Ethiopian Railways Corporation

Ethiopian Railways Corporation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Railways Corporation, Government Organization, Addis Ababa.

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከኮሜርሺያልኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ..ማህ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ-----------------(ኢምባኮ ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም) የኢትዮጵያ የምድር ...
19/08/2026

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከኮሜርሺያልኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ..ማህ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
-----------------
(ኢምባኮ ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ኃላ.የተ.የግ..ማህ በጋር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ነሀሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ የተለያዩ የኢንጂነሪንግ፣ የመሰረተ ልማት እና የቢዝነስ አገልግሎቶችን በጋራና በትብብር ለመስራት የሚያስችል ሲሆን ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ሲያቀርባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ለማጠናከር እና በአዳዲስ የቢዝነስ መስኮች በጋራ ለመስራት መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ለረጅም ጊዜ አብረው ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም ኮርፖሬሽኑ በመንገድ፣ በህንፃ ግንባታና ማማከር ስራዎች እየሰራ በመሆኑና ኮሜርሺያል ኖሚኒስ በሪል ስቴት ዘርፍ ለመሰማራት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በኮንስትራክሽን እና የማማከር መስኮች በጋራ ለመስራት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ የመግባቢያ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ኃብት እና እውቀት በጋራ በመጠቀም ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበርክቱ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያሉ የኢንጂነሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎችን፣ የአዋጭነት ጥናቶች፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኒክ ስልጠናዎችን፣ የማማከር ሥራዎችን እና ሌሎች ተግባራትን የሚያከናውን ሲሆን በሌላ በኩል ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የንብረት እና ኃብት አስተዳደር፣ የሰው ሀይል አቅርቦት፣ ስልጠና፣ የካሳ ክፍያዎችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለኮርፖሬሽኑ ለማቅረብ የሚያስችለው ነው፡፡

ከባቡር መሰረተ-ልማት እስከ አረንጓዴ ኢኮኖሚ፦ የኢምባኮ ዘላቂ ቁርጠኝነት! (ኢምባኮ) — ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኢምባኮ) «ተስፋን እንትከል» በ...
03/08/2026

ከባቡር መሰረተ-ልማት እስከ አረንጓዴ ኢኮኖሚ፦ የኢምባኮ ዘላቂ ቁርጠኝነት!

(ኢምባኮ) — ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኢምባኮ) «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደውንና በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታለመውን ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በስኬት አከናወነ።

በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) እና የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በቢሾፍቱ ባቡር አካዳሚ በመገኘት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በዚህ መርሃ-ግብር የአካባቢውን የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ሀገር በቀል ዛፎች እንዲሁም ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ለምግብ ዋስትና አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዘመናዊ የባቡር መሠረተ-ልማት ዝርጋታ እና አገልግሎት ሀገራችን የያዘችውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይ ዕውን ለማድረግ ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

"ዛሬ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ ሀገራችን ያቀደችውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይ ዕውን የሚያደርግ ነው፤ ለነገው ትውልድ የተመቸች፣ አረንጓዴና ጽዱ ኢትዮጵያን ለማስረከብ በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ ሂደት ላይ በንቃት በመሳተፋችን የላቀ ክብር ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካባቢን ከአፈር መሸርሸርና ከተፈጥሮ አደጋዎች ከመጠበቅ ባለፈ፣ኮርፖሬሽኑ ከማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ያለውን መልካም ግንኙነትና አጋርነት ያጠናከረ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዕለቱ የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁና ለተፈለገው ውጤት እንዲበቁ አስፈላጊውን ክትትልና እንክብካቤ እንደሚያደርግ ያረጋገጠ ሲሆን፣ የአካባቢው ማህበረሰብም የዚሁ ዘላቂ ጥበቃ እና እንክብካቤ ባለቤት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

03/08/2026
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የባቡር ትራንስፖርት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን «ዘመነች ኢትዮጵያ» ፕሮግራም የተዘጋጀውን ልዩ ዶክመንተሪ ይመልከቱ!
23/07/2026

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የባቡር ትራንስፖርት
በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን «ዘመነች ኢትዮጵያ» ፕሮግራም የተዘጋጀውን ልዩ ዶክመንተሪ ይመልከቱ!

Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/c...

14/07/2026

Proud moment for Ethiopian Railways Corporation!

Congratulations to our 14 ERC professionals who successfully graduated from the 6th Cohort FIATA Diploma Program, organized by the Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA).

This internationally recognized qualification strengthens ERC's commitment to developing world-class expertise in railway transportation, logistics, and supply chain management—empowering our workforce to support Ethiopia's economic growth and regional connectivity.

Congratulations to all graduates on this outstanding achievement!


RESPECT ERC!!

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (EFFSAA) በ6ዙር በዓለም አቀፉ የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር (FIATA) የዲፕሎማ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸ...
14/07/2026

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (EFFSAA) በ6ዙር በዓለም አቀፉ የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር (FIATA) የዲፕሎማ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው ደማቅ ስነ-ስርዓት እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 14ቱ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ERC) ባለሙዎች ትምህርታቸውን በስኬት ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ ይህ እርምጃ ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ የባቡር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት እና የሎጂስቲክስ ኮሪደሮች ላይ ያለውን የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ ለሰው ኃይል ልማት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!!

የማምረቻ ማዕከሉ ስራ ጀመረ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በአዋሽ ኮምቦልቻ ወልዲያ /ሀራገበያ/ የባቡር ፕሮጀክት የሚገኘው የኮምቦልቻ ባቡር ጥገና እና የማሽነሪ አካላት የማምረት ስራ ...
30/06/2026

የማምረቻ ማዕከሉ ስራ ጀመረ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በአዋሽ ኮምቦልቻ ወልዲያ /ሀራገበያ/ የባቡር ፕሮጀክት የሚገኘው የኮምቦልቻ ባቡር ጥገና እና የማሽነሪ አካላት የማምረት ስራ በይፋ አስጀመረ፡፡

/ኢምባኮ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም/ የባቡር እና የማሽነሪ አካላት/መለዋወጫ/ማምረቻ ማዕከሉ በራስ አቅም ለማምረት የሚያስችሉትን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ወደ ስራ መግባቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው /ኢ/ር/ ገልፀዋል፡፡

በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁብታሙ ሀ/ሚካኤል፣የኢምባኮ ቦርድ ሰብሳቢ ብርሀኑ ተስፋዬ /ኢ/ር/ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት የመሠረተ ልማት አማካሪ ክቡር አቶ ደሴ አሰሜ፣ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የማምረቻ ማዕሉን ጎብኝተዋል፡፡
የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት የካምፖች፣ የሀዲድ መስመር እና የባቡር ጥገና ስራዎች የጀመረ ሲሆን የጥገና ሂደቱን በራስ አቅም በማከናወን በበተያዘለት ጊዜ አገልግሎት ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የአካባቢውን የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማነቃቃት እንዲሁም ለአገር እድገት ትልቅ መሰረት በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል፡፡

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለኮርፖሬሽኑ የስራ መሪዎች ስልጠና ተሰጠ(ኢምባኮ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን  የስራ ኃላፊዎች  ‹‹የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋ...
21/05/2026

ለኮርፖሬሽኑ የስራ መሪዎች ስልጠና ተሰጠ

(ኢምባኮ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ‹‹የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ›› በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በሃገራችን በየዘርፉ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ስነ-ምግባራዊ እንዲሆኑና በሚመሩት ዘርፍ የጥቅም ግጭትን ለመከላከልና ለማስተዳደር የሚያስችላቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት እንዲያዳብሩ የሚያስችል አቅም ማጎልበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በሲቪል ሰርቪስ ዪኒቨርሲቲ መምህርና ተባባሪ አማካሪ የሆኑት ዮሀንስ ጴጥሮስ(ዶ/ር) ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊነትና ተገቢነት ያላቸው ሃሳቦችን ያካተተ እና በሰራተኞች፤ በተቋማትና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት አስቀድሞ በማጤንና በመተንተን ውሳኔ መስጠት ለስራ አመራሮች ታማኝነትና ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ምንነት፤ የዘርፎች ተጋላጭነት፣ የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር፣ የስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች፣ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሰ ሲሆን የጥቅም ግጭት ሙስና እንዲስፋፋ ምቹ አጋጣሚዎችን ከሚፈጥሩ መንስኤዎች አንዱ በመሆኑ ይህንን መከላከል ተገቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

17/05/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Railways Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share