29/07/2026
በአሜሪካ መንግሥት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል ከተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር የነበረን ፍሬያማ ቆይታ
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአሜሪካ መንግሥት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል የተመራን ከፍተኛ ልዑክ ተቀብለን የሥራ ጉብኝት አድርገናል። በቆይታችንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ፣ ኢንስቲትዩታችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ እያከናወናቸው ባሉ ዋና ዋና የምርምር እና ልማት ስራዎች ላይ ፍሬያማ ዉይይት አድርገናል።
ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል በበኩላቸው በኢንስቲትዩታችን በሮቦቲክስ፣ በሆሎግራም፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና በስታርታፕ ድጋፍ የታዩ ስራዎች ከጠበቁት በላይ እና ለአርአያነት የሚበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከጉብኝቱ ባሻገርም ሁለቱ ሀገራት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው የትብብር እድሎች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል። ኢትዮጵያን የኤአይ ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ የምናደርገውን ጉዞ በጋራ ጥረትና በትብብር አጠናክረን እንቀጥላለን!
A Fruitful Engagement with a High-Level Delegation Led by U.S. Deputy Assistant Secretary for Middle East and Africa, Mark Mitchell
We hosted and conducted a working visit with a high-level delegation led by Mark Mitchell, U.S. Deputy Assistant Secretary for Middle East and Africa, at the Ethiopian Artificial Intelligence Institute. During our time together, reflecting on the long-standing historical relations between the two countries, we held fruitful discussions on the key research and development initiatives our institute is carrying out in the field of artificial intelligence.
For his part, Deputy Assistant Secretary Mark Mitchell noted that the work demonstrated at our institute in robotics, holograms, natural language processing, and startup support exceeded expectations and serves as an exemplary model. Beyond the tour, we engaged in productive discussions regarding opportunities for collaboration where both nations can work together in AI technology. We will continue to strengthen our shared efforts and cooperation on our journey to position Ethiopia as an AI technology hub!