Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን

Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን Ethiopian Intellectual Property Authority is responsible to provide adequate legal protection & prom

የጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ስናስብ ግዙፍ ሀገራዊ  ፕሮጀክቶቻችንን እያሰብን ብቻ ሳይሆን በቀጣይነትም የሚወጠኑትንና እውን የሚደረጉትን በማሰብ ጭምር ነው።
07/09/2026

የጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ስናስብ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቻችንን እያሰብን ብቻ ሳይሆን በቀጣይነትም የሚወጠኑትንና እውን የሚደረጉትን በማሰብ ጭምር ነው።

06/09/2026
የዕቅድ አፈጻጸምና ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም ተካሄደ ===================ባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም ነሐሴ 30/2...
06/09/2026

የዕቅድ አፈጻጸምና ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም ተካሄደ
===================
ባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ፕሮግራም ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት አካሄደ። ፕሮግራሙ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ በባለስልጣኑ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው መርጊያ ቀርቦ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ምን እንደሚመስልና በቀጣይ በጀት ዓመትም ምን መሠራት እንዳለበት አሀዝን መሰረት አርጎ ቀርቧል።

ይህም ሲባል በበጀት ዓመቱ 8492 ማመልከቻዎችን የተቀበለ መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም ከበፊቶቹ በጀት ዓመታቶች ጋር ሲነጻጸር በማመልከቻ ቅበላና ምዝገባ በየ ዓመቱ እየተሻሻለ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።

የአፈጻጸም ሪፓርቱ የአዕምሯዊ ንብረት ቅበላ ምን ያክል አደገ፣የሰው ኃይል መጠንን ማሳደግ፣ ምቹ ሥራ አካባቢን መፍጠር ስለበጀት አጠቃቀም፣የፋይናንስ ግዥ አስተዳደር አሠራር ውጤታማነት፣ ግልጽነት የሰፈነበት የሰው ኃይል ማሟላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት፣ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ የሚሉ ጉዳዮችን በስፋት ያካተተ ነው።

የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድም መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ማስታወቂያ ማስነገር ለማህበረሰቡ ስልጠና መስጠት ለውስጥ ሠራተኞች ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በትኩረት ሚሠራበት መሆኑ ተመላክቷል።

ከተሳታፊዎች ከተነሱ ሀሳቦች የሰው ኃይል ቢሟላ፣በዕቅድ መመራት ቢቻል ለአንድ አንድ የሥራ ክፍሎች የሥራ ላይ ስልጠና ቢሰጥ፣ ደረጃ ዕድገት ላይ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ቢሠራ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቢፈቱ፣ የተቋም የውስጥ አሠራር መመሪያ ቢኖር፣ ኢ ሰርቪስ አጠቃቀም መዘመን ቢችል የስልጠና አመራረጣችን ሚዛናዊ መሆን ቢችል ሚሉት ከብዙ በጥቂቱ የተነሱ ሲሆን በኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሉ ሞሲሳ ልንደርስበት ምንፈልገው ግብ ላይ ለመድረስ ግብዓቶች ይረዳሉ። በመሆኑም ለውጤታማነት ሚጠቅመን የጋራ ዓላማን ማወቅ፣ ኃላፊነትን መረዳት፣የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት አመለካከትን ማስፋት፣ ግልጽ የአገልግሎት አሰጣጥ መስፈርትን ማስቀምጥ፣ደረጃውን የጠበቀ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ ቴምፕሌት ማዘጋጃት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል። አያይዘውም በጋራ መሥራት ከምንም በላይ ውጤቱ የላቀ ስለሆነ የትብብር ሥራዎች ትኩረት ይሰጣቸው ብለዋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል በማጠቃለያቸው ሪፎርምን በተመለከተ ወደ ተቋሙ ከተቀላቀልኩበት ጊዜ ጀምሮ ህግን ማሻሻል፣ ዲጅታይዜሽን፣ ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠርና ሌሎችንም ትኩረት ባደረገ መልኩ እየሠራንበት የቆየን በመሆኑ የአሁኑ ሪፎርም ቀልጣፋ እንዲሆን አግዞናል ብለዋል። አያይዘውም እቅዳችን የሰፋበት ምክንያት ይች ሀገር ትልቅ ናት ስለዚህ ሰፋ ያለ ሥራ እንሠራለን ብለን ስላሰብን ሀገሪቷን የሚምጥን ዕቅድ መኖር አለበት ተግባራትንም በጽናትና በስፋት በመሥራት ውጤታማ መሆን እንደሚገባ በአጽኖት በመግለጽ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።

የአእምሯዊ ንብረትዎ ሀብት ነው!Your Intellectual Property Right is an asset!
03/09/2026

የአእምሯዊ ንብረትዎ ሀብት ነው!
Your Intellectual Property Right is an asset!

TikTok | Make Your Day

“I will always love you” ይህ ቀላል የሚመስል ሐረግ ከጀርባው ያለው ታሪክ ምንድን ነው?በ1973 Dolly Parton ከPorter Wagoner ጋር የነበራትን የሙያ አጋርነት ለ...
01/09/2026

“I will always love you” ይህ ቀላል የሚመስል ሐረግ ከጀርባው ያለው ታሪክ ምንድን ነው?

በ1973 Dolly Parton ከPorter Wagoner ጋር የነበራትን የሙያ አጋርነት ለማቋረጥ ስትወስን ፖርተር በውሳኔዋ ቅር ተሰኝቶ ነበር። ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ Dolly የራሷን የሙዚቃ መንገድ መከተል ፈለገች። እሱ ግን ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ታለንቷን አይቶ በ1967 ወደ ታዋቂው የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ያመጣት እሱ ነበር፤ እሷ ገና ከእርሱ ጎን መቆየት እንዳለባት ያምን ነበር፤ መለየቷን አይፈልግም ነበር። Porter Wagoner ለ Dolly Parton የስራ አማካሪዋ፣ የሙዚቃ እና የቴሌቪዥን አጋርዋ ብቻ አልነበረም፤ በሙያ መንገዷ ላይ ሁሉ ጉልህ ድርሻ የነበረው ሰው ነበር።

የእርሱ መከፋት ለእሷ ቀላል አልነበረም። በደል፣ ቂም ወይም ጥላቻ ስላለ የሚደረግ የመለያየት ውሳኔ አልነበረም የወሰነችው። የነፍስን ጥሪ ለመቀበል እና የመኖርን ዓላማ () ለመፈለግ በሚደረግ ጉዞ እና በክብር፣ በፍቅር እና በውለታ መካከል ያለውን ሚዛን ነበር ያጣቸው፡፡ አንድን ሰው እያከበሩ፣ እያመሰገኑ እና እየወደዱ ከእሱ መለየት ሲኖር የሚሰማ የሚያስጨንቅ ስሜት ላይ ነበረች።

በመጨረሻም Porter Wagoner ለዋለው ውለታና ለረዳት እርዳታ ሁሉ ምስጋናዋን፣ ክብሯን እና ፍቅሯን ለመግለጽ፣ እንዲሁም በውሳኔዋ ላይ የፀናች መሆኗን ለማሳወቅ “I will always love you”ን እንደ ስንብት ደብዳቤ አድርጋ ጻፈችው። በማግስቱ በቢሮው ውስጥ ዘፍና አሰማቸው፡፡ ዘፈኑን ከሰማ በኋላ Porter አለቀሰ፤ እናም እንዲህ አላት፡-
“That's the prettiest song I ever heard.”

ያን ጊዜ የሁለት ሰዎች ግጭት በአንድ ዘፈን ውስጥ ረገበ። ከዚያም Dolly መሄድ እንደምትችል ተስማማ፡፡ ነገር ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ፡፡ ቀረጻውን እሱ እንዲያዘጋጅላት ፈለገ። Dollyም ደስ አላት። የመጀመሪያውን ማስተር ሪከርዲንግ ቀረጸች፡፡ በ1974 ተለቀቀ፡፡ ከ19 ዓመታት በኋላ በ1992 Whitney Houston ዘፈኑን በራሷ ልዩ የድምፅ ቃና እና የሙዚቃ አቀራረብ እንደገና ቀረጸችው። ዓለምም ተናወጠ፡፡ የWhitney ቀረጻም ለ14 ተከታታይ ሳምንታት በBillboard Hot 100 ቁጥር 1 ላይ ቆየ፣ በ1994 Record of the Year እና Best Pop Vocal Performance, Female የGrammy ሽልማቶችን አሸነፈ። The Bodyguard soundtrack ደግሞ የዓመቱ ምርጥ አልበም (Album of the Year) ሆነ።

Dolly ዘፈኑን ፈጠረችው፤ Whitney ግን አዲስ ሕይወት ሰጠችው። አዲስ ሕይወት መስጠት የመጀመሪያውን ፈጣሪ መርሳት ማለት አይደለም። በቅጅ መብት ሕግም የcover version አዲስ የፈጠራ አስተዋጽኦ ሊኖረው ቢችልም፣ የመጀመሪያው የዘፈን ጸሐፊ የሙዚቃ ቅንብሩ እና ግጥሙ ላይ ያለው መብት የራሱ ይሆናል። ፈጣሪው ሥራውን ይፈጥራል፤ ሌላው አርቲስት አዲስ ሕይወት ይሰጠዋል፤ Copyright ግን የሁለቱን የፈጠራ አስተዋጽኦ በልዩነት ያከብራል።”

Dolly → Porter → መለያየት → ዘፈን → Whitney → The Bodyguard → Global Success → Copyright
በስሜነህ አንተነህ

የአእምሯዊ ንብረት ጋዜጣ ቅጽ 22 ቁጥር 50 ነሐሴ 22/2018IP Gazette Vol 22 No 50 August 28, 2026
29/08/2026

የአእምሯዊ ንብረት ጋዜጣ ቅጽ 22 ቁጥር 50 ነሐሴ 22/2018
IP Gazette Vol 22 No 50 August 28, 2026

የካንትሪ ሙዚቃ ሌጀንዷ ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች!ከ Joshua (1971) እስከ Tyrant (2024) ዘፈኖቿ ድረስ የተዘረጋው የ60 ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ለ...
26/08/2026

የካንትሪ ሙዚቃ ሌጀንዷ ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች!

ከ Joshua (1971) እስከ Tyrant (2024) ዘፈኖቿ ድረስ የተዘረጋው የ60 ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ለዶሊ ፓርተን “የካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት” የሚል ታላቅ የክብር ማዕረግ አጎናጽፏታል፡፡

ፓርተን እጅግ ብዙ ዜማዎችን ከደረሱ የሙዚቃ ሰዎች አንዷ ሆና አልፋለች። በእሷ ግምት ከ3,000 በላይ ዘፈኖችን የጻፈች ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከ1,000 በላይ የሚሆኑት ተቀርጸው ለሕዝብ ተለቀዋል።

በአልበም ደረጃ 49 የስቱዲዮ አልበሞችን ለቃለች፣ እንደ Jolene፣ I Will Always Love You፣ 9 to 5፣ Islands in the Stream እና Coat of Many Colors የመሳሰሉ ስኬታማ ዜማዎቿ በቢልቦርድ የካንትሪ ሙዚቃ ቻርት ላይ ለ25 ጊዜ ያህል ቁጥር 1 ደረጃን የያዙ ዘፈኖችን በማስመዝገብ ከማንኛውም ሴት የካንትሪ ሙዚቃ ድምፃዊ በላይ ቀዳሚ ሆናለች።

ዶሊ ፓርተን “ከካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት”ነት በተጨማሪም የፊልም ኮከብ እና ባለሀብት ነበረች። ስሟን ከአልባሳትና ከሽቶ እስከ ብረት ድስቶችና የቤት እንስሳት ምግብ ድረስ ላሉ የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶች የንግድ ምልክት (Trademark) አድርጋ አስመዝግባለች። በተጨማሪም Dollywood የሚለውን ስም ለመዝናኛ ፓርኳ፣ ለመዝናኛ አገልግሎቶች፣ ለጤናና እስፓ ማዕከል፣ ለሆቴልና ለሬስቶራንት ንግዶቿ በንግድ ምልክትነት አስመዝግባዋለች። የሙዚቃ አልበሞቿን የምታሳትምበትን Dolly Records የተሰኘውን የሙዚቃ መቅረጫ ድርጅቷንም የራሷ ብራንድ አድርጋዋለች። የንግድ ስሟ በዓለም ዙሪያ የታወቀ ሲሆን፣ የንግድ ሥራ ፈጠራዋንና የንግድ ኢምፓየሯን ይበልጥ አጠናክሮላታል።

ይህች ባለብዙ ፕላቲነም የሙዚቃ አልበም ባለቤት፣ የሆሊዉድ ተዋናይት፣ እና ባለሃብት የበጎ አድራጎትም ተምሳሌት ነበረች። ማንበብና መጻፍ የማይችለውን አባቷን ሮበርት ሊ ፓርተንን ለማክበር በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሕፃናት ከ200 ሚሊዮን በላይ መጻሕፍትን በስጦታ ያበረከተውን Imagination Library አቋቁማለች። በ2020 (እ.ኤ.አ) ለቫንደርቢልት ዩኒቨርሲቲ የቫይረስ ምርምር 1 ሚሊዮን ዶላር ያበረከተች ሲሆን፣ ይህም የሞደርናን የኮቪድ-19 ክትባት ፈጣን ውጤት ለማስገኘት ረድቷል።

ባጠቃላይ ዶሊ ፓርተን በደግነት እና በበጎ አድራጎት ተምሳሌትነቷ፣ በባለራዕይ ሥራ ፈጣሪነቷ እና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ዘፈኖችን በመፍጠር፣ የካንትሪ ሙዚቃን ለአለም በማስተዋወቅ ረገድ በነበራት ሚና ትውልድ ሲዘክራት ይኖራል፡፡ ዶሊ ሆይ በሰላም እረፊ!

በጣም ከምወድላት ዜማዎች እንዱ እና በ Country Music ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ የሆነውን፣ «Islands in the Stream»ን ተጋበዙልኝ፡፡

…Islands in the stream
That is what we are
No one in between
How can we be wrong? ...
— Written by Barry, Robin, and Maurice Gibb (Bee Gees)
በስሜነህ አንተነህ

የሥራ ዕድል Job Opportunities @የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንEthiopian Intellectual Property Authority
26/08/2026

የሥራ ዕድል
Job Opportunities @
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን
Ethiopian Intellectual Property Authority

24/08/2026

የስልጠና እድል / Training Opportunities

የፍላጎት መግለጫ ጥሪ፡ ነፃ የ World Intellectual Property Organization አካዳሚ የስልጠና እድል ለአፍሪካ ወጣቶች (ለኦክቶበር 2026 ሰልጣኞች)
በዚህ ተለዋዋጭና ዕውቀት በማይረጋበት ዓለም ውስጥ ራስን በሙያና በእውቀት ማበልጸግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) አካዳሚ # Project 1% for Africa በተሰኘ ፕሮግራም ስር ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የፍላጎት መግለጫ በመቀበል ላይ ይገኛል።
በዚህ ሙሉ በሙሉ በነፃ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ካላችሁ፣ እስከ ኦገስት 30 ድረስ በተያያዘው ሊንክ በመጠቀም ፍላጎቶን እንዲገልጹ እናሳስባለን። ፍላጎታቸውን ላወቁ ተሳታፊዎች በሙሉ የሴፕቴምበር 1 ቀን 2026 ይፋዊ የምዝገባ ሊንክ በኢሜይል ይላክላቸዋል።
የስልጠናው ዋና ዋና ነጥቦች
• ዓላማ፡ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ቢያንስ 1 በመቶ የሚሆነውን የአፍሪካ ወጣት በመሰረታዊ አእምሯዊ ንብረት እውቀት ማስታጠቅ (እስካሁን ከ11,800 በላይ ወጣቶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል)።
• የትምህርት ዘርፎች፡ የፓተንት እና የኢንዱስትሪ ንድፍ መብቶች፣ የንግድ ምልክት እና የጂኦግራፊያዊ አመላካቾች፣ የቅጂ መብት፣ ባህላዊ እውቀቶችና የጄኔቲክ ሀብቶች፣ እንዲሁም አእምሯዊ ንብረት ለልማት።
• ክፍያ፡ ሙሉ በሙሉ በነፃ (Fully Sponsored)።
• የስልጠናው አይነት፡ በኢንተርኔት (በራስ ጊዜ የሚሸፈኑ ሞጁሎች እና የቀጥታ ገለጻዎች)።
• ቋንቋ፡ በእንግሊዝኛ
• ጥቅሞች፡ ይፋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና ከፍተኛ ውጤት ለሚያመጡ ተሳታፊዎች የላቁ የ WIPO ትምህርቶች የስኮላርሺፕ እድል።
አስፈላጊ ቀናት
• የፍላጎት መግለጫ ማጠናቀቂያ ቀን፡ እ.አ.አ ኦገስት 30, 2026
• የኢሜይል መልእክት የሚላክበት ቀን፡ ሴፕቴምበር 1, 2026
• ይፋዊ የምዝገባ ጊዜ፡ ከሴፕቴምበር 1 እስከ ኦክቶበር 15, 2026
• የስልጠናው ጊዜ፡ ከኦክቶበር 7 እስከ ኖቬምበር 30, 2026
• የመጨረሻ ፈተና፡ ከኖቬምበር 27 እስከ 30, 2026
እድሉ እንዳያመልጥዎ - ዛሬውኑ ፍላጎቶን ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ያሳውቁ!
የሊንክዴን አካውንት የሌላችሄ በኮሜንት መስጫው ሴክሽን ላይ በሚገኘው ኤክስ ኤል ሸት ላይ መረጃውን ሞልታችሁ ወደ እኔ ላኩልኝ
Project 1% for Africa Learner Registration – Fill out form https://forms.cloud.microsoft/e/5jWKBEXqmw
1% Africa
Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን
Ethiopian Academy of Sciences
Arts Tv World
Ethiopian Broadcasting Corporation
Ethiopian Artificial Intelligence Institute- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት
Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia
Juliana Imam
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Amhara Culture Tourism & Sport Bureau
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia
Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
South Ethiopia Region Innovation and Technology Bureau
Bahir Dar University, Ethiopia
Addis Ababa Science and Technology University
Adama Science and Technology(ASTU) students
Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia
Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology
Debre Berhan University
Debre Tabor University Ethiopia
Debark University /ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ/official
Injibara University
Selam Ethiopia
CfCA - Connect For Culture Africa
PANAF
https://linkedin.com/company/wipo

Address

Addis Ababa
P.O.BOX25322/1000

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115527202

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን:

Shortcuts

Share