Lafto woreda 05 Communication

Lafto woreda 05 Communication peace for Ethiopia

ተስፋን መትከል ጀምረናል !!አንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር
03/08/2026

ተስፋን መትከል ጀምረናል !!
አንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር

ትውልዱ አሻራውን በደማቁ እያኖረ ነው - "ተስፋን እንትከል"በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 05
03/08/2026

ትውልዱ አሻራውን በደማቁ እያኖረ ነው - "ተስፋን እንትከል"
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 05

አረንጓዴ ዐሻራ - ለነገዋ ኢትዮጵያበላፍቶ-05  (በከፊል)
03/08/2026

አረንጓዴ ዐሻራ - ለነገዋ ኢትዮጵያ
በላፍቶ-05 (በከፊል)

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል 8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ​ለዚሁ የ...
03/08/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል 8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

​ለዚሁ የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በወረዳው በተለዩ ቦታዎች ሲሆን፣ የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን በሚጨምር መልኩ በባለሙያዎች ታግዞ እየተከናወነ ይገኛል።

​ዛሬ የሚተከለው ችግኝ የነገው ትውልድ ተስፋ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያውያንን በሐሳብ አንድ የሚያደርግና አስተሳስሮ አገሪቱን አረንጓዴ የማድረግ ጉዞ ነው።

​ዛሬ በሚከናወነው በዚህ ታሪካዊ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞች በኢትዮጵያውያን የተቀናጀ ህብረትና ተሳትፎ በአንድ ጀንበር ይተከላሉ።

​በወረዳው እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማማሩ አቦል ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች፣ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ሀምሌ 27/2018

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው​ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ተስፋን እን...
03/08/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

​ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል 8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

​ለዚሁ የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክፍለ ከተማው 17 ያህል ቦታዎች የተለዩ ሲሆን፣ የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን በሚጨምር መልኩ በባለሙያዎች ታግዞ እየተከናወነ ይገኛል።

​ዛሬ የሚተከለው ችግኝ የነገው ትውልድ ተስፋ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያውያንን በሐሳብ አንድ የሚያደርግና አስተሳስሮ አገሪቱን አረንጓዴ የማድረግ ጉዞ ነው።

​ዛሬ በሚከናወነው በዚህ ታሪካዊ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞች በኢትዮጵያውያን የተቀናጀ ህብረትና ተሳትፎ በአንድ ጀንበር ይተከላሉ።

​በክፍለ ከተማው እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራው፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ሀሰን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ 1ሚሊየን፤በኢትዮጵያ 800 ሚሊየን ችግኞች፤-በዛሬዉ እለት "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር በመዲናችን አዲስ አበባ 1ሚሊየን፤በኢትዮጵያ 800 ሚሊ...
03/08/2026

በመዲናችን አዲስ አበባ 1ሚሊየን፤በኢትዮጵያ 800 ሚሊየን ችግኞች፤-

በዛሬዉ እለት "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር በመዲናችን አዲስ አበባ 1ሚሊየን፤በኢትዮጵያ 800 ሚሊየን ችግኞችን ተፈጥሮ በለገሰችን ምድር ለመትከል ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የከተማችን ነዋሪዎች የራሳቸዉን ታሪካዊ አሻራ በማኖር ላይ ናቸዉ፡፡
#ተስፍን እንትከል

ስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር!የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በህዝባዊ ቁርጠኝነት እና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን አረንጓዴ እና ዘላቂነት ያለው ነገን መገንባት ይችላሉ በሚለው የጋ...
03/08/2026

ስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር!

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በህዝባዊ ቁርጠኝነት እና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን አረንጓዴ እና ዘላቂነት ያለው ነገን መገንባት ይችላሉ በሚለው የጋራ እሳቤ እየተመራ ይበልጥ እየጠነከረ ቀጥሏል። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ዐሻራ ለማሳረፍ በጋራ የሚሰባሰቡበት ዓመታዊው የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብራችን ነው።

ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር እንዲሁም ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የራሳችንን ዐሻራ በማሳረፍ ለዚህ የጋራ ጉዞ የበኩላችንን አስተዋፅኦ አበርክተናል። የተቀመጠውን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ታላቅ ግብ ለማሳካት በጋራ እየሰራን በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ቀኑን ሙሉ ጥረታችሁ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን የስነ-ምህዳር እና የኢኮኖሚ ችግርች በዘላቂነት እየፈታ ያለ ሀገራዊ ትልም ነው- አቶ አደም ፋራህበኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሀገራዊ ችግሮ...
03/08/2026

አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን የስነ-ምህዳር እና የኢኮኖሚ ችግርች በዘላቂነት እየፈታ ያለ ሀገራዊ ትልም ነው- አቶ አደም ፋራህ

በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

አቶ አደም ፋራህ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብርን በይፋ አስጀምረዋል።

አቶ አደም ፋራህ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፣ ዘንድሮ የሚከናወነው ተግባር ባለፈው ዓመት የተመዘገበውን የ714 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ ክብረ ወሰን በማሻሻል ለነገዋ የበለጸገች ሀገር አረንጓዴ መሰረት የሚጥል ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ነው።

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ2011 ዓ.ም ሲጀመር፣ ዋና መነሻው የኢትዮጵያን የተወሳሰቡ የስነ-ምህዳር እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ እንደነበር አቶ አደም አብራርተዋል።

ደን ሲጨፈጨፍ አፈር እንደሚሸረሸር፣ የውሃ ምንጮች እንደሚደርቁ እና የግብርና ምርታማነት በመቀነሱ ለስራ አጥነት፣ ለምግብ ዋስትና እጦት፣ ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪና ለሉዓላዊነት ስጋት እንደሚዳርግ የጠቆሙት ኃላፊው፤ መርሃ ግብሩ ይህንን የተሳሰረ የችግር አዙሪት ለመበጠስ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ብቻ 48 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።

በዚህም እንደ አቮካዶና ቡና ያሉ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸው ተክሎች በመተከላቸው የውጭ ምንዛሬ ግኝት አድጓል፣ የደን ሽፋን እየጨመረ፣ የስነ-ምህዳር ደህንነት እየተጠበቀ እና የውሃ አካላት እየታደሱ ይገኛሉ ብለዋል።

AMN

03/08/2026
03/08/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto woreda 05 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share