Iftu Anwar

Iftu Anwar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Iftu Anwar, Addis Ababa.
(7)

08/05/2026

ዓላማችን አንድ፤ ግባችን ብሩህ ይሁን!

የአንድ ሕዝብ ህልውና በጥቂቶች ፍላጎት አይወሰንም፤ የትግራይ ሕዝብ በሰላም ምርጫው እንደጸና ሊቀጥል ይገባል።ሰሞኑን በትግራይ ክልል የታዘብነው የሹመት ድራማና የፖለቲካ ትኩሳት አንድ እውነታ...
07/05/2026

የአንድ ሕዝብ ህልውና በጥቂቶች ፍላጎት አይወሰንም፤ የትግራይ ሕዝብ በሰላም ምርጫው እንደጸና ሊቀጥል ይገባል።

ሰሞኑን በትግራይ ክልል የታዘብነው የሹመት ድራማና የፖለቲካ ትኩሳት አንድ እውነታን በግልጽ አሳይቶናል። ይኸውም፣ በጃጀና በነተበ የፖለቲካ እሳቤ የተነከሩ ጥቂት ግለሰቦች ሕዝብን እንደ መያዣ አድርገው አሁንም ድረስ የሕዝብን ትዕግስት እንደ ፍርሃት፣ ዝምታን ደግሞ እንደ ስምምነት እየቆጠሩት መሆኑን ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክና ማንነት ከጦርነት ይልቅ በሰላማዊ አብሮነት የታነጸ ነው። የትግራይ ህዝብ ደግሞ የዚህ እሴት ግንባር ቀደም ማሳያ ነው። ባለፉት አስከፊ የጦርነት ዓመታት ተስፋ፣ ጧሪና ቀባሪውን ያጣው፣ ልጆቹን ለጥፋት ማገዶ አድርጎ የሰጠውና በመከራ አቅፉ ውስጥ ያለፈው እነዚህ ግለሰቦች በጎነጎኑት ተንኮል፣ በሸረቡት ሴራ እና ባጠራቀሙት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተታሎ ነበር። ሆኖም ለጥላቻ ሲቀሰቅሱ የነበሩት በደሃ ልጅ ደምና አጥንት ተከብበው አሁንም “ከወንበር በላይ ነፋስ” እያሉ ይገኛሉ።

ከጦርነቱ በፊትም የግል ስልጣንና ጥቅም እንጂ ሌላ አጀንዳ አልነበራቸውም። ከጦርነቱ በኋላም የበለጠ ሃብት የማጋበስና ለስልጣን የመናጨት ልምዳቸው ተባብሶ ቀጥሏል። የጦርነትን አስከፊ ዋጋ የከፈለው የትግራይ ሕዝብ ግን ዛሬ ላይ በፅኑ ዝምታው ትልቅ መልዕክት እያስተላለፈ ይገኛል። ይኸውም “እኛ የምንፈልገው ልማትን እንጂ ጦርነትን አይደለም፤ የምንናፍቀው ሰላምን እንጂ የፖለቲካ ቁማርን አይደለም!” የሚል ነው።

የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት እንደ ጊዜ መግዣና እንደ ዳግም ዝግጅት የሚጠቀሙበት ጥቂት ግለሰቦች፣ አሁንም የሀገር ተስፋ የሆነውን ወጣቱን ለግል የስልጣን ጥማቸው ለመማገድ እያኮበኮቡ ነው። ሆኖም ግን ህዝቡ በተደጋጋሚ እያሳየ ያለው ፍላጎት ልማት፣ ደህንነትና መረጋጋት ብቻ ነው። የፌዴራል መንግስት የትግራይ ህዝብ ለሰላም እያሳየ ያለውን ጽናትና ለሁከት የማይገዛ ማንነቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ከጎኑ ሊቆም ይገባል። እነዚህ የጥፋት እርዝራዦች ሕዝቡን እንደማይወክሉ ግልጽ ነው። ሕዝቡ የሰላምን አየር መተንፈስ፣ የልማትን ፍሬ መቅመስ ይፈልጋልና!

በሰማያዊው ውቅያኖስ ላይ በኩራት የምናሰማራቸው መርከቦቻችን የኢትዮጵያን ታላቅነትና የማይበገር ማንነት ለዓለም ይመሰክራሉ። እኛ የባሕር ላይ ፈርጦች ነን! በትጋታችን ዓለምን እናገናኛለን፤ በ...
06/05/2026

በሰማያዊው ውቅያኖስ ላይ በኩራት የምናሰማራቸው መርከቦቻችን የኢትዮጵያን ታላቅነትና የማይበገር ማንነት ለዓለም ይመሰክራሉ።
እኛ የባሕር ላይ ፈርጦች ነን! በትጋታችን ዓለምን እናገናኛለን፤ በጠንካራ ክንዳችን የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ እናቀላጥፋለን። ይህ ተቋም ያንተ ነው፣ የኔ ነው፣ የእኛ ነው! የታላቅነታችን መገለጫ፣ የህዝባችን የጋራ ሃብት!

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ!

Beyond the SEA!

05/05/2026

Ethiopian Shipping and Logistics
Beyond the Sea!

ሀገር ማለት ተራራና ወንዝ ብቻ ሳትሆን፣ በዜጎቿ የሞራል ልክና በጋራ ህልማቸው ልቀት የምትገነባ ህያው አካል ናት። ዛሬ ግን ግብረገብነታችን እንደ አሮጌ ግድግዳ እየተሰነጣጠቀ፣ ለሀገር ግንባ...
04/05/2026

ሀገር ማለት ተራራና ወንዝ ብቻ ሳትሆን፣ በዜጎቿ የሞራል ልክና በጋራ ህልማቸው ልቀት የምትገነባ ህያው አካል ናት። ዛሬ ግን ግብረገብነታችን እንደ አሮጌ ግድግዳ እየተሰነጣጠቀ፣ ለሀገር ግንባታ የሚሆን ትኩስ ጉልበት በከንቱ ቅሬታ እና ብሶት እየተገበረ ይገኛል።

ብዙዎቻችን ያለፈውን ቁስል እንደ ትልቅ ሀብት አቅፈን እንኖራለን። ትላንት የሆነውን ነገር ለመቀየር በሚደረግ ከንቱ ጥረት፣ ዛሬ መከናወን ያለባቸው ትልልቅ ተግባራት ተዘንግተዋል። በታሪክ እዙሪት ውስጥ መሽከርከር ማለት፣ ፊት ለፊት ያለውን ብሩህ ተስፋ እያዩ በኋሊት መኪናን ለመንዳት የመሞከር ያህል አደገኛ ነው። በአሁኑ ወቅት ብሶት ማውራትና ቅሬታን መሸመት ትልቅ ገበያ ሆኗል። ለፈጠራ፣ ለሳይንስና ለልማት መዋል የሚገባው የአእምሮ ንቃት፤ ሰበብ በመፈለግና የሌሎችን ስህተት በመቁጠር እየባከነ ነው።

ብሶት ሻማ ነው፤ ለጊዜው በጨለማ ውስጥ ያለህን ቦታ ያሳይህ ይሆናል እንጂ፣ መንገዱን አያበራልህም፤ አይመራህምም።
ዛሬ የምናባክነው እያንዳንዱ ደቂቃ፣ ነገ ልጆቻችን የሚከፍሉት የዕዳ ደረሰኝ መሆኑን አንርሳ።

ዛሬ የምንገኝበት ምዕራፍ የጊዜ ሽግግር ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የታሪክ ትርክት በአዲስ መልክ የምንፅፍበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። ዓለም በቴክኖሎጂ ፍጥነት እየተናወጠችና የኢኮኖሚ አውታሮች በሰው ...
03/05/2026

ዛሬ የምንገኝበት ምዕራፍ የጊዜ ሽግግር ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የታሪክ ትርክት በአዲስ መልክ የምንፅፍበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። ዓለም በቴክኖሎጂ ፍጥነት እየተናወጠችና የኢኮኖሚ አውታሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተቃኙ ባለበት በዚህ ዘመን፤ ዘመናዊነትን ታጥቆ በንቃት መጓዝ ብቸኛ አማራጫችን ነው።

ይህንን እውነታ ቀድመው የተገነዘቡት መሪያችን፣ ሀገራችንን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ባለቤት ለማድረግ አርቆ አሳቢ እርምጃዎችን ወስደዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ መመስረቱና የተለያዩ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች መገንባታቸው፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የዲጂታል ፉክክር ውስጥ ቦታዋን እንድታረጋግጥ የተጣለ ጠንካራ መሰረት ሲሆን፣ ይህ ራዕይ ለነገው ትውልድ የእውቀትና የብልፅግና በር የሚከፍት የታሪክ አሻራ ነው።
ምክንያቱም የዓለምን ተሞክሮ ስንቃኝ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን ቀድመው የተገነዘቡ ሀገራት በቢሮክራሲና በሙስና የሚባክነውን ሀብት በማዳን፣ ለዜጎቻቸው ምቹና ቀልጣፋ ዓለም መፍጠር ችለዋል። በደቡብ ምስራቅ እስያ የታየው የኢኮኖሚ ተአምርም መነሻው የሰው ኃይልን በዲጂታል እውቀት ማስታጠቅና ቴክኖሎጂን ለምርታማነት ማዋል መሆኑን ልምድ ያስተምረናል።
ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ዲጂታላይዜሽን አማራጭ ሳይሆን የህልውናችን መሰረት ነው። አገልግሎቶቻችንን ከወረቀት ንክኪ ነፃ በማድረግ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ዘመናዊ ሥርዓት መዘርጋት ከአገልግሎት አሰጣጥ አልፎ ለዲጂታል ግብርና፣ ለተሳለጠ ሎጂስቲክስና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የማይተካ ሚና ይኖረዋል።
ስለሆነም፣ በመሪያችን የተጀመረውን ይህን ታላቅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ዳር ለማድረስና ራዕዩን እውን ለማድረግ ሁላችንም በቁርጠኝነት ልናግዘው ይገባል። እያንዳንዱ የፈጠራ ሃሳባችንና የምናስተዋውቀው አዲስ አሰራር የሀገራችንን ትንሳኤ የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ ዲጂታላይዜሽንን ለብሔራዊ ብልፅግናችን ዋስትና፣ ለነገው ትውልድ ደግሞ የማይደበዝዝ የታሪክ ውርስ እናድርገው።

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

እያንዳንዳችን የምንመኛት አንዲት የበለጸገች ሀገር አለች። ያቺን ሀገር እውን ለማድረግ ግን መነሻውም መድረሻውም አንድ ነው "አንድነት"ልዩነት ውበት ነው፣ አንድነት ግን ጥንካሬ ነው! የምንመ...
01/05/2026

እያንዳንዳችን የምንመኛት አንዲት የበለጸገች ሀገር አለች። ያቺን ሀገር እውን ለማድረግ ግን መነሻውም መድረሻውም አንድ ነው "አንድነት"
ልዩነት ውበት ነው፣ አንድነት ግን ጥንካሬ ነው! የምንመኛት ሀገር የምትገነባው በቃላት ሳይሆን በተግባር፣ በፉክክር ሳይሆን በትብብር ነው። ዛሬ የምናደርገው እያንዳንዱ የሰላምና የአብሮነት ጥረት ነገ ለምንገነባት ጠንካራ ሀገር መሰረት ነው። ዛሬ በምናያቸው ጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ከምናባክነው ጉልበት ይልቅ፣ በሚያስተሳስሩን የጋራ እሴቶች ላይ በማተኮር ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

30/04/2026

ታሪክ የሚለካው ባለፍንበት ፈተና ሳይሆን፣ በቆምንለት ዓላማ ነው። ዛሬ የምናየው ለውጥ የጥቂቶች ጥረት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመን ዳግም የመመለስ የጋራ ቃል ኪዳን ነው። እየገነባን ያለነው መንገድን ብቻ አይደለም፤ የተሻገረ ተስፋን እንጂ! እያለማን ያለነው መሬትን ብቻ አይደለም፤ የልጆቻችንን ብሩህ እድል እንጂ! መረጋጋታችን የብልፅግናችን መሰረት፣ አንድነታችን ደግሞ የድላችን ምስጢር ነው። ነገን ለመኖር ዛሬን እንስራ።

ዓላማችን አንድ፤ ግባችን ብሩህ ይሁን!

አንድ የማያወላውል እውነት አለ፤ የሀገር ትንሳኤና ሁለንተናዊ ለውጥ በምኞት ብቻ የሚገነባ ሳይሆን በተባበረ ክንድ የሚቆም ማገር ነው። ዛሬም ቢሆን የሀገራችን ማንሰራራት የማይዋጥላችሁ፣ ለተሻ...
29/04/2026

አንድ የማያወላውል እውነት አለ፤ የሀገር ትንሳኤና ሁለንተናዊ ለውጥ በምኞት ብቻ የሚገነባ ሳይሆን በተባበረ ክንድ የሚቆም ማገር ነው። ዛሬም ቢሆን የሀገራችን ማንሰራራት የማይዋጥላችሁ፣ ለተሻለ ነገ የራሳችሁን ድርሻ ሳታበረክቱ በአጋጣሚዎች ላይ ተቀምጣችሁ የሀገር ሸክም ለመሆን የምትመርጡ ጥቂቶች አይደላችሁም።
ልማትን በማንቋሸሽና የሚገነባውን በማጣጣል የምትቆም ሀገር የለችም። ሀገር ማለት የጋራ ጥረት፣ የፅናትና የትጋት ውጤት ናት። ቁጭ ብሎ መተቸት በሚቀልበት ሜዳ ላይ ሆናችሁ ለዘላቂ የሀገር ግንባታ የሚለፉትን መፈረጅ ከንቱ ድካም ነው።

እውነት ነው፣ በጉዟችን ውስጥ ተግዳሮቶች መኖራቸው የጥረታችን አንድ አካል ነው፤ ስህተቶችም ቢፈጠሩ ማረም የሚቻለው በስድብና በማማረር ሳይሆን ስነምግባር በተሞላበት በዳበረ ሀሳብና በተሻለ አማራጭ ሀሳብ ብቻ ነው። ዛሬ ሀገራችን ከእኛ የምትፈልገው አፍራሽ ትችትን ሳይሆን፣ ግባችንን የሚያሳካ አሰባሳቢና መፍትሄ አመንጪ በሳል አእምሮን ነው። ቆም ብለን እናስተውል፤ ሀገር የምትለወጠው በጩኸትና በቃላት ጋጋታ ሳይሆን በጋራ የመፍትሄ ባለቤት ስንሆን ብቻ ነው!

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

28/04/2026

ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ መዋቅራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅፋቶችን በስልታዊ አመራርና በህዝባዊ ተሳትፎ በስኬት እየሰበርን እንገኛለን። የሀገር ሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ነፃነት የጋራ ጥረታችን ውጤቶች መሆናቸውን በተጨባጭ እያስመሰከርን ነው። ቀደም ሲል ሊሳኩ የማይችሉ ተብለው የታሰቡ ግቦች ዛሬ በሥራችን ፍሬ አፍርተዋል። የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የምናደርገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Iftu Anwar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share