Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC

Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC, Public & Government Service, Addis Ababa.

12/08/2026
12/08/2026
ኮርፖሬሽኑ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለትየድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፈው በጀት ዓመት የክረምት በጎ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ለከተማው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች  ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉ ...
07/08/2026

ኮርፖሬሽኑ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፈው በጀት ዓመት የክረምት በጎ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ለከተማው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ባዘጋጀው የምስጋና እና እውቅና መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንን የእውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት አመስግኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ይህን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል::

የሕንጻ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
05/08/2026

የሕንጻ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

04/08/2026

ኮርፖሬሽኑ ሰሚት በሚገኘው ለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ውስጥ የከፈተው ሱፐር ማርኬት በቻናል 1 የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲቃኝ
ይምጡ! ይጎብኙ! ይሸምቱ!

የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱእንደ ሀገር 800 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዛሬ...
03/08/2026

የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ

እንደ ሀገር 800 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞችም በዚህ ታሪካዊ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ቃሊቲ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ የቡና ማደራጃና ማዘጋጃ ማዕከል አካሂደዋል፡፡

የችግኝ ተከላውን መርሃ-ግብር ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ እንኳን ለዚህ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊየን ችግኞች ለሚተከሉበት ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ በማለት እንደ ሃገር ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ኢኒሺዬቲቭ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም እንደ ኮርፖሬሽን ባለፉት ዓመታት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ሲካሄድ መቆየቱን በመጥቀስ በዛሬው ቀንም በኮርፖሬሽኑ እና በቅርንጫፍ ማዕከላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ችግኝ ከመትከል ባለፈ ዋናው ተግባር መንከባከብና እንዲጸድቁ መከታተል በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

ዛሬ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚተከሉት 800 ሚሊየን ችግኞች ውስጥ እስከ 60 በመቶ የሚይዘው የማንጎ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶና ቡና ችግኝ ነው፡፡ ይህም ኮርፖሬሽኑ ለገበያ የሚያቀርባቸው የግብርና ምርቶችን መጠንና ጥራት በማሳደግ ረገድ የጎላ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረውይጠበቃል::

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 16:30
Thursday 08:00 - 16:30
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC:

Shortcuts

Share