ከጨርቆስ ሰማይ ሥር

ከጨርቆስ ሰማይ ሥር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ከጨርቆስ ሰማይ ሥር, kirkos, Addis Ababa.
(1)

"ትናንት የዛሬ መነሻ፣ ዛሬ ደግሞ የነገ መሰረት ነው። ዛሬ ላይ ሆነን ወደ ኋላ ስንመለከት፣ እነዚያን የማይደበዝዙ ትዝታዎች ስናወሳ፣ ለዛሬው ማንነታችን ጉልበት፣ ለነገው ጉዟችን ደግሞ ስንቅ ይሆናሉ ። የማይደበዝዘው ትዝታ በጨርቆስ ምድር ሰላም...ፍቅር... አንድነት

04/09/2026
የበግተራና አከባቢው ጤና ስፖርት ማሕበር ለቅዱስ ቂርቆስ እግር ኳስ ክለብ ላስመዘገበው ድል የተሰማውን ደስታ በአባላቱ ስም የበግተራ አከባቢው ጤና ስፖርት ማሕበር ሊቀመንበር  አቶ ያለው አየ...
03/09/2026

የበግተራና አከባቢው ጤና ስፖርት ማሕበር ለቅዱስ ቂርቆስ እግር ኳስ ክለብ ላስመዘገበው ድል የተሰማውን ደስታ በአባላቱ ስም የበግተራ አከባቢው ጤና ስፖርት ማሕበር ሊቀመንበር አቶ ያለው አየለ አማካኝነት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

02/09/2026

የሚገርም ጎል የሴካ ልጅ ባባ ልክ እንደ አባቱ ሰይፈ ደምሴ ያለው ወኔ ጨዋታውን የመምራት የተከላካይ መስመሩ አለማስደፈር በዘንድሮ ውድድር የሚገርም ብቃት ነበርው !!

በኤጂያን ባሕር ለ3 ሰአታት በመዋኘት የ20 ስደተኞችን ሕይወት ያዳነችው የ17 አመቷ ታዳጊ የ17 ዓመቷ ሶሪያዊት ታዳጊ ዩስራ ማርዲኒ በኤጂያን ባሕር (Aegean Sea) ውስጥ ለሦስት ሰዓታ...
02/09/2026

በኤጂያን ባሕር ለ3 ሰአታት በመዋኘት የ20 ስደተኞችን ሕይወት ያዳነችው የ17 አመቷ ታዳጊ

የ17 ዓመቷ ሶሪያዊት ታዳጊ ዩስራ ማርዲኒ በኤጂያን ባሕር (Aegean Sea) ውስጥ ለሦስት ሰዓታት በመዋኘት የ20 ስደተኞችን ሕይወት ማዳን ችላለች::

ዩስራ እና እህቷ ሳራ ከሶሪያ በመሸሽ ወደ 20 የሚጠጉ ሰዎችን በጫነችና በተጨናነቀች ጀልባ ተሳፍረው ከቱርክ ወደ ግሪክ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ ሳሉ የጀልባዋ ሞተር ተበላሽቶ ውኃ ማስገባት ይጀምራል ቀጥሎም እህትማማቾቹ እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ወደ ባሕሩ በመግባት ሁሉም ሰው ሰላማዊ ቦታ እስከሚደርስ ድረስ ጀልባዋን ከሦስት ሰዓታት በላይ እየመሩ የሰዎቹን ህይወት ታድገዋል።

ይህን የተበላሸውንና ሊሰጥም የነበረውን ጀልባ ዋናተኛ በመሆኗ ወደ አስተማማኝ ቦታ ለመምራት የረዳችው እና በመጨረሻም የኦሊምፒክ ሕልሟን ለማሳካት የስደተኞች ኦሊምፒክ ቡድን አባል በመሆን በሪዮ ኦሊምፒክ የተወዳደረችው ሻምፒዮኗ ዩስራ ታሪኳ እንደ «ኤቨረስት»፣ «ኖቲንግ ሂል» እና «ለቭ አክቹዋሊ» ያሉ ዝነኛ ፊልሞችን ባዘጋጀው «ወርኪንግ ታይትል ፊልምስ» አዘጋጅነት ሙሉ በሙሉ የሆሊዉድ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል።

02/09/2026

ከጨርቆስ ሰማይ ስር "በቦታ አይወሰንም፣ በወንድማማችነት አይላላም!"

የጨርቆስ አፈር የበላ፣ በየቀበሌው አቧራ ውስጥ ተንከባሎ ያደገ ልጅ፡ ምንም እንኳን ባህር ማዶ ቢሻገርም የሰፈሩ ፍቅር ከደሙ አይወጣም! የጨርቆስ ልጆች በየትኛውም የዓለም ጥግ ቢኖሩ ለሰፈራቸውና ለወገናቸው ያላቸው ፍቅር ሁልጊዜም ልዩ ነው!

ከአሜሪካ ሜሪላንድ የሚኖረው የጨርቆስ ልጅ ሸዋንግዛው ውድነህ ለቂርቆስ ለገሃር የጤና ስፖርት ማሕበር በሁለት ዙር 17800 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጎአል ። እናመሰግናለን ሸዋንግዛው ውድነህ ! 🙌🏾

02/09/2026

«እንዴት አደራችሁ ፈጣሪ
ይመስገን!»

የቡሬ ካፕ ዋንጫ ባለቤት በሌላ ውድድር ተመለሰ !!ሪቼ የጤና ስፖርት ክለብ  በክረምት ላይ በሚደረጉ ውድድሮች ተሳትፎ እንደቀጠለ ነው። አምና በሁሉ ስፖርት ቡሬ ካፕ ውድድር አሸናፊ በመሆን ...
01/09/2026

የቡሬ ካፕ ዋንጫ ባለቤት በሌላ ውድድር ተመለሰ !!
ሪቼ የጤና ስፖርት ክለብ በክረምት ላይ በሚደረጉ ውድድሮች ተሳትፎ እንደቀጠለ ነው። አምና በሁሉ ስፖርት ቡሬ ካፕ ውድድር አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ና 100,000 ሺ ብር ተሸላሚ ነበር። ዘንድሮም በአዲስ ሚኒ ካፕ አዘጋጅነት በጊዮን ፉትሳል ሜዳ እየተወዳደረ ይገኛል ቲሙ ወደ ስምንት ውስጥ በመግባት አመርቂ ጉዞ እያደረገ ይገኛል ። አርብ 29/2018 ጠዋት 1:30 በጊዮን ሜዳ ወሳኝ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ።

የቂርቆስ አከባቢ ቀበሌ 14 «አብሮ አደጎች» እድር — የዝምታ አብዮት፣ የእውነተኛ አብሮነት ቁመና!በአጭር ዓመት ውስጥ ትልቅ ታሪክ መፃፍ እንደሚቻል በጨርቆስ ቀበሌ 14 አከባቢ የሚገኘው «...
01/09/2026

የቂርቆስ አከባቢ ቀበሌ 14 «አብሮ አደጎች» እድር — የዝምታ አብዮት፣ የእውነተኛ አብሮነት ቁመና!

በአጭር ዓመት ውስጥ ትልቅ ታሪክ መፃፍ እንደሚቻል በጨርቆስ ቀበሌ 14 አከባቢ የሚገኘው «አብሮ አደጎች » እድር በተግባር አሳይቶናል። ዛሬ 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ሲያከብር የታየው የአዛውንቱ ምርቃት ፣ እና የአካባቢው ነዋሪ እውነተኛ ፍቅርና መከባበር ለማንኛውም ማህበረሰብ የሚያስቀናና የከፍታ ማሳያ ነበር።

ይህ እድር ከተመሰረተበት አጭር ጊዜ አንስቶ በዝምታና በጥንካሬ የአከባቢው ማህበረሰብ በሰው ላይ ክፉ ነገር ሲመጣ ግንባር ቀደም ሆኖ ሐዘንን በመጋራት፣ በደስታም ጊዜ አብሮነቱን በማረጋገጥ በአራት አመታት የታማኝ ወገንተኝነትን ትርጉም አስተምሯል።

የሰፈራችንን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በመደገፍ የበጎነት ተግባርን ልምዱ አድርጎታል 5ኛ ዓመት በዓሉን ባከበረበት በዚህ ታላቅ ዕለትም ለተቸገሩ ወገኖች መዓድ በማጋራት እና የገንዘብ ስጦታ በማበርከት የደስታቸውም ተካፋይ ሆኗል።

«አብሮ አደጎች » እድር ስሙ ብቻ ሳይሆን ተግባሩም የአብሮነታችን፣ የቁስላችን ማበሻና የሰፈራችን ኩራት መሆኑን አረጋግጧል። ለአካባቢያችንም ብቻ ሳይሆን ለሌሎች እድሮች ትልቅ ተምሳሌትና የሰብአዊነት ትምህርት ቤት ሆኗል!

እንኳን ለ5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችሁ በሰላም አደረሳችሁ!

ይህ ፍቅርና ይህ ጠንካራ አንድነት እስከ ዘላለም ተጠናክሮ ይቀጥላል!

"ከጨርቆስ ሰማይ ስር" ቤተሰቦች ታላቅ የምስራች እና የነጻ ስጦታ (Giveaway) ለእድለኞች ተዘጋጅቷል!!ውበትዎን የበለጠ የሚያደምቅ፣ ዘመናዊ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት "አልሚ...
01/09/2026

"ከጨርቆስ ሰማይ ስር" ቤተሰቦች ታላቅ የምስራች እና የነጻ ስጦታ (Giveaway) ለእድለኞች ተዘጋጅቷል!!

ውበትዎን የበለጠ የሚያደምቅ፣ ዘመናዊ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት "አልሚ የውበት ሳሎን" በሰፈራችን በደመቀ ሁኔታ ስራ ጀምሯል!

በዚህም አጋጣሚ አልሚ የውበት ሳሎን ከከጨርቆስ ሰማይ ስር ገጽ ጋር በመተባበር ለገጻችን ተከታታዮች ልዩ የነጻ ስጦታ (Free Giveaway) አዘጋጅቷል!

ይህንን ፖስት Like እና Share ያድርጉ

በኮሜንት ስር አልሚ የውበት ሳሎን ብለው ለጻፉ ብዙ ላይክ ላገኘ እድለኛ ለ 2 እህቶቻችን ፀጉር make up እና ጥፍር በነፃ የምንሰራ ይሆናል!!

ሳሎናችን ለየት የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ እቃዎች የተደራጀ መሆኑ፣ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠቱ እና ለደንበኞቻችን ምቹና ማራኪ ማዘጋጀቱ ነው።

📍 አድራሻችን: ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ አራተኛ ክፍለ ጦር ፊት ለፊት አሁኑኑ መጥተው ይጎብኙን፤ ልዩነቱንም ይመስክሩ! ለበለጠ መረጃ እና ቦታ ለማስያዝ በስልክ ቁጥራችን ይደውሉልን።

0940 95 92 95 / 09 81 69 95 49

የአልሚ ውበት ሳሎን Page Follow ያድርጉ 👇
አልሚ የሴቶች ውበት ሳሎን

ከጨርቆስ ካፕ የጤና ማሕበር እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት !!
01/09/2026

ከጨርቆስ ካፕ የጤና ማሕበር እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት !!

Address

Kirkos
Addis Ababa

Telephone

+251976051514

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከጨርቆስ ሰማይ ሥር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ከጨርቆስ ሰማይ ሥር:

Shortcuts

Share