27/05/2026
የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ
===============
ከግንቦት 23-27/2018 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባሉን ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ሀኪሞችና ከእስራኤል ሐገር በሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::
አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------
1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)
2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)
3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)
4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና
5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::
የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!
ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ