Lula Ethiopia

Lula Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lula Ethiopia, Social service, Addis Ababa.

አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከአማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ...አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል...ልጅም አባቱን...ማነው የሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል፡...
31/03/2025

አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከአማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ...አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል...
ልጅም አባቱን...ማነው የሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አባትም በር ላይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነሱ ናቸው ይለዋል...

ልጁም ይገረምና... ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል፡፡

አባትም የኮረኮሩትን ያህል ይስቅና... እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም! ብሎ መለሰለት፡፡

ከአንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ "ደራሲው" በተሰኘው መፅሐፉ ውስጥ ከገፅ 125-126

"እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም!" የምትለዋን አረፍተ ነገር ሳነባት አስገረመችኝ! አስደነገጠችኝም!

ዛሬ ላይ አንድነትን የማይሹ እና መተባበርን የማይፈልጉ አካላቶች ሀገራችን ውስጥ በሁሉም ብሄርና ሀይማኖት ውስጥ አሉ፡፡

እነዚህ አካላቶች እብዶች ይሆኑ እንዴ?! ...እብዶች በመሆናቸው ይሁን መተባበርንና አንድነትን የማይፈልጉት?

እነዚህን እብዶች እንደ በግ እየተነዳ የሚከተላቸው የሀገሬ መንጋ ህዝብስ እንደነሱ አብዶ ይሆን?

እኔንጃ!
Mp Ethiopia 👌 በትክክል ተግልጾል😊

❶መጽሐፉ ከምስጋና ገጹ ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦                           እነሆ                     ገጸ በረከት       ከቃለት ብልግና ላለፉ ነቄ ዜጎች❷ስብሐት ት...
29/03/2025



መጽሐፉ ከምስጋና ገጹ ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦

እነሆ
ገጸ በረከት
ከቃለት ብልግና ላለፉ ነቄ ዜጎች



ስብሐት ትኩሳት ላይ እንዲህ ይላል፦

"የፈረንጅ ሽማግሌዎች እና አሮጊቶች በጣም ነው የሚቀፉት . . . የወየበ እና የተጨማደደ ቆዳ፣ የተንጠለጠለ ከንፈር፣ ባለ ሙስታሽ(የከንፈር ጺም) አሮጊቶች፣ በኤክስ ጎዳናዎች ላይ ተቀምጠው የሚያንጎላጁ፣ የመኖር ግዜ አልቆባቸው ዘመናዊ ሕክምና ሞት ከልክሏቸው በጣም ይቀፋሉ"

ሌቱም አይነጋልኝ መጀመሪያ ላይ ደግሞ ሌላ የማይመች እውነት እንዲህ ይነግረናል፦

"ምግብ በልተን አር እንወልዳለን፤ በጣም ያሳፍራል። እስቲ! የከተማችን ምግብ ቤቶች ጎራ በል። ህዝበ አዳም አይኑን ጨፍኖ ሲግጥ፣ ሲያላምጥ ትታዘባለህ። ይሄ ሁሉ መጋጋጥ ያቺኑ የፈርስ ስልቻ ለመሙላት ነው። ቀበቶህን ጠበቅ ባደረግህ ቁጥር ፈርስ እየጨፈለቅክ መሆኑን አትዘንጋ"

§§§

ነገሮቹ እውነት ናቸው። ለአብነት ያህል ሁለቱን ጠቀስኩ እንጂ ስብሐት ሁሌም አስደንጋጭ እውነት እንደነገረን ነው። መጀመሪያ ለሚሰማቸው ያስደነግጣሉ። ስብሐትን የምታደንቀው ይሄኔ ነው። ማህበረሰቡ እርስበራሱ የሚመች፣ የማይቆረቁር ውሸት እየተነጋገረ ይሸነጋገላል። እውነተኛ ደራሲ እውነትን አይሸፋፍንም፤ ደፋር ነው! ማህበረሰቡ ቢቀየምም ፍርጥ አድርጎ እውነቱን ይናገራል። ይህ ትልቅ እሴት ነው። የታደሉት ጥቂቶች ናቸው!



ወይኔ ወጣትነቴ የማውቃቸው ወጣቶች ነበሩ

አንዶቹ፣ ቤተስኪያን ሄዱ፤ ከግዜር ተዛመዱ፤ መንፈሳዊ ሀብትን ዘሩ፣ ሰሙነኛ ሆኑ።

ሁለቶቹ፤ በአውቀት ለመበልፀግ፤ ወደፊት ለማደግ፤ ወዳጅ አገር በረሩ፤ ዘመናዊ ሆኑ።

ሶስቶቹ፣ በወጣትነቴ እሳት አለምን ላቃጥላት፤ ብለው ተነስተው እንዳያፍሩ ሰከሩ፣ አንዳይፈሩ ፎከሩ፣ ሸርሙጣ አቅፈው አደሩ።

ሌሎቹ፣ ልጃገረድ ከነፈሩ፣ የሰው ሚስት አነጣጠሩ፣ አንድዋን ሳቱ፤ አንድዋን መቱ።



ትንሽ ብታስብበት መብላት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው:: ቄራ ውረድና አንድ ሰአት ያህል አስተውል፡፡ በሬውን አንገቱን ገዝግዘው ሲያርዱት፣ ቆዳውን ሲገፉት፣ ብልቱን ሲለያዩት፣ ፈርሱን ሲጎለጉሉ ተመልከት። ሆቴል ግባና አይንህን ጨፍነህ ህዝቡ ሲያኝክ፣ አጥንት ሲቆረጣጥም ስማ። ኣክl ምን ኣይነት መጨማለቅ ይሄ ሁሉ ያችን የግማት ስልቻ ለመሙላት ቀበቶህን ባጠበቅክ ቋጥር ሲርስ እንደምትጨፈልቅ አስበህበታል? ልክ የጎለጎሉትን የበሬውን ፈርስ የሚመስል። ለመሆኑ፣ በሬውን ሲያርዱት በስመአብ ብሰው ሲጃምሩ አይገርምህም? እኔ በበኩሌ ይህን በስመአብ ብሎ ማረድ የጀመረ ቀልደኛ ቁስ ነው እላለሁ። ቀልድ ካልሆነ፣ እንዴት የእብን ፍጠር በአብ ስም ትገድለዋለህ?

ማራት መቸስ አንድ ትልቅ ውርጃት ነው፡፡ አፍንጫህንና እይንህን እንዲሁም ጆሮህን ብትጠይቅ ይህን ያረጋግጡሀል። ቂጥህን በጠረግክ ቁጥር አይቀፍህም? ምግብ በልቶ አር የሚወልድ ሁሉ እንዴት በአፍረት አይሞትም? ይሄ ሁሉ ሲሆን «አር ሲቀብጥ የንግላል ይወድቃል» ግን የአስተያየት ጉዳይ ነው፡፡ ማለቴ፣ አሩ እንግላል የሚወድቀው ሲቀብጥ ነው ወይስ ሲዘንጥ ነው? ሲቀልድ እንደሆነስ? ወይስ ጅምናስቲክ መስራቱ ይሆን? የሆነ ሆኖ፣ አሩን አፍንጫችንን ይዘን እንለፈው።



"ሌቱም አይነጋልኝ" በ2004 ወደ ፈረንሳይኛ ተተርጉሟል። የፈረንሳይኛው ርእስ "የአዲስአበባ ምሽቶች" የሚል ድምፀት አለው። ስብሐት ፈረንሳይ ኖሯል። የኤሚሊ ዞላ ተፅእኖ አለበት። ዞላ ደግሞ ፈረንሳዊ ነው። በዚያ ላይ ፈረንሳውያን ወሲብን ያመልካሉ፤ ወሲብን ይተነፍሳሉ፤ ወሲብን ይኖራሉ። ሶስት ማሳያዎች፦

፩) ፓሪስ ውስጥ ራቁትን ሆኖ የሚበላበት ሬስቶራንት፣ ራቁትን ሆኖ የሚዝናኑበት የሃይቅ ዳርቻ(beach) እንዲሁም የራቁት ቀን የሚከበርባት ብቸኛ ሃገር ናት።

፪) ፈረንሳዮች በወሲብ በጣም ከመመሰጣቸው የተነሳ ፍሬንች ኪስን ፈልስፈዋል።

፫) ሶስተኛው ቀልድ ነው። ቢሆንም ፈረንሳውያንን በደንብ ይገልፃቸዋል። ሰውዬው ካቶሊክ ነው። ሃጥያቱን ለመናዘዝ ቄሱ ጋር መጣ።

"ይፍቱኝ አባቴ"
"ምናጠፋህ ልጄ"
"ሚስቴ ከቤት ስትወጣ ሰራተኛችንን ወደ መኝታ ቤት ጠራኋት"
"እሺ"
"አልጋ ላይ እንድትቀመጥ ነገርኳት"
"እሺ"
"መሳሳም ጀመርን"
"እሺ"
"ልብሳችንን ማውለቅ ሳንጀምር ሚስቴ ተመለሰች"
"ሜርድ" አሉ ቄሱ ከሃጥያቱ ይልቅ ወሲቡ በመቋረጡ ተናደው።"😆😆

ታድያ የ"ሌቱም አይነጋልኝ" ወደ ፈረንሳይኛ መተርጎም ስነፅሁፍ ትክክለኛ ቦታውን አገኘ ማለትም አይደል!



የስብሐት ገብረእግዚአብሔር ልብወለድ "ሌቱም አይነጋልኝ" ዋና ገፀባህርይ ክንፈ ነው። የክንፈ ገድሎች ብዙ ናቸው። መርጬ ጥቂቱን ልንገራችሁ።



ክንፈ ጨዋታ አሳማሪ፣ ከባድ ጠጪ፣ ሴት አውል ፈረንጆቹ womanizer የሚሉት ነው። ስብሐት ስለ ክንፈ ሲናገር አለም ሁሉ ንቆኝ ክንፈ ካከበረኝ በቂዬ ነው እያለ ነው።



ክንፈ መልከቀና ነው። የውቤ በረሃ ሴቶች ይሞቱለታል። ስለ ክንፈ እንዲህ ይላሉ፦ ክንፈ መልኩ ኤልቪስ ፕሪስሊን ነው የሚመስለው። ግን የኤልቪስ ከንፈር የሴት ነው። ከንፈርስ የክንፈ ይምጣብኝ።



አንዴ ክንፈ ከጓደኞቹ ጋር አስመራ ውስጥ እየጠጡ ነው። በመሀል ማሚት እሹሩሩ ናፈቀችው። ውቤ በረሃ ውሰዱኝ አለ። ከሚጠጡበት ቤት ወጥተው ፈረስ ጋሪ አስቆሙ።

"ማሚት እሹሩሩ ቤት ውሰደን
"ዋይ! ማሚት እሹሩሩ ቤት የት ነው?"
"ውቤ በረሃ?"
"ደግሞ ውቤ በረሃ የት ነው?"
ጭራሽ ውቤ በረሃን የማያውቅም አለ። በቃ ይሄ ህዝብ ተስፋ የለውም ብለው ደመደሙ።
"አዲሳባ ነዋ"
"ዋይ! ከዚህ አዲሳባ በፈረስ ጋሪ ልትሄዱ ትፈልጋላችሁ?!"



ክንፈ ውቤ በረሃን ሳይሳለም አያድርም። ገና ወደ ውቤ በረሃ መምጣት እንደጀመረ አንድ ገድል ለመፈፀም ይነሳል። የውቤ በረሃ ሴቶችን ተራ በተራ እየቀረበ "ገና አዲስ ወታደር ነኝ። ነገ ወደ በረሃ ልዘምት ነው" ብሎ አስተዛዝኖ ሴቶቹን ይተኛቸዋል። ሲጨርስ ድፍን 100 ብር አውጥቶ ይሰጣቸዋል። ሴቶቹ ግድየለም ሌላ ግዜ ትሰጠናለህ እያሉ ያሰናብቱታል። የዋህነታቸውን ተጠቅሞ ሰባት ሴቶችን ከተኛ በኋላ ሴቶቹ እርስበእርስ መነጋገር ይጀምራሉ። የሰራቸውን ጉድ ሲረዱ የድንጋይ ናዳ ሊያወርዱበት ሲፈልጉት እግሬ አውጪኝ ብሎ አጥር ዘሎ ያመልጣቸዋል።



ክንፈ ደግ አክስት አሉት። እጅ ሲያጥረው ሊጠይቃቸው ይሄዳል። ታዲያ ሁሌም ከኪሱ የማትለየው መሃረብ አለችው። መሃረቧ በበርበሬ የታጠነች ናት። አክስቱ ጋር ሄዶ ደህንነቱን ሲጠይቁት ችግር ሊያወራ ይጀምራል። ወዲያውኑ መሃረቡን አውጥቶ አይኑን ሲያብስ በርበሬው ይለበልበውና እንባው ይወርዳል። አክስቱ እንባውን ሲያዩ ይደነግጡና ከኪሱ ብር ይሸጉጣሉ።



በነገራችን ላይ በሌቱም አይነጋልኝ ውስጥ ተራኪው ገፀባህርይ ምናሴ ነው። ያው ምናሴ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ነው። ስብሐት ለክንፈ ያለው አክብሮት ለትኩሳቱ ባህራም ካለው ጋር ይመሳሰልብኛል። ደራሲው ስብሐት የሁለቱንም ገፀባህርይ ነፍስ እርቃን አስቀርቶ ከነድክመታቸው ያሳየናል። ከድክመታቸው ባሻገር ለሁለቱም ጥልቅ ክብር ነበረው።

ለዛሬ ነበር የቀጠሩት። ሳይዘገይ በሰአቱ ደርሷል። እርሳሳቸውን እየቀረፁ ነበር። እንዲቀመጥ በምልክት አሳዩት። ተቀመጠ።

"መፅሀፍህ ብዙ ሚስጥር አለው" አሉት ገና ከመቀመጡ።

"እንዴት?"

"ለምሳሌ ገፅ 1 ላይ 'ፀሀይዋ ጠለቀች' ብለሃል። ምን ለማለት ነው?! ተው ተው ራሴ እነግርሃለሁ። ፀሃዩ ንጉሳችን ጠለቁ፣ ሞቱ ለማለት ነው አይደል። ንጉሳችን ላይ ለሟሟረት ነው አይደል?!"

"እንደሱ አይደለም። በቃ ፀሃይዋ ጠለቀች ማለት ነው"

"የለም የለም! መፅሀፍህ በቅኔ የታጨቀ ነው። በእርጋታ ማጥናት ያስፈልጋል። እዚያው ገፅ አንድ ላይ እናትየው ደክሟቸው አረፍ አሉ ብለሃል። እናት ሃገር ኢትዮጵያ ደክሟታል ለማለት ነው?!"

"መፅሀፌን መመርመር ከጀመሩ 2 ወር ሆኖታል―በዚህ ሁሉ ግዜ ሳንሱር ያደረጉት 3 ገፅ ብቻ ነው።"

"እንደነገርኩህ ነው። መፅሀፍህ ብዙ ሚሰጥር አለው። በእርጋታ ማየት ይጠይቃል"

"በዚህ ፍጥነት መች ሊያልቅ ነው?! ሳንሱር አድራጊ ሲቀየር ብመጣ ይሻለኛል"

"አዪ! መስሎሻል እኔ የትም አልሄድም።"

ደራሲው ድንገት ተነሳና በሩን ከኋላው ዘግቶ ወጣ። ይህን ግዜ የሳንሱር ሹሙ በእርሳሳቸው 400ን ለ3 ማካፈል ጀመሩ።

(ሌቱም አይነጋልኝ ላይ ካነበብኩት ቆየት ያለ ታሪክ ነው። የማስታውሰውን ያህል ፅፌዋለሁ)

▼ኮሎኔል አጥናፉ አባተ #ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ኾኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የ...
23/03/2025

▼ኮሎኔል አጥናፉ አባተ

#ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ኾኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። "አብዮት ልጆቿን በላች" ተባለ።

#ሲያልቅ አያምር ሆኖ እንጂ መንጌና አጥናፉ ጎረቤት ነበሩ። ሚስቶቻቸው ውባንቺና አስናቀች በአንድ ስኒ ቡና ጠጥተዋል። ትምህርትና ትዕግስት ከነሱራፌል አጥናፉ ጋር ኳስ ሲራገጡ፣ መሐረቤን ያያችሁ ሲጫወቱ ይውሉ ነበር። ጨርቆስ፣ መሿለኪያ፣ 4ኛ ክፍለ ጦር ግቢ የሟችም የ'ገዳይ'ም ቤት ነበር።

#መንጌ ቀኝ እጃቸው፣ ጎረቤታቸውና ለአጭር ጊዜም ቢሆን አለቃቸው በነበሩት ሻለቃ አጥናፉ ላይ ድንገት "ሲጨክኑ" ሐዘኑ ከባድ ሆነ። የሟች ልጅ ሱራፌል አጥናፉ እንደሚያስታውሰው ከሆነ ገራገሯ ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው ለቅሶ ደርሰዋቸዋል። "ትዝ ይለኛል እማዬ ወይዘሮ ዉባንቺን 'ባልሽ ባሌን ገደለው!' እያለቻት ተቃቅፈው ሲላቀሱ" ይላል ሱራፌል።

#ለመሆኑ ከኮሎኔል አጥናፉ አባተ መገደል በኋላ ልጆቹ እንደምን ኖሩ? ከ8ቱ ልጆች 5ኛው ሱራፌል አጥናፉ "መንጌ አባቴን ካስገደለ በኋላ እኛን እንዳሮጌ ዕቃ ከቤት አውጥተው ጣሉን..." ሲል ረዥሙን ቤተሰባዊ ምስቅልቅ በአጭር ዐረፍተ ነገር ይጀምራል፡፡

"ሁለቱ ወንድሞቼ በብስጭት ሞቱ"

#ሱራፌል አጥናፉ አባተ እባላለሁ። የኮ/ል አጥናፉ 5ኛ ልጅ ነኝ። አሁን እኔ ራሴ አምስት ልጆች አሉኝ። የምተዳደረው በሹፍርና ነው።

#የአጥናፉ ልጆች 8 ነን። አሁን በሕይወት ያለነው ግን አምስት ስንሆን ሦስቱ በሕይወት የሉም። የሁለቱ ሞት ከአባታችን መገደል ጋር የተያያዘ ነው። አባታችን አጥናፉ የተገደለው ሁለቱ ወንድሞቼ ራሺያ በሄዱ ልክ በ10ኛው ቀን ነበር።የታላቄ ታላቅ ሰለሞን አጥናፉ ይባላል። ራሺያ ለከፍተኛ ትምህርት እንደሄደ ያባታችንን ሞት ሲሰማ በዚያው የአእምሮ በሽተኛ ሆነ። እዚህ መጥቶ አማኑኤል ሆስፒታል ተሞከረ፤ አልተቻለም። እናታችን ብዙ ደከመች። አልሆነም።

#በጣም ይበሳጭ ነበር፤ በአባታችን ሞት። ለምሳሌ እንደማስታውሰው ድንገት ተነስቶ በእግሩ ጎጃም ድረስ ይሄድ ነበር። አእምሮው ታወከና በመጨረሻ ብዙም አልቆየ ራሱን አጠፋ።

#የሁላችንም ታላቅ ዶክተር መክብብ አጥናፉ ይባላል። እሱም እንዲሁ በአባታችን አላግባብ መገደል በጣም ይበሳጭ ነበር። ራሺያ ሕክምና ተምሮ ከተመለሰ በኋላ ብዙ ዓመት ሆሳዕና "መንግሥቱ ኃይለማርያም ሆስፒታል" ሠርቷል። አባቱን በገደለው ሰው ስም በተሰየመ ሆስፒታል ውስጥ መሥራት ምን ስሜት እንደሚሰጥ አስበው።

#ከሆሳዕና ሕዝብ ዶክተር መክብብን የማያውቅ የለም ማለት ይቻላል። ተወዳጅ ሐኪም ነበር። ግን በአባታችን ሞት እጅጉኑ ይበሳጭ ነበር። እኔ እጨቃጨቀው ነበር።

'በቃ አባታችን የሚያምንበትን ሠርቶ አልፏል። እኛ የራሳችንን ሕይወት ነው መኖር ያለብን' እለው ነበር። እሱ ግን ብዙ ምስጢር ያውቅ ስለነበር አይሰማኝም፤ በጣም ብስጩ ሆነ። በመጨረሻ እሱም ጭንቅላቱ ተነካና ሞተ።

#ሟች ወንድሞቻችን ሰለሞንና ዶክተር መክብብ አባታችን ነገሌ፣ 4ኛ ክፍለ ጦር እያለ የተወለዱ ነበሩ። ሌሎቻችን ግን እዚህ መሿለኪያ 4ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ውስጥ ነው የተወለድነው። ቴድሮስ፣ ጌታሁን፣ ሳምሶን፣ እንዳለ፣ እህታችን አብነት፣ እኔን ጨምሮ- ሁላችንም የመሿለኪያ ልጆች ነን፡፡

◈ምንጭ -BBCNewsAmharic

ስለዩኒቨርስቲ ህይወት ሀይስኩል ላለው ታናሸ የላኩለት!በ ሀቅ እና ድንቅ  በመጀመሪያ በተለያየ መጠንና ግብዓት የተዘጋጀ ዳቦ ቆሏችንና በሷችንን ጆንያ በሚያስንቅ ፔስታልና ኮንቴነር በሚያክል ...
05/03/2025

ስለዩኒቨርስቲ ህይወት ሀይስኩል ላለው ታናሸ የላኩለት!
በ ሀቅ እና ድንቅ
በመጀመሪያ በተለያየ መጠንና ግብዓት የተዘጋጀ ዳቦ ቆሏችንና በሷችንን ጆንያ በሚያስንቅ ፔስታልና ኮንቴነር በሚያክል ሻንጣ ይዘን ያስገረመንን ትልቅ በር አልፈን ወደዩኒቨርስቲው ገባን። በመጀመሪያዎቹ ቀናት ምድብ ድልድል ወጣልን፡፡
ልዩ የቅበላ ፕሮግራም ከአማራ ክልል ለመጣችሁ፣ ለኦሮሚያ ተወላጆች፣ ለተጋሩ፣ በጌታ ለሆናችሁ፣ ለኦርቶዶክሳዊያን፣ ለሙስሊም ወንድሞቻችን ወ.ዘ.ተ አይነት ማስታወቂያዎች ግድግዳዎቻችንን አጨናነቁት፡፡ “እየመደቡን ይሁን እየሰደቡን ፈጣሪ ይወቀው፡፡” ነቄ ያልነው ሰኞ የአማራ ክልል የስነፅሁፍ ፕሮግራም፣ ማክሰኞ የተጋሩ የጥበብ ምሽት፣ እሮብ የኦሮሚያ የባህል ምሽት፣ ሃሙስ ከኦርቶዶክሶች ጋር ግቢጉባዔ፣ አርብ ከሙስሊሞች ጋር መስጊድ፣ ቅዳሜ ከጴንጤዎች ጋር ፌሎውሺፕ፣ እሁድ ማታ ጭፈራ ቤት... እያልን ሰባቱንም ቀናት መታደም ጀመርን፡፡ ምንያቱም ፍሬሽ ነበርና፡፡ ገና ዶርም ሲደለደል የሀገር ልጅ የሚለው ሃሳብ የክልልና የጎጥ ልጅ የሚለውን እንደሚወክል ተማርን፡፡
በገባንበት ሰሞን ለመጀመሪያ ጊዜ ካፌ ገባን፡፡ ሽታው እያጥወለወለን መሰለፍ ጀመርን፡፡ “አመቱን ሙሉ ይሄንን እንዴት ነው የምንለምደው” ስንል ተገረምን፡፡ በዚያው ሰሞን ላውንጅ የሚባል ማስታገሻ እንዳለ አወቅን፡፡ እዚያም ሄደን ተሰለፍን፡፡ የያዝነው ገንዘብ፣ በሶ እና ዳቦ ቆሎ ስላለቀ ባንክ ቤትም ሄደን ተሰለፍን፡፡
ታናሼ ህይወት በካምፓስ እንዲህ ይጀምራል፡፡
ብዙ ሳትቆይ ክላስ ትጀምራለህ፡፡ ገና በመጀመሪያው ቀን ናይጀሪያዊ ወይም ህንዳዊ መምህር ይገባና በቋንቋ ት/ቤት ከተማሩ ልጆች ጋ ሲያወሩ አስደንጋጭ እንግሊዘኛ ጆሮህ ላይ እንደ መብረቅ ይወርድብሃል፡፡ “እኔ ከእነዚህ ጋ ተምሬ አንድ ሴሚስተር እዘልቃለሁን?” ትላለህ፡፡ ለማንኛውም አትፍራ፡፡ በሴሚስተሩ መጨረሻ አንተ አስኮራጅ እነሱ ኮራጅ በአመቱ መጨረሻ ደግሞ አንተ ሰቃይ እነሱ ወራጅ ልትሆኑ ትችላላችሁና፡፡
ከጎንህ የብርጋዴር ጀነራል እከሌ ልጅ ይቀመጣል፡፡ ከሱ ፊት የፓስተር እእንትና ልጅ አለች፡፡ ከኋላህ ሰለሳ ግመልና መቶሃምሳ ፍየል ያለው የአርብቶ አደር ልጅ አለ፡፡ ከሱ ጎን “የጤፍ ተክል አይቼ አላውቅም” ያለችዋ ልጅ፥ “የዶሮ ብልት ስንት እንደሆነ አላውቅም” ካለችዋ ሞልቃቃ ጋ ተቀምጠው ስለናይት ክለብ ሲወያዩ ወይም ባቡር ደግሞ ምንድን ነው ባለችው ኮርነር ላይ በተቀመጠችው የገጠር ልጅ ቀሚስና ሹራብ ሙድ ሲይዙ ትሰማለህ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ወደክፍልም ሆነ ወደግቢ በጊዜ ገብተው አያውቁም፡፡ ከነሱ ጎን ከሁሉም ቆንጆ ነኝ ብላ የምታስበዋ፣ አንገቷን እንኳን ስታዞር ሜካፕዋ እንዳይበላሽ የምትጠነቀቅ የምትመስለው ቄንጠኛ ልጅ ትቀመጣለች። እኛ ግን አንወዳትም፡፡ ጥግ ላይ ከሁሉም ቆንጆ ናት ብለን የምናስባትና የምንወዳት አይናፋር ትቀመጣለች፡፡ ከሁላችንም ፊት ክረምት ላይ በሚሰራው የቀን ስራ ራሱን የሚያስተዳድረው ሰቃይ ይቀመጣል፡፡ ከጎኑ እንትን ህንፃ በስሙ የተሰየመለት የዲታ ልጅ አለ፡፡ ይህ ሁሉ የሚገባህ ግን ስትቆይ ነው፡፡ ስትቆይ በኢትዮ-ኤርትራ ጊዜ የዘመተ ልታከብረው የሚገባህ ሰው አብሮህ እንደሚማር ታውቃለህ፡፡ ስትቆይ በጣም ዝምተኛው ልጅ ጎበዝ ሰአሊ እንደሆነ ይገባሃል፡፡ ብረት የሚገፋው ጉልቤው ልጅ ከሁሉም ፀባየኛ እና ምስኪን ይሆንብሃል፡፡ ከሁሉም ሴቶች አስቀያሚ ናት ያልካት የሚያምር ድምፅ ያላት ዘማሪ ትሆናለች፡፡ ከዛ ደግሞ እንደኔ አይነት አንድ ሁለት “ጥበብ ጠራችኝ ወይም አጠናገረችኝ የሚሉ ፍሪኮች” እንኖራለን፡፡ ጎበዝ ዘፋኝ፣ ጎበዝ አትሌት፣ ጎበዝ እግርኳስ ተጫዋችና ሁሉንም አይነት ተማሪዎች ታያለህ፡፡ ስምንት ሴቶች ሲጀምሩ በቡድን ይንቀሳቀሱና ሲጨርሱ ስምንት ባላንጣዎች ይሆናሉ፡፡ ሲጀምሩ ስምንት ብቸኛ የነበሩ ወንዶች ሲጨርሱ አንድ ቡድን ይፈጥራሉ፡፡
ክፍል እንደ ማቅለጫ ድስት (Melting Pot) እንደማለት ነው፡፡ ሁላችሁም አንድ ላይ ተቀምጣችሁ ትማራላችሁ፡፡ ፈተና ይደርሳል፡፡ ቴንሽን ያከሳሃል፡፡ ያንጨባርርሃል፡፡ እስኪነጋ ታጠናለህ፡፡ በሶ ስትበጠብጥ ታድራለህ፡፡ ታስጠናለህ ታጠናለህ፡፡ ትኮርጃለህ ታስኮርጃለህ፡፡ ውጤት ሲመጣ የተገላቢጦሽ ይሆናል፡፡ ከለፈለፉት ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ዝም ካሉትም ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ነጋ ጠባ ካጠኑትም ጥቂቶች ይሰቅላሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ ያጠናህ አንተም ትሰቅልና ትገረማለህ፡፡ በተገለጠለት እንጂ በገለጠ አይደለም ትላለህ፡፡ እንኳን ሊያስኮርጁህ አሳይመንት እንኳን የሚደብቁህም አሉ፡፡ የቡድን ስራ ብቻህን ሰርተህ ትቀፍላለህ፡፡ ወራጅ እየተጫረ፣ ሰቃይ እየሰቀለ አብዛኛው በመሃል ቤት ሆኖ ጊዜው እንደዚህ ይነጉዳል፡፡ በዚህ መልኩ ስማቸውን የማይፅፉ አብረውህ ይመረቃሉ፡፡ የአራት አመት ትምህርት ሰባት አመት የሚፈጅባቸውም ይመረቃሉ፡፡
ሴሚስተሮች ያልፋሉ፡፡ ፍሬሽነት ቀርቶ ሲኒየር ትሆናለህ፡፡ ስትቆይ ከብዙ ሰዎች ጋር ትግባባለህ፡፡ ባህሪ ትወራረሳለህ፡፡ ፀጉርህን ታንጨባርራለህ፡፡ የማታውቀውን ብሄር ቋንቋ ከሆነ ትማራለህ ያለዚያም ትለምደዋለህ፡፡ የፅዳት ሰራተኛ እናቶች የግቢ እናት ይሆኑሃል፡፡ ካፌ ሳይገቡ የመኖር ሚስጥር ይገለጥልሃል፡፡ ትቀፍላለህ፡፡ ካልሆነልህ ትሰቅላለህ፡፡ ሰልፍ የማጭበርበር ክህሎትን ታዳብራለህ፡፡ ከብረት ገፊዎች ጋ ዶርም ከደረሰህ ብረት ገፊ ትሆናለህ፡፡ “በጌታ ነኝ” ትል የነበረችውና ነጠላ ለብሳ ደጀሰላም የማትቀር የነበረችው አይናፋር ሴት ከ6 ወር በኃላ የበግተራ ቦዘኔዎች የጋራ ንብረት ይሆናሉ፡፡ ምናልባት ሰክራ ወድቃ ተሸክመህ አስገብተሃትም ይሆናል፡፡ አስካለች ...ፌቨን ነኝ ትላለች፡፡ ያምራል የሚባለው ልጅ እንኳን የሚያምር ስሙን ያሚ በሚል ይቀይራል፡፡ እልል ያለ ቃሚ፣ ጠጪና ወመኔ ሆኖ የገባው ጌታ ይጠራውና “አመለጥኩ” የሚለውን መዝሙር በነጋ በጠባው እየከፈተ ሰፈር ይረብሻል፡፡ ነጠላ ውዳሴ ማርያም ይዞ የገባው የኦሾን አንድ መፅሀፍ 10 ገፅ እንዳነበበ እሮብ አርብ መግደፍ ይጀምራል፡፡ አንተም ከአጫሾች ጋር ውለህ ማጨስ ትማራለህ፡፡ መቃም ትማራለህ፡፡ ሲጠጡ እያነጉ ባጥር ዘሎ መግባት ትማራለህ፡፡ ቢጤህን ሴት አሾልከህ ወንድ ዶርም ማስገባት ትማራለህ፡፡ ጭፈራ ትማራለህ፡፡ ቁማር ትለምዳለህ፡፡ ደህና ሰው ያልከው ይበላሻል፡፡ ተበላሸ ያልከው ደህና ሰው ይወጣዋል፡፡ የኮፒ ከየትም ታጣለህ፥ የድራፍት ግን ከየት እንደሆነ ምንጩ ባይታወቅም ወይ ከአንተው ወይ ከሌላ ሰው ኪስ ታገኛለህ፡፡ ሃንድአውት እሽ ካሉህ ትዋሳለህ እምቢ ካሉህ ትሰርቃለህ፡፡ አጤሬራ ኮፒ ታደርጋለህ፡፡ ወደግራህ ዞር ስትል “እግዜር የለም፥ አንተም የለህም” የሚሉህ ጀማሪ ፈላስፋዎች ታገኛለህ፡፡ ወደቀኝ ዞር ስትል ደግሞ በንባብና በአስተውሎት የበሰሉ ልጆችን ታገኛለህ፡፡ ማታ ማታ ወክ እያደረክ ወይም ቡና እየጠጣህ የከረሩ እሳቤዎችን ትለዋወጣለህ፡፡ እመነኝ.... እናንተ በተመስጦ ያወራችሁትን ወሬ በስንተኛው ቀን የሆነው ኮርስ ላይ በሆነው ፈረንጅ ስም የሆነ አይነት ቲዎሪ ተብሎ ሲመጣልህ እንዳትገረም፡፡ በጊዜ ቀደሙህ እንጂ አልበለጡህም፡፡ በገንዘብ የበለጡህን፥ በግሬድ ትበልጣለህ፡፡ በግሬድ የበለጡህን በጠቅላላ እውቀት ትበልጣለህ፡፡
ከክላሳችሁ ብዙዎች ተግባብተው ታያለህ፡፡ ስታየው ያስጠላህ የነበረው ልጅ ምርጥ ጓደኛህ ይሆናል፡፡ ያች ቀበጧ ከተሜ እንደገባችሁ በገጠር ልጅነቱ ሙድ ስትይዝበት የነበረውን የገጠር ልጅ አፍቅራ ከዶርም ጥሩልን እያለች በብርድ ስትመላለስና ሰው ስታስቸግር ታያለህ። ረጅሙ ጺማሙ ሙስሊም አክራሪዋን ነጠላ ለባሽ ኦርቶዶክስ ይጠብሳል፡፡ በግቢው የሚያስቀኑ ጥንዶች ይወጣቸዋል፡፡ አንተም ከማን አንሼ ብለህ በግተራ ቆመህ ትለክፋለህ፡፡ ፉንቃ ይገባልሃል፡፡ ትጀናጀናለህ፡፡ በለስ ይቀናህና ትጠብሳለህ፡፡ ኪሲንግፑል ስትሳሳም ታመሻለህ፡፡ ቤተመፅሃፍት አብረህ ታድራለህ፡፡ ወደስፔስ(ቀን የምትማርበት ክፍል ስፔስ ይባላል) ሄደህ በእኩለ ሌሊት ትዳራለህ፡፡ አንድ ቀን ግን ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ትይያያለህ። ሌላ ትጠብሳለህ፡፡ እሱም አንድ ቀን ያበቃል። ከግቢ ፍቅር ዘላቂ የሚሆነው በጣም ጥቂቱ ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከመጡበት ቦታ ትዳራቸውን አስቀምጠውት እንደመጡ አትዘነጋ፡፡ ጊዜው እየሄደ አመት ትጨምራለህ፡፡
በዩኒቨርስቲ ውስጥ አመት ሲጨምር የሴቶች ተፈላጊነት ይቀንሳል፥ አዳዲስ ሴቶች ስለሚመጡ፡፡ አመት ሲጨምር የወንዶች ተፈላጊነት ይጨምራል፥ በልምድ፣ በብልሃትና በድፍረት ከፍሬሹ ወንድ ስለሚሻሉ፡፡ አመት ሲጨምር የገበያውን መጣበብ እና ይህንን ችግር የተገነዘቡ ሲኒየር ሴቶች ሹገር ዳዲ ይጠብሳሉ፡፡ ካጣበስካቸው ደግሞ አንተም ከጥቅሙ ትካፈላለህ፡፡ ቢያንስ ማታ ማታ ላውንጅ ፍርፍር ትጋበዛለህ፡፡
ከእለታት ባንዱ ቀን የአንዱ ብሄር ልጆች የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ እንደጀመሩ ከየት መጣ የማትለው ፌደራል ፖሊስ ዶርም ድረስ ገብቶ በካልቾ እያለ ያስነሳሃል፡፡ ሲመሽ የሌሎች ብሄር ልጆች ተቧድነው ለድብድብ ሲጠራሩ ትሰማለህ፡፡ ደህና ጓደኛ ካለህ አስቀድሞ ይነገርህና ሳትመታ ትወጣለህ፡፡ ሳትወድ በግድ ቡድን ትለያለህ፡፡ በዲፓርትመንት እና በከተማ እየተደራጀህ ኳስ ትጫወታለህ፡፡ የሃዋሳ ቡድን እና የአዲሳባ ቡድን ሁሌም ቢደባደቡ አይግረምህ፥ ኮምፕሌክስ ነው፡፡ የሽሬና የመቀሌ ቡድኖችም ሳይቀር ይደባደባሉ፥ይህም ኮምሌክስ ነው፡፡ ያኔ የውጪውን ካልሆነ ኳስ ማየት ታቆማለህ፡፡
እድለኛ ሆነህ የስድስትኪሎ ተማሪ ከሆንክ ታዋቂ ሰዎችን ታገኛለህ፡፡ ታዋቂ የረጅም አመት ልምድ ያላቸውንና ሀይስኩል እያለህ የፃፏቸውን መፅሀፎች አንብበህ የተደሰትክባቸውን ወይም የተናደድብባቸውን ምሁራንን ታገኛለህ፡፡ እነዶ/ር መረራን ጉዲናን፣ እነዘሪሁን አስፋውን፣ እነዶ/ር ዳኛቸውን አሰፋን፣.... የመሳሰሉ ሰዎችን ታገኛለህ፡፡ ታዋራቸዋለህ፡፡ ደህና ደህና መምህራኖችህ መፅሃፍ ይሰጡሃል፡፡ ይረዱሃል፡፡ መጥፎዎቹ ደግሞ ያንቋሽሹሃል፡፡ ሚስትህን በግሬድ ያባልጉብሃል፡፡ እኔ ግን የገባሁት አዲስ ዩኒቨርስቲ ስለሆነ መምህራኖች ወትቶች ናቸው። አብረውን ይቅማሉ፤ ይጠጣሉ፤ ሴት ያሳድዳሉ፣ ይሰግዳሉ፤ ያስቀድሳሉ፤ መፅሀፍ ቅዱስ ያጠናሉ። ከሚፈልጓት ጋር ካዩህ ደግሞ ተደራጅተው ያዋክቡሀል። ግሬድህም ካዘኑልህ ዝቅተኛው F መካከለኛው D ከፍተኛው ደግሞ C ይሆናል።
እንዲህ እንዲያ እያለ መጨረሻህ ይደርሳል፡፡ ጂሲ ነኝ ብለህ ሁሉንም አይነት ቡዘናዎች ትቦዝናለህ፡፡ ጠጥቶ ማያውቅ ልጅ ታጠጣና የፌሚኒስት ነኝ ባይ እንስት ጡት ነክቶ በክስ ስትጉላላ ትከርማለህ፡፡ ዘበኛ ወይ ፕሮክተር መታወቂያ ይቀማህና ትጉላላህ፡፡ ላይብረሪ መሃል ትጨፍራለህ፡፡ አራት አመት የኖርከውን ሁሉ ደጋግመህ ትኖረዋለህ፡፡ አራት አመት ያልኖርከውን ሁሉ ፈልገህ ትኖረዋለህ፡፡ በስተመጨረሻም ተመርቀህ በገባህበት በር ሻንጣህን እየጎተትክ ትወጣለህ፡፡ ብዙ ሰው ግን በፌስታል ነው የሚወጣው ለምን? ሻንጣውን ሸጦታል፡፡
ምን ይተርፍሃል?
ጨጓራ በሽታ፥ ዲግሪ እና ብዙ ትዝታ፡፡
ከወጣህ በኋላ ማንንም አታገኝም፡፡ ብትንትንህ ይወጣል፡፡ የኔን ልንገርህ ፡፡ ከነበርነው ተማሪዎች አስሩ የክፍለሃገር ዩንቨርስቲ መምህራን ሆኑ፡፡ አስሩን መንግስት ቀጠራቸው፡፡ አስሩን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ወሰዷቸው፡፡ አምስቱ ማስተርስ ቀጠሉ፡፡ በጣም ጥቂቶች ከቤተሰብ ጋ ቢዝነስ ጀመሩ፡፡ ሁለት ልጆች አለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ገቡ፡፡ ቆንጆ ነኝ ብላ የምታስበዋ ሆስተስ ሆነች፡፡ ኮስቲኔት ገብቶ የተበላው ልጅ ወዲያው ምርጥ ነጋዴ ሆኗል። እኔ ደሞ እዚህ ጋ ነኝ፡፡
ታናሼ አደራ ስለተቀሩት እንዳትጠይቀኝ፡፡
ስትወጣ የት እንዳሉ ወይም ምን እንደሆኑ ትደርስበታለህ፡፡
በሰላም ለአይነስጋ ያብቃን።
ውድ ወንድምህ ሄ.አ. ከ.
ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ

05/08/2023

እረ ጃውሳ !! እንደ ጁንታ እያረጋት ነው አይደል ? ክክክ

  "አቤል ለምን ወንድሙን ቃኤልን  ገደለው  ???አቤል እና ቃኤል የመጀመሪያው  #ሰው የመጀመሪያ ልጆች ናቸው   የሚለው ቃል የተፈጸመው አዳም እና ሔዋን እኒህን ልጆችከወለዱበት ጀምሮ ሲሆ...
05/06/2020


"አቤል ለምን ወንድሙን ቃኤልን ገደለው ???

አቤል እና ቃኤል የመጀመሪያው #ሰው የመጀመሪያ ልጆች ናቸው የሚለው ቃል የተፈጸመው አዳም እና ሔዋን እኒህን ልጆች
ከወለዱበት ጀምሮ ሲሆን ……

የሰው ልጅ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነም ማሳያዎች ናቸው
አቤልና ቃየል ወንድማማች ሲሆኑ ሁለቱም መንትያ እህቶች ነበሯቸው የመንትዮቹም እህቶቻቸው ስም ሉድና አቅሌማ ይባላሉ ።
አዳም አቤልና ቃኤል ሉድና አቅሌማ ስለተወለዱለት እጅግ ደስተኛ ነበር ይሁን እንጅ በአንጻሩ ደግሞ ልጆቹ ባጠፉት ጥፋት አዝኗል ታሪኩ እንዲህ ነው፦

አቤልና ቃኤል ለአቅመ አዳም ሲደርሱ አባታቸው አዳም ልጆቹን ትዳር ማስያዝ ፈለገ ሆኖም እግዚአብሄር የሚሠራው የጋብቻ ሕግ ለአዳም ተገልጾለት አራርቆ ለማጋባት ሲል
➡የአቤልን መንትያ ለቃኤል
➡ የቃኤልን መንትያ ለአቤል አድርጎ ለማጋባት ወሰነ በዚህ ጊዜ የጋብቻውን ነገር የሚቃወም
የአባቱን ምክር ያልተቀበለ ቃኤል አኮረፈ የአባቱንም ውሳኔ ላለመቀበል በዓመጽ ቃል ተናገረ።

አዳም ለልጁ የማይጨነቅ ሰው ሆኖ ሳይሆን ልጁ ለአባቱ የማይታዘዝ በመሆኑ ነው✔

ዛሬም እኮ የአባታቸውን ትእዛዝ የማይቀበሉ በስሜት እንጅ በዕውቀትና በእውነት የማይጓዙ ለጊዜያዊ እርካታ ሲሉ ዘላለማዊውን ክብር የዘነጉ የእግዚአብሔርን ቃል የጣሱ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣረሱ ለስጋቸው የኖሩ በነፍሳቸው የከሰሩ ለዓለም የሚሮጡ ለክፉ ምኞት የተሰጡ
በሰይጣን ሐሳብ የቀለጡ በዲያብሎስ ምክር የተቀጠቀጡ በስጋ ስራ የተዋጡ በመንፈሳዊ የታጡ
ብዙዎች አሉ
ከመልካም ነገር የለዩ የምድርን እንጅ የሰማዩን ክብር የማያዩ አሉ ከዚህ አይነት ሕይወት ይጠብቀን
የአባትን ትእዛዝ ማክበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማክበር ነው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማክበር ደግሞ የመንፈሳዊ ሰው መገለጫ ነው✔

ታድያ የአባቱን ትእዛዝ ያላከበረው የቃኤል ምክንያት የቁንጅና ጉዳይ ነበር ምክንያቱም የቃኤል መንትያ መልከ መልካም ስትሆን የአቤል መንትያ ደግሞ መልከ ጥፉ/የማታምር ነበረች በዚህም ምክንያት የእኔን መልከ መልካም ለወንድሜ ሰጥቶ
የወንድሜን መልከ ክፉ ለእኔ እንዴት ይሆናል?

የሚል ሐሳብ ነበር ያቀረበው የልጁን መከፋት የተመለከተው አዳምም ሁለታችሁም መስዋዕት አቅርቡ እግዚአብሔር የፈቀደለት መልካሟን ሊያገባ ይችላል በማለት ሁለቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድመጠየቅ እንዳላባቸው ነገራቸው
በአዳም ትእዛዝ መሠረት ሁለቱም ከእግዚአብሔርን ፈቃድ አግኝተው ለማግባት መስዋዕት
ለማቅረብ ተዘጋጁ በዚህ ጊዜ

#አቤል በግ ጠባቂ ነበርና
ከበጎቹ ቀንዱ ያልከረከረውን ጸጉሩ ያልዘረዘረውን
የሚያምር በግ ለመስዋዕት አቀረበ

#ቃኤል ደግሞ ገበሬ ነበርና ከአዝርእቱ ያገኘውን ምንም ሳይመርጥ እግዚአብሔር እንደሆነ ወርዶ አይመገበው በማለት በቸልተኝነት ድብልቅልቁን አቀረበ

በዚህ ሰዓት እግዚአብሔር ወደ አቤል ና
ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ ወደ ቃኤልና ወደ መስዋዕቱ ግን አልተመለከትም ምክንያቱም አቤል እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሕ ነገር ሊያቀርቡለት ይገባል በማለት ተገቢውን መስዋዕት ሲያቀርብ ቃኤል ግን እግዚአብሔር አይበላው በማለት የተገኘውን ግብስብስ ነገር በማቅረቡ ለእግዚአብሔር ከልቡ
አለመገዛቱን ያመለክታል በዚህ የቃኤል መስዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም

የሰው ልጅ ገንዘቡን
ከመስጠቱ በፊት ራሱን ለፈጣሪው ሊሰጥ ይገባል ገንዘብን ከመስጠት ራስን መስጠት ይቀድማልና
ደግሞም የሰው ልጅ የሚፈልገውን ለማግኘት እግዚአብሔርን መጠየቅ እንደሚገባ እንማራለን
ከእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ሁልጊዜም መልካም ነውና

ታድያ በዚህ ጊዜ ቃኤል መስዋዕቱን ስላልተቀበለው አዳም ቢፈርድ ለአቤል እግዚአብሔር ቢፈርድ ለአቤል ብሎ በወንድሙ ላይ ቂም ያዘበት ወንድሙንም ለመበቀል ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ይከታተል ጀመር

ዓለም ሁልጊዜም በዓመጽ የተሞላች የክፉዎች መንገሻ
የንጹሆች መርከሻ ነችና
ጌታችንም ደቀ መዛሙርቱን
"ከዓለም አይደላችሁምና ዓለም ይጠላችኋል" ያላቸው በምድር አትኖሩም ለማለት ሳይሆን በምድር
ሲኖሩ ምድራዊ ስራ አለመስራታቸውን ያመለክታል እነርሱ በዓለም ተገፉ እንጅ ዓለምን አልገፉም ተገረፉ እንጅ አልገረፉም ተገደሉ እንጅ አልገደሉም የእውነት ጉዞ ሁልጊዜም ከዝቅታ ወደ
ከፍታ ነውና ይህም ሰማያዊ ዋጋን ያሰጣልና

ይሁን እንጅ ወንድሙን ለመበቀል የተመቻቸ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ እንቅልፍ አልነበረውም የሚገርምና የሚያሳዝን ልብን የሚነካ ነገር ነው
ሰው እንዴት ወንድሙን ለመግደል ይህን ያህል ያደባል ?ደግሞም በአንጻሩ አቤል ወንድሙ
ቃኤልን እጅግ ይናፍቀው ይንከባከበው ይጨነቅለትም ነበር

ዓለም በገዳይ እና በተገዳይ በአሸናፊና በተሸናፊ የተሞላች ነች አንዱ ሲያገኝ አንዱ
ሲያጣ አንዱ ሲደሰት ሌላው ሲከፋ አንዱ ሲስቅ አንደኛው ሲያለቅስ አንዱ ሲሾም ሌላኛው ሲከብር አንዱ ሲከብር ሌላኛው ሲዋረድ ነው ዓለም ሁሉንም በእኩልነት
አስተናግዳ አታውቅም የቃኤል ቅናት ወደ ገዳይነት ከፍ ስላለ ይህን ለማድረግ እንዲህ ብሎ አሰበ ወንድሙን ወደ ውጭ ወስዶ ለመበቀል
ወንድሙ አቤልም የቃኤልን ክፋት ስላላወቀ ከወንድሙ ጋር ጉዞ አደረገ
ብዙ ጊዜ እንደ አቤል በደግነት ምንም አይነት ክፉ ስራ ሳይሰሩ በመኖራቸው ከኃጢአት ጋር ባለመተባበራቸው የተወነጀሉ ብዙዎች ናቸው አቤል ልቡ ንጹሕ ነው ቃኤል ግን ቂም ይዟል ወንድሙን በአንደበቱ እንደሚወደው ይነግረዋል በልቡ ግን ሊገድለው ተዘጋጅቷል "በአፉሆሙ ይድኅሩ ወበልቦሙ ይረግሙ"በማለት በአንደበታቸው የሚመርቁ በልባቸው ግን የሚራገሙ ሰዎች እንዳሉ ቅዱስ ዳዊት ተናግሯል ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ምግባር ነው "አፍኒ ወልብ ኅቡረ ይእመኑ =አንደበትና ልቡና በአንድነት ይመኑ ይህ ካልሆነ ግን መልካም ስራ መስራት አይቻልም የአቤልና የቃኤል ኑሮ በአንደበት እንጅ በልብ የተለያዩ ነበሩ
ይህ የዘመናችን የብዙዎች ችግር ነው
ባል ከሚስቱ ባልንጀራ ከባልንጀራው
የማይግባባው በአንደበት እንጅ በልብ መግባባት ስላልተቻለ ነው ይህንን የልዩነት መንፈስ እግዚአብሔር ከምድራችን ያስወግድልን

ቃኤልም የልቡን ምኞት ለመፈጸም
ወደ ወንዝ ዳር ወንድሙን ወስዶ ውሀ በሚጠጣበትሰዓት በድንጋይ ቀጥቅጦ እንደዕባብ
ገደለው ከዚህች ዕለት ጀምሮ
ቃኤል ሰላሙን አጣ ተቅበዝባዥ ሆነ የሚያየውን ሁሉ
ተጠራጣሪ ተንከራታች ሆነ ደግሞስ ሰው ወንድሙን ገድሎ ምን ሰላም ይኖረዋል?

እግዚአብሔርም የቃኤልን ስራ ተመለከተ በመጥፎ ስራውም አዘነ እንዲህም አለው አቤል ወንድምህ የት አለ?አለው ቃኤልም እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?አላውቅም በማለት በትእቢት ቃል መለሰ መጽሐፍ "እስመ እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ" =ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል ማቴ12፥33 እንዳለ በክፉ ስራው ምክንያት ክፉ መልስ ለፈጣሪው መለሰለት

ሁልጊዜም ስራው ክፉ የሆነ ሰው
ከአንደበቱ መልካም ነገር ማፍለቅ
አይችልም ከኩርንችት በለስ እንደማይለቀም ሁሉ ከክፉ ሰውም መልካምነትን ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም
እንግዲህ ወንድሙን በበቀል በድንጋይ የገደለው ቃኤል ዘመኑን በሙሉ በጭንቀት ኖረ አቤል አንድ ቀን ሞተ ቃኤል ግን በክፋቱ ምክንያት ቀን በቀን በስሜት እንደሞተ የሰቀቀን ዘመን ኖሮ በመጨረሻው እራሱ የሚኖርበት ቤት ተጭኖት ወንድሙን በድንጋይ እንደ ገደለው እሱም በድንጋይ ሞተ
" የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው"ሮሜ6፥23 እንዳለው በኃጢአት ከመሞት አምላካችን ይጠብቀን ዘመናችንን የፍቅር እድሜያችንን የበረከት ያድርግልን

"አምላኬን ሆይ ሕይወቴን በበረከት ባርክ ከክፉ ምኞት አንተ ጠብቀኝ"

እኔም አየኹ እንሆም፥ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና የሚበርቅም እሳት መጣ፥በዙሪያውም ጸዳል ነበረ፥በመካከልም በእሳቱ ውስጥ እንደሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ ነበረ።ከመካከልም የአራት እ...
04/06/2020

እኔም አየኹ እንሆም፥ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና የሚበርቅም እሳት መጣ፥በዙሪያውም ጸዳል ነበረ፥በመካከልም በእሳቱ ውስጥ እንደሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ ነበረ።
ከመካከልም የአራት እንስሳዎች አምሳያ ወጣ።መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፥ሰውም ይመስሉ ነበር።
ለያዳንዱም አራት አራት ፊት፥ለያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት።
እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ የእግራቸውም ኰቴ እንደ ጥጃ እግር ኰቴ ነበረ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር።
በክንፎቻቸውም በታች በያራቱ ጐድናቸው እንደሰው እጅ ነበረ ለአራቱም እንደዚህ ያሉ ፊትና ክንፍ ነበሯቸው።
የፊታቸው አምሳያ እንደ ሰው ፊት ነበረ፥ለአራቱም በስተቀኛቸው እንደ አንበሳ ፊት፥በስተግራቸውም እንደ ላም ፊት ነበራቸው፥ለአራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 1 - 5 : 10

አንበሳው ዝቅ አለ ፧ ጃ !
02/06/2020

አንበሳው ዝቅ አለ ፧ ጃ !

ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ዐሰብኹት ጸሎቴም ወዳንተ ወደ ቅዱስ መቅደስኽ ገባች።ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልኻለኹ የተሳልኹትንም ...
25/05/2020

ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ዐሰብኹት ጸሎቴም ወዳንተ ወደ ቅዱስ መቅደስኽ ገባች።
ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።
እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልኻለኹ የተሳልኹትንም እከፍላለኹ።ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ትንቢተ ዮናስ 2 : 8 - 10

በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው።ርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።ወደ ቆላስይስ 2 :14
17/04/2020

በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው።ርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።
ወደ ቆላስይስ 2 :14

አቤቱ፥በልቤ ዅሉ አመሰግንኻለኹ፥ተኣምራትኽንም ዅሉ እነግራለኹ።ባንተ ደስ ይለኛል፥ሐሤትንም አደርጋለኹ ልዑል ሆይ፥ለስምኽ እዘምራለኹ።መዝሙረ ዳዊት 9 : 1-2
13/04/2020

አቤቱ፥በልቤ ዅሉ አመሰግንኻለኹ፥ተኣምራትኽንም ዅሉ እነግራለኹ።
ባንተ ደስ ይለኛል፥ሐሤትንም አደርጋለኹ ልዑል ሆይ፥ለስምኽ እዘምራለኹ።
መዝሙረ ዳዊት 9 : 1-2

አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥እልል በዪ እንሆ፥ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ኾኖ በአህያም፥በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አን...
11/04/2020

አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥እልል በዪ እንሆ፥ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ኾኖ በአህያም፥በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ትንቢተ ዘካሪያስ 9:9

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lula Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category