02/06/2026
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የክልሉን ህዝብ አመሠገኑ!
ሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግንቦት 25/2018
ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በምስጋናቸው እንደገለፁት የዘንድሮው ምርጫ እንዳይሳካ የቅርብ ሆድ አደሮች፤ የሩቅ ስትራቴጂያዊ ጠላቶች በቅንጅት ተግተው የሠሩ ቢሆንም አሰተዋዩ ህዝባችን ጠላቶቻችንን አሳፍሮ ሀገሩን አሸናፊ አድርጓል ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ነዋርዎችም በዚህ ታርካዊ ምዕራፍ በማለዳ ወጥቶ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ቆይቶ የሚፈልገውን ፓርቲ በሰላም መርጦ በመመለሱና በድምሩ ሀገራችን የተሳካ ምርጫ እንድታካሂድ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረጉ በክልሉ መንግሥት ስም ከልብ አመሠግናለሁ ብለዋል።
ሌሎች በዚህ ሂደት የተሳተፉና የማስተባበርና የመምራት ሚና ለተጫወታችሁ ሁሉ ምሥጋናችን ይድረሳችሁ ብለዋል።
በመቀጠልም አሁን የምርጫ ተግባር በተሳካ ሁኔታ የፈፀምን በመሆኑ በዚህ ሰበብ ከሚፈጠር መዘናጋት ተሻግረን፤የድህነት ጉቶ ነቅለን ሁላችንም ፊታችንን ወደ ጀመርነው ብልጽግናን የማፅናት ተግባሮቻችን ላይ ትኩረት እናድርግ ብለዋል።
ለበለጠ መረጃ
➚ድረ ገጽ፦ https://sidamanrsps.gov.et
➚ፌስቡክ፡- Sidama National Regional State Communication Affairs Bureau
➚ዩትዩብ፦https://youtube.com/.bureau?si=r5EAWg8x4kXmLqQN
➚WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029VadMPA2DDmFbMwfTjG3l
➚ቴሌግራም፦ https://t.me/SidamaCommunicationbureau