Addis Ababa Public Recreation Areas and Parks Corporation

Addis Ababa Public Recreation Areas and Parks Corporation በ2022 ዓ.ም የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች በሚሰጡት አገልግሎት ሰታንዳርድ፣ጥራትና አይነት ከ10ሩ የአፍሪካ ከተማ ፓርኮች ተመራጭ ይሆናሉ

በእንጦጦ ፖርክ የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጥቷል!! ታላቁ   ሩጫ በኢትዮጵያ፣  ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር  ኮርፓሬሽን ጋር በመተባ...
07/12/2024

በእንጦጦ ፖርክ የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጥቷል!!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፓሬሽን ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደው የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊዎች ሽልማት ተሰጥቷል።በሰፍራው ተገኝተው ሽልማቱን የሰጡት የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች ናቸው።

YOU GO ENTOTO PARK!!

የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ በእንጦጦ ፖርክ ተካሄደ!ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣  ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር  ኮርፓሬሽን ጋር በመተባበር " ሩጫን የሕይዎት ዘይ...
07/12/2024

የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ በእንጦጦ ፖርክ ተካሄደ!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፓሬሽን ጋር በመተባበር " ሩጫን የሕይዎት ዘይቤ ማድረግ"በሚል መሪ ቃል በየወሩ በእንጦጦ ፓርክ የሚያካሂደው የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ ዛሬ በእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተጀምሯል።በውድድሩ በርካታ ተሳታፊዎች የታደሙበት ሲሆን ሩጫዉ አዝናኝ አስደሳች እና አጓጊ እንደነበር ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።
YOU GO ENTOTO PARK!!

06/12/2024

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአዲስ ዙ ፓርክ ተጨማሪ አንበሳ አስገባ።
የጎብኝዎችን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በተከታታይ የተለያዪ የዱር እንስሳትን ሲያስገባ የነበረው ኮርፖሬሽን በዛሬው እለት እንስት እንበሳ አዲስ ዙ ፓርክ አስገብቷል።
ባለፉት ጊዜያቶች አናብስትን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረው ኮርፖሬሽን በቅርቡ በዶ/ር ግርማ መንገሻ የሚመራ ቡድን በማደራጀት አናብስት ሊገኙ ወደሚችሉበት አካባቢ በህጋዊ መንገድ በማንቀሳቅስ ባደረገው ጥረት የተሳካ ስራ መስራት መቻሉ ተረጋግጧል።
በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ አናብስትን ወደ ፓርክ ለማስገባት ጥረቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

የጽዳት ዘመቻ በአዲስ ዙ ፓርክ !ጽዱ ፣ውብ እና ማራኪ ፖርክ ለሁላችን!   ህዳር 23/2017 ዓ.ምየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የህዝብ   መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን  አመራር...
02/12/2024

የጽዳት ዘመቻ በአዲስ ዙ ፓርክ !
ጽዱ ፣ውብ እና ማራኪ ፖርክ ለሁላችን!
ህዳር 23/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራር እና ሰራተኞች እንደተለመደው ዛሬም በአዲስ ዙ ፓርክ የጽዳት ዘመቻ እያካሄዱ ነው።

Follow Like, Share

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/
👉YouTube
www.youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC
YOU GO PARK

የምስራች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአዱስ ዙ ፓርክ ውስጥ ከአራት አመት በፊት የተጀመረውን ከጥልቅ ጉድጓድ  ውሃ የማውጣት እና  የቧንቧ ...
21/10/2024

የምስራች
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአዱስ ዙ ፓርክ ውስጥ ከአራት አመት በፊት የተጀመረውን ከጥልቅ ጉድጓድ ውሃ የማውጣት እና የቧንቧ መስመር ዝርጋታ ስራ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ።

የመስመር ዝርጋታው መጠናቀቁ እና አገልግሎት እንዱስጥ መደረጉ በአዲስ ዙ ፓርክ ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት እንደሚቀርፍ በተለይም ከውሃ እጥረት ጋር ተያይዞ በእጽዋት ልማት ስራው ላይ የነበረው ተግዳሮት እንደሚቀረፍ፣በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ የዱር እንስሳት መጠጥነትም ሆነ ለንጽህናቸው መጠበቂያነት እንደሚያገለግል፣ በተጨማሪም በኮርፓሬሽኑ ስር ለሚተዳደሩ ሌሎች ፓርኮች የእጸዋት ልማት ስራ እገዛ እንደሚያደርግ የኮርፓሬሽኑ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ፣አቶ ውብነት በላይ ገልጸዋል።

Follow Like, Share

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/
👉YouTube
www.youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC

11/10/2024
10/10/2024
09/10/2024

እንጦጦ ፓርክ 4ኛ አመት እንኳን አደረሳችሁ !
🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/
👉YouTube
www.youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC
Follow Like, Share

የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን  የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ። የሩብ አመቱን ሪፖርት ያቀረቡት የኮርፖሬሽኑ ...
08/10/2024

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ። የሩብ አመቱን ሪፖርት ያቀረቡት የኮርፖሬሽኑ እቅድ እና በጀት ሃላፊ አቶ ውብሽት አደፍርስ ሲሆኑ የኮርፖሬሽኑ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ውብነት በላይ ውይይቱን መርተውታል።በእቅድ አፈጻጸም ግምገማው የኮርፖሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ዳይሬክተሮች ፣ የፓርክ ሃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆነ በእቅድ አፈጻጸም የነበሩ ጥንካሬ እና እጥረቶችን በመለየት በተለይ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል ።

አፍሪካ ፓርክ /AFRICA PARk!!!   አፍሪካ ፓርክ በመሃል አዲስ አበባ በቄርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08  በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ፊት ለፊት መንገድ አካፋይ ላይ በ45,707 ሜ/ካ ላይ ...
08/10/2024

አፍሪካ ፓርክ /AFRICA PARk!!!

አፍሪካ ፓርክ በመሃል አዲስ አበባ በቄርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ፊት ለፊት መንገድ አካፋይ ላይ በ45,707 ሜ/ካ ላይ የሚገኙ ሶስት ፓርኮችን/ኢትዮጵያ ፓርክ አዲስ አበባ ፓርክ አፍሪካ ፓርክ/ ያከተተ ሆኖ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ ፓርክ ነው፡፡
ቦታወ ለብዙ ጊዜ በመናፈሻነት ሲገለግል የቆየ ቢሆንም በተለይ በ1997 ዓ.ም በሼህ አሊ አላሙዲ ሙሀመድ ድጋፍ ደረጃውን የጠበቀ ዲዛይን ተዘጋጅቶለት እንዲለማ ከተደረገ በኋላ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ተጨምረውለት በፓርክነት/በመዝናኛ ስፍራነት እንዲያገለግል ተደርጓል፡፡
ፓርኩ ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ ለኢግዚቢሽን፣ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሉት ሲሆን በተለይ በግቢው ውስጥ ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች እና ጣፋጭ የህጻናት ምግቦች፣ የካፍተሪያ አገልግሎቶች ፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፈራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው በመራመድ ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ምቹ የመናፈሻ መንገድ ወዘተ ይገኙበታል፡፡
አፍሪካ ፓርክን ለየት ከሚያደረጉት ውስጥ የመጀመሪያውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሰረቱ የአፍሪካ መሪዎች እና የአፍሪካ ህብረትን የመሰረቱ የአፍሪካ መሪዎች የተከሏቸው የመሪዎቹ ስም የተጻፉባቸው ታሪካዊ ቅርስ የሆኑ ዛፎች የሚገኙበት ስፍራ መሆኑ ነው፡፡

🌐 Website
www.AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
www.Tiktok.com/
👉YouTube
www.youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC
Follow Like, Share

Address

Addis Ababa
141414

Telephone

+251947151836

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Public Recreation Areas and Parks Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Public Recreation Areas and Parks Corporation:

Share