Andex Asfaw

Andex Asfaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Andex Asfaw, Public Service, Addis Ababa.

18/06/2025
20/04/2025
20/04/2025
19/03/2025

እርስበርሳችሁ ተዋደዱ!
፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”
-ቅዱስ መፅሐፍ

ፍቅር ትዕዛዝ ነው፣ መውደድ የእግዚአብሔር ልጅነት መገለጫ ነው፣ መተጋገዝ፣ አብሮ ማደግ፣ ፈጣሪ በወደደን ልክ ሰዎችን መውደድ መቻል ፈጣሪን የመውደዳችን መገለጫ ነው። አምላክህን ታውቃለህ፣ ስለርሱ ፍቅር ደጋግመህ ታወራለህ፣ የታደሉህን በረከቶች ታስተጋባለህ፣ የመውደዱ ጥግ፣ የቸርነቱ መጨረሻ ያስደንቅሃል። ነገር ግን ከመደነቅና ከመገረም በላይ ያንተስ ምላሽ ምንድነው? ለርሱ ያለህን ፍቅር ለምትገልፅበት ትዕዛዝ ምንያህል ቀናኢ ነህ? የእርሱ ልጅ መሆንህን ለማስመስከር ምንያህል ትተጋለህ? የሰውን ልጅ መርዳትና ከልብ መውደድ የእግዚአብሔር አምላክ ልጅነት መገለጫ ከሆነ ስንቶቻችን ልጆቹ እንደሆንን እራሱ ፈጣሪ ያውቀዋል። ለወዳጅህ እንቅፋት እየሆንክ፣ በልብህ ጥላቻን ይዘህ፣ ለቂም በቀል እራስህን እያዘጋጀህ፣ በውስጥህ ንቀትን እያስቀመጥክ እንዴትም ስለ ፈጣሪ ልጅነት አፍህን ሞልተህ ማውራት አትችልም።

ደቀመዛሙርቴ፣ ተማሪዎቼ እንዲሁ ልጆቼ መሆናችሁ ይታወቅ ዘንድ እርስበርሳችሁ ተዋደዱ መባሉን ከልብህ አስገባው። ፍቅርን እየገፉ ጥላቻን እያገዘፉ፣ መውደድን ችላ እያሉ ልዩነትን እየሰበኩ፣ ይቅርታን እያንቋሸሹ ክፋትን እያጠናከሩ ስለፈጣሪ ልጅነት ማውራት አይቻልም። ወገን በችግር ውስጥ ሆኖ በረሃብ በጥማት እየተሰቃየ፣ ወንድም እህቶች የህይወት ካርታ ጠፍቶባቸው ሳለ አንድ ሰው ቢያንስ በቁስ ወይም በገንዘብ መርዳት ባይችል እንኳን ድምፅ በመሆን ህመማቸውን ሌሎች ጋር ማድረስ ሲችል ስላፈራው ንብረትና ስለደረሰበት ስኬት ደጋግሞ ቢያወራ ምንም ትርጉም የለውም። የአንዳችን መኖር ለአንዳችን ብርታት ሊሆን ይገባል፣ ያንተ ጥንካሬ ለወንድምህ ችግር መፍትሔ ማምጣት ይኖርበታል🙏

አዎ! ለብቻ ኖሮ ማለፍ፣ የእራስን ሆድ ብቻ መሙላት፣ ፅንፍ በያዘ ጥላቻ የሰውን ልጅ ማንቋሸሽ፣ ነገ ምን እንደሚሆን በማይታወቅ ሃብትና ንብረት ከልክ በላይ መመካት በምንም መመዘኛ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊወደድ አይችልም። ብንወድቅ የሚያነሳን ፈጣሪ ነው፣ ብንስት የሚመልሰን የዘላለም አባታችን ነው፣ በጥፋት በበደል አንገታችንን ብንደፋ በይቅርታው ቀና የሚያደርገን ቸሩ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ትልቁ የምድር ጌጥ ንብረት፣ ዝና፣ ሰው ወይም ገንዘብ አይደለም ትልቁ ጌጥ የእግዚአብሔር ልጅነት ነው። ሌላው ሁሉ ትርፍና ጠፊ ነው። እርስበርስ በመዋደድ የፈጣሪያችንን ልጅነት እናስመስክር፣ በመልካም ስራ ነፍሳችንን ወደ ፅድቁ መንገድ እንምራት።
የተባረከ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍️ (Epha A.)

19/03/2025

እርስበርሳችሁ ተዋደዱ!
፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”
-ቅዱስ መፅሐፍ

ፍቅር ትዕዛዝ ነው፣ መውደድ የእግዚአብሔር ልጅነት መገለጫ ነው፣ መተጋገዝ፣ አብሮ ማደግ፣ ፈጣሪ በወደደን ልክ ሰዎችን መውደድ መቻል ፈጣሪን የመውደዳችን መገለጫ ነው። አምላክህን ታውቃለህ፣ ስለርሱ ፍቅር ደጋግመህ ታወራለህ፣ የታደሉህን በረከቶች ታስተጋባለህ፣ የመውደዱ ጥግ፣ የቸርነቱ መጨረሻ ያስደንቅሃል። ነገር ግን ከመደነቅና ከመገረም በላይ ያንተስ ምላሽ ምንድነው? ለርሱ ያለህን ፍቅር ለምትገልፅበት ትዕዛዝ ምንያህል ቀናኢ ነህ? የእርሱ ልጅ መሆንህን ለማስመስከር ምንያህል ትተጋለህ? የሰውን ልጅ መርዳትና ከልብ መውደድ የእግዚአብሔር አምላክ ልጅነት መገለጫ ከሆነ ስንቶቻችን ልጆቹ እንደሆንን እራሱ ፈጣሪ ያውቀዋል። ለወዳጅህ እንቅፋት እየሆንክ፣ በልብህ ጥላቻን ይዘህ፣ ለቂም በቀል እራስህን እያዘጋጀህ፣ በውስጥህ ንቀትን እያስቀመጥክ እንዴትም ስለ ፈጣሪ ልጅነት አፍህን ሞልተህ ማውራት አትችልም 🙏

ደቀመዛሙርቴ፣ ተማሪዎቼ እንዲሁ ልጆቼ መሆናችሁ ይታወቅ ዘንድ እርስበርሳችሁ ተዋደዱ መባሉን ከልብህ አስገባው። ፍቅርን እየገፉ ጥላቻን እያገዘፉ፣ መውደድን ችላ እያሉ ልዩነትን እየሰበኩ፣ ይቅርታን እያንቋሸሹ ክፋትን እያጠናከሩ ስለፈጣሪ ልጅነት ማውራት አይቻልም። ወገን በችግር ውስጥ ሆኖ በረሃብ በጥማት እየተሰቃየ፣ ወንድም እህቶች የህይወት ካርታ ጠፍቶባቸው ሳለ አንድ ሰው ቢያንስ በቁስ ወይም በገንዘብ መርዳት ባይችል እንኳን ድምፅ በመሆን ህመማቸውን ሌሎች ጋር ማድረስ ሲችል ስላፈራው ንብረትና ስለደረሰበት ስኬት ደጋግሞ ቢያወራ ምንም ትርጉም የለውም። የአንዳችን መኖር ለአንዳችን ብርታት ሊሆን ይገባል፣ ያንተ ጥንካሬ ለወንድምህ ችግር መፍትሔ ማምጣት ይኖርበታል።

አዎ! ለብቻ ኖሮ ማለፍ፣ የእራስን ሆድ ብቻ መሙላት፣ ፅንፍ በያዘ ጥላቻ የሰውን ልጅ ማንቋሸሽ፣ ነገ ምን እንደሚሆን በማይታወቅ ሃብትና ንብረት ከልክ በላይ መመካት በምንም መመዘኛ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊወደድ አይችልም። ብንወድቅ የሚያነሳን ፈጣሪ ነው፣ ብንስት የሚመልሰን የዘላለም አባታችን ነው፣ በጥፋት በበደል አንገታችንን ብንደፋ በይቅርታው ቀና የሚያደርገን ቸሩ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ትልቁ የምድር ጌጥ ንብረት፣ ዝና፣ ሰው ወይም ገንዘብ አይደለም ትልቁ ጌጥ የእግዚአብሔር ልጅነት ነው። ሌላው ሁሉ ትርፍና ጠፊ ነው። እርስበርስ በመዋደድ የፈጣሪያችንን ልጅነት እናስመስክር፣ በመልካም ስራ ነፍሳችንን ወደ ፅድቁ መንገድ እንምራት።
የተባረከ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍️ (Epha A.)

17/02/2025

Address

Addis Ababa
212121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Andex Asfaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category