የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ በጎነት ግዴታ የሌለበት የህሊና ፈቃድና የውስጥ ደስታ ነው!
(4)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ ወዳጅነት ፓርክ ካስተላለፉት መልዕክት፦“በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ...
11/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ ወዳጅነት ፓርክ ካስተላለፉት መልዕክት፦

“በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው። ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል።”

Prime Minister Abiy Ahmed’s message about Friendship Park:

“Friendship Park, located in the heart of Addis Ababa, is one of the first multifunctional public spaces built by the Medemer Government over the past eight years. In the past four years alone, the park has generated close to one billion birr in revenue, while creating employment opportunities and economic benefits both directly and indirectly.”


በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ እና የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚ...
10/08/2026

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የኢትዮጵያ ወጣቶች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን እንዲቀላቀሉ እና የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎ይህ ዝግጅት የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የኢኒሼቲቩን ተመራቂዎች እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድነት ያገናኘ ነው። ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን በመፍጠርም፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል።

‎መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ኃላፊዋ በንግግራቸው የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።

‎በመቀጠል በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ልምዳቸውንና እይታቸውን ያካፈሉ አራት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ፓናሊስቶቹም፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሔም ደሴ፣ እንዲሁም የኢኒሼቲቩ ምሩቃን የሆኑት አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም ነበሩ።

ተሳታፊዎችና ወጣቶች ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣ በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉ እና በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች አበረታተዋል። ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው። ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ እና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።

Following Prime Minister Abiy Ahmed’s public call for Ethiopia’s youth to join the 5 Million Ethiopian Coders Initiative and expand its reach to 7 million participants by the end of the rainy season, the Office of the Prime Minister hosted an experience-sharing program on the Initiative. The event brought together certified graduates, industry leaders, policymakers, and young professionals to share their experiences and insights, while contributing to the advancement of the Digital Ethiopia 2030 agenda through practical digital skills development.

The program opened with a tour of an exhibition on Artificial Intelligence, followed by a followed by a keynote from Billene Seyoum, Head of the Press Secretariat at the Office of the Prime Minister, who framed youth technical capability as a vital national asset and reaffirmed the Prime Minister's call to reach 7 million coders this summer.

A panel discussion that ensured featured four speakers who shared their experiences and perspectives on the 5 Million Ethiopian Coders Initiative. The panel featured Dr. Abiyot Bayou, Senior Advisor to the Minister of Innovation and Technology; Bethlehem Dessie, CEO of gheero (ጊሮ); and Initiative alumni Azimeraw Taddese and Mahlet Seyoum, a tech entrepreneur. The panellists encouraged participants to continuously hone their skills, develop practical solutions, and contribute to growth and innovation within Ethiopia’s digital ecosystem.

The program concluded with an open networking session, during which young participants engaged the panellists with thoughtful and insightful questions. The exchange reaffirmed the 5 Million Ethiopian Coders Initiative’s role as a catalyst for developing digital talent and driving national transformation.

09/08/2026
በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ...
08/08/2026

በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በትጥቅ ትግል በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ወይም ፍላጎትን ለመጫን የሚደረግ ሙከራ እንደማይሳካ ገልጸው፤ በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች በርካታ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሳቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጫካ የቀሩትም ቢሆኑ በሂደት ነገሩ እየገባቸው ይመጣሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

መንግሥት በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን ፈትቶ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋ ቢሆንም፣ የተወሰኑ አካላት ግን ትናንት ካሰሯቸው እና ከገረፏቸው አካላት ጋር ድብቅ ጥምረት ፈጥረው ወደ ጫካ መግባታቸው አሳዝኖናል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ሰፊ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ተሳትፎ ዕድል በመኖሩ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በጫካ የሚገኘው የሸኔ ቡድን ግልጽ ዓላማ እና ግብ የሌለው "ተቀጣሪ ኃይል" ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ቡድኑ ሽፍታ ሆኖ ሰዎችን ከመግደልና ከመዝረፍ ውጭ የፖለቲካ ፍላጎቱን ማሳካት እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኦነግ መስራች ታጋዮች በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ እና በፓርላማ ተቀምጠው እየታገሉ ባሉበት ሁኔታ፣ በጫካ ያለው ቡድን የማንን አጀንዳ ይዞ እንደሚታገል ሕዝቡ ሊጠይቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ማንኛውም አካል ፍላጎቱንና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እና በምክክር ማሳካት እንደሚችል ያመላከቱት ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አሁንም ቢሆን የመንግሥት የሰላም በር ክፍት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የእኩልነት እንጂ የበላይነት አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው...
08/08/2026

የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የእኩልነት እንጂ የበላይነት አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በወቅታዊ የሀገራችን የፖለቲካ ትርክቶች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም፣ የኦሮሞ ሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎን በተመለከተ የሚንፀባረቁ ሁለት ጽንፈኛ እና ተቃራኒ ሀሳቦች፣ ፖለቲካዊ ብስለት የጎደላቸው ናቸው ብለዋል።

የመጀመሪያው ቡድን "ኦሮሞ ተረኛ ሆኗል" የሚል ትርክት የሚያራምድ መሆኑን አንስተው፣ ይህ ቡድን ከዚህ ቀደም ሀብት እና ንብረት ሲዘርፍ የነበረና አሁን ያ አድሏዊ የጥቅም መረቡ በመበጠሱ ምክንያት የሚያለቅስ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፣ "ኦሮሞ የሚገባውን አላገኘም" የሚል ትርክት የሚያራምደው ሁለተኛው ቡድን፣ "እኔ ካልመራሁ" በሚል አግላይ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተጠመደ እና የሌሎችን ኦሮሞነት ጭምር በጥርጣሬ የሚመለከት መሆኑን አብራርተዋል።

አያይዘውም፣ የሚገርመው ጉዳይ ግን እነዚህ እርስ በርስ የሚቃረን ሀሳብ ያላቸው ሁለት የተለያዩ ቡድኖች፣ መንግሥትን በማፍረስ እና ሀገርን በማተራመስ ዓላማ ላይ በአንድነት እየሠሩ መሆናቸው ነው ብለዋል።

ይህም፣ ተነሳሽነታቸው ከግል ጥቅም እንጂ ከሕዝብ እውነተኛ ጥያቄ የመነጨ አለመሆኑን በግልጽ ያሳያል ነው ያሉት።

የኦሮሞ ሕዝብ መቼም ቢሆን የሰውን ሀብት ቀምቶ እንደማያውቅ እና ይልቁንም ለጋስ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግሉ ዋና ዓላማም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት እና በጋራ በሕግ የበላይነት ስር መኖር እንጂ የሌላውን ነጥቆ የበላይነትን ለማረጋገጥ አለመሆኑን አስምረውበታል።

በማጠቃለያቸውም፣ ማንም አካል የኦሮሞን ሀብት በጉልበት ሊቀማ እንደማይችል በማስጠንቀቅ፣ አሁን ላይ ያለው መንግሥት የጋራ ሀብትን በሕግ አግባብ፣ የራስን ደግሞ በፍቅር እና በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ መንገድ የማካፈል ፖለቲካን እንደሚከተል አብራርተዋል።

የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን ፍላጎት ላላቸው የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ...
08/08/2026

የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን ፍላጎት ላላቸው የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ስለመጣሱ ተናግረዋል።

የህወሓት ቡድን ዳግም ለጦርነት እያደረገው ስላለው ዝግጅት በሰጡት አስተያየት፣ ቡድኑ አሁንም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት በነበረው አሮጌ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ እሳቤ እና አመራር ውስጥ ተቀርቅሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ቡድኑ ለ27 ዓመታት ሀገርን አስተዳድሮ ከወረደ በኋላም ራሱን እንደ ነጻ አውጪ ግንባር በመቁጠር የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሳይሆን የራሱን ጠባብ የቡድን ፍላጎት ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህም ባለፈ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ታጣቂዎችን እንደ እኩል አጋር ሳይሆን እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ በማድረግ ሀገርን የማፍረስ ዓላማ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ እንደሚገኝ እና ፌደራል መንግሥትም ይሁን ሌላ አካል አንድም ሜትር መሬትም ሆነ ሀብት እንዳልወሰደበት ገልጸዋል።

ይህም የቡድኑ ወቅታዊ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት እውነተኛ የሕዝብ ጥያቄን መሠረት ያደረገ አለመሆኑን እንደሚያሳይ አስምረውበታል።

ቡድኑ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ፍላጎት ላላቸው ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ብለዋል።

ቡድኑ በ1980ዎቹ መጨረሻ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን አግልሎ ሥልጣን እንደያዘበት ዓይነት አካሄድ በአሁኑ ወቅት በፍጹም ሊሠራ እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አሁን ያሉበት የፖለቲካ ንቃት እና ተሳትፎ ከትናንቱ በእጅጉ የተለየ መሆኑንም ተናግረዋል።

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጋቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ  ኃይሎች ዛሬ ጥምረት መፍጠራቸው እየተዳከሙ መምጣታቸውን ያሳያል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚ...
08/08/2026

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጋቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ጥምረት መፍጠራቸው እየተዳከሙ መምጣታቸውን ያሳያል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በሀገራችን ብሎም በኦሮሚያ ክልል ለሚታየው የጸጥታ ችግር መሠረታዊ ምክንያቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

ለችግሮቹ ዋና ዋና ምክንያቶች ያሏቸውም የፖለቲካ ሽግግሩ ተፈጥሯዊ ፀባይ፣ የሥልጣን ማዕከል ሽግግር እና የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ የተፈጠረ ያልተጠበቀ ጥምረት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የሥልጣን ማዕከል ሽግግሩን እና የፖለቲካውን ተፈጥሯዊ ፀባይ በተመለከተ ሲያብራሩ ቀድሞ ኢትዮጵያን በብቸኝነት ሲመራ የነበረው ቡድን ሥርዓቱ ሁሉንም አሳታፊ ወደሆነ መንገድ መግባቱን ባለመቀበል ሥልጣን በጉልበት ለመመለስ እያደረገ ያለው ጥረት ለግጭቶች መንስኤ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ እምነቶች፣ ቋንቋዎች እና ባህሎች ባለቤት በመሆኗ በአንድ ብሔር ወይም ቡድን የበላይነት ብቻ ልትመራ እንደማትችልም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ ስለተፈጠረው ያልተጠበቀ ጥምረት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ያልተቀደሰ ጋብቻ መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጓቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች፣ ዛሬ ተጣምረው መሰለፋቸው ምን ያህል እንደተዳከሙ እና ተስፋ እንደቆረጡ የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዚህም አልፎ እነዚህ ኃይሎች እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ የውጭ አካላትን ለእርዳታ እየጋበዙ መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ይህንን የተዛባ ትርክት በማረም እንዲሁም አፍራሽ ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት፣ ሁሉንም የሚያስታርቅ እና የተሻለ ሀሳብ የሚያመጣ ውህድ መንገድ መከተል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

08/08/2026

Turtii Oromiyaa Biroodkaastingi Neetwoork (OBN) waliin taasifame - Kutaa 2ffaa.

ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር የተደረገ ቆይታ - ክፍል 2

08/08/2026
ቀንዎን በጎ በማድረግ ይጀምሩ! ወደ 6400 A ብለው ይላኩ! "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!"
08/08/2026

ቀንዎን በጎ በማድረግ ይጀምሩ! ወደ 6400 A ብለው ይላኩ!

"በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!"

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share