05/09/2026
"የመረጃ እና የትርክት የበላይነትን መጎናፀፍ ዋና ስትራቴጂካዊ ግባችን ነው!"
በብልፅግና ፓርቲ የአራዳ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ በከ8ቱም ወረዳዎች የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች እና ከበጎ ማህበረሰብ አንቂዎች የዘርፉን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በውይይት አዳብረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአራዳ ቅ/ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጆቴ በመድረኩ እንዳስገነዘቡት በበጀት ዓመቱ በሀሳብ ልህቀት፣ በተጨባጭ ስኬት የገዘፈውን ብልፅግና ፓርቲን፣ በሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን እና በፈጣን ለውጥ ላይ የምትገኘውን ክፍለ ከተማችን ብሎም አዲስ አበባን የሚመጥኑ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎችን ለማከናወን ሁሉንም አቅሞች በማቀናጀት ብርቱ ርብርብ ይደረጋል።
አርቆ ማለም፣ አስፍቶ ማቀድ፣ አልቆ መተግበር እና የላቁ ድሎችን ማስመዝገብ የብልፅግና ፓርቲ መለያ መሆኑን የገለፁት አቶ ደቻሳ ዘርፉም አንድ ዕቅድ፣ አንድ ምዘና፣ አንድ ሪፖርት በሚል የተልዕኮ ስምሪት የተናበበና የተቀናጀ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
የመረጃና የትርክት የበላይነትን መጎናፀፍ የዘርፉ ዋና ስትራቴጂካዊ ግብ መሆኑን የጠቆሙት በሰው ሀይል፣ በአሰራር እና በግብዓት የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማላቅ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባ የገለፁት በልጽግና ፓርቲ የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪ ት ቤተልሄም ትደሩ የህዝባችንን የአብሮነት እሴት የሚያጠናክሩ፣ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብቱ፣ ስኬቶቻችንን የሚያሰፉ፣ የፓርቲያችንን እና የመንግስትን ቅቡልነት የሚያሳድጉ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎችን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ በአፅንዖት ገልፀዋል።
ክፍለ ከተማችን ብሎም ከተማችን አዲስ አበባ በፈጣን ለውጥ ላይ የምትገኝ ፣ አዳጊ የህዝብ ፍላጎት ፣ ለቴክኖሎጂ የቀረበ ህዝብ ያላት ዓለም አቀፍ መዲና መሆኗን ታሳቢ ያደረጉ የዘርፉ ግቦች የቀረቡ ሲሆን የበሰለ ውይይትም ተደርጎባቸዋል።
ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ቁርጠኝነትን በመላበስ የዘርፉን ስትራቴጅካዊ ግቦች አልቆ ለመፈፀም ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም፣ ሁሉንም አቅሞች በማስተባበር ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
በማጠቃለያም የዕቅድ ግቦች ላይ የተመሠረተ አፈጻጸም በKPI መመዘኛ ከወረዳ ዘርፍ አመራሮች ጋር በመፈራረም የዕቅድ ዉይይቱ መድረክ ተጠናቋል።