14/06/2023
የወል እወነት እንዲረጋገጥ የሁሉም ሰዉ አሻራ ያስፈልጋል
ኢትዮጵያ የብዙ ታሪክ ባለቤት ነች ። አባቶቻችን ብዙ ታሪክ ሰርተው ይችን ያቆዩልን በብልሃት እና #በወል እውነት ነው ። የወል እውነት የሌለበት ሀገር ይቅርና አንድ ቤተሰብ እንኳን በሰላም መኖር አይችልም። መገፋፋት ፣ መኖቃቆር ፣ መጠላለፍ እና ፅንፈኝነት ስለሚኖር #ሀገር ልታድግ አትችልም ።
⁉️የወል እውነት ይህን ያክል ካስፈለገን እንዴት መሬት ማስያዝ ፣ እንቅፋቶቹንስ እንዴት ማሸነፍ እንችላለን ?
የወል እንውነት እንድንለማመድ የመጀመሪያው አንዱ ለአንዱ እውቅና ሲሰጥ ነው። #ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት ፤ ሀገራችን እዚህ እስከምትደርስ ድረስ ፣ ሉዓላዊነቷ እንዲጠበቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ተወቷል ።
እውነተኛ መሬት ማስያዝ ግን በቀላሉ አይመጣም። ለሀገር ይህን ያክል የሚጠቅም ነገር ሲጀመር እንዲው ሊመጣ አይችልም ለምን ከተባለው ሀገራችን ስትረጋጋ ጥቅማቸው የሚቀንስባቸው ብዙ ስላሉ ። ስለዚህ ከግራና ከቀኝ ጥላቻ የሚሰብኩንን ትተን በአንድነት ኢትዮጵያን እናልማት ።