03/09/2026
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አካሂዷል።
መድረኩ ላይ የከተማው፣ የሁሉም ክፍለ ከተማና የወረዳዎች የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ወልዴ፤ “በጎነትና እህትማማችነት የሴቶችን ማህበራዊና ፖለቲካዊ አቅም በማጎልበት ረገድ ትልቅ መሠረት ነወ” ሲሉ ገልጸዋል።
ፓርቲው ሴት አመራሮችን በብቃት ለማዘጋጀትና ለማብቃት በርካታ አወንታዊ ተግባራትን ማከናወኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በተግባር ያሳዩት አርአያነት ያለው የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነት፣ ሴቶች ወደፊት እንዲመጡና ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸው እንዲያድግ ትልቅ ብርታትና ድምቀት መሆኑን አብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ፋንታሁን “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ የመላው ህብረተሰብ እድገት ይፋጥናል” ብለዋል።
ፓርቲው ለሴቶች እያደረገ ያለው አጠቃላይ ድጋፍና የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ያመላከቱት ወ/ሮ ማስተዋል፤ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የሚያሳዩት ጠንካራና አቅጣጫ ጠቋሚ አመራር ለሌሎች ሴት አመራሮች የመንፈስ ብርታትና ታላቅ የቁርጠኝነት ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል።
ሴቶች በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።