ።
በኢንስቲትዩቱ በዓመቱ ከታቀደው አሥራ አምስት ሺህ ችግኝ ተከላ ውስጥ ዛሬ ነሐሴ 11/2018 ዓም በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዴ ሐይቅ ዳርቻ ባለው ኮረብታማ ስፍራ ተከላው ተከናውኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካርታ ካስኬ በዘንድሮው ዓመት እስካሁን ድረስ ከ80% በላይ የሀገር በቀል ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰው የችግኝ ተከላው ቀጣይነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ ለተሳተፉ የማኔጅመንት አባላት ላሳዩት ቁርጠኝነትና መረባረብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አቶ አበራ ስዩም የደንና ግጦሽ መሬት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ዛሬ እዚህ የተገኘነው ከቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እንድንንከባከበው በተሰጠን ቦታ ላይ ከሦስት ሺህ በላይ የሆኑ ዘጠኝ ዓይነት ዝርያዎች ለመትከል ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዓይነቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ህይወት በፍቃዱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ የሃገር በቀል ችግኞችን በማልማት ለትውልድ ምሣሌ መሆን እንደሚያስፈልግ እና ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ከተሳትፎ ባሻገር ለምግብነት የሚያገለግሉ የፍራፍሬ ችግኞችን መትከላችን እንደ ሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የሀገር በቀል ችግኞችን መትከል ለአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው በመርሀ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የማኔጅመንት አባላት ገልጸዋል፡፡

Inception Workshop Launches GEF-8 Wildlife Conservation Project to Strengthen Wildlife and Landscape Conservation in Eth...
13/08/2026

Inception Workshop Launches GEF-8 Wildlife Conservation Project to Strengthen Wildlife and Landscape Conservation in Ethiopia.

አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ገጽ 24ልዩ ዕትምከገፅ 23 የዞረ የመጨረሻ ክፍል «የምተክለው ችግኝ ሕይወቴን የሚታደግ... ላይ የኅብረተሰቡ ያለመረዳት ችግሮ መኖሩ አይቀሬ ...
06/08/2026

አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ገጽ 24

ልዩ ዕትም
ከገፅ 23 የዞረ የመጨረሻ ክፍል
«የምተክለው ችግኝ ሕይወቴን የሚታደግ...

ላይ የኅብረተሰቡ ያለመረዳት ችግሮ መኖሩ አይቀሬ ነው። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ይህ ክስተት ተፈጥሮ ነበር። ቀደም ሲል የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እንደ “ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ” ወይም ጊዜያዊ ዘመቻ አድርጎ የመመልከት አዝማሚያዎች ነበሩ። ዛሬ ግን ማህበረሰቡ ይዘቱን በጥልቀት በመረዳት፡ «ይህ ነገ የምተነፍሰው አየር ነው፤ የሚመጣብኝን የሙቀት መጠን የሚቀንስልኝ ነው፤ የነገ ዝናብና የምግብ ዋስትና ነው» ወደሚል ሙሉ ግንዛቤና ባለቤትነት ተሸጋግሯል።

ተክሎች የሚያስገኙትን ተጨባጭ ጥቅም ሲረዳ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት ተፈጥሮበታል። አርሶ አደሩ በአቮካዶ ተክል ወይም በቡና ማደስ የተገኘውን ተጨባጭ ለውጥ ከተመለከተ በኋላ፣ ያለ ምንም ተጨማሪ ቅስቀሳ በራሱ ፍላጎት በደጃፉና በተራቆቱ መሬቶች ላይ ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ተግባርን እንደ ባህል ወስዶታል።
ለዚህም ውጤት የአመራሩ ውሳኔና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከፍተኛ ሚና ነበረው። ነገር ግን በቀጣይ የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ መንግሥት የማስተባበር ሥራውን ከዚህ በበለጠ መሥራት አለበት። ክፍተቶችን እያየ መምራትና የመፍትሔ ሃሳቦችን መስጠት ይገበዋል። በተመሳሳይ አርሶ አደሩ የልፋቱን እንዲያገኝ በሙያ እንዲታገዝ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ሲሆን ከግል ገቢ ባሻገር የሀገር ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል።

አዲስ ዘመን፡- መርሃ-ግብሩ ከወቅታዊ ዘመቻነት አልፎ ዘላቂ የኑሮ ዘይቤና ባህል እንዲሆን ለማድረግ ምን መሠራት አለበት?
ካርታ(ዶ/ር)፡- አብዛኞቹ የማህበረሰብ ንቅናቄዎችና ሀገራዊ መርሃ-ግብሮች በሚጀምሩበት ወቅት ትልቅ መነቃቃትና ከፍተኛ የተሳትፎ ማዕበል ይፈጥራሉ። ነገር ግን የብዙዎች ፈተና የሚጀምረው የወቅቱ ትኩረትና ቅስቀሳ እያቀዘቀዘ ሲሄድ ነው። መርሃ-ግብሩ የወቅቱ “ትኩስ አጀንዳ” ሆኖ ከመቅረት አልፎ የማህበረሰቡ ዕለታዊ የኑሮ ዘይቤ፣ ልማድና ዘላቂ ባህል እንዲሆን ከተፈለገ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል። አንድን ጊዜያዊ እንቅስቃሴ ወደ ዘላቂ ባህል ለመቀየርም ተቋማዊ መሠረት ሊኖር ይገባል።

ማንኛውም መርሃ-ግብር በሰዎች በጎ ፈቃድና በወቅታዊ ቅስቀሳ ብቻ ዘላቂ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም መርሃ-ግብሩ በየተቋማቱ ዕለታዊ አሠራር፣ ደንብና ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ እንዲካተት ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ለሥራው የሚሆን ቋሚ በጀት፣ ኃላፊነት የሚወስድ ክፍልና ባለሙያ መመደብና ንቅናቄው እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባል። ይህንን ሥራ በትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት ውስጥ ማካተትም ጠቀሜታው የጎላ ነው። ምክንያቱም ልማድ የሚገነባው ከልጅነት ጀምሮ በሚሰጥ ተደጋጋሚ እውቀትና ልምምድ ነው። ስለዚህ የመርሃ-ግብሩን እሴቶች በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ በማካተት አዲሱ ትውልድ ከተፈጥሯዊ ባህሪው አንዱ አድርጎ እንዲወስደው ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃዎችን በቋሚነት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃንና የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ማቅረብም ተገቢ ነው።

ከላይ ወደ ታች የሚወርድ መመሪያ ብቻውን የሥራ ባህልን አያሰርጽም። ስለሆነም ማህበረሰቡ «ነገሩ የእኔ ነው» ብሎ እንዲቀበለው ማድረግ ላይ መሥራት ይገባል። ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ወጣቶችንና የማህበረሰብ መሪዎችን ግንባር ቀደም አምባሳደሮች ማድረግ ያስፈልጋል። እያንዳንዱ ማህበረሰብ እንደየሁኔታው አሠራሩን አሻሽሎ እንዲጠቀምበት ማስቻልም ይገባል። በተጨማሪ ሰዎች የሚያደርጉት በጎ አስተዋጽኦ እውቅና ሲያገኝና ውጤቱ ሲለካ ልምዱ እየጠነከረ ይሄዳል። በመርሃ-ግብሩ አርአያ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ተቋማትንና አካባቢዎችን መሸለምና ማበረታታት ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡- ኢትዮጵያ በቀጣናው አረንጓዴ ዐሻራን ለማስፋት እያደረገች ያለውን ጥረት እንዴት ያዩታል?
ካርታ(ዶ/ር)፡- “ቤትህ ሰላም እንዲሆን ጎረቤትህ ሰላም ማደር አለበት” እንደሚባለው ሁሉ፣ የአንድ ሀገር የዝናብ ስርጭትና የተፈጥሮ ሀብት ደኅንነት አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው የጎረቤት ሀገራት የአካባቢ ሁኔታ ሲሻሻል ነው። ኢትዮጵያም ይህንን በማሰብ ሰፊ ሀገራዊ ተግባራትን እያከናወነች ነው። አንዱ የራሷን መሬት በአረንጓዴ ከማልበስ ተሻግራ ለቀታናዊ ሀገራት የምትተርፍበትን እድል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነው።

ይሄ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በጋራ ከመመከት አኳያ የማይተካ ሚና ይጫወታል። ዲፕሎማሲንም ያጠነክራል። ችግኞችን ወደ አጎራባች ሀገራት በመላክ በጋራ የመልማት አስተሳሰብ ተፈጥሯል። ይህም የአካባቢ ጥበቃን ለፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከሪያ ድልድይ አድርጓል።

ሌላው የተፈጥሮ ሀብት ድንበር ተሻጋሪ አወንታዊ ተጽዕኖ የአፈር መሸርሸር፣ የበረሃማነት መስፋፋት እና የውሃ እጥረትን መታደግ ነው። በኢትዮጵያ ተራራዎች ላይ የሚተከለው ዛፍ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት የጎርፍ አደጋን ቀንሷል። የወንዞችን የውሃ መጠን በመጠበቅ በኩልም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

የአፍሪካ ቀንድ በተደጋጋሚ ከደርስበት ድርቅና የጎርፍ አደጋ ወጥቶ፣ በተፈጥሮ ጥበቃ እና ዘላቂ ልማትን እንዲገነባ እድል ይሰጣል። ስለሆነም ይህ መልካም ጅምር የበለጠ ዘላቂ፣ ፍሬያማ እና ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ከችግኝ ተከላ ወደ እንክብካቤ መግባት ያስፈልጋል። ዋናው ትኩረት የተተከሉት ችግኞች በቁጥር ማብዛት ሳይሆን የመጽደቅ መጠናቸው መጨመር ነው። ስለሆነም ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር የሚስማሙ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎችን በመምረጥ ዘላቂ የውሃ እና የእንክብካቤ ሥርዓት መዘርጋት ይገባል።

እንቅስቃሴው በፖለቲካዊ ፍላጎት ላይ ብቻ ሳይመሰረት በቀጣናው ሀገራት ዘላቂ ስምምነቶች፣ በኢጋድና በአፍሪካ ኅብረት ስር በቋሚነት የሚመራበት መዋቅር ቢኖረው መልካም ነው። ምክንያቱም ይህ አካሂድ የመንግሥታት መቀያየር ሳይበግረው ዘላቂነት እንዲኖረው ያደርገዋል። በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ የመንግሥታት ጥረት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር፣ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ቀጥተኛ ተሳታፊ እና ጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ መፍጠር ያስፈልጋል።

ትክክለኛውን የዛፍ ዓይነት ለትክክለኛው አፈርና አየር ንብረት መምረጥ እንዲቻል የቀጣናው ሀገራት የምርምር ተቋማት በጋራ የሚሠሩበትን መድረክ ማመቻቸት፣ የተተከሉ ቦታዎችን የዕድገት ደረጃ በየጊዜው መከታተል ይገባል። የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ ከፍተኛ በጀት ይጠይቃል። በዚህም ኢትዮጵያ እና የጎረቤት ሀገራት በጋራ የአየር ንብረት ፋይናንስን መሳብ ይኖርባቸዋል። የሕዝቦችን አብሮ የመኖር ሰላም የሚያጠናክር አረንጓዴ የዲፕሎማሲ መሣሪያ ሆኖ እንዲቀጥልም የተቀናጀ እና ሳይንሳዊ አመራር ያስፈልገዋል።

አዲስ ዘመን፡- የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ በአንዲት ሀገር ሥራ ብቻ የሚለወጥ አይደለም። ስለሆነም እንደ አህጉር ከፍ ሲልም እንደ ዓለም ተጋግዞ መሥራት ያስፈልጋል። ይህ ተግባር እንዴት ሊከወን ይገባል ይላሉ?
ካርታ(ዶ/ር)፡- የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ዋና መነሻዎች በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት የሚለቁት ከፍተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ነው። ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለጋዝ ልቀቱ ያላቸው አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፤ በጉዳቱ ሰለባ ከመሆን አንጻር ግን ቀዳሚ ስፍራን ይይዛሉ። በዚህም ኢትዮጵያ ሕዝቧን አስተባብራ ችግኞችን በመትከል ይህንን ችግር ለመታደግ እየሠራች ትገኛለች። የተከለችው እያንዳንዱ ችግኝ በአማካይ 1 ዶላር እንኳን ቢገመት፣ ሀገሪቱ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለመታገል ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ግዙፍ እሴት (ኢንቨስትመንት) በራሷ አቅም አውጥታለች። የዓለምን የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ዐሻራዋን አኑራለች። ይህ የኢትዮጵያ ጥረት በዓለም ላለው የአየር ንብረት ጫና መቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቢያደርግም፤ በኢትዮጵያ ደረጃ ብቻ ተሠርቶ እንደ ዓለም ለውጦችን ማምጣት አይቻልም። ስለሆነም ኢትዮጵያ በራሷ ሕዝባዊ ጉልበትና ሀብት የምታደርገውን ጥረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያግዝ ይገባል። ሥራው በተሞክሮነት ተወስዶ ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ማድረግ ያስፈልጋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ከሀገር ውስጥ ሕዝባዊ ግንዛቤ ጀምሮ እስከ ቀጣናዊ ወንድማማችነትና ዓለም አቀፋዊ የአየር ንብረት ፍትሕ ጥያቄ ድረስ የተዘረጋ ሰፊ ራዕይ በመሆኑ ይህንን መልካም ጅምር በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ጎረቤቶችንና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ተሳታፊነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። በተጨማሪም የአየር ንብረት ፍትሕን በማረጋገጥ ዙሪያ ለሚሠሩ ሥራዎች፣ እውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡- በመጨረሻ ቀረ የሚሉት ሃሳብ ካለ ይግለጹ?
ካርታ(ዶ/ር)፡- የአካባቢ ጥበቃ እና የችግኝ ተከላ
ሥራዎች በዘላቂነት ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት በመንግሥት ተቋማትና በኅብረተሰቡ መካከል ያለው የማስተባበርና የማነቃቃት ሥራ ሳይቋረጥ ሲቀጥል ነው። ይህ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየታየ ነው። በኅብረተሰቡ ዘንድ የአመለካከት ለውጥ መጥቷል። ከዚያም ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎቹ ለኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው እድገት ምንጭ እንዲሆን አድርጓል።

ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብረት ሚዛን መጠበቅ ያላት አበርክቶ የሀገርን ገጽታ ገንብቷል። በተጨማሪም የተለያዩ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችንና ስብሰባዎችን እንድታስተናግድ እድል ሰጥቷል። እነዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና ለቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ በር የከፈቱ ናቸው። በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገር እንግዶችና ተሳታፊዎች በሀገር ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ለሀገር ውስጥ ቢዝነሶች ከፍተኛ የመነቃቃት እድልን ሰጥተዋል። በተለይም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማሳደግ፣ በሆቴል፣ በትራንስፖርትና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ሰፊ የሥራ እድል እንዲያገኙ አስችሏል።

ይህንን አጋጣሚ በአግባቡ ለመጠቀምና የኢትዮጵያን በጎ ምስል ለሚመጡ እንግዶች አጉልቶ ማሳየት ግን በቱሪዝም ዘርፉ ከሚሳተፉ ባለድርሻ አካላትና ከኅብረተሰቡ ይጠበቃል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የጠፋውን ብዝሃ ሕይወት ከማስመለስ ባሻገር የወደፊቱ ትውልድ የተሻለና ንጹህ አየር የሚተነፍስበትን፣ እንዲሁም በጽዱና በለምለም አካባቢ መኖር የሚችልበትን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ይህ ተግባር ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።

አዲስ ዘመን፡- ስለሰጡን ማብራሪያ እናመሰግናለን።
ካርታ(ዶ/ር)፡- እኔም አመሰግናለሁ።

አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ገጽ 23  ልዩ ዕትም«የምተክለው ችግኝ ሕይወቴን የሚታደግ... ከገፅ 22 የዞረአማካኝነትም የዝናብ ጠብታዎች በቀጥታ ከመሬት ጋር እንዳይጋጩ ያ...
05/08/2026

አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ገጽ 23
ልዩ ዕትም

«የምተክለው ችግኝ ሕይወቴን የሚታደግ...

ከገፅ 22 የዞረ
አማካኝነትም የዝናብ ጠብታዎች በቀጥታ ከመሬት ጋር እንዳይጋጩ ያግዳሉ። ይህም የውሃውን የጠብታ ኃይል በመቀነስ ከባድ ዝናብ በጣለ ጊዜ ውሃው አፈሩን ጠርጎ እንዳይወስደው ይከላከላሉ። በተጠበቀ አፈር ውስጥ ዝናብ ሲጥል ውሃው ከመሬት በላይ ፈስሶ ከመሄድ ይልቅ ወደ ታች ይሰርጋል። ይህም በሌላ በኩል እንደ አዲስ ምንጮችና ወንዞች ሆኖ የመውጣት ተፈጥሯዊ ኡደትን እንዲያከናውን ይረዳል።

ከደኖች የሚረግፉ ቅጠሎችና ቅርንጫፎች በስበስው የአፈሩ ለምነት ይጨምራሉ። ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች፣ በወደቁ ቅጠሎቻቸውና የዛፍ ግንዶች አማካኝነት በምድር ላይ የሚፈሰው ውሃ በከፍተኛ ፍጥነት እንዳይሄድ ያግዳሉ። በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው የዝናብ ውሃ ወደ መሬት ውስጥ እንዲሰርግ በማድረግ የመሬት ውስጥ የውሃ መያዣዎችን አቅም ይጨምራሉ። በምድር ላይ የሚፈሰውን የጎርፍ መጠንም በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳሉ። በአሁኑ ወቅት የከባቢ አየር ብክለት ለዓለም አቀፍ የጤና ችግሮች እና ለላቀ የአየር ንብረት መዛባት ዋና ምክንያት ነው። በዚህም ደኖች አየርን ለማጽዳት የተፈጥሮ ማጣሪያ ሆነው ያገለግላሉ። ምክንያቱም በደኖች አማካኝነት ምግባቸውን ለማዘጋጀት ጎጂ የሆነውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከአየር ውስጥ ስበው በመውሰድ ኦክስጅንን ይለቃሉ። ይህ ደግሞ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ ይረዳል። በተመሳሳይ ቅጠሎችና ቅርንጫፎች በአየር ላይ የሚንሳፈፉ አቧራዎችን፣ ጢሶችን እና ጎጂ ኬሚካሎችን (እንደ ናይትሮጅን ኦክሳይድ እና ካርበንዳይኦክሳይድ ያሉ)
አጥርተው በመያዝ አየሩን ጤናማ ያደርጋሉ።

የደን ሽፋኑን ማሳደግ አፈርን ከመሸርሸር በመጠበቅ ግብርናን ያጠናክራል፣ የጎርፍ አደጋን በመቀነስ ሕይወትንና ንብረትን ይታደጋል፣ እንዲሁም አየርን በማጽዳት ለጤናማ አኗኗር አስተዋጽኦ ያደርጋል። በመሆኑም ደኖችን መንከባከብ እና አዳዲስ ዛፎችን መትከል ለአሁኑ እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚደረግ ትልቅ ኢንቨስትመንት መሆኑን መረዳት ይገባል።

መርሃ-ግብሩ የወቅቱ “ትኩስ አጀንዳ” ሆኖ ከመቅረት አልፎ የማህበረሰቡ ዕለታዊ የኑሮ ዘይቤ፣ ልማድና ዘላቂ ባህል እንዲሆን ከተፈለገ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል። አንድን ጊዜያዊ እንቅስቃሴ ወደ ዘላቂ ባህል ለመቀየርም ተቋማዊ መሠረት ሊኖር ይገባል

አዲስ ዘመን፡- በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሀገር በቀል እጽዋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ይሄ ለምን ይሆን?

ካርታ(ዶ/ር)፡- ሀገር በቀል እጽዋት ከአካባቢው አፈር፣ አየር ጠባይና ሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ጋር ለዘመናት አብረው የኖሩና የተላመዱ ናቸው። ይህ ደግሞ የአካባቢው አእዋፍ፣ ነፍሳትና እንስሳት ለምግባቸውና ለመኖሪያቸው ሙሉ በሙሉ የሚጠቀሙባቸው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። እነርሱ የማይኖሩ ከሆነ ደግሞ አዕዋፉም ሆኑ እንስሳቱ ለመኖር ይቸገራሉ። ከምድረ ገጽ ጭምር ሊጠፉ ይችላሉ። ስለዚህም ለእነዚህ ችግኞች ትኩረት ተሰጥቷል። በሌላ በኩል ሀገር በቀል እጽዋት የከርሰ-ምድር ውሃን በስርዓት ከመጠበቃቸውም በላይ የውሃ ምንጮች እንዳይደርቁ ያደርጋሉ። የሥር ስርአታቸው ከአፈሩ ጋር የተዋሃደ ስለሆነ የአፈር ለምነት እንዳይጠፋና ተሸርሽሮ እንዳይሄድ ይታደጋሉ።

ሀገር በቀል እጽዋት በአካባቢው የሚከሰቱ ድርቆችን፣ የበሽታ ወረርሽኞችንና የአየር ንብረት መለዋወጥን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ችሎታ አላቸው። በዚህም ከፍተኛ የውሃ አቅርቦትና ልዩ እንክብካቤ ሳይሹ ረጅም ዘመን ያገለግላሉ። ለዘላቂ የደን ልማት አስፈላጊ ናቸው። ሀገር በቀል እጽዋት ወይራ፣ ኮሶ፣ ፅድ፣ ግራር ወዘተ ለባህላዊ መድኃኒትነትና ለተለያዩ ሕክምናዎች ያገለግላሉ። እንዲሁም የዕርቅ፣ የስብሰባና የማህበራዊ ሁነቶች ጥላና ምልክት ናቸውም።

ሀገር በቀል እፅዋት ሲመለሱ ከእነሱ ጋር ይኖሩ የነበሩ አእዋፋት፣ የዱር እንስሳትና ደቂቅ አካላት ወደ ነበሩበት ተፈጥሯዊ ሁኔታ ይመለሳሉ። የተሟላ ሥርዓተ-ምህዳር እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ባህላዊ እውቀትንም ያሰፋሉ። የምግብ ዋስትናንም ያረጋግጣሉ። ለምሳሌ፡- ለፍራፍሬና ለምግብነት የሚያገለግሉ ሀገር በቀልና ተስማሚ የዛፍ ዝርያዎችን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ውስጥ ማካተት፣ አካባቢን ከማልማት ጎን ለጎን ለአካባቢው ኅብረተሰብ ተጨማሪ ገቢና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው። ኢትዮጵያን ለኑሮ ምቹ፣ ለእንስሳትና ለአእዋፋት መኖሪያ፣ እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ የተረጋገጠ የተፈጥሮ ሀብት ያላት አረንጓዴ ሀገር አድርጎ ለመረከብና ለማስረከብ የሚያግዝም ነው።

አዲስ ዘመን፡- አረንጓዴ ዐሻራ የአጭርና የረጅም ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ምንድን ነው?
ካርታ (ዶ/ር)፡- ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ብዝሃነቷ እና በባህላዊ እውቀት ጥልቀቷ የምትታወቅ ሀገር ናት። በቅርብ ዓመታት እየተከናወነ ያለው የ“አረንጓዴ ዐሻራ” መርሃ ግብር ደግሞ ይህንን ከማስረጽ አኳያ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከልና ተፈጥሮን ከመንከባከብ ባለፈ፣ ለሀገሪቱ አርሶ አደሮችና ለአካባቢው ሕብረተሰብ ሁለገብ የኢኮኖሚ ዕድሎችን እያበሰረ ነው።

ይህ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሚታዩ ፈጣን የኢኮኖሚ ጥቅሞች ጀምሮ፣ እስከ ዘላቂና የረጅም ጊዜ የሃብት ምንጮች ድረስ ለሀገሪቱ አኗኗርና ኢኮኖሚ አዲስ ተስፋ ፈንጥቋል። በአጭር ጊዜ ከመጡ ድሎች ስንነሳ አንዱ የሥራ እድል ፈጠራ ነው። ችግኞችን በማዘጋጀት፣ በማፍላትና መንከባከብ ዙሪያ በርካታ ወጣቶችና ሴቶች ተሳትፈዋል። ይህም ለማህበረሰቡ አዲስ የገቢ ምንጭ ሆኗል። በችግኝ ጣቢያዎች የሚሰሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ችግኞችን ለግልና ለበጎ አድራጎት ተቋማት በመሸጥ ፈጣን ገቢ ያገኛሉ።

ሌላው በተከለከሉና በተንከባከቡ ተፋሰሶች ላይ በፍጥነት የሚበቅሉ የሳርና የተፈጥሮ መኖ ዓይነቶች ለአርሶ አደሩ የከብት መኖ በመሆን አፋጣኝ እፎይታን ይሰጣሉ። ይህም የወተትና የሥጋ ምርታማነትን ወዲያውኑ እንዲጨምር ያደርጋል። ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት እንዲኖርም እድል ይሰጣል።

በተመሳሳይ በፍጥነት የሚያድጉ የዛፍ ዓይነቶችን በመተከል፣ አርሶ አደሩ ለዕለት ተዕለት ማገዶና ለአነስተኛ ግንባታዎች የሚሆኑ እንጨቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ ይረዳል። ከዚያም ባሻገር እንደ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ እና አቮካዶ ያሉ በፍጥነት ፍሬ የሚሰጡ የፍራፍሬ ዛፎችን በመትከል በአጭር ጊዜ ማህበረሰቡ የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ ይችላል። ተጨማሪ የገበያ ገቢ ያገኛል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ትልቁ ስኬት የሚለካው በሂደት በሚመጡና የማህበረሰቡን ሕይወት በዘላቂነት በሚለውጡ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ውጤቶች ነው። ከዚህ አንጻር ጥቅሞቹን ስናይ ችግኞች አፈርን ከውሃና ከነፋስ መሸርሸር በመጠበቅ እርጥበትን ይይዛሉ። በሂደት የአፈር ለምነት በመጨመር የአርሶ አደሩ የሰብል ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ። የከርሰ ምድር ውሃ እንዲያገግም፣ ምንጮች እንዲፈልቁና ሚዛናዊ የሆነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋሉ። ይህም አርሶ አደሩ በዓመት ሁለትና ሦስት ጊዜ በመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ አምርቶ ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ዕድል ይከፍታል።

ሌላው እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ዘይቱን፣ ቡና እና የቅመማ ቅመም ተክሎች በስፋት በመተከላካቸው ለአርሶ አደሩ የረጅም ጊዜና አስተማማኝ የንግድ ምርት ይፈጥርለታል። አርሶ አደሩ በቂ ሰብል እንኳን ቢያጣ ከፍራፍሬ ሽያጭ ዘላቂ ገቢ እንዲያገኝ ያግዘዋል። የተጠበቁ ደኖችና ያበቡ ዛፎች ለንብ ማነብ ተስማሚ ሁኔታ ይፈጥራሉ። አርሶ አደሮች ጥራት ያለው ማርና ሰም በብዛት በማምረት ከፍተኛ የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የተጠበቁ ደኖችና የተተከሉ ዛፎች ካርቦንን በመምጠጣቸው ምክንያት ማህበረሰቡ ከዓለም አቀፍ የካርቦን ገበያ የገንዘብ ድጋፍና ክፍያ የሚያገኝበት መንገድ ያመቻቻል።

በመስኩ በሚሰጡ ስልጠናዎች ወጣቶች በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በችግኝ እርባታ እና በመሬት እንክብካቤ ላይ የካበተ እውቀት እንዲያገኙ ያደርጋል። እሴት የመጨመር ባህልን በማላመድ አዳዲስ የንግድ ሥራዎችን ለመፍጠርም ያግዛል።

አዲስ ዘመን፡- የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣል ሲባል ምን ማለት ነው?
ካርታ(ዶ/ር፡- መርሃ-ግብሩ በምግብ ዋስትና በኩል የሚጫወተው ሚና በቀጥታ ከአፈር እንክብካቤ እና ከፍራፍሬ ልማት ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ እና ብርቱካን ያሉ የፍራፍሬ ዛፎች መተከላቸው የቪታሚን እና የሚነራል እጥረትን በመቅረፍ የኅብረተሰቡን ጤና ያሻሽላል። አፈር እንዳይሸረሸር መከላከል፣ እርጥበት የመያዝ አቅሙን መጨመር እና የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን መጠቀም የአፈርን ምርታማነት በመጨመር የሌሎች ሰብሎች ምርት እንዲያድግ ያደርጋል። ይህ ደግሞ ተጨማሪ ገቢ እና የምግብ መግዛት አቅምን ያጎለብታል። አርሶ አደሮችና ወጣቶች የሚያመርቱትን ፍራፍሬ ለገበያ በማቅረብ በሚያገኙት ተጨማሪ ገቢ ሌሎች አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶችን የመግዛት አቅም እንዲኖራቸው ያግዛቸዋል።የፍራፍሬ ዛፎች የከባቢ አየርና የመሬት ለምነትን ከመጠበቅ ባለፈ አርሶ አደሮች አስተማማኝ ምርት እና ገቢ እንዲያገኙ ያደርጋል። የሥራ እድልን ያሰፋል።

አዲስ ዘመን፡- የኅብረተሰቡ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜትን እንዴት ይበልጥ ማጎልበት ይቻላል?
ካርታ(ዶ/ር፡- በማንኛውም እንቅስቃሴ መጀመሪያ
ወደ ገፅ 24 ዞሯል

Address

Addis Ababa
Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Biodiversity Institute - EBI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Biodiversity Institute - EBI:

Shortcuts

Share