ቦሌ ወረዳ 06 ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና Anti Corruption

ቦሌ ወረዳ 06 ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና  Anti Corruption Ethics and Anti-Corruption

29/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
28/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
28/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

25ቱ የሙስና ወንጀሎች (አዋጅ ቁጥር 881/2007)

*************************

1. በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል (አንቀጽ 9)

2. ጉቦ መቀበል (አንቀጽ 10)

3. የማይገባ ጥቅም መቀበል (አንቀጽ 11)

4. አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች ሰዎች የሚፈፅሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል (አንቀጽ 12)

5. የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት (አንቀጽ 13)

6. አደራ በተሠጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ (አንቀጽ 14)

7. በሥራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል (አንቀጽ 15)

8. በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀጽ 16)

9. በህገወጥ መንገድ መሰብሰብ ወይም ማስረከብ (አንቀጽ 17)

10. ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀጽ 18)

11. ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀጽ 19)

12. ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀጽ 20)

13. ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ (አንቀጽ 21)

14. የሥራ ሚስጥርን መግለፅ (አንቀጽ 22)

15. መንግሥታዊ ወይም የህዝባዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት፣ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀጽ 23)

16. መንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ (አንቀጽ 24)

17. ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀጽ 25)

18. ዋጋ ያለዉን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት (አንቀጽ 26)

19. ማቀባበል (አንቀጽ 27)

20. በሌለው ሥልጣን መጠቀም (አንቀጽ 28)

21. በግል ተሰሚነት መነገድ (አንቀጽ 29)

22. በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ (አንቀጽ 30)

23. ከባድ የእምነት ማጉደል (አንቀጽ 31)

24. ከባድ አታላይነት (አንቀጽ 32)

25. በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ ስለመርዳት (አንቀጽ 33)

ዜጎች ሙሰኞችን በማጋለጥ በንቃት ይሳተፉ!

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
28/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

28/08/2026

የተቋማት አመኔታ እና የማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ትችቶች፣

*****************

በዲጂታል ሚዲያ ዘመን፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች አሉታዊ ይዘት ያላቸው አስተያየቶችን በመንግሥት እና ሕዝባዊ ተቋማት መስጠት እየተለመደ መጥቷል።

ከፀረ-ሙስና ትግል አንጻር፣ በማህበራዊ ሚዲያ የተቋማት መሪዎች፣ ሥራ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች ስም ተጠቅሶ የሚሰራጩ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማዎችን (እውነተኛ/ሐሰተኛ) ተቋማት ምላሽ እና ማብራሪያ ባይሰጡ፣ ከግልጽነት እና ተጠያቂነት መርሆዎች አንጻር ምን ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?

የመንግስት ተቋማት ለማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ መስጠት አለባቸው ወይስ የለባቸውም?

በየተቋማቱ የተደራጁት የኮሙኒኬሽን ሥራ ክፍሎች ሚናቸው እንዴት ይታያል?

ለገንቢ አስተያየትዎ እናመሰግናለን!

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
27/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

የሙስና አበይት ችግሮች፦
🌿🌿🌿🌿🌿

ሙስና በሀገር፣ በማህበረሰብ እና በግለሰብ ደረጃ በርካታ ከፍተኛ ጉዳቶችን ያስከትላል። ከእነዚህም መካከል አበይት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦

➾ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፦
የታለመላቸው የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በጊዜ እንዳይጠናቀቁ በማድረግ የመንግስት ሀብት በከንቱ እንዲባክን ያደርጋል።

ፍትሃዊ የገበያ ውድድርን ስለሚያጠፋ እና ግልጽነትን ስለሚቀንስ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ኢንቨስት ለማድረግ እንዲሰጉ ያደርጋል።

በታክስና በታሪፍ ማጭበርበር ምክንያት የመንግስት የገቢ ስብሰባ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል።

➾ማህበራዊ ችግሮች፦
መሰረታዊ አገልግሎቶች (እንደ ጤና፣ ትምህርት እና ፍትህ) በገንዘብ ወይም በትውውቅ ብቻ እንዲገኙ በማድረግ የድሆችን መብት ይረግጣል።

ለህዝብ ጥቅም መዋል የነበረበት ሀብት በጥቂቶች እጅ ስለሚከማች የደሃውን እና የሀብታሙን ልዩነት ያሰፋዋል።

ታማኝነትን እና ጠንክሮ መስራትን አዋጭ እንዳይሆኑ በማድረግ፣ በአቋራጭ የመበልጸግ እኩይ ባህል እንዲስፋፋ ያደርጋል።

➾ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮች፦
የህዝብ ተቋማት ሙያዊ ብቃት እና ገለልተኝነት አጥተው እምነት የሚጣልባቸው እንዳይሆኑ ያደርጋል።

የመንግስት አሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት የጎደለው እንዲሆን በማድረግ የህግ የበላይነትን ያናጋል።

ህዝብ በመንግስት እና በፖለቲካ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር ያደርጋል።

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
27/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

የሙስና መከላከል ስትራቴጂክ ስልቶች
**********
ሙስና ብዙ ዘርፎችን የሚዳስስ፣ መፈጸሚያ መንገዱም በየጊዜው እየተለዋወጠና እየረቀቀ የሚሄድ ወንጀል ነው፡፡

ለመከሰቱ ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችም እንዲሁ በርካታ ናቸው፡፡ ታዲያ ይህን ተለዋዋጭ ባህርይ ያለውን ሙስና ለመዋጋት በየጊዜው የሚሻሻል፣ መጠነ ሰፊ ጉዳዮችን የሚዳስስ የተቀናጀ ስትራቴጂ መንደፍ ተገቢ ነው፡፡

ምንም እንኳን ሙስናን ለመዋጋት አንድና ብቸኛ አማራጭ መንገድ ባይገኝም አንዳንድ ጸሃፊዎች /“There is no one-fits- all anti-corruption strategy”/ እንደሚሉት ቢሆንም፣ በዘርፉ ምርምር ያካሄዱ አብዛኞቹ ባለሙያዎች ሙስናን ለመዋጋት ዋና ዋና ስትራቴጂዎች ተብለው የሚጠቀሱት፡-
1. አስተዳደራዊ አሰራርና ውስጣዊ ቁጥጥርን ማጠናከር ስርዓት
2. የትስስር ስርዓት መፍጠር
3. ጠንካራ የህግ ማስከበር ስርዓት መፍጠር
4. ግንዛቤን በማሳደግ ሙስናን መከላከል
5. የአሰራር ጥናቶችን በማካሄድ ሙስናን መከላከል

ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”
👇👇👇👇👇👇
ለጥቆማ
በነፃ የስልክ መስመር 8887
Facebook
https://www.facebook.com/share/1AxqPkYgNQ/
ቴሌግራም:- https://t.me/aaethics2015
ቲክቶክ:–https://www.tiktok.com/.ababa.ethic?_t=ZM-8tqgdUzDifn&_r=1
ዩቲዩብ:– https://youtube.com/?si=KYuB2L8_rwYnrtQK
ኢሜል ፡- [email protected]

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
26/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?

ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤

👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡

በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡

ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

፡-
በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
26/08/2026

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

ሙስናን በአንድነትና በቁርጠኝነት መታገል ለነገ የማባይባል ተግባር ነውǃ

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቦሌ ወረዳ 06 ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና Anti Corruption posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share