Addis ketema woreda 9 communication

Addis ketema woreda 9 communication this is adis ketema woreda 9 communnication office

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ...
28/08/2026

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 በአገልግሎት ቀን ሁሉም ሰራተኛ እና አመራር በቢሮው ተገኝቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::

በተቀናጀ አገልግሎት ባለጉዳዮችን እያስተናገዱ ያሉ ሰራተኞች ህዝባችንን ዝቅ ብለን በማገልገል በአገልግሎታችን የረካ ማህበረሰብ ለመፍጠር በመትጋት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር በመሆኑ በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን እያገለገሉ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ነሀሴ 22 -2018ዓ.ም

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡********************ነሐሴ...
28/08/2026

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
********************
ነሐሴ 22-2018ዓም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በአገልግሎት ቀን ሁሉም ሰራተኛ እና አመራር በቢሮው ተገኝቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::

በተቀናጀ አገልግሎት ባለጉዳዮችን እያስተናገዱ ያሉ ሰራተኞች ህዝባችንን ዝቅ ብለን በማገልገል በአገልግሎታችን የረካ ማህበረሰብ ለመፍጠር በመትጋት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር በመሆኑ በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን እያገለገሉ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ  ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት"  ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ...
28/08/2026

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት" ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ወጣቶችን አበረታተዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው፥ ውድድሩ በአደጉና በበለፀጉ ሀገራት እጅግ ተወዳጅ ስፓርት ሲሆን፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፓር መሰረተ ልመቶችን የሚፈልግ በመሆኑ እስከአሁን በአገራችን ሲካሄድ አይስተዋልም፥ ዛሬ ግን በከተማችን በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ምቹ የስፓርት መሰረተ-ልማቶች እውን በመሆናቸዉ አዳዲስ የፓርት አይነቶች እየተካሄዱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

በመቀጠልም፥ ውድድሩ ወጣቶች ልዩ ተሰጥኦና ችሎታቸዉን የሚዳብሩበት ፣ለስፖርት ቱሪዝም፥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት፣ የከተማችንን ገፅታ የሚቀይር እና ተወዳዳሪነታችን የሚጨምር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም እንዲህ አይነት ውድድሮች፥ ወጣቱን ታሳቢ ያደረጉ መሠረተ-ልማቶችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንሰራ ያደርገናል፤ ወጣቱም አለማቀፍ የተወዳዳሪነት መንፈስ እንዲያሳድግ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው አዘጋጆችን “በርቱ” ያሉ ሲሆን፤ ለተወዳዳሪዎችም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ ናቸው - ኢ/ር አያልነሽ ሃ/ማርያምበአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩ...
27/08/2026

በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ ናቸው - ኢ/ር አያልነሽ ሃ/ማርያም

በአዲስ አበባ የተገነቡት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንሱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሃ/ማርያም ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ሥርዓትን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ አሠራር የሚያሸጋግሩ መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ኢንጂነር አያልነሽ ሃብተ ማርያም እንደገለጹት፤ አዲስ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና ተርሚናሎች የህብረተሰቡን እንግልት በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ናቸው።

እያንዳንዳቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጁ፣ ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ልዩ ምቾትን የሚያጎናጽፉ ናቸውም ብለዋል፡፡

በውስጣቸው የታክሲ እና አውቶብስ ተርሚናሎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀሮች እንዲሁም የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ተካተዋል።

በተጨማሪ የንግድ ሱቆች፣ ካፊቴሪያ እና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻ እና ማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች ተሟልተዋል።

ተርሚናሎቹ አሳንሰሮችን እና ንጹህ መጸዳጃ ቤቶችን እንዲሁም የደህንነት እና አደጋ ቅድመ መከላከያ ስርዓቶችን ያካተቱም ናቸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ በሙሉ አቅማቸው ወደ አገልግሎት ሲገቡ በከተማዋ ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የተሽከርካሪ ፍሰት እና የእግረኛ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከማስቻላቸውም ባሻገር ለከተማዋ የ«ስማርት ሲቲ» ውጥን እውን መሆን ጉልህ ሚና ይጫወታሉ።

እየተሰጠ ያለው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የተሻለ እውቀት ይዘን ጥሩ ውጤት እንድናስመዘግብ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተማሪዎች ተናገሩ::********************ነሐሴ 21-2018ዓም በ...
27/08/2026

እየተሰጠ ያለው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የተሻለ እውቀት ይዘን ጥሩ ውጤት እንድናስመዘግብ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተማሪዎች ተናገሩ::
********************
ነሐሴ 21-2018ዓም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ ት/ቤቶች የተማሪዎችን ወጤት በማላቅ ለቀጣይ የትምህርት ክፍል ዝግጁ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል::

አዲስ ከተማ ኮሙኒኬሽን በክላስተር ተከፍሎ እየተሰጠ ያለውን የማጠናከሪያ ትምህርት በሚኒሊየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በአስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ተማሪዎችንና መምህራንን አነጋግሯል::


በሚኒሊየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በክላስተር እየተሰጠ ያለውን የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንዳሉት የክረምት ጊዜያችንን በቤት ውስጥ ከማሳለፍ ይልቅ ከትምህርት ገበታ ሳንርቅ እንድናሳልፍ መደረጉ ለውጤታችን መሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል::

የአስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በበኩላቸው የክረምት ትምህርቱ በስነ-ምግባርና በእውቀት ቀረፃ ረገድ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ተማሪዎቹ ከተለያዩ የግልና የመንግስት ት/ቤት የተወጣጡ ተማሪዎች ተቀላቅለው እንዲማሩ መደረጉ የልምድና የእውቀት ልውውጥ እንድናደርግ አግዞናል ሲሉ ገልፀዋል::

ተማሪዎች የክረምቱን ጊዜ በአልባሌ ቦታ ከመዋል እና በቤት ውስጥ ሊገጥማቸው ከሚችል ማህበራዊ ችግር እራሳቸውን ያዳኑበት መሆኑን የገለፁት መምህራን በበኩላቸው በቀጣይ ለሚጀመረው መደበኛ ትምህርትም ዝግጁና ውጤታማ የሚያደርጋቸውን ነው ብለዋል::

የሚኒሊየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ልዑልሰገድ ይፍሩ በበኩላቸው ከአምስት ት/ቤቶች ከ1 እስከ 30ኛ ደረጃ የወጡ ተማሪዎች ትምህርቱን እየወሰዱ መሆናቸውን ገልፀው ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተግባር በመሆኑ በልዩ ክትትል እየተመራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል::

የማላቅ ስትራቴጂ በሚል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኙ ሶስት ከሰላስተሮች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እየተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ! ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና)   መርቀን ...
26/08/2026

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ!

ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና) መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የትራፊክ መጨናነቅን የሚያቃልሉ፣ የትራንስፖርት ሥርዓትን የሚያሻሽሉ፣ ህዝባችንን ከዝናብና ፀሐይ እንግልት የሚከላከሉ፣ በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ ምቹ ፣ ንፁህ እና የሰውን ክብር የሚመጥኑ የዘመነ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

መሰረተ ልማቶቹ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች፣ ሰፊ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች፣ ካፍቴሪያና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻና ማረፊያ ስፍራዎች፣ ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የአስተዳደር እና የትኬት መቁረጫ ቴክኖሎጂዎች፣ አሳንሰሮች እና ንፁህ መፀዳጃ ቤቶች እንዲሁም የደህንነትና የአደጋ ቅድመ መከላከል ሥርዓቶች የተሟሉላቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም እና ምንም ያልነበረንን ተርሚናል በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል ።
ለከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ቃላችንን በተግባር ስራዎችን እየፈጸምን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እንገኛለን። አዲስ አበባ ከዚህ በላይ ይገባታል ቀጣይም ከሰራነው በላይ እንተጋለን!

የዛሬዎቹ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ለተጋችሁ፣ ላስተባበራችሁ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች በዚህ ስራ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በባለጉዳይ ቀን እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ሆኖ መቀጠሉ ተገለፀ::********************ነሐሴ 20-2018ዓ.ምበክፍለ ከተማ አስተዳደሩ አገል...
26/08/2026

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በባለጉዳይ ቀን እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ሆኖ መቀጠሉ ተገለፀ::
********************
ነሐሴ 20-2018ዓ.ም

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሰራተኛና አመራር ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ::

አገልግሎት ሲቀበሉ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ሆኖ መቀጠሉን ተናግረዋል ::

መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

በፌዴራል ደረጃ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በበጎ ፈቃድ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የመስክ ምልከታ አካሄደ::*****************ነሐሴ 19-2018ዓምበብልፅግና...
25/08/2026

በፌዴራል ደረጃ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በበጎ ፈቃድ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የመስክ ምልከታ አካሄደ::
*****************
ነሐሴ 19-2018ዓም

በብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደስታ ብዙአየሁ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ዘርፍ ህብረተሰቡን በማስተባበር የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል::

በሱፐርቪዥን ቡድኑ ምልከታ ከተደረገላቸው ፕሮጀክቶች መካከል በወረዳ 6 በጎነት መንደር የተገነባው የጋራ መኖሪያ ህንፃ፣ በወረዳ 4 እህል በረንዳ አካባቢ የተገነባው የጋራ መኖሪያ ህንፃ፣ በወረዳ 14 የሚገኘው አዲስ ኢኮ ፓርክ፣ ተረጅነትና ልመናን ለማስቀረት የተገነባው የእህል መጋዝን እንዲሁም ጫካ ሜዳ የወጣቶች ማዘውተሪያ ስፍራ ተጠቃሾች ናቸው::

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የገለፁት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በፌዴራል ደረጃ የተደረገው ድጋፋዊ ሱፐርቪዥኑ ጥንካሬዎቻችንንና ክፍተቶቻችንን ለይቶ የሚያሳይ በመሆኑ በእጅጉ ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በብልፀግና ፓርቲ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደስታ ብዙአየሁ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የበጎ ፈቃድ ስራዎች በላቀና ከፍ ባለ ደረጃ የሲቪክ ማህበሩን ባሰተፈ መልኩ መሰራታቸውን በተደረገው ምልከታ መረጋገጡን ጠቅሰው የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ለሌሎች ክፍለ ከተሞችም ዓርዓያነት ያለው ተግባር ፈፅሟል ሲሉ ተናግረዋል::

ሌሎች የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው
በክረምት በጎ ፈቃድ የነዋሪውን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተዘዋውረው ባደረጉት ምልከታ ማረጋገጣቸውን ገልፀው አዲስ ከተማ ክ/ከተማ በትክክለኛው የልማት ጉዞ ላይ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል ብለዋል፡፡

በተለይ ከለውጡ ወዲህ ለበጎ ፈቃድ ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ያሻሻሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወናቸው ይህ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል::


በተካሄደው ምልከታ ከላይ ከተጠቀሱት የስራ ሃላፊዎች በተጨማሪ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

ዛሬ የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች እና የቦርድ ሃላፊ ክቡር ክሪስ ሆን እና ቡድናቸውን ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና  ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን አስጎብኝተናል። ለ...
25/08/2026

ዛሬ የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች እና የቦርድ ሃላፊ ክቡር ክሪስ ሆን እና ቡድናቸውን ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን አስጎብኝተናል።

ለነገዋ ጅማሮው በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ ሴቶች እህቶቻችን ተስፋና እድላቸው እዲለመልም፣ ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ከልብ በመነጨ ስሜት የተፀነሰ፣ ተፀንሶም ወደ ተግባር የተቀየረ ትልቅ ራዕይን የሰነቀ ስራ ነው።

የእነዚህ እህቶቻችንን ህይወት ለመቀየር፣ ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2016 ዓ.ም ጀምረነው በ5 ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 3,259 ሰልጣኞችን በክህሎት እና በስብዕና ግንባታ አሰልጥነን ወደ ስራ አሰማርተናል።

ዛሬ ሁሉም ተመራቂዎች ክብር ያለው ኑሮ፣ ብሩህ ተስፋን ሰንቀው አዲስ ህይወት መኖር ጀምረዋል።

“ከምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ትልቁ ስራ በሰው ላይ የምንሰራው፣ በተለይም በሴቶች ላይ የምንሰራው ነው” የሚለውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት የስራችን ማዕከል አድርገን እየፈፀምን እንገኛለን።

በከተማችን ላይ ከሚታየው ለውጥ ሁሉ የሚልቀው በለነገዋ ሴቶች ላይ እያየን ያለው ለውጥ ነው።

ለ”ለነገዋ የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል” የሰነቅነው ራዕይ፣ በዓመት እስከ 10 ሺህ ሴቶችን የሚያበቃ፣ እንዲሁም አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ልምድ የሚቀሰምበት የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ማስቻል ነው ።

ይህ ራዕይ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ሊደግፋን የመጡት የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች ክቡር ክሪስን በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አስጎብኝተን በቀጣይም በጋራ በምንሰራቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይተናል።

ለራዕያችን ግብ ስኬት ሌት ተቀን ተግተን እንሰራለን ፤ ፈጣሪም ይረዳናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው  የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉን  ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis ketema woreda 9 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share