Lemi Kura DVLCA

Lemi Kura DVLCA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lemi Kura DVLCA, Public Service, Hayat Adebabay Khalid Plaza, Addis Ababa.

12/10/2025

“ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮያ ሕዳሴ!”
በሚል መሪ ቃል ነገ ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ. ም ይከበራርል፡፡

29/07/2025
21/07/2025
10/07/2025
28/06/2025

1ዐዐ የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች ሊገዙ ነው
የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻልና ተጨማሪ አውቶብሶችን ለመግዛት የጨረታ ሂደት መጠናቀቁን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስቴር አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም አድምጧል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ እንደተናገሩት፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ከማዘን ባለፈ ተጨማሪ 100 አውቶብሶችን ወደ ሥራ ለመሰማራት የጨረታ ሂደት ተጠናቋል ብለዋል።

የትራፊክ አደጋን በዘላቂነት ለመቀነስ በአሽከርካሪዎች ስነምግባር ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ አሽከርካሪዎች ከሙያ ብቃት በተጨማሪ በስነምግባር የታነፁ እንዲሆኑ፤ ለሀገር አቋራጭ አውቶብስ አሽከርካሪዎች የስነምግባር ስልጠና ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የህገወጥ ኬላዎች መበራከት ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል ያሉት ዶክተር ዓለሙ፤ ይህንን ማነቆ ለመፍታት በቀጣይነት የተጠናከረ ሥራ ይሰራል ብለዋል።

የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በቴክኖሎጂ ልማትና የተቋማት የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

https://www.facebook.com/share/p/15kVy5yZPm/
17/01/2025

https://www.facebook.com/share/p/15kVy5yZPm/

ከ730 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር አገልገሎት ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከ730 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች አገልገሎት መስጠት መቻሉን የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለፀ፡፡

ባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት የአሽከርካሪዎች ስልጠና ምዝገባ፣የብቃት ማረጋገጫ፣የአሽከርካሪዎች የመንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት እና የውጭ መንጃ ፈቃድ ቅያሬ አገልግሎቶችን ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም አዲስ መኪና ምዝገባ፣የተሸከርካሪዎች ዓመታዊ ብቃት ማረጋገጫ(ቦሎ)፣የስም ዝውውር እና ድንገተኛ ምርመራ አገልግሎቶችም በባለስልጣኑ በግማሽ አመት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡

በዚህም በአጠቃላይ በአሽከርካሪ እና በተሽከርካሪ ዘርፍ ለ733 ሺህ 541 ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠጡን እና ከተሰጠዉ አገልግሎት ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ የባለስልጣኑ አመራሮች፣ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የተቋሙን አገልግሎት በማዘመን የተመዘገቡ ውጤቶችን እንዲያስቀጥሉ መመሪያ መሰጠቱን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

25/02/2024

Address

Hayat Adebabay Khalid Plaza
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lemi Kura DVLCA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category