27/08/2026
"ሞዴል ብሎክ ለልደታ ከፍታ"
"ከተሜነት በመደመር መንግስት ዕይታ " በሚል መሪ ቃል የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት መልሶ ያደራጃቸውን 307 ብሎክ ካውንስል አባላት የማስተዋወቂያና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
መድረኩ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚና የካውንስሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፣ የብሎክ ካውንስል አባላት በክፍለ ከተማዋ የልማት፣ የአገልግሎት፣ የማህበራዊ ጉዳዮችና የህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራዎች ውስጥ ያላቸውን ሚና በተሻለ ሁኔታ እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ነው።
በመድረኩ “ከተሜነት በመደመር መንግስት ዕይታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የከተማ ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር በመቀናጀት የሚያደርጉት ተሳትፎ ለከተማ ልማትና ለአካባቢ ምቹነት ያለው ሚና ተነስቷል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በመድረኩ እንደገለፁት፣ የተሻለችና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለመገንባት የመንግስት ሥራ ብቻ በቂ አይደለም። ንቁ የዜጎች ተሳትፎ፣ የጋራ ኃላፊነትና የመተባበር ባህል መጎልበት እንዳለበት ገልጸዋል።
ከተሜነት ማለት በከተማ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ ለከተማው ዕድገት የራስን ድርሻ መወጣትና የጋራ ንብረትን እንደራስ ንብረት መጠበቅ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አስገንዝበዋል።
ከተማን የሚያምርና ለነዋሪዎች ምቹ የሚያደርጉት መሰረተ ልማቶች የመንግስት ኃላፊነት ብቻ እንዳልሆኑ ወ/ሮ ልዕልቲ ጠቁመው፣ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንፅህና መጠበቅ፣ የከተማ ውበትን ማስጠበቅ፣ ህግና ደንብን ማክበር፣ የጋራ ንብረትን መጠበቅና በበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፍ የዘመናዊ ከተሜነት መገለጫዎች መሆናቸውን አብራርተዋል።
በተለይም የብሎክ ካውንስል አባላት ከነዋሪዎች ጋር በቀጥታ የሚሰሩ በመሆናቸው፣ በመንግስትና በህብረተሰቡ መካከል የጠነከረ የሥራ ትስስር ለመፍጠር አስተዋፆቸው ከፍተኛ እንደሆነም ገልጸዋል።
የብሎክ ካውንስል አባላት የነዋሪዎችን ጥያቄና ችግር በቅርበት በመለየት፣ ችግሮችን ወደሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ፣ የልማት ተሳትፎን በማስፋትና የበጎ ፈቃድ ባህልን በማጠናከር የነዋሪዎች የጋራ ተሳትፎ እንዲጎለብት ማድረግ እንደሚገባቸው ወ/ሮ ልዕልቲ አስገንዝበዋል።
የ307 ብሎክ ካውንስል አባላት መልሰው መደራጀታቸውም በየአካባቢው የሚነሱ የነዋሪዎችን ጥያቄዎች በቅርበት ለመመልከት፣ በልማትና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የህዝብን ተሳትፎ ለማሳደግና የብሎክ ደረጃ የተሳትፎ ሥርዓትን ለማጠናከር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በበኩላቸው፣ በየብሎካቸው የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተባበር ለጋራ ልማትና ለከተማ ውበት መጠበቅ የሚደረገውን ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ወ/ሮ ፀሐይ አክለውም፣ የብሎክ ካውንስሎችን አቅም በማጎልበትና ከነዋሪዎች ጋር ያላቸውን ቅርበት በማጠናከር በክፍለ ከተማዋ የተሳትፎ ባህልን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራንኦል በበኩላቸው፣ “ሞዴል ብሎክ ለልደታ ከፍታ” የሚለውን ዓላማ በተግባር ለማሳካት በእያንዳንዱ ብሎክ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ የብሎክ ካውንስል አባላትና የመንግስት አካላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ፍራንኦል እንዳሉት፣ ሞዴል ብሎክ ማለት በአካባቢው የንፅህና፣ የከተማ ውበት፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የማህበራዊ ትስስርና የዜጎች ተሳት