Lideta Woreda 3 Communication Office

Lideta Woreda 3 Communication Office govermental organization

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የአዲስ ዓመት በዓል ባዛር ተከፈተ።መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የተዘጋጀው የበዓ...
03/09/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የአዲስ ዓመት በዓል ባዛር ተከፈተ።

መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የተዘጋጀው የበዓል ባዛር ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሃይማኖት ዳንኤል በበኩላቸው ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ እንደ አቅማቸው ጥራት ያለውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ታስቦ የበዓል ባዛር መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ባዛሩ ከዛሬ ነሐሴ 28 ቀን እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የገለጹት ወ/ሮ ሃይማኖት ነዋሪዎች በቦታው በመገኘት እንዲገበያዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሺ እድገት በአንድነት ሸማቾች መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል ተመረቀበልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ሥር የሚገኘው የሺ እድገት በአንድነት ሸማቾ...
03/09/2026

የሺ እድገት በአንድነት ሸማቾች መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል ተመረቀ

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ሥር የሚገኘው የሺ እድገት በአንድነት ሸማቾች መሠረታዊ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበር የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል ተመርቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የገበያ ማዕከሉ በተለይም መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በበቂ መጠን፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች በማቅረብ የነዋሪውን የመግዛት አቅም ለማጠናከርና የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል አስተዋፅዖ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከሉ መመረቅ በበዓላት ወቅት የሚታየውን የሸማቾች የመግዛት ፍላጎት ለማሟላት፣ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግና ከአምራች ወደ ሸማች የሚደርሰውን የገበያ ሰንሰለት የበለጠ ለማሳጠር ጉልህ ሚና እንዳለው ተመልክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሐመድ በማዕከሉ ምርቃት ወቅት እንደገለፁት፣ ደረጃውን የጠበቀና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ያማከለ የገበያ ማዕከል ለነዋሪው ክፍት መሆኑ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል።

ኮሚሽነሯ እንዳሉት፣ ህብረት ሥራ ማህበራት የሸማቾችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ያላቸውን ሚና ይበልጥ እንዲወጡ በመደገፍና በመምራት ተመሳሳይ ተግባራት በቀጣይም በትኩረት ይሰራሉ ሲሉ ገልፀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና የሥራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ በዛብህ በበኩላቸው፣ ዛሬ የተመረቀው የገበያ ማዕከሉ የምርት እጥረትና የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ያስችላል ብለዋል።

የሸማች ማህበራት ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ህብረተሰቡን ለማገልገል በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ አዳሙ፣ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት እንዲችሉ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በማዕከሉ ምርቃት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ፣ ህብረት ሥራ ማህበራት የ«ይቻላል» መንፈስን በማጠናከር የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ምርቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ባዬ እንዳሉት፣ የህብረት ሥራ ማህበራት ዋና ተግባር ከትርፍ በላይ የአባላትንና የማህበረሰቡን ጥቅም ማስጠበቅ በመሆኑ፣ የተፈጠረውን የገበያ ዕድል በሚገባ በመጠቀም ህብረተሰቡን በተሻለ ደረጃ ማገልገል ይጠበቅባቸዋል።

አዲሱ የገበያ ማዕከል ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች በማቅረብ የአምራችና የሸማች ትስስርን ለማጠናከር፣ የምርት ተደራሽነትን ለማሻሻልና በአካባቢው የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተለይም በዓላት ወቅት የሚፈጠረውን የገበያ ጫና ለመቀነስ አቅርቦትን ማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ በመጠቆም፣ የገበያ ማዕከሉ በተለይም ለመጪው አዲስ ዓመት የሸማቾችን ፍላጎት ለማሟላት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በወረዳ 3 የተከፈተውን የየሺ እድገት በአንድነት ሸማቾች መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር የገበያ ማዕከል በመጠቀም ጥራት ያላቸውን የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች በአቅራቢያቸው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል።

የማዕከሉ መመረቅም የሸማቾችን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ፣ የህብረት ሥራ ማህበራት በገበያው ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና በማጠናከር ፍትሃዊ፣ ተደራሽና በሸማች ተኮር የገበያ ሥርዓት ለመገንባት የሚያግዝ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።

በልደታ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው የበዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ...
03/09/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ

መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው የበዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሐመድ፣ ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሚሽነሯ በ11 ክፍለ ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ መከፈታቸውን ገልጸው፣ ሸማቾች ከትራንስፖርት እንግልት ነፃ በሆነ መልኩ በየአቅራቢያቸው ከሚገኙ የሸማቾች ሱቆችና የባዛር ማዕከላት መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በበቂ መጠን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ በዛብህ በበኩላቸው፣ ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ እንደ አቅማቸው ጥራት ያለውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ታስቦ በክፍለ ከተማው በ15 አካባቢዎች የበዓል ባዛር መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ባዛሩ ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የገለጹት አቶ አዳሙ፣ ነዋሪዎች በተዘጋጁት የግብይት ስፍራዎች በመገኘት ግብይታቸውን እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው፣ የበዓል ባዛሩ ዋና ዓላማ በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የኑሮ ውድነትና የገበያ ጫና ለማቃለል መሆኑን ገልጸዋል።

በባዛሩ መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች በጥራት፣ በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች መቅረባቸውን ወ/ሮ ተስፋነሽ አስታውቀዋል።

በባዛሩ ይፋዊ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ነጋዴዎች፣ የነጋዴ ማኅበራት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

Today, I oversaw the signing of a landmark Framework for Cooperation between the National Bank of Ethiopia and the IFC to establish our country’s first dedicated Mortgage Refinance Company.

Capitalized at 100 Billion ETB, with the IFC set to contribute a minimum of $200 million, this wholesale institution will resolve long-standing liquidity mismatches in our banking sector and unlock accessible mortgage financing across Ethiopia.

This partnership is a critical step toward realizing our goal of delivering 1.5 million affordable, dignified homes for Ethiopian families while expanding private-sector participation in our financial system. Ethiopia continues to build a modern, resilient, and inclusive economy.
Abiy Ahmed Ali

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕ...
02/09/2026

የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው 33ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ በመዲናዋ ያለፉትን የትምህርት ስትራቴጂዎችን በማሻሻል በአዲስ ስትራቴጂ የሚመራበት ዓመት መሆኑ የዘንድሮውን ጉባኤ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

ባለፉት ጊዜያት ተረባርበን በሰራንባቸው የትምህርት ዘርፎች ላይ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ፣ በዚህም የተማሪዎች ውጤት ላይ ፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እና የአመራሩና የትምህርት ባለሙያው የጋራ ውህደት የተረጋገጠበት ሆኗል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን ገልጸው ፣ በዚህም በትምህርት ዘርፍ ውጤት እየመጣ ይገኛል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመዲናዋ ቀደም ሲል በደረጃ 4 ምንም የመንግስት ትምህርት ቤት ባልነበረባቸው አካባቢዎች ጭምር አሁን ላይ 23 ትምህርት ቤቶች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከቀዳማይ ልጅነት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ የሰጠው ትኩረትና እያከናወነው ያለው ተግባር ለዘርፉ ሰፊ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ፤ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የበለጠ ከፍ ለማድረግ የሁሉም አካል ርብርብ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ይህ ጉባኤ በቀጣይ በትምህርቱ ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት በርካታ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑም ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)
አብራርተዋል።

የልደታ ወረዳ 03 የአብነት ጤና ጣቢያ የክረምት በጎፍቃድ የማህበረሰብ ጤና ላይ በማተኮር ሙሉ  የነፃ ህክመና አገልግሎት እና የጤና ባዛር በአብነት አደባባይ አካሂዷል።ከተሰጡ የህክምና አገል...
01/09/2026

የልደታ ወረዳ 03 የአብነት ጤና ጣቢያ የክረምት በጎፍቃድ የማህበረሰብ ጤና ላይ በማተኮር ሙሉ የነፃ ህክመና አገልግሎት እና የጤና ባዛር በአብነት አደባባይ አካሂዷል።

ከተሰጡ የህክምና አገልግሎቶች መካከል ነፃ
1 የደምግፍት ልየታና ህክምና
2.የሰኳር
3. የአይን ህክምና
4. ከአንገት በለይ ህምና
5. የማህፃን በረ ጫፍ ካንስር
6. የጡት ካንሰር ምርመራ
7. የኤች አይ ቪ
8.የቲቢ
9.ሙሉ ህክምና የላብራቶሪና የመድሃኒት አገልግሎት ጨምሮ በአብነት አደባባይ ዝቅተኛ ገቢ ላለቸዉ ማህበረሰብ ተሰቷል።

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የትምህርት ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

ህብረተሰቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ።በልደታ ወረዳ 3 ምክር ቤት በተካሄደው የ14ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ህብረተሰቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ በት...
01/09/2026

ህብረተሰቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ።

በልደታ ወረዳ 3 ምክር ቤት በተካሄደው የ14ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ህብረተሰቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ በማጠቃለያ ተገልጿል።

የልደታ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ሀይማኖት ዳንኤል በበጀት አመቱ ውጤታማ ተግባሮች እንዲኖሩ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ውጤታማ መሆን የተቻለ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የህብረተሰቡን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የልደታ ወረዳ 3 ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት የተከበሩ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ የወረዳው ነዋሪ ያለምንም መሰላቸት በሁሉም ተግባር ላይ ተሳታፊነታቸውን በማሳየታቸው ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ ጉባኤው መጠናቀቁን ገልፀዋል።

የ2018 በጀት አመት በተሰሩ ተግባራት አጋዥ ለነበሩ አካላት እና የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስፈፃሚ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ።የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ምክር ቤት ...
01/09/2026

የ2018 በጀት አመት በተሰሩ ተግባራት አጋዥ ለነበሩ አካላት እና የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስፈፃሚ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የ14ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በ2018 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስፈፃሚ አካላት እና በተሰሩ ተግባራት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚህ መርሀ ግብር በበጀት አመቱ በተሰሩ በርካታ ተግባራተ ከምክር ቤቱ ጋር በመቀናጀት በመስራት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እና በበጀት አመቱ በምክር ቤቱ በተደረገ የማጠቃለያ ምዘና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እና እርካታ ከማሳደግ እንዲሁም የተሻለ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር ከ1-3 በመውጣት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የወረዳው ሴክተር ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Address

Around Abnet Square
Addis Ababa

Telephone

+251911260360

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta Woreda 3 Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Lideta Woreda 3 Communication Office:

Shortcuts

Share