Ethiopian Geological Institute

Ethiopian Geological Institute የሃገር ውስጥ የምርምር አቅም እንዲጠናከር በማድረግ፣ በተለያዩ የሥነ-ምድር ጥናት ዘዴዎች ምርምር ማካሄድ::

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብሩን በማረቆ ልዩ ወረዳ አከናወነ::(GIE) # # # # # # #(ነሐሴ 21/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ጂኦሎ...
27/08/2026

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብሩን በማረቆ ልዩ ወረዳ አከናወነ::

(GIE)
# # # # # # #

(ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብር አካል የሆነውን የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ በማከናወን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል።

በመርሃ ግብሩ የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ የተከናወነ ሲሆን፣ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ልጆች የሆኑ 100 ተማሪዎች ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የመማሪያ ቁሳቁሶችና ቦርሳዎች ድጋፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ማዕከል ያደረገ የልማት ስራዎች የሚከተል መሆኑን ጠቁመው ይህ በተግባር የሚገለጸው ህዝብን በቀጥታ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሥራዎች መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ ኢጃራ፣ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ልጆች የሆኑ 100 ተማሪዎች ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የመማሪያ ቁሳቁሶችና ቦርሳዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ተማሪዎችን መደገፍ የነገን ትውልድ መደገፍ መሆኑን ጠቁመው፣ አካባቢን መጠበቅም ለመጪው ትውልድ የተሻለ ሀገር ለማስረከብ የሚያግዝ ዘላቂ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብሩ አካል የሆነ የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ በልዩ ወረዳው መከናወኑ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ በማህበራዊ ኃላፊነቱ ለህብረተሰቡ የሚያበረክተውን ተግባር በቀጣይም እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ ያደረገው ድጋፍ የሚደነቅና የሚመሰገን መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ድጋፉ ተቸግረው ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ጉዟቸውን ለማገዝ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ የክትትል እና የእንክብካቤ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወን አቶ ጀማል ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬን ጨምሮ የልዩ ወረዳውና የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

"ኢትዮጵያ ሉአላዊነትዋን እያረጋገጠ የመጣው የማዕድን ዘርፍ ነው::" የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) (GIE) # # # # # # #(ሐምሌ 30,2018ዓ,ምየማዕድን ዘርፍ በ2018...
06/08/2026

"ኢትዮጵያ ሉአላዊነትዋን እያረጋገጠ የመጣው የማዕድን ዘርፍ ነው::" የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)

(GIE)
# # # # # # #
(ሐምሌ 30,2018ዓ,ም

የማዕድን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ "ኢትዮጵያ ሉአላዊነትዋን እያረጋገጠ የመጣው የማዕድን ዘርፍ ነው::" የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ሲሉ ገልጸዋል::

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡(GIE) # # # # # # #(ሐምሌ 30,2018ዓ,ም)በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ...
06/08/2026

ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡

(GIE)
# # # # # # #
(ሐምሌ 30,2018ዓ,ም)

በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡

የማዕድን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በበጀት አመቱ 44 ነጥብ 067 ቶን ወርቅ ማምረት ተችሏል፡፡
ከዚህ ውስጥ 40 ነጥብ 86 ቶን ያህሉ በባህላዊ ማዕድን አምራቾች የተመረተ ሲሆን፥ ቀሪው 3 ነጥብ 209 ቶን ወርቅ ደግሞ በኩባንያዎች መመረቱን ጠቁመዋል።
በዚህም ከወርቅ ምርት ከ5 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ዘርፉ አመርቂ ውጤት እንዲያስመዘግብ በጥናት እና ምርምር የአንበሳውን ድርሻ መያዙን በሪፓርቱ አመላክተዋል::

በአጠቃላይ ከማዕድን ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትሩ፥ በተያዘው የ2019 በጀት አመት 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን አመልክተዋል፡፡
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

05/08/2026
የሀገር በቀል ዛፎች ለደን መልሶ ማልማት ያለው ጠቀሜታ የደን መጨፍጨፍን፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋትን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ ትልቅ መሳሪያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢ...
03/08/2026

የሀገር በቀል ዛፎች ለደን መልሶ ማልማት ያለው ጠቀሜታ የደን መጨፍጨፍን፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋትን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ ትልቅ መሳሪያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ፡፡

(GIE)
# # # # # # #
(ሐምሌ 27/2018ዓ,ም)
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መልዕክት የሀገር በቀል ዛፎች ለደን መልሶ ማልማት ያለው ጠቀሜታ የደን መጨፍጨፍን፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋትን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ ትልቅ መሳሪያ እንደሆነ ገልፀዋል::

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

GIE # # # # # # #ሐምሌ 23/2018ዓ,ም
30/07/2026

GIE
# # # # # # #
ሐምሌ 23/2018ዓ,ም

በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት 14 የማዕድን አለኝታ ቦታዎች መለየታቸው ተገለጸ፡፡(GIE) # # # # # # #(ሐምሌ 20/2018 ዓ/ም)የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮ...
27/07/2026

በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት 14 የማዕድን አለኝታ ቦታዎች መለየታቸው ተገለጸ፡፡
(GIE)
# # # # # # #
(ሐምሌ 20/2018 ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈጻሚዎች የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 መሪ ዕቅድን ገመገሙ፡፡ በበጀት ዓመቱ 14 የማዕድን አለኝታ ቦታዎች መለየታቸውም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

በኢንስቲትየቱ በ2018 በጀት ዓመት (የብረት፣ ክሮማይት፣የፎስፌት፣ኒኬል፣ ሊቲየም፣ ታንታለም፣የኢንዱስትሪያል ማዕድናት፣የድንጋይ ከሰል፣የጌጣጌጥ ማዕድናት) በድምሩ 14 አለኝታ ቦታዎች መለየት ተችሏል፡፡ በተያያዘ መረጃ በሲዳማ ክልል እና በደቡብ ምራዕብ ኢትዮጰያ ሁለት የጂአተርማል አለኝታ ቦታዎቸ ተለይተዋል፡፡ የማዕድን ዘርፍ በማሳደግ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን በዚህ ረገድ አበረታች ውጤቶችን መመዝገባቸውን በአፈጻጸሙ ተመላክቷል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በሲዳማ ክልሎች ውስጥ ባሉ የተመረጡ የጥናት ቦታዎች (ይርጋለም፣ውጂግራ፣አርባ ጎና፣ ኪነዶ ሃላሌ፣በሌ፣ አረቃ፣ ከምባና ቤቶና መላ) የሥነምድር አደጋዎች እና የኢንጅነሪግ ጂኦሎጂ መረጃዎች በመሰብሰብ የሪፖርት ጥንቅርና ካርታ ሥራ ተጠናቆ ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ተደርጓል፡፡
የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይም በመወያየት ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ያለው ተቋም ለመገንባት የሚከናወኑትን ሥራዎች ለማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና ብልሹ አሰራሮች ለመፍታት በትኩረትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ አሳስበዋል፡፡
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:-https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

ኢንስቲትዩቱ በመጪው የክረምት ወራት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከወዲሁ ገለፀ፡፡(GIE) # # # # # # #(ሰኔ 26/2018ዓ/ም) ኢትዮጵያ ባላት መልካምድራዊ አቀማመጥ ...
03/07/2026

ኢንስቲትዩቱ በመጪው የክረምት ወራት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከወዲሁ ገለፀ፡፡

(GIE)
# # # # # # #
(ሰኔ 26/2018ዓ/ም)

ኢትዮጵያ ባላት መልካምድራዊ አቀማመጥ ለተለያዩ የስነምድር አደጋዎች ተጋላጭነቷ የጎላ እንደመሆኗ በሃገሪቷ በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ከፊል የደቡብ ምስራቅ ደጋማ ቦታዎች በክረምትና በበልግ ወቅት አንጻራዊ ከፍተኛና የተራዘመ ዝናብ የሚያገኙ አካባቢዎች ስለሆኑ ተደጋጋሚ የመሬት መንሸራተት ይስተዋላል፡፡

ከ60% በላይ የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰፍሮ የሚገኝባቸዉና መሰረታዊ ፍጆታዎችን ለማሟላት በሚደረግ የደን ምንጠራና የመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት በሚፈጠር የመሬት አለመረጋጋት በአካባቢዉ ላይ የመሬት መንሸራተት፣ መደርመስ፣ የአለት ናዳና መሰል የሥነ ምድር አደጋዎች ይከሰታሉ፡፡ ከመልካምድራዊ አቀማመጥ እና የአለት አወቃቀራቸው ዋነኛዉ ምክንያት ሲሆነ በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ዉስጥ የሚከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ለመሬት መንሸራተትና የአለት ናዳ እንዲከሰት እያደረገ ያለ ሌላ ተጨማሪ አነሳሽ ምክንያት ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የስነምድር አደጋዎችና ኢንጂነሪንግ ጂኦሎጂ ምርምር በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የሰነምድር አደጋዎችና ኢንጂነሪንግ ጂኦሎጂ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ የስነምድር አደጋዎች ተጋላጭነት ቦታዎችን በመለየት ገላጭ ሪፖርት በማዘጋጀት ላለፉት በርካታ አመታት ሲሰራ ቆይቷል አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ዘንድሮ ባካሄደው ጥናትና ምርምር በመጪው የክረምት ወራቶች በሚጥለዉ ዝናብ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከወዲሁ ገለፀ፡፡ በከፍተኛ ተዳፋታማ ቦታዎች ቀደም ሲል ለሥነ ምድር አደጋዎች የተጋለጡ እና አዲስ የመሬት መንሸራተት እንደሚከሰት ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ስለሆነም በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ከፊል የደቡብ ምስራቅ ደጋማ ቦታዎች አካባቢ ባለዉ ማህበረሰብ የህይወት መጥፋትና የንብረት ዉድመት አደጋ ከወዲሁ ለመከላከል እንዲረዳ ተቋሙ በጥናት የለያቸውን የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ አጋርቷል፡፡

የመሬት መንሸራተት መከሰትን አመላካች ምልክቶች፡-

Ø በፊት እርጥብ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ አዳዲስ ምንጮች መፍለቅና በፊት የነበሩ ምንጮች መጥፋት ወይም አቅጣጫ ቀይረዉ መዉጣት፡፡
Ø በመሬት ውስጥ በተለይም በዳገቶች ላይ የሚፈጠሩ ስንጥቆች
Ø የአፈር ፣ የድንጋይ ወይም የእፅዋት ቁልቁል ድንገተኛ እንቅስቃሴ መታየት
Ø ከዳገቶች ግርጌ ላይ የሚፈነዳ መሬት፣ የግፊት መጨመርን ያሳያል
Ø ያልተለመዱ ድምፆች በመሬት ዉስጥ መሰማት
Ø የአለቶች መሰነጣጠቅ
Ø የወንዞች በድንገት መደረቅና በድንገት የዉሀ መጠን መጨመር
Ø የቤቶች ማዘመምና የኮንክሪት ወለሎች መሰንጠቅ፡፡
Ø የውሃ መስመሮች እና ሌሎች የመሬት ውስጥ መገልገያዎች መቆረጥና መጣመም፡፡
Ø የቴሌፎን ምሰሶዎች፣ ዛፎች፣ ግድግዳዎች ወይም አጥሮች ማዘንበል።
Ø በሮች ወይም መስኮቶች ከበፊት ቦታቸዉ በመልቀቅ ለመዝጋትና ለመክፈት ማስቸገር፡፡
Ø ወ.ዘ.ተ…..

የመሬት መንሸራተት ከመከሰቱ በፊት ቅድመ እርምጃዎችን መውሰዱ በህይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

v መሬት ከመንሸራተቱ በፊት ምን መደረግ አለበት

Ø ገደላማና ተዳፋታማ ቦታወች አጠገብ፣ ከተራራ ስር፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መንገዶችና የዉሃ መዉረጃ ቦዮች ላይ በቅርብ ርቀት ቤቶችን አለመገንባት።
Ø የመሬት መንሸራተት ካሁን ቀደም ይከሰትበት በነበረ ቦታ ላይ በድጋሜ የመከሰት እድሉ ሰፊ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ።
Ø የመሬት መንሸራተት ምልክቶች ሲመለከቱ በፍጥነት ለሚመለከተዉ አካል ማሳወቅና መፍትሄ ማፈላለግ
Ø በአካባቢዉ ስላለው የአደጋ ምላሽ እና የመልቀቂያ ዕቅዶች ማወቅ።
Ø ለቤተሰብና ለራስ የድንገተኛ አደጋ እቅድ ማዘጋጀት።
Ø በዳገታማ ቦታወች ላይ ስር ሰደድ ዛፎችን መትከልና ተዳፋታማ ቦታወችን ለእርሻነት አለመጠቀም፡፡
Ø ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ መረጃወችን በመጠየቅ በሰዉ ህይወትና ንብረት ጉዳት እንዳይደርስ ሊወሰዱ ስለሚችሉ እርምጃዎች ባለሙያ መጠየቅ ማወቅ።
Ø ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ዞኖች ልማትን ለመገደብ የመሬት አጠቃቀም አከላለልን ተግባራዊ ማድረግ

ከመሬት መንሸራተት በኋላ መደረግ ያለባቸዉ ጥንቃቄዎች፡-

Ø አካባቢዉን ለቀው እንዲወጡ ከተነገረ በፍጥነት ወደተዘጋጀው የሕዝብ መጠለያ መሄድ፡፡
Ø ከሚንሸራተቱ አካባቢወች መራቅ።
Ø በባለሙያ የሚሰጡ መረጃወችን ማዳመጥና መተግበር።
Ø ከመሬት መንሸራተት በኋላ ሊከሰት ከሚችለው የጎርፍ መጥለቅለቅ እራስንና ንብረትን መጠበቅ።
Ø ወደ ተንሸራተተዉ ቦታ ሳይገቡ የተጎዱ ሰዎች ካሉ ማረጋገጥ።

መሬት በሚንሸራተትበት ጊዜ ምን መደረግ አለበት፡-

Ø ንቁ መሆን። ሰዎች በሚተኙ ጊዜ ብዙ ፍርስራሾችና ፍሰቶች ይከሰታሉ።
Ø መሬት ከሚንሸራተትበት አቅጣጫ በፍጥነት መዉጣት።

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የምስጋና ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።(GIE) # # # # # # #(ግንቦት 26/2018ዓ/ም)የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን...
03/06/2026

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የምስጋና ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።

(GIE)
# # # # # # #
(ግንቦት 26/2018ዓ/ም)

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን በወቅቱ በማስወገዱ እና ብክነትን በመከላከሉ ከፌደራል መንግስት ግዥ አገልግሎት የምስጋና ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል::

በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ንብረቶች በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከማችተው የቆዩትን በርካታ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎችን በስክራፕ እና በጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ አድርጓል::

በተጨማሪም ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መሥራች ለክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ አስረክቧል። በዚህም ኢንስቲትዩቱ ላበረከተው አስተዋፅኦ የምስጋና ዋንጫ ከፌደራል መንግስት ግዥ አገልግሎት ተበርክቶለታል ።

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Address

9. 0154525, 38. 8237591
Addis Ababa
486

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Geological Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share