12/10/2025
በአፋር ክልል በደረሰ የመሬት ወንቀጥቀጥ አደጋ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተገለጸ ።
በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ።
የሰሜናዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ አስሓብ የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል።
በአደጋው የ12 ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወት ሲያልፍ 6 ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የስረዱት ኃላፊው 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ መቅረታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለቱ ወረዳዎች መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ለተጎጂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚደረግ አመላክተዋል።
የባራሕሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን በበኩላቸው÷ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንተ ኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳወቁ.....