Bole 05 communication

Bole 05  communication ፈጣን እና ተዓማኒነት ያለው መረጃ እናደርሳለን�

Permanently closed.
27/08/2026
27/08/2026

ፕሬስ ሪሊዝ
ምክር ቤቱ ጉባኤዉን ሊያካሔድ መሆኑ ተገለጸ!"
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ምክር ቤት የ2ኛ ምርጫ ዘመን 14ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ቅዳሜ ነሐሴ 23 /2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰአት ጀምሮ በወረዳው አደራሽ እንደሚካሔድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ዘላለም ተስፋዬ ገለጹ ።
የጉባኤዉ አጀንዳዎች
1.የ2ኛ ምርጫ ዘመን 13ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ተወያይቶ ማጸደቅ።
2.የ2019 በጀት አመት የምክር ቤቱ እቅድ ቀርቦ ተወያይቶ ማጸደቅ።
3.የ2019 በጀት አመት የማሕበራዊ ፍርድ ቤት እቅድ ቀርቦ ተወያይቶ ማጸደቅ።
4. የ2019 በጀት አመት የአስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር እና መደበኛ እቅድ ቀርቦ ተወያይቶ ማጸደቅ
5.የ2019 በጀት አመት የአስተዳደሩ በጀት እቅድ ቀርቦ ተወያይቶ ማጸደቅ።
6. የተለያዩ ሹመቶች በአስተዳደሩ ቀርበው መርምሮ ማጽደቅ እንደሆነ ተጠቁመዋል።
ቦሌ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

27/08/2026
የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ! ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና)   መርቀን ...
26/08/2026

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ!

ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና) መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የትራፊክ መጨናነቅን የሚያቃልሉ፣ የትራንስፖርት ሥርዓትን የሚያሻሽሉ፣ ህዝባችንን ከዝናብና ፀሐይ እንግልት የሚከላከሉ፣ በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ ምቹ ፣ ንፁህ እና የሰውን ክብር የሚመጥኑ የዘመነ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

መሰረተ ልማቶቹ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች፣ ሰፊ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች፣ ካፍቴሪያና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻና ማረፊያ ስፍራዎች፣ ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የአስተዳደር እና የትኬት መቁረጫ ቴክኖሎጂዎች፣ አሳንሰሮች እና ንፁህ መፀዳጃ ቤቶች እንዲሁም የደህንነትና የአደጋ ቅድመ መከላከል ሥርዓቶች የተሟሉላቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም እና ምንም ያልነበረንን ተርሚናል በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል ።
ለከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ቃላችንን በተግባር ስራዎችን እየፈጸምን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እንገኛለን። አዲስ አበባ ከዚህ በላይ ይገባታል ቀጣይም ከሰራነው በላይ እንተጋለን!

የዛሬዎቹ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ለተጋችሁ፣ ላስተባበራችሁ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች በዚህ ስራ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

26/08/2026
25/08/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው  የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉን  ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

24/08/2026

Address

Megenagna
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole 05 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share