civil service

civil service We can change and develop our country of Ethiopia,

የሃማስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ በጋዛ በቁጥጥር ስር ዋለየእስራኤል የደህንነት ኤጀንሲ (ISA/Shin Bet) ልዩ ኃይሎች እና የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) በሰሜናዊ ጋዛ ባካሄ...
02/09/2026

የሃማስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ በጋዛ በቁጥጥር ስር ዋለ

የእስራኤል የደህንነት ኤጀንሲ (ISA/Shin Bet) ልዩ ኃይሎች እና የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) በሰሜናዊ ጋዛ ባካሄዱት የተቀናጀ ዘመቻ የሃማስ የሀገር ውስጥ ደህንነት (Hamas’ Internal Security) ኃላፊን በጋዛ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ህንፃ ውስጥ ገብተው በቁጥጥር ስር አውለውታል።
የሺን ቤት ልዩ ኃይሎች ወደ ህንፃው በመግባት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በሚያውሉበት ወቅት፣ የእስራኤል አየር ኃይል ለስምሪቱ ስጋት የሆኑ አካባቢዎችን በአየር ጥቃት መቷል። በእስራኤል ወታደሮች ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም።

የተያዘው የሃማስ ደህንነት ኃላፊ በሰሜናዊ ጋዛ የሃማስን ቁጥጥር መልሶ ለማጠናከር እና «ቢጫ መስመር» (Yellow Line) ተብሎ በሚጠራው ዞን ባሉ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃቶችን ለማዘጋጀት ሲሰራ የነበረ ነው።
ተጠርጣሪው ለተጨማሪ ጥልቅ ምርመራ ወደ እስራኤል ግዛት እንዲዛወር ተደርጓል።

የእስራኤል ወታደራዊ አካላት እንደገለጹት፣ ይህ ድንገተኛ ጥቃት በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኘውን የሃማስ የደህንነት እና የእዝ መዋቅር ለማፍረስ፣ ድርጅቱ በእስራኤል ዜጎች እና ወታደሮች ላይ ለማካሄድ ያቀዳቸውን ጥቃቶች ለማስተጓጎል የተደረገ ነው ብለዋል።

Via World News

የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን እንደዘገበው፡ በደቡብ ምስራቅ ኢራን በሚገኙት የቻባሃር እና ኮናራክ የወደብ ከተሞች ስድስት አዳዲስ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። ፍንዳታዎቹ የተሰሙት አሜሪካ በኢራን ል...
02/09/2026

የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን እንደዘገበው፡ በደቡብ ምስራቅ ኢራን በሚገኙት የቻባሃር እና ኮናራክ የወደብ ከተሞች ስድስት አዳዲስ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። ፍንዳታዎቹ የተሰሙት አሜሪካ በኢራን ልዩ ልዩ አካባቢዎች እያካሄደች ባለችው መጠነ ሰፍ ወታደራዊ ጥቃቶች ሳቢያ ነው ተብሏል።

Via World News

 #በኢራን ቀሽም ደሴት ስምንት ፍንዳታዎች ተሰሙ!በኢራን ደቡባዊ ሆርሞዝጋን ግዛት በሚገኘው የቀሽም ደሴት ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ስምንት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የሀገሪቱ ታስኒም የዜና ወኪል ...
02/09/2026

#በኢራን ቀሽም ደሴት ስምንት ፍንዳታዎች ተሰሙ!

በኢራን ደቡባዊ ሆርሞዝጋን ግዛት በሚገኘው የቀሽም ደሴት ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ስምንት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የሀገሪቱ ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።

World News

 | በኢራን በሚገኙ ኢላማዎች ላይ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ፈጸመየአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ማክሰኞ ዕለት በኢራን በሚገኙ የኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኢላማዎች ላይ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥ...
02/09/2026

| በኢራን በሚገኙ ኢላማዎች ላይ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ፈጸመ

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ማክሰኞ ዕለት በኢራን በሚገኙ የኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኢላማዎች ላይ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ።

ሴንትኮም በይፋዊ ኤክስ (X) ገጹ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ወታደራዊ እርምጃው የተጀመረው በምስራቃዊ አሜሪካ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6:00 (12 p.m. ET) ጀምሮ ነው።

ይህ የአሜሪካ ጦር እርምጃ፣ በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ወሽመጥ በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ የኢራን ጦር ኃይሎች የፈጸሟቸውን የጥቃት ሙከራዎች ተከትሎ የተወሰደ ቀጥተኛ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ ተሰማርተው በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ አባላት ላይ የተቃጡ ተመሳሳይ የጥቃት ሙከራዎች ለዚሁ የአየር እና ሚሳኤል ጥቃት ምክንያት መሆናቸውን ሴንትኮም አረጋግጧል።

በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፣ ከአሜሪካ ወታደራዊ ክፍሎች ተጨማሪ መግለጫ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Via World News

 | የኢራን አየር መከላከያ የአሜሪካን MQ-9 ድሮን መጣሉ ተገለጸየኢራን የአየር መከላከያ ኃይሎች በቅርቡ ሥራ ላይ ባዋሉት አዲስ የአየር መከላከያ ሥርዓት በመጠቀም የአሜሪካን MQ-9 ሰው ...
02/09/2026

| የኢራን አየር መከላከያ የአሜሪካን MQ-9 ድሮን መጣሉ ተገለጸ

የኢራን የአየር መከላከያ ኃይሎች በቅርቡ ሥራ ላይ ባዋሉት አዲስ የአየር መከላከያ ሥርዓት በመጠቀም የአሜሪካን MQ-9 ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (ድሮን) በኾሜይን ከተማ አየር ክልል ላይ መጣላቸውን የታስኒም ዜና ወኪል ዘጋቢዎች ዘገቡ።

World News

 ፡ ኢራን በአርቢል ዒራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ፈጸመችበኢራን በተፈጸመ ሚሳይል እና ድሮን ጥቃት በዒራቅ ኩርዲስታን ክልል በሚገኘው የአርቢል ከተማ ፍንዳ...
02/09/2026

፡ ኢራን በአርቢል ዒራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ፈጸመች

በኢራን በተፈጸመ ሚሳይል እና ድሮን ጥቃት በዒራቅ ኩርዲስታን ክልል በሚገኘው የአርቢል ከተማ ፍንዳታ መከሰቱን እና ከፍተኛ ጭስ ወደ አየር እየወጣ መሆኑን የሚያሳዩ ምስሎች ወጥተዋል።

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሰጠው መግለጫ፥ በአካባቢው እያካሄደ ያለው አጠቃላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አካል አድርጎ በአርቢል የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ተቋማትን ኢላማ ማድረጉን አረጋግጧል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ ባየለበት እና ሁለቱም ወገኖች
በመካከለኛው ምስራቅ ክልል ጥቃቶችን እየሰነዘሩ ባሉበት ወቅት ነው።

በጥቃቱ ሳቢያ በሰዎች እና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን አሁንም በግምገማ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

Via World News

ሩሲያ ኢራን ሱፐር ሶኒክ የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንድትገነባ በምስጢር እያገዘች መሆኑ ተጋለጠሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካን የአውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦች እና ሌሎች የጦር መ...
02/09/2026

ሩሲያ ኢራን ሱፐር ሶኒክ የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንድትገነባ በምስጢር እያገዘች መሆኑ ተጋለጠ

ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካን የአውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦች እና ሌሎች የጦር መርከቦች ላይ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ የላቁ ሱፐር ሶኒክ የክሩዝ ሚሳይሎችን በማልማት ሂደት ኢራንን በምስጢር እየደገፈች መሆኗን «ፋይናንሻል ታይምስ» ባወጣው የምርመራ ዘገባ ይፋ አደረገ።

«ሲ430ኤል» (C430L) የሚል የምስጢር ኮድ ስም የተሰጠውና ላለፉት በርካታ ዓመታት የዘለቀው ይህ ፕሮግራም እ.ኤ.አ. በ2023 የተጀመረ ሲሆን፤ በሩሲያ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን የሚሳይል ባለሙያዎች አሳታፊ አድርጓል። ይህ ወታደራዊ ትብብር በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ግጭት በነበረበት ወቅትም ጭምር መቀጠሉ ተዘግቧል።

የፋይናንሻል ታይምስ ምርመራ ዝርዝር መረጃዎችን የከተተባቸው ቴክኒካዊ ሰነዶች፤ ከተሾለኩ የሩሲያ የደብዳቤ ልውውጦች፣ የጉዞ መዝገቦች እና የጦር መሳሪያዎች የፓተንት ትንተናዎች የተገኙ ናቸው። ሂደቱም ከሞስኮ ወደ ቴህራን ከተደረጉ እጅግ ስትራቴጂካዊና ታላላቅ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ዝውውሮች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል።

የፕሮግራሙ ዋና ትኩረት የክሩዝ ሚሳይሎች ከድምፅ ፍጥነት በበርካታ እጥፍ እንዲበርሩ የሚያስችለውን «ራምጄት» (ramjet) የተባለውን የመገፍት ኤንጂን ቴክኖሎጂ ማስተላለፍ መሆኑ ታውቋል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ቴክኖሎጂው የባህር ኃይል መርከብ መቺ እና የምድር ላይ ጥቃት የክሩዝ ሚሳይሎችን ለመገንባት የታለመ ነው። ከድምፅን ፍጥነት በላይ የሚበሩ ሚሳይሎች ከፍተኛ ፍጥነትን ከዝቅተኛ የበረራ ከፍታ ጋር በማቀናጀት የአየር እና የሚሳይል መከላከያ ስርአቶች እንዳያገኙአቸውና እንዳያከሽፏቸው ጊዜውን በእጅጉ ያጥሩባቸዋል።

በኮንፍሊክት አርማመንት ሪሰርች የኢራን ሚሳይሎች ባለሙያና ከፍተኛ ተንታኝ ፋቢያን ሂንዝ «ይህ ኢራናውያን ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማግኘት ሲመኙት የነበረ እና ከሩሲያ የተደረገ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ዝውውር ነው» ብለዋል። አክለውም እንደዚህ ዓይነቱ መረሃ ግብር ከሩሲያ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ፈቃድ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሩሲያ የመንግስት የጦር መሳሪያ ላኪ የሆነው ሮሶቦሮንኤክስፖርት (Rosoboronexport) ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ከ2014 ጀምሮ በአሜሪካ ማዕቀብ ከተጣለበት ዋና የሩሲያ የሮኬት ዲዛይን ቢሮ «ኤንፒኦ ማሺኖስትሮየኒያ» (NPO Mashinostroyenia) ጋር በመተባበር ነው። የተሾለኩ የጉዞ መዝገቦች እንደሚያሳዩት የሩሲያ ባለስልጣናት እና ከፍተኛ መሐንዲሶች ውሉ ከኢራን የመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በህዳር 2023 ከመፈረሙ በፊት ወደ ኢራን ተደጋጋሚ ጉዞዎችን አድርገዋል።

እ.ኤ.አ. በ2025 የሩሲያ ወገን ከኢራን የተላኩ የራምጄት ስርአት ቴክኒካል መረጃዎችን በመቀበል የበረራ ሙከራዎችን መርምሯል፤ እንዲሁም እንደ የነዳጅ ስርአት፣ የቃጠሎ ተረጋጋጋነት፣ የአየር ማስገቢያዎች እና ኖዝሎች ባሉ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር መመሪያዎችን ሰጥቷል። የዚህ ሁለተኛው ምዕራፍ ውይይቶችም እስከ 2026 ድረስ ቀጥለዋል።

በዘገባው መሠረት ኢራን የራምጄት ሞተር ስርአትን ገንብታ የበረራ ሙከራዎችን አድርጋለች፤ ይሁን እንጂ በሩሲያ እገዛ የተሰራ ድምፅን ፍጥነት በላይ የሚበሩ የክሩዝ ሚሳይል ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት መግባቱን የሚያሳይ እስካሁን የተረጋገጠ ማስረጃ የለም።

World Daily News

 #በሆርሙዝ ወሽመጥ በሳዑዲ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ፊሊፒናውያን ተገደሉ።በሆርሙዝ ወሽመጥ ዉስጥ በሚገኝ አንድ የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በተሰነዘረ ጥ...
02/09/2026

#በሆርሙዝ ወሽመጥ በሳዑዲ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ፊሊፒናውያን ተገደሉ።

በሆርሙዝ ወሽመጥ ዉስጥ በሚገኝ አንድ የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ፊሊፒናውያን የባህር ላይ ሰራተኞች መገደላቸው ተረጋገጠ።

የሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ የመርከብ ትራንስፖርት ኩባንያ የሆነው «ባህሪ» (Bahri) ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በጥቃቱ ሳቢያ የሁለት ሕይወት ህይወት ማለፉን አስታውቋል።

እንደ ኩባንያው መግለጫ ከሆነ፣ «ሲድር» (SIDR) የተሰኘችው የነዳጅ ጫኝ መርከብ ጥቃቱ የደረሰባት ሰኞ ነሐሴ 31 ቀን ምሽት ስልታዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ሰላጥ አቋርጣ በማለፍ ላይ በነበረችበት ወቅት ነው። ኩባንያው በማህበራዊ ትስስር ገጹ (X) ላይ ባሰፈረው መልእክት፣ «መርከቧ የደህንነት አደጋ ገጥሟታል» ሲል ክስተቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የሁለቱን ፊሊፒናውያን ሰራተኞች ህይወት ማለፍ በሀዘን ገልጿል።

የጥቃቱን አፈፃፀም እና ከጀርባው ማን እንዳለ ኩባንያው እስካሁን ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፣ የዓለም አቀፍ የነዳጅ መስመር በሆነው በዚህ ቀጠና ውስጥ የተከሰተው አደጋ የአካባቢውን የደህንነት ስጋት እንደገና አያንሰራርቶታል።

Via World News

የኢራን የሚሳኤል ኃይል ሙሉ በሙሉ ማሳያ - ትኩረት የሚጠይቅ የጥንካሬ ማሳያ ነው፤ፅናትና ጥንካሬ የጠላት ማበርከኪያ ትልቁ መሳሪያ ነው።ክብር በፅናት ለሀገራቸው ባንዴራ ለሚዋደቁ ጀግኖች
28/08/2026

የኢራን የሚሳኤል ኃይል ሙሉ በሙሉ ማሳያ - ትኩረት የሚጠይቅ የጥንካሬ ማሳያ ነው፤
ፅናትና ጥንካሬ የጠላት ማበርከኪያ ትልቁ መሳሪያ ነው።

ክብር በፅናት ለሀገራቸው ባንዴራ ለሚዋደቁ ጀግኖች

ግሪክ ከቱርክ ጋር የተደረጉ ታሪካዊ ስምምነቶችን በመጣስ ከወራት በፊት የእስራኤል ፓትሪዮት የአየር መከላከያ ስርዓቶችን በኤጂያን ባህር ክልል ውሰጥ በሚገኝ በካርፓቶስ ደሴት ላይ በማሰማራት ...
28/08/2026

ግሪክ ከቱርክ ጋር የተደረጉ ታሪካዊ ስምምነቶችን በመጣስ ከወራት በፊት የእስራኤል ፓትሪዮት የአየር መከላከያ ስርዓቶችን በኤጂያን ባህር ክልል ውሰጥ በሚገኝ በካርፓቶስ ደሴት ላይ በማሰማራት ትልቅ ስህተት ፈጸመች።

ሆኖ ግን ቱርክ ይህንን እርምጃ እንደማትፈቅድ እና እንደምትበቀል ለአቴንስ ጠንካራ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ልከለች። እናም አቴንሰ በእነዚያ ደሴቶች ላይ የአንካራን ማሰጠንቃቂያ ችለ በማለት ድርጊቷን ብታጠናክር ኖሮ፣ ይህ በቀጥታ ለቱርክ ወታደራዊ የሀይል እርምጃ አጸፈዊ የአማራጭ እድልን እየፈጠረች እንደሆነ ግሪክ ሁኔታውን ተረድታ ሰረአቶቹን ወደኋላ በመመለሰ ከካርፓቶስ አስወጣች።

ይሁን እንጂ ግሪክ ወደኋለ ከፈገፈገች ከጥቂት ሰምንታት ቦኋለ ደግሞ ቱርክ በሰሜን ኤጂያን ባህር 22.000 ስኩዌር ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ክልል በቱርክ የውሃ ግዛት በማካለል ብሔራዊ የማሪታይም ፓርክ በሚል ስያሜ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አዋጅን በማጽደቅ አስደንጋጭ ውሳኔ አስተላለፋች። እናም ግሪክ ባለኮሰችው ድንገተኛ እሳት ቱርክ አጋጣሚውን ተጠቅማበት የራሷን እርምጃዎች በመውሰድ ለአቴንስ ቆረጥ ምለሸ ሰጠች።

በነገራችን ላይ ከቀናት በፊት ታዋቂው የቱርክ ጸሀፊ ኢብራሂም ካራጉል የቱርክን አቋም ሲገልጹ እንዲህ በማለት ነበር:- "ቱርክ አሰፈለጊ ከሆነ ቆጵሮስንና ግሪክን በመያዝ ሙሉ ወታደራዊ ጥቃት ትሰነዝራለች፣እንዲሁም እስራኤል እኛን ከጠቃች በመሬት፣ በባህር እና በአየር ትወርራለች"።

አለም ጠንካሮችን ብቻ ነው የምትመለከተው!!

Address

Hossana
Addis Ababa
261

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when civil service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share