A.A City Administration Code Enforcement Authority

A.A City Administration Code Enforcement Authority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from A.A City Administration Code Enforcement Authority, Public & Government Service, Addis Ababa City, Addis Ababa.

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥርአዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ  ስራዎች ብቻ ሳይ...
04/09/2026

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥር

አዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ ስራዎች ብቻ ሳይሆን፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ ለማድረግ አጠቃላይ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ማዕከል በሆነው የሰብዓዊ ልማት እና ትውልድን በማነጽ ላይ በሰራችው ስር ነቀል ለውጥ ጭምር ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም”ን በብቃት በመምራታቸው በዓለም አቀፉ “አክት ፎር ኤርሊ ይርስ” (Act For Early Years) ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው ተሸልመዋል። ይህ ትልቅ እውቅና ከተማዋን ለህፃናት የምትመች ከተማ እና ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ መዲና ለማድረግ የሰነቀችውን ራዕይ የሚያንፀባርቅ፣ እንዲሁም ለትውልድ ግንባታ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ያመጣውን ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።

የዚህ ስኬት እና የከተማዋ አስደናቂ እድገት ማሳያ የሆነው ከቁጥር በላይ የሆነው መረጃ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የሕፃናት ማቆያዎች መስፋፋት ነው። 20 የመጫወቻ ስፍራዎች ብቻ የተነሳው የከተማዋ አስተዳደር በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 5 ሺህ 500 ማድረስ ችሏል። በሌላ በኩል 5 ሺህ 3 የሚሆኑት የልጆችን የዕድገት ደረጃና ሥርዓት ታሳቢ ያደረጉ የመጫወቻ ቦታዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም የሕዝብ የሕፃናት ማቆያዎች ከ11 ብቻ ተነስተው በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 100 ደርሰዋል። ይህ በተለያዩ ሞዴሎች የተደራጀው የማቆያ ቁጥር በጥቅሉ 1 ሺህ 155 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሺህ 302 ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ይህ ስኬታማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በመዲናችን የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ሕፃናትን፣ በተለይም 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ታዳጊዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለሙ አምስት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

አዲስ አበባ ዛሬ አለምን ያስገረመችው እና የትኩረት ማዕከል የሆነችው በውብ የኮሪደር ልማቷ፣ በወንዝ ዳርቻዎቿ ውበት፣ ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቿ ብቻ አይደለም። ብሩህ አእምሮ ያለው ጤናማ ትውልድ በማፍራት፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ መሆኗን በተግባር በማሳየትና የዜጎችን በተለይም የሕፃናትን ሕይወት በሚቀይር የሰብዓዊ ልማት ሥራዋ ጭምር ነው። ይህ በሰብዓዊነት እና በትውልድ ላይ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት የመንግስትን የመደመር እሳቤ መሬት ያወረደ፣ ዜጎችን በአንድነት አስተባብሮ ከተማዋን እውነተኛ የብልፅግና ተምሳሌት ያደረጋት ሲሆን፣ ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድትቀዳጅ ያስቻላት ዋነኛ ሚስጥርም ይኸው ነው።

03/09/2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
03/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

02/09/2026

"መሰረተ ልማቶቻችን ዛሬን ብቻ ታሳቢ ያደረገ መሆን የለበትም"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን የሐረሪ ክልል የኮሊደር ልማቶችን ጥበቃ ስራና የምሽት የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎበኙ           26/12/20...
01/09/2026

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን የሐረሪ ክልል የኮሊደር ልማቶችን ጥበቃ ስራና የምሽት የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎበኙ

26/12/2018 ዓ.ም
****ሐረር****

የሐረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማት የተገነቡ ፕሮጀክቶችን እና የከተማ ቅርስነት ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥበቃ ላይ ትኩረት ሰቶ እየሰራ ያለው ስራ ልምድ ሊወሰደሰበት እንደመመገብ እንደሆነ ተገለፀ።

የሐረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት አባላት ለባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን የኮሪደር ልማት ጥበቃ ና ታሪካዊ ቦታዎች አስጎብኝተዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ           ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም               ****ሐረር**** የ...
01/09/2026

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ

ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም
****ሐረር****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር መሠረተ ልማት ጥበቃና የደንብ መቸላለፎች ቅድመ መከላከል እና ቁጥጥር
አስመልክቶ ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮው የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሳ አልዮ እና የተቋሙ ሰራተኞች አጋርተዋል።

በልምድ ተሞክሮ ልውውጡ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር አሰራሮች እና ተሞክሮዎች የሐረሬ ከተማ አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ ከመቅጣት ይልቅ በቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት አድርግው ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ለልዑካን ቡድን አባላቱ የሐረሪ ክልል የደንብ ማስከበር ፅ/ኃላፊ አቶ ኢብሳ አልዪ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገው ልምድና ተሞክሮአቸው አጋርተዋል።

መረጃው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕ...
01/09/2026

የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው 33ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ በመዲናዋ ያለፉትን የትምህርት ስትራቴጂዎችን በማሻሻል በአዲስ ስትራቴጂ የሚመራበት ዓመት መሆኑ የዘንድሮውን ጉባኤ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

ባለፉት ጊዜያት ተረባርበን በሰራንባቸው የትምህርት ዘርፎች ላይ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ፣ በዚህም የተማሪዎች ውጤት ላይ ፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እና የአመራሩና የትምህርት ባለሙያው የጋራ ውህደት የተረጋገጠበት ሆኗል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን ገልጸው ፣ በዚህም በትምህርት ዘርፍ ውጤት እየመጣ ይገኛል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመዲናዋ ቀደም ሲል በደረጃ 4 ምንም የመንግስት ትምህርት ቤት ባልነበረባቸው አካባቢዎች ጭምር አሁን ላይ 23 ትምህርት ቤቶች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከቀዳማይ ልጅነት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ የሰጠው ትኩረትና እያከናወነው ያለው ተግባር ለዘርፉ ሰፊ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ፤ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የበለጠ ከፍ ለማድረግ የሁሉም አካል ርብርብ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ይህ ጉባኤ በቀጣይ በትምህርቱ ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት በርካታ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑም ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)አብራርተዋል።
AMN

Address

Addis Ababa City
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A.A City Administration Code Enforcement Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to A.A City Administration Code Enforcement Authority:

Shortcuts

Share