FDRE Defence War College

FDRE Defence War College FDRE Defence War College Ethiopia’s highest military academic & research institution that trains s

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ለ5ኛ ዙር  ያሰለጠናቸው  እስትራቴጂክ አመራሮች በዛሬ ዕለት አስመረቀ።የካቲት 20/2018  ዓ/ምየመከላከያ ዋር ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ለ5ኛ ዙር  ያሰለጠ...
28/02/2026

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ለ5ኛ ዙር ያሰለጠናቸው እስትራቴጂክ አመራሮች በዛሬ ዕለት አስመረቀ።

የካቲት 20/2018 ዓ/ም

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ለ5ኛ ዙር ያሰለጠናቸው እስትራቴጂክ አመራሮች በዛሬ ዕለት አስመርቋል ።

በምርቃቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ሌ/ጄኔራል በላይ ስዩም ናቸው ተማሪዎች ተመርቃቹ ወደ ስራ ገበታችሁ ስትመደቡ የሠራዊታችን የማድረግ አቅሙን የሚጨምር ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት ዉጤታማ አመራር በመስጠት የሠራዊታችንን ልዕልና እንድታረጋግጡ እያሳሰብኩኝ በዛሬ ዕለት የተመረቃችሁ አመራሮች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብሏል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በአለማቀፋዊ፣ አሁጉራዊ፣ ቀጠናዊ እንዲሁም ሀገራዊ የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች በአጭር ኮርስ በረጅም ኮርስ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ የትምህርት ፕሮግራም እያስተማረና እያሰለጠነ የወደፊት መሪዎች እያዘጋጀ ይገኛል።

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ  የፕሮፌሽናሊዚም ስርዓተ-ግንባታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህር ተሰጠ።የካቲት 17/2018ዓ/ምበመከላከያ ዋር ኮሌጅ የኘሮፌሽናል ሰራዊት ስርዓተ- ግንባታ ለ4ኛ ባች መደበኛ...
28/02/2026

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ የፕሮፌሽናሊዚም ስርዓተ-ግንባታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህር ተሰጠ።

የካቲት 17/2018ዓ/ም

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ የኘሮፌሽናል ሰራዊት ስርዓተ- ግንባታ ለ4ኛ ባች መደበኛ ተማሪዎችና ለ5ኛ ዙር አጭር ኮርስ ሰልጣኞች እንዲሁም ለእስታፍ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት ኮሎኔል ቶማስ አለሙ ናቸው።

የኘሮፌሽናሊዚም ባህሪና ሚና ምን እደሚመስልና በየተመደብንበት የስራ መስክ
ቴክኒካል ችሎታ ፣ ንድፍ ሀሳባዊ ችሎታ እና ሀለገብ ችሎታውን ሊያሳድግ የሚችል እስትራቴጂካዊ ዕውቀት መላበስጠ አስፈላጊ እንደሆነ ነው በውይይቱ የተገለፀው።

ማንኛው ፕሮፌሽናል የሆነ ሙያ ያለው ግለሰብ በህብረትም በጋራም ማህበረሰቡን የሚያገለግልበት እውቀትና ክህሎት ሊገነባ ግድ ይላል ነው ያሉት።

ከተለያዩ የፕሮፌሽናል ዓይነቶች በተለየ የመከላከያ ሰራዊታችን ህገ መንግታዊ ተልዕኮውን መጠበቅ የሚችልበት ሀላፊነት ስላለው ሙያዊ ስብዕና በጠበቀ መንገድ የሀገሩን ሉአላዊነት መጠበቅና ማስጠበቅ ግዴታ ስላለበት የተሻለ ግንዛቤ መውሰድ ይጠበቅበታል ነው የተባለው።

በፕሮፌሽናሊዚም የተገነቡ ተቋማት የተቋሙን መመሪያና ደንብ ተከትሎ ድርጅታዊ ባህልን ማዳበርና በየዕለት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ኘሮፌሽናል ሰራዊት ከተገነባ ለህዝብና ለሀገር ሊጠቅም የሚችል ተልዕኮና ራዕይ የሚያሳካበት አሰራር ይዘረጋል እንዲተገበርም ያደርጋል ተብሏል።

የፕሮፌሽኑ ዋና አንቀሳቃሽ እነ ማን እንደሆኑ መለየትና የሚመለከታቸውን የሙያ ዘርፎች ስልጠና በመስጠት አቅንም እንዲያዳብሩ ማድረግና የሚሰራው ስራ መቸ እና የት የሚለውን በመረዳት የሚገባውን በጀት በመመደብ ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የወታደራዊ ኘሮፌሽን ዋነኛ ተግባር መሪና ተመሪ መሰረት አድርጎ እንደሚገነባ ነው የተገለፀው።

የውትድርና ኘሮፌሽናሊዚም የህይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅና በተጨማሪም በተለያየ የሙያ ዘርፍ የሚያገለግል ክህሎትና ዕውቀት የሚጠይቅ እንደሆነ ነው በውይይቱ የተገለፀው።

በተለያየ የሙያና የዕውቀት ደረጃ ያለውን ማንኛውም ሙያተኛ ራሱን ማብቃትና ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ነው የተገለፀው።

በሀገራችን ያሉ ኘሮፌሽናሊዚም ሊያረጋግጡ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ የሠራዊታችን የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ጠቅሰው የተገነቡ ተቋማት ማሻሻልና ማዘመን ይጠበቅበታል ነው የተባለው።

በውስጣችን ያለውን የፕሮፌሽናል አቅም ለመገንባት መማር መሰልጠን ከማንኛው የፖለቲካ ድርጅት የፀዳ አስተሳሰብ በማዳበር ሙያዊ አቅም ማሳደግ አስፈላጊ ነው ብሏል።

ፕሮፌሽናል ሰራዊት ለመገንባት አፍርሶ ማደስ ሳይሆን ባለበት ሁኔታ በማስተካከልና በማዘመን እያሻሻሉ አቅም ማሳደግ አስፈላጊ ነው ብሏል ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶ ግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

28/02/2026
09/02/2026
በጄኔራል Teffahi Laid የተመራው የአልጀሪያ  ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዑካን ቡዱን  የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሎጅን  ትምህርታዊ ጉቡኝት አደረጉ።ጥር 25/2018 ዓ/ምበጄኔራል Teff...
02/02/2026

በጄኔራል Teffahi Laid የተመራው የአልጀሪያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዑካን ቡዱን የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሎጅን ትምህርታዊ ጉቡኝት አደረጉ።

ጥር 25/2018 ዓ/ም

በጄኔራል Teffahi Laid የተመራው የአልጀሪያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዑካን ቡዱን የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሎጅን ትምህርታዊ ጉቡኝት ሲያደርጉ በሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ገለፃ ተደርጓላቸዋል።

ልኡካን ቡድኑ በተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ የተሰማቸው ደስታ ገልፀው ጉቡኝቱ በኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅና በአልጄሪያ ዋር ኮሌጅ ያለውን የእርስ በርስ ትስስርና የእውቀት ሽግግር ያጠናክራል ብሏል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አለማቀፋዊ ይዘቱን ጠብቆ አገልግሎት ለመስጠት በአሰራር ስርዓትና በመሰረተ ልማት ዘመና ተቋም ለማድረግ በከፍተኛ ትጋት እየተሰራ ይገኛል።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

በኢትዮጵያ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በሚል ርእስ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲና በኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ  በትብብር የተዘጋጀው የምክክር መድ...
30/12/2025

በኢትዮጵያ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በሚል ርእስ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲና በኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በትብብር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ።

ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም

በኢትዮጵያ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በሚል ርእስ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲና በኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በትብብር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ተዘጋጅቷል።

በፓናል ውይይቱ አበይት ርዕሰ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ የሚዳሰሱ ሲሆን ታላላቅ የሀገራችን ሚጋ ፕሮጀክቶች ሲገነቡ የመከላከያ ሰራዊታችን የሚያበረክተው አስተዋፆኦም ከፍተኛ እንደሆነ የሚዳሰስ ይሆናል።

ሀገረ- መንግስት ለማፅናት የኢኮኖሚና የወታደራዊ አቅም ማጎልበትና ሜጋ ፕሮጆክቶችን በማልማት የሀገራችንን አይደፈርነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ።

በሀገራችን ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተገነቡ ያሉትን ሚጋ ኘሮጆክቶች ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ርብርብርብ ከፍተኛ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ከውይይቱ የሚጨበጡ ግቦች ተብለው የተዘረዘሩት :-
1ኛ የሀገራችን የመልማት ፍላጎትከፍተኛ እንደሆነ ፣
2ኛ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር መንግስት ግንባታ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ
3ኛ ሜጋ ፕሮጆክቶቾ የሚያጋጥማቸው ተግዳሮች የሚዳሰሱ ይሆናል
4ኛ ሜጋ ኘሮጆክቶች ሲገነቡ በቀጠናዊና አከባቢያዊ የበላይነትን ለማረጋገጥ ያለው አንድምታ፣
5ኛ ሜጋ ፕሮጆክቶች ሲገነቡ የመከላከያ ሰራዊታችን ያለው አስተዋፆ ከላይ የተዘረዘሩ አበይት ጉዳዮች በዉይይቱ መልስ ያገኛሉ ነው የተባለውን።

የክብር እንግዳው ክቡር ዶክተር ዲማ ነገዎ የሕ/ተ/ወ/ም/ቤት የዉ/መደ/ጉ/ቋ/ኮ/ሰ አንደገለፁት ሜጋ ፕሮጆክቶችን ሲገነቡ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የሚያጓላ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄነራል ቡልቲ ታደስ በበኩላቸው ከውይይቱ የሚገኝ ጠቀሜታ በመግለፅ ሜጋ ኘሮጀክቶች ሲገነቡ የእርስ በርስ ትብብር ያጠናክራሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣሉ እንዲሁም የኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ አቅምን ያሳድጋሉ ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ የመልማት አቅም፣ የመልማት ፍላጎት እና ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የሚገኙበት ሁኔታ በሚል ርዕስ የመጀመርያ ፁሁፍ ያቀረቡት ኮ/ል በላቸው ካህሳይ ናቸው።

የልማት ፕሮጀክቶች ለሀገር ግንባታና ለሀገረመንግስት ግንባታ ያላቸው አስተዋፆኦ እና ተያያዥ ፈተናዎች በሚል ርዕስ ሁለተኛው ፁሁፍ ያቀረቡት ዶክተር ስራው ደማስ ናቸው።

ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ኘሮጀክቶችን ለሀገር ግንባታ ለሀገረመንግስት ግንባታ ለአሁጉራዊ ትስስር እና የኢትዮጵያን ዓለማቀፋዊ ዕውቅና በሚል ሶስተኛ ፁሁፍ ያቀረቡት ክቡር ዶክተር ቀነዓ ያዴታ ናቸው።

በገለፃቸው እንዳብራሩት አረንጓዴ አሻራ፣የባህር በር የማግኘት መብት የኑኩሌር ማብላሊያ እንዲሁም በዲጅታላዜሽንና በግብርና ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብሏል።

የከተማ ኮሪደር ልማት በኢያንዳንዱ ከተማ እየተሳለጠ ይገኛል በመሆኑም አንድ ከተማ ሲለማ የሀገር ገፅታ ግንባታ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የልማት ፕሮጀክቶች ቀጠናዊና አሁጉራዊ ትስስር እና ለኢትዮጵያ ዓለማቀፍ ዕውቅና ያላቸው ሚና በሚል አራተኛ ፁሁፍ ያቀረቡት ዶክተር ግዛቸው አስራት ናቸው።

አወያይ ሌ/ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ የሁሉም ፁሁፍ አቅራቢዎች ጠቅለል ባለ መልኩ አስተያየት ሲሰጡ እንደገለፁት ለአንድ ሀገር እድገትና ልማት ለማረጋገጥ ብሔራዊ መግባባትና ኢኮኖሚያዊ፣ወታደራዊ እንዲሁም ዲፕሎማስያዊ አቅም መገንባት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብሏል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቶማስ ቱት የወደፊት አቅጣጫና የውይይቱ ማጠቃለያ ይሰጣሉ።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አራተኛ ባች መደበኛ ተማሪዎችና አምስተኛ ዙር አጭር ኮርስ ሰልጣኞች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ  ትምህርታዊ  ጉብኝት አደረገ።ታህሳስ 13/ 2018 ዓ/ም 4ኛ ባች...
22/12/2025

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አራተኛ ባች መደበኛ ተማሪዎችና አምስተኛ ዙር አጭር ኮርስ ሰልጣኞች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረገ።

ታህሳስ 13/ 2018 ዓ/ም

4ኛ ባች መደበኛ ተማሪዎችና 5ኛ ዙር አጭር ኮርስ ተማሪዎች የመማር ማስተማር አንዱ አካል የሆነውን በንድፍ ሃሳብ የተማሩትን በተግባር ለማየት የተለያዩ ትምህርታዊ ጉብኝቶችን በማድረግ የማጠቃለያ የትምህርት ኮርሶችን የሚሰጥበት አንዱ ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ማድረግ ነው።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ኘሬዝዳንት ወ/ሮ መሠረት ደስታ እና ዶክተር ወንድየ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልአከ ሲያስታላለፉ እንደገለፁት የመከላከያ ሰራዊታችን ሀገር ነው እኛ ደግሞ ሀገርን የሚመሩ አመራሮችን በማሰልጠንና በማስተማር ላይ እንገኛለን ለዚህም የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የእስትራቴጂክ አመራር ተማሪዎች ወደ ተቋማችን ስለመጣችሁ በጣም ደስታ ይሰማናል ብሏል።

በአፍሪካ ተቀዳሚ የሆነ የልህቀት ማዕከልና ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ያላቸው አመራሮችን በመፍጠርና ራስን ማብቃት በሚል መርህ እየተከተልን ከተለያዩ ተቋማት በጋር በመስራት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት።

ትራንስፎሜሽናል ሊደር ሺፕ የስትራቴጂክ አስተሳሰብ በሁሉም ደረጃዎች የለውጥ ኃይል እንዲሆንና አመራሩ በእውቀትና በክህሎት ዘመናዊ አመራር በመፍጠር ሂደት የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ነው የተገለፀው።

ስትራቴጂክ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ዓለምን የሚመለከቱበት ልዩ መንገድ አላቸው። ስኬታቸውም በመሠረታዊ ልማዶች ላይ የተመሠረተ ነው ።

ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ያላቸው አመራሮችን በማስተማርና በማሰልጠን አፍሪካን በአፍሪካዊያን እንድትለማና በቴክኖሎጂ እንድትበለፅግ የሰለጠነ የተመረጠ አመራር መፍጠር የሚያስችን ተቋም ተገንብቷል ነው ያሉት።

እስትራቴጂክ አመራር ሰንሰለትን በጣጥሶ መፍትሔ ማፍለቅ የሚችል በእውቀት የካበተና የነገ ተስፋን ማሳየት የሚችል አመራር መሆን አለበት ነው የተባለው።

እስትራቴጂክ አመራር የነበረውን የማይጠቅም የበፊት አስተሳሰብ ወደ ሚጠቀም አስተሳሰብን መቀየር የሚያስችል ለለውጥ የተዘጋጀ መሆን አለበት ነው ያሉት።

እስትራቴጂክ አመራር የወደፊትና አሁናዊው በማጣመር ለሚመራር ተቋምና ሀገር የወደፊት እጣፈንታን ብሩህ ለማድረግ የሚሰራና የሚያሰራ ነው ብሏል።

ስትራቴጂክ አመራር የወደፊት ራዕይን የሚታየውና ለውጥ የሚተጋ የእስትራቴጂክ እሳቤ ያለው ትልቅ ስዕል የሚታየው ከውጭ ወደ ውስጥ የሚመረምር እና ሲስተም የሚዘረጋ እና ወደፊት የሚያጋጡሙ ተግዳራትችን አሻግሮ በማየት መፍትሔ የሚያፈልቅ መሆን አለበት ነው የተባለው።

የስትራቴጂክ አመራር ፈጠራ፣ግልፅነት ተወዳዳሪነት እና ውሳኔ ሰጪ በጊዜና በሁኔታ የሚተጣጠፍ አካታችና በቅንጀት የሚመራ የተግባር መሪ መሆን አለበት ነው የተባለው።

ፈጣንና ተለዋዋጭ በሆነው የአለም ሁኔታ መረዳትና መገንዘብ የሚስችል እሳቤን ማፍለቅና መተግበር አስፈላጊ ነው ብሏል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ሀገር የሚገነባው የትምህርት ተቋማትን በመገንባትና በጋራና በትብብር የመስራት ነው ብሏል።

አካባቢያዊና ቀጠናዊ የደህንነት ሁኔታ በመረዳትና መፃኢ የሀገርና የተቋማት እጣ ፈንታ በመረዳት የመሪነት ሚናውን የተረዳና በእስትራቴጂክ አመራነት ለውጥ የሚያመጣና የሚያስቀጥል መሆን አለበት ነው ያሉት።
ወ/ሮ መሰረት በበኩላቸው ፈጠራ፣ ፍጥነት ፣ዝላይ መርህ አድርጎ የጎጠኝነትና የግለኝነት ድሪቶን ጥሎ ወደ ዲጅታል አርበኝነትና መልካም አስተዳደር በማስፈን ሁሉን አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የተለወጠ እሳቤ ማምጠት የሚችል አገልጋይ መሪ መፍጠር አስፈላጊ ነው ተብሏል።

ሴቶችን ለማበረታታት ለማብቃት እየተሰራ ያለ በርካታ ስራ እንዳለ ጠቅሰው ሃምስ ፐርሰንት በካቢኒ የሚሰሩ ሴቶች እንዳሉ ጠቅሰው ሴቶችም በራሳቸው የሚወጡት ሚና እንዳለ ተረድተው በትኩረት መስራትና መምራት ሴቶችን መደገፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ጉብኚዎች በአስተያየታቸው እንደገለፁት በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ የተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በቀሰሙት ትምህርታዊ ጉብኝት ለተቋማት ግንባት እንደሚጠቀሙበት ነው የገለፁት።

አያይዘውም ማህበረሰብን ሠራዊትም በእስትራቴጂክ ሲመራ በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ያተኮረ አሰራር መዘርጋትና ለውጥ ማምጣት የሚችል አመራር በመፍጠር ረገድ አፍሌክስ እና የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተስፋ ሰጪ ተቋማት ናቸው ተብሏል።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፈር ኢፍቱ ቢራቱ

ማቀድ ማስተማር  መከለስ  ማሻሻል ማስቀጠልየመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ ሙሁራን የመማር ማስተማሩን ሂደት የካሪኩለም ክለሳ ግብረመልስ ውይይት አየተካሄደ ነው ።ታህሳስ 11...
20/12/2025

ማቀድ ማስተማር መከለስ ማሻሻል ማስቀጠል

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ ሙሁራን የመማር ማስተማሩን ሂደት የካሪኩለም ክለሳ ግብረመልስ ውይይት አየተካሄደ ነው ።

ታህሳስ 11/ 2018ዓ/ም

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ ሙሁራን የመማር ማስተማሩን ሂደት የካሪኩለም ክለሳ ግብረመልስ ውይይት ሲደረግ በመክፈቻ ንግግር የጀመሩት የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የትምህርት ሂደት ጥራት ለመጠበቅና የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ ከተቋማት ጋር ግንኙነት በማጠናከር የውስጥ አቅም ማሳደግ ተገቢ ነው ብሏል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ የፀጥታና ደህንነት እስትራቴጂክ አመራሮች እያስተማረና እያሰለጠነ የቆየ ቢሆኑም እስከ አሁን በተከናወነው የመማር ማስተማር ሂደት በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚያስችል መልኩ መቃኘትና ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የአልሙናይ ተማሪዎችና የሌሎች ሙሁራን አስተያየታቸው በመቀበል አሰራራችን ለመከለስና ለማሻሻል እንደ ግብአት የምንጠቀመው ይሆናል ነው ያሉት።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ምክትል አዛዥ ለትምህርትና ስልጠና ዲን ብርጋዴር ጄኔራ ጥላሁን ደምሴ በበኩላቸው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተመሠረተው ሰባት ተከታታይ አመታት ያስቆጠረ መሆኑን ገልፀው ባሳለፋቸው አመታት በርካታ እስትራቴጂክ አመራሮች በመደበኛ ትምህርት፣ በአጭር ኮርስ፣ በተንቀሳቃሽ የስልጠና መስክ በርካታ አመራሮች አስተምሮ ያስመረቀ ኮሌጅ ነው ብሏል።

አደረጃጀቱና የአሰራር ስርአቱን በተለያየ ጊዜያት በመከለስና አቅሙን በማጠናከር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ካሊኩለም መከለስና ማዘመን አስፈላጊ ነው ብሏል።

የካሊኩለም ክለስው 12 ወራትን የፈጀ በርካታ ሙሁራን የተሳተፉበትና በጥናት ላይ ተደግፎ የተሰራ ስራ እንደሆነ ነው በገለፃቸው ያብራሩት።

በጥናቱ በተለያየ ጊዜያት በኮሎጁ የተማሩና ሌሎች ሙሁራን እንዲሁም የአካዳሚ ክፍሉን የተሳተፉበት ኘሮጀክት እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የኮርስ ኮንተንት የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም የሰው ሃይል ጥራትና አቅም እንዲሁም ከሌሎች ጋር በአብሮነት ከመስስራት ጋር ያለውን ክፍተት ለማየት ተሞክሮዋል ነው ያሉት።

አጠቃላይ የካሪኩለም ክለሳው በርካታ ሙሁራን የተሳተፉበት በጥናት ላይ የተደገና ሌሎችም ባለ ድርሻ አካላት ያሳተፈ በአለማቀፍ ደረጃ ሊየሰራ የሚችል የካሪኩለም በመሆኑ ተሣታፊዎች እና ሙሁራኑ ሰፊ ጊዜ ወስደው በቡዱን እየተወያይቡት ይገኛሉ፡፡

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራም ኢፍቱ ቢራቱ

PSI እና War College የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (ፒኤስአይ) እና  የኢፌዲሪ የመከላከያ ዋር  ኮሌጅ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረሙ።ታህሳስ 9/2018 ዓ/ምበ...
20/12/2025

PSI እና War College የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (ፒኤስአይ) እና የኢፌዲሪ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

ታህሳስ 9/2018 ዓ/ም

በትናትና ዕለት የመከላከያ ዋር ኮሌጅ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት በእስትራቴጂክ እና ሃገራዊ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተቋማዊ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ተቋማዊ ትብብርን በፖሊሲ ጥናትና ምርምር፣ በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች፣ በአቅም ግንባታ አብሮ ለመስራት እንዲሁም የተቀናጀና የተጠናከረ ሀገራዊ አጀንዳዎችን በፖለሲና በእስትራቴጂ አቅም ለማጎልበት በአንድነት መስራት በሚያስችል መልኩ በትብብር ለመስራት አስቻይ ስምምነት አድርገዋለል።

ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የኮሌጁን ራዕዩን፣ ተልእኮውን፣ እና የምርምር የትኩረቱን አቅጣጫ አብራርቷል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2010 ዓ.ም በይፋ በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር መቋቋሙንና በመደበኛነትም የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ተብሎ እንደሚጠራ ገልጿል። ኮሌጁ በብሔራዊ ደህንነት ጥናትና ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጓል ይሠራል ነው ያሉ።

የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ ሁኔታን እና የአለም አቀፍ ፀጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ በጂኦፖለቲካ፣ በፀጥታ፣ በአገራዊ ጥቅምና የወደፊት ስጋቶች ላይ እና በወታደራዊ ዲፕሎማሲ ላይ በርካታ ውይይቶችን እና አውደ ጥናቶችን እንደሚያዘጋጅ ነው በገለፃቸው የተናገሩት ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ።

ዲፕሎማሲ በኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር ተግባር ተሳትፎና አስተዋፅዖ፣ የኢትዮጵያ ጦርነት አስተምህሮ እና መርሆች፣ በአሚሶም እና በኤቲኤምኤስ የሚገኙ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አስተዋፆኦ እያበረከተ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ኮሌጁ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ፍልስፍና እና ታሪክ ላይ ያተኮረ ትልቅ ትምህርታዊ ፕሮጀክት በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝና በአምስት ጥራዞች ለህትመት በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ኮሌጁ እያካሄደ ላለው የማሻሻያ ጥረቶች በተለይም ከፍተኛ ጥራት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት ላይ እገዛን እንደሚያስፈልገው ነው የተጠየቀው።

የተመራማሪዎች እና የአስተማሪዎችን አቅም ማጠናከር; የምርምር እና የማስተማር እንቅስቃሴዎችን መደገፍና በወታደራዊ ተኮር የምርምርና ጥናት ላይ አትኩረት በመስጠት እንዲሁም በአገራዊ ደህንነትና አገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ላይ አውደ ጥናቶችን፣ ውይይቶች እና ፓናሎችን በሚያዘጋጀበት ጊዜ የ PSI ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ነው የተገለፀው።

አቶ ፋቃዱ ፀጋ የፖሊሲ ጥነት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ በሀገራዊና ቀጠናው የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በፖሊሲና እስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተቋማቸው. ዝግጁ መሆኑ ጠቅሰው ከተቋማቸው ለኮሌጁ. የሚደረግ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የብዝኃነታችንን  መገለጫ ቀን ነው።   የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ኀዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕገ- መንግሥታዊ ቃል...
08/12/2025

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የብዝኃነታችንን መገለጫ ቀን ነው።


የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ኀዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕገ- መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበትና የብዝኃነታችንን መገለጫ ቀን ነው አለ

የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ 20ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ ይላል።

ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሚገለጽ ብዝኃነት ባለቤት ናት፡፡ የቋንቋ፣ የባህል፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካዊ አመለካከት፣ የዕድሜ፣ የፆታ ብዝኃነቶቿ የሚያስጌጧት ድንቅና ቀደምት ሀገር ናት፡፡

ይህንን ብዝኃነቷን እንደ እሴት የምታዳብርበት፣ እሴቱን ወደ መፈጸም አቅም የምትለውጥበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት ባለቤትም ናት፡፡

ለዚህም ነው የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ በሆነው ሕገ መንግሥታችን አንድ የጋራ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በነፃ ፈቃዳችን የተስማማነው፡፡

ምንም እንኳን የሥርዐተ መንግሥት ታሪካችን በርካታ ሺህ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ሕገ መንግሥታዊ ልምምዳችን ግን በበቂ ያልዳበረ፣ ከአንድ ክፍለ ዘመን ያልተሻገረ ነው፡፡ ለዚህም ነው የዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ሂደታችን በምንሻው ልክ ያልጎለበተው፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐታችንን መሠረት ለማስያዝ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ስኬቶችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩና እንዲጠበቁ፣ የግልጽነትና ተጠያቂነት ሥርዐት እንዲጎለብት፣ ገለልተኛና ጠንካራ ሀገራዊ ተቋማት እንዲፈጠሩ፣ የሕዝቦች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሠራ አስደማሚ ስኬቶችም እየተመዘገቡ ነው፡፡

በሕገ መንግሥታችን ዕውቅና ያገኙ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአግባቡ እንዲከበሩና እንዲጠበቁ ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማት እየተገነቡ ነው፡፡
በማለት የመንግስት ኮሙኒክሽን አገልግሎት መግለጫ አውጥቷል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተሰጠው ተልዕኮ እና ራዕይ በመነሳት ብዝሃነትን በማስተናገድ ከተለያየ ክልሎች ጋር በመተባበር አለማቀፋዊ አህጉራዊ እና ቀጠናው እንዲሁም ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታ ሊረዱ ሊያስተባቡሩና ሊመሩ የሚችሉ እስትራቴጂ ክ አመራሮች እያሰለጠነ እያስተማረ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣ ላይ የሚገኘው።

ኢትዮጵያ ብዝኃነቷን የሚያስተናግድ ሥርዐት ዘርግታለች፡፡ ብዝኃነት ጌጧ እና ዐቅሟ መሆኑንም ተገንዝባለች፡፡
በውስጥ ባንዳዎችና በሩቅ ባዕዳን ሴራ ልዩነታችን መለያያችን ሆኖ ለዘመናት ተቀንቅኗል፤ አብሮነታችን ሲፈታተንና ከስኬታችን ሲጎትትም ኖሯል፡፡

ለዚህም ነው “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልእክት የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን እያከበርን የምንገኘው፡፡

ለመከላከል ዋር ኮሌጅ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ እንኳን ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ።

Address

Kore Square አምሰት ቁጥር ማዞሪያ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FDRE Defence War College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share