Odeeffannoo press

Odeeffannoo  press Page kun odeeffannoo madda sirrii qabu qofa dhiyeessinaa like gochiu hin dagatiina

Qophiin Ayyaana Irreechaa Hora Finfinnee Bara 2018 Kan Kanaan Duraarraa Adda.
02/10/2025

Qophiin Ayyaana Irreechaa Hora Finfinnee Bara 2018 Kan Kanaan Duraarraa Adda.

የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ውስጥ በማስረጽ እያጠናከሩ መሄድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2018የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ው...
30/09/2025

የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ውስጥ በማስረጽ እያጠናከሩ መሄድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2018

የኢሬቻን ሀገራዊ እሴቶች ጥንካሬ በትውልዱ ውስጥ በማስረጽ እያጠናከሩ መሄድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሃይሉ አዱኛ ተናገሩ።

"ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረውን የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ላይ ያተኮረ 'ጉሚ በለል' የውይይት መድረክ በክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት እና በኮሙኒኬሽን ቢሮ ትብብር ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ቢሮው ኃላፊ ሃይሉ አዱኛ፤ የገዳ ስርዓት ትሩፋት የሆነውን የኢሬቻ በዓል የበለጠ ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

ኢሬቻ ከሰላም፣ እርቅ እና አንድነት ጀምሮ በሀገር ግንባታ እና ህብረ ብሔራዊ እንድነትን ከማጠናከር አንጻር በርካታ ሀገራዊ እሴቶች ያሉት መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህን እሴቶች በጎ አስተዋጽኦ የበለጠ በማጠናከር ለትውልድ ግንባታ ማዋል እንደሚገባ አመልክተው ለዚህም ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ በዓል መሆኑን አንስተው፤ የዘንድሮው ኢሬቻ በተሻለ መልኩ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የገዳ ትምህርት መምህር መሐመድ ነሞ(ዶ/ር)፣ ኢሬቻ የበለጠ እንዲያድግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመክተዋል።

በዓሉን ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ በቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ የገቢ ምንጭ ማድረግ እንዲቻል የባለድርሻ አካላት ሚናም ማደግ እንዳለበት አስረድተዋል።

በባህልና ቋንቋ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችም የበዓሉን በጎ ገጽታ ማጉላት የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም ህብረትና ትስስር የሚያጠናክርበት ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ የኢሬቻ በዓል አብሮነት፣ ይቅርታ፣ እርቅ፣ አንድነትና መተባባር የሚጎለብትበት መሆኑን ጠቅሰው የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ እውን ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ኢሬቻ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በኅብረቱ ዓባይን ገርቶ ለልማት ያዋለው ሕዝብ የኢትዮጵያን ማንሠራራት ለማሳካት አይሳነውም፦ ርዕሰ መስተዳድር  ሽመልስ አብዲሳ*********************ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕ...
18/09/2025

በኅብረቱ ዓባይን ገርቶ ለልማት ያዋለው ሕዝብ የኢትዮጵያን ማንሠራራት ለማሳካት አይሳነውም፦ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ
*********************

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝብ ከጥሪቱ እስከ ሕይወቱ መስዋዕትነት ከፍሎ የገነባው የአዲሱ ትውልድ አሻራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በዚህም አይቻልም የሚለው አስተሳሰብ መሰበሩን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው የተናገሩት።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአሁኑ ትውልድ በላቡ እና በደሙ ጠብታ ባኖረው አሻራ ዳግማዊ ዓድዋን እውን ያደረገበት ነው ብለዋል።

ግድቡ ከውጭ እና ከውስጥ የተቃጡበትን ፈተናዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብቁ አመራር እና በሕዝብ መስዋዕትነት አልፎ ለፍጻሜ መብቃቱንም ጠቅሰዋል።

የግድቡ መጠናቀቅ የምሥራቅ አፍሪካን እና የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን የውኃ ፖለቲካ የቀየረ እንደሆነ አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

ይህ በሕዝብ ኅበረት እና መስዋዕትነት የተገኘው ድል ለሀገር ፍቅር በሚከፈለው መስዋዕትነት የተገኘ እና ሁሌም የሚታሰብ ነው ብለዋል።

ሙሉውን ለማንበብ አስተያየት መስጫው ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

Qeerroofi Qarreen riqicha dhaloota darbeefi dhaloota dhufuuti!= = ="Sirni goobees ta’ee shinooyyee ittifufiinsa firiifi ...
05/09/2025

Qeerroofi Qarreen riqicha dhaloota darbeefi dhaloota dhufuuti!
= = =
"Sirni goobees ta’ee shinooyyee ittifufiinsa firiifi sanyii irratti kan xiyyeeffataniidha. Qeerroofi Qarreen riqicha dhaloota darbeefi dhaloota dhufuuti. Akka duudhaa ofiitti jiraachuu, abdii kudhaammachuu, ittigaafatamummaaf of-qopheessuufi gaaddisa, akkasumas utubaa maatii ta’uu kan itti shaakalaniidha.

Aadaan kun salphaatti as hingeenye. Humnoonni hedduu Oromoo ofitti alageessufi gaaddidduu aadaa isaa akka baqatu gochuuf tabbi hinbaane, sulullii hinbuune hinturre. Sirna taliila, safuufi safeeffannaa walsimaa, bulmaata irraaf jalaa, heera waaqaaf lafaa, handhuuraa aayyoof aabboo Oromoo gachisiisuuf, falfalli hintolfamneefi qoqqobbiin hinkaa’amne hinturre. Ayyaanotaafi sirnoota hedduu seeraan laganiiru.

Uummanni Oromoo qabsoo obsa fixachiisaa, wareegama lubbuu qaalii kitilee aayyoo, aabboof ilmaanii, akkasumas gootummaa labatatti fulla'een boqonnaa seenaa roorroo sana dandamateera. Haata’u malee, adeemsa seenaa moggeeffamuufi eenyummaa ofiiraa ittifamuu har’a olaantummaa irratti goonfanne kana hanga dhumaatti awaaluun, boqonnaa seenaa kabajaa, walqixxummaafi abbaa biyyummaa michichila hinraafamnerra dhaabuuf, hojii ayyaana goobefi shinooyyee kabajuu bira taru raawwachuun dhimma murteessadha.

Mootummaan Jijjiiramaa Naannoo Oromiyaa yaadama kanarraa dhaabbachuun kallattii lamaan sochii baldhaa taasisuu irratti argama. Kallattiin duraa, galmoota tarsiima’oo qabsoo Oromoo sadi: dorgomummaa dhalootaa, cimina dinagdee ummataafi ijaarsa sirna si’oomaa adda baasee hiree haq-qabeessa uummanni Oromoo gatii qaaliin argate bu’uura fulla’insaa qabsiisuuf hojiilee baldhaa raawwachaa jira.

Kallattii birootiin, akkaataa galmoota tarsiima’oo sadan kunniinin walsimuun, Haaromsa Aadaa Oromoo toorawwan xiyyeeffannoo shan: Beekumsa Omishuu, Dinagdee Ceesisuu, Aartii Oromoo Ammayyeessuu, Aadaa Oromoo Ceesisuu akkasumas Miidiyaafi Kominikeeshinii Ammayyeessuu qabu labsuun sochii baldhaa taasisaa jira!" Obbo Shimallis Abdiisaa, PMNO

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃብት እንዲጨምር አስችሏል-ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃ...
04/09/2025

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃብት እንዲጨምር አስችሏል-ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሃብትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጎርፍን በመከላከል በውሃ የሚወሰድ አፈርና ደለልን በመቀነስ ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው።

መርሃ ግብሩ በውሃ ሀብት ላይ ያስገኘውን ጠቀሜታ በተመለከተ በቅርቡ በተካሔደ ጥናት የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ መረጋገጡን ጠቅሰዋል።

የዋና ዋና ወንዞችና የጅረቶች የውሃ መጠን መጨመሩንም ተናግረዋል።

ጥናቱ በሐዋሳ ዙሪያ፣በዓባይ እና አዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ መካሄዱን ጠቅሰው፥ በእነዚህ አካባቢዎች ችግኞች ከመተከላቸው በፊትና ከተተከሉ በኋላ የታየው ተጨባጭ ለውጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መረጋገጡን አንስተዋል።

በዚህም የአረንጓዴ አሻራ አካባቢውን አረንጓዴ ከማድረጉ ባለፈ በዝናብ ወቅት ሊፈጠር የሚችል ጎርፍ እንዲቀንስና የዝናብ ውሃ ወደ መሬት እንዲሰርግ ማድረጉን በተግባር አረጋግጠናል ነው ያሉት።

በዋናነት የተተከሉት ችግኞት የተጎዱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ እና የጎርፍ መጠን እንዲቀንስ ከማድረግ ባሻገር የከርሰ ምድር ውሃን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ነው ያሉት።

ደርቆ የነበረው የሐሮማያ ሐይቅ መልሶ ያንሰራራው በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ሥራ መሆኑን በማንሳት፥ የአረንጓዴ አሻራ ምንጮች እንዲጎለብቱ በማድረግ የውሃ ፍሰትን ለማስተካከል ማስቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ጎርፍን በመከላከል አፈር እንዳይሸረሸር፣ ግድቦችና ወንዞች በደለል እንዳይሞሉና ንጹህ የውሃ ሀብት እንዲኖር በማድረግ ትልቅ ለውጥ ማመጣታቸውንም ገልጸዋል።

02/09/2025

ረጅም እድሜ ይስጣት
ለጤናም ይደርብለት
በሰው ማሚ ከልብ እናት ናት

02/09/2025
ታሪካዊ ከፍታ ላይ የሚገኘው የሩሲያ እና ቻይና ግንኙነት  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017  የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከቻይና ጋር ያላት ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ታሪካዊ ከ...
02/09/2025

ታሪካዊ ከፍታ ላይ የሚገኘው የሩሲያ እና ቻይና ግንኙነት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከቻይና ጋር ያላት ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ታሪካዊ ከፍታ ላይ እንደሚገኝ ተናገሩ።

የሩሲያ እና ቻይናን ትብብር ለማጠናከር ያለመ የዓለም አስተዳደር ኢኒሼቲቭ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህ ከሻንጋይ ትብብር ፎረም ማግስት በቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዛሬ ይፋ በሆነው በዚህ መድረክ የተሳተፉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ሀገራቸው ከቻይና ጋር ወዳጅ መሆኗን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን “የረጅም ጊዜ ጓደኛየ’ ሲሉ ስላላቸው ወዳጅነት ገልጸዋል።

የቻይና እና ሩሲያ ግንኙነት በዓለም አቀፍ ጫናዎች ሳይበገር በታሪካዊ ከፍታ ላይ ይገኛል ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ የሀገራቱ ግንኙነት በዲፕሎማሲያው ዓለም የጠንካራ ግንኙነት ምሳሌ መሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረውን የባለ ብዙ ዋልታ የዓለም አስተዳደር ስርዓትን ለማስጠበቅ በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ከሩሲያ ጋር ትናንት አብረን ነበርን፣ ዛሬም አብረን ነን፣ ትብብራችን ለወደፊትም ይቀጥላል ነው ያሉት።

የሀገራቱ ግንኙነት ከሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ ትብብሮች እንዲሁም በደቡብ ለደቡብ ትብብር እና ብሪክስ ማዕቀፎች በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ የሆነችው ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ 240 ቢሊየን እንደሚደርስ ቢቢሲ እና አናዶሉ ዘግበዋል፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251965765418

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Odeeffannoo press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Odeeffannoo press:

Share