በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን

በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ይህ የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የፌስቡክ ገፅ ነው።በዚህ ገፅ ወቅታዊ ከባቢዊ ፣ክልላዊ፣ሀገራዊ፣አህጉራዊ ብሎም አለም አቀፋዊ ተአማኒነት ያለቸው መረጃዎች ለተከታዮቻችን ይቀርቡበታል!
(2)

ጷግሜ 2 “የማንሰራራት ቀን” በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በድምቀት ተከበረ!ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)በስልጤ ዞን ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጷግሜ 2 ቀን "ዘላቂ ልማት...
07/09/2026

ጷግሜ 2 “የማንሰራራት ቀን” በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በድምቀት ተከበረ!

ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)

በስልጤ ዞን ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጷግሜ 2 ቀን "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል፤ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በዕለቱ በተካሄደውና የተለያዩ የከተማዋ ባለድርሻ አካላት፣ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት መርሃ ግብር ላይ፤ የከተማዋን ሁለንተናዊ ማንሰራራት እና በግልጽ የሚያሳዩ የከተማዋ አረንጓዴ ስፍራዎች ጉብኝት ተካሂዷል።

የተጎበኙ የአረንጓዴ ስፍራዎች ቀጣይ ወደ ፓርክነት በእንደሚያድጉ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በጉብኝቱም ወቅት በከተማዋ የሚገኙ እና ለምግብነት የሚውሉ ተክሎች (ፍራፍሬዎችና አትክልቶች) የለሙባቸው ስፍራዎች ተጎብኝተዋል።

ይህ ማህበረሰባዊ ተጠቃሚነትን ከከተማ ውበት ጋር ያያያዘው አረንጓዴ ልማት ስራ የከተማችንን የለምነት አቅም እና የነገ ተስፋ በጉልህ የሚያሳይ መሆኑም በዕለቱ ተገልጿል።

ከተማችንን በሁሉም ዘርፍ የብልጽግና እና የዕድገት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት እና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ አረጋግጧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌሰቡክ➲https://www.facebook.com/100069056625352/
ዩቲዩብ➲https:youtube.com/-f7l?si=Gs5LfmtbTH2MAtGn
ቴሌግራም➲https://t.me/alemgebeyacommunicationoffice
ቲክቶክ➲tiktok.com/
ኤክስ X➲https://x.com/alemgebeyacommu/status/1803607427415232695?t=6Ar4b99EJ3yLzGds4RQhDA&s=
ኢንስታግራም ➲https://www.instagram.com/alemgebeyacommnication/profilecard/?igsh=MWp6OGR6YWN2Z3VidQ==

 !ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጷግሜ 2 ቀን “የማንሰራራት ቀን”ን በማስመልከት በከተማ ግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለኃብቶች የስራ እንቅስቃ...
07/09/2026

!

ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)

በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጷግሜ 2 ቀን “የማንሰራራት ቀን”ን በማስመልከት በከተማ ግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለኃብቶች የስራ እንቅስቃሴዎች ተጎብኝተዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የጉብኝት መርሃ ግብር የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፤ በከተማዋ በከተማ ግብርና ዘርፍ ዘመናዊና ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ባለኃብቶች የልማት ስራዎች ታይተዋል።

ይህ የከተማ ግብርና ልማት የከተማችንን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ አረንጓዴና ፅዱ ከተማን እውን ለማድረግ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩም ለዘርፉ ባለሀብቶች እና አምራቾች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት እውን ለማድረግ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች እና ኢንተርፕራይዞች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ!ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)በስልጤ ዞን የ...
07/09/2026

የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት እውን ለማድረግ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች እና ኢንተርፕራይዞች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ!

ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)

በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጷግሜ 2 ቀን “የማንሰራራት ቀን”ን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የከተማዋን ኢንተርፕራይዞች ስራዎች በመጎብኘትና በሌሎች የተለያዩ ሁነቶች አክብሯል።

በዕለቱ በተካሄደው የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና ማህበረሰቡ ተገኝተዋል።

በጉብኝቱም በከተማዋ የሚገኙ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የተለያዩ ኢንተርፕራይዞች ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን ይህም የከተማዋን ኢንዱስትሪያዊ ማንሰራራት፣ (የምርት) አቅም እና የፈጠራ ስራዎች በግልጽ ያሳየ መድረክ ሆኗል።

የጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ረሻድ ሀሰን የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት እውን ለማድረግ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች እና ኢንተርፕራይዞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ረሻድ አክለዉም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለባለሀብቶች እና ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዉ አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌሰቡክ➲https://www.facebook.com/100069056625352/
ዩቲዩብ➲https:youtube.com/-f7l?si=Gs5LfmtbTH2MAtGn
ቴሌግራም➲https://t.me/alemgebeyacommunicationoffice
ቲክቶክ➲tiktok.com/
ኤክስ X➲https://x.com/alemgebeyacommu/status/1803607427415232695?t=6Ar4b99EJ3yLzGds4RQhDA&s=
ኢንስታግራም ➲https://www.instagram.com/alemgebeyacommnication/profilecard/?igsh=MWp6OGR6YWN2Z3VidQ==

 በከተማ አስተዳደሩ አቅመ ደካማ ወገኖችን የመደገፍ ሰብዓዊ ስራዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል!ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ዩኒት ከሰራ...
07/09/2026



በከተማ አስተዳደሩ አቅመ ደካማ ወገኖችን የመደገፍ ሰብዓዊ ስራዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል!

ዓ/ገበያ፣ ጷግሜ 02/2018 (ዓገከመኮ)

የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ዩኒት ከሰራተኛና ማህበራዊ እና ከኢንተርፕራይዝ ዩኒቶች ጋር በመተባበር በክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር እየተገነቡ ለሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶች ድጋፍ አድርጓል።

በክረምት ወራት በበጎ ፈቃደኞች ማህበረሰብ ተሳትፎ እየተገነቡ ለሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ የሚውሉ፤ ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች እና ባለድርሻ አካላት ያሰባሰባቸውን የበር እና የመስኮት ቁሳቁሶች ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።

ይህ በወጣቶች እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ የበጎ ፈቃድ ስራ የህብረተሰባችንን አብሮነት፣ ትስስር እና የእርስ በርስ መደጋገፍ ባህል የሚያጠናክር ተግባር መሆኑም ተገልጿል።

ለተቸገረ ወገን መድረስ የሁላችንም የሞራል ግዴታ ነውና፤ የበጎ ፈቃድ ማዕበላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!

#በጎነትለኢትዮጲያከፍታ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌሰቡክ➲https://www.facebook.com/100069056625352/
ዩቲዩብ➲https:youtube.com/-f7l?si=Gs5LfmtbTH2MAtGn
ቴሌግራም➲https://t.me/alemgebeyacommunicationoffice
ቲክቶክ➲tiktok.com/
ኤክስ X➲https://x.com/alemgebeyacommu/status/1803607427415232695?t=6Ar4b99EJ3yLzGds4RQhDA&s=
ኢንስታግራም ➲https://www.instagram.com/alemgebeyacommnication/profilecard/?igsh=MWp6OGR6YWN2Z3VidQ==

ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን!
07/09/2026

ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን!

 ጳጉሜ 1/2018
07/09/2026


ጳጉሜ 1/2018

 !ጳጉሜ 1/2018✍️  .የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር የሴቶች ማህበር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትኩረት  ላይ ተወያየ፤✍️ .በአለም...
07/09/2026

!
ጳጉሜ 1/2018

✍️ .የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር የሴቶች ማህበር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትኩረት ላይ ተወያየ፤

✍️ .በአለም ገበያ ከተማ የሚገኘው «ቆር ኮሌጅ» 82 ተማሪዎችን በውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና አስመዘና፤

✍️ .የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን አፈፃፀም ገመገመ፤

✍️ .በከተማ አስተዳደሩ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈንና ተረጂነትን በማስቀረት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ተገለፀ፤

✍️ .የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ የዘጠኛ ሳምንት አፈፃፀሙን ገመገመ፤

✍️ .የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ ማሻሻልና ህብረተሰቡን ያማከለ የቅድመ-መከላከል ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንደሚገባዉ ተገለፀ፤

✍️ .የአለም ገበያ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ፤

✍️ .በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 1 «የእመርታ ቀን» በድምቀት ተከበረ፤

✍️ .በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር “በአንድ ቀበሌ ሁለት መቶ በሬ የማድለብ” ኢንሼቲቭ በስፋት እየተተገበረ ነው፤

06/09/2026

በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን የመስክ ጉብኝት የቪዲዮ ፕሮዳክሽን በከፊል፦

06/09/2026
በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር “በአንድ ቀበሌ ሁለት መቶ በሬ የማድለብ” ኢንሼቲቭ በስፋት እየተተገበረ ነውጳጉሜ 1 ቀን 2018 የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን የእንስ...
06/09/2026

በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር “በአንድ ቀበሌ ሁለት መቶ በሬ የማድለብ” ኢንሼቲቭ በስፋት እየተተገበረ ነው

ጳጉሜ 1 ቀን 2018 የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን

የእንስሳት ሀብት ልማትን በማሳደግ የሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል “በአንድ ቀበሌ ሁለት መቶ በሬ የማድለብ” ኢንሼቲቭ በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር
በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌያት ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌያት በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተከናወኑ የሚገኙት ሥራዎች፣ የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድጉ ተጠቁሟል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share