Akaki Kality Woreda 9 communication-አቃቂ ቃሊቲ

Akaki Kality Woreda 9 communication-አቃቂ ቃሊቲ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኮሙኒከሽን ጉዳዮች ቢሮ በወረዳችን የተሰሩ ስራዎች እና መሰራት ያለባቸውን የህዝብ ጥያቄዎች ተደራሽ ያደርጋል።

በበዓል መዳረሻ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ  የተለያዩ የግብርናና የፍጆታ ምርቶች እየቀረቡ ይገኛል:: # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #...
05/09/2026

በበዓል መዳረሻ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ የተለያዩ የግብርናና የፍጆታ ምርቶች እየቀረቡ ይገኛል::
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
ነሃሴ 30/20118 ዓ.ም (ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን )

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለመከላከልና ነዋሪው የግብርና የምግብ ፍጆታዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ ቃሊንጦ መስቀለኛ በተከፈተው የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያ ባዛር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ውድ የወረዳችን ነዋሪዎች በሙሉ የሰንበት ገበያ በቅዳሜ እና እሁድ ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡ የተለያዩ ምርቶች በገበያው ላይ የተካተቱ ሲሆን በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸመት የኑሮ ውድነቱንና የዋጋ ንረቱን ለማርገብ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋኦ በማበርከት የቅናሹ ተጠቃሚ ይሁኑ ሲሉ የወረዳው ንግድ እና ህብረት ስራ ጽ/ ቤቶች በጋራ ጥራቸውን ያስተላልፋሉ ፡፡

በወረዳ9 የወጣትና ስፖርት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት የኪነ ጥበብ ምሽት ተካሄደ። # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #በመርሃግ...
04/09/2026

በወረዳ9 የወጣትና ስፖርት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት የኪነ ጥበብ ምሽት ተካሄደ።
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
በመርሃግብሩ ላይ የወረዳ9 ዋና ሰራ አሰፈጻሚ አቶ ቀነኒ ዋቅሹማ እና የወረዳው አስተባባሪዎች
ወጣቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሙያ ተወካዮችና የማኅበረሰቡ አባላት ተሳትፈዋል።

በምሽቱ የሙዚቃ፣ የግጥም፣ የድራማና የባህላዊ ዳንስ ትርኢቶች ቀርበዋል። ትርኢቶቹ የወጣቶችን ተሰጥኦ ለማሳየት፣ ባህልና እሴቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ወጣቶችን በአዎንታዊ ተሳትፎ ለማሰባሰብ ያለውን ሚና አሳይተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ እንግዶች እንደገለጹት፣ እንዲህ ዓይነት የኪነ ጥበብ መድረኮች ወጣቶች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ ልምድ እንዲለዋወጡና ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ የሆኑ መልዕክቶችን እንዲያስተላልፉ ዕድል ይፈጥራሉ።

የወረዳ 9 የወጣትና ስፖርት ጽሕፈት ቤትም የወጣቶችን ተሰጥኦ ለማበረታታትና የኪነ ጥበብ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ተመሳሳይ መርሃ ግብሮችን በቀጣይነት እንደሚያካሂድ ገልጿል።
29/12/2018ዓ/ም (ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን )

አስተማማኝ ሠላምን በማስፈን ልማትን እናረጋግጣለን !========================ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም (ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን)በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ሠላም...
04/09/2026

አስተማማኝ ሠላምን በማስፈን ልማትን እናረጋግጣለን !
========================
ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም (ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን)

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ ።

ስምሪቱን በማስመልከት የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቀነኒ ዋቅሹም ሲሆኑ"ባለፋት አመታት ሠላም ሠራዊት ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል በዚህ ሊመሠገን ይገባል ስለሆነም አስተማማኝ ሠላም በማስፈን ልማትን እናረጋግጣለን " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በስምሪቱ የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራር ወረዳ አመራሮች፣ ፖሊስ ፣ደንብ እና ሠላም ሠራዊት ተሳትፈዋል ።

በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ"""     ******************  ቀን:-30/12/2018ዓ.ም  ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን                     በወረዳችን በተለይ በክረምቱ በርካታ ...
04/09/2026

በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ""" ****************** ቀን:-30/12/2018ዓ.ም ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን በወረዳችን በተለይ በክረምቱ በርካታ የበጎ ፍቃድ ተግባራት እየተከናወኑ ነዉ። ከዚህም መካከል አንዱና ዋነኛዉ የአቅመ ደካሞች ቤት መገንባት ሲሆን በዛሬዉ እለት በቤጂንግ ቀጠና የቤት እድሳት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የክፍለ ከተማዉ ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ፈለቀ እንዲሁም የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ዋና ስራስኪያጅ ዶክተር እሸቱ ታደሰ የወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቀነኒ ዋቅሹማ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካለት ተገኝተው መርሀግብሩ ተከናዉኗል።

የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የባዛር መክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ።=======================ነሃሴ28/2018 ዓ.ም (አቃ/ቃ/ወረዳ 9 ኮሙዩኒኬሽን)የገበያ ትስስር የነዋሪ...
03/09/2026

የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የባዛር መክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ።
=======================
ነሃሴ28/2018 ዓ.ም (አቃ/ቃ/ወረዳ 9 ኮሙዩኒኬሽን)

የገበያ ትስስር የነዋሪዎችን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ያለው የሁሉንም አቅም ባገናዘበ መልኩ የደመቀ ባዛር የወረዳው አስተዳደር አቶ ቀነኒ ዋቅሹማ እና የወረዳው ሃላፊዎች በተገኙበት መከፈቱ ተገለጸ።

የባዛሩ መክፈቻ ላይ የንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ ፈለቀ በዚህ ባዛር ላይ የተለያዩ የምርት አቅርቦት መሰረታዊ የሆኑ የግብርና ምርቶች (ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች) እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶች ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በስፋት ቀርበዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን አውቆ የዚህ እድል ተጠቃሚ ይሁኑ ሲል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ደማቅ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ"መሰረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣ...
03/09/2026

መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ደማቅ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

"መሰረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን " በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2019 የዘመን መለወጫ እና ቀጣይ የሚከበሩ በዓላትን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ የገበያ አማራጮችን ለማቅረብ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና የበዓል ግብይትን ለማሳለጥ ያለመ ደማቅ የአዲስ ዓመት ባዛርና ኤግዚቢሽን በክፍለ ከተማው ፊት ለፊት ተከፈተ።

በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ፈለቀ ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅንጅት ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኪያ ትኩ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብነት አሰግድን ጨምሮ የክ/ከተማ አመራሮች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎችና ሸማቾች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ፈይሳ ፈለቀ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ አስተዳደሩ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመወያየት በቂ ምርት በማዘጋጀት ባዛሩን ማስከፈቱን ገልጸዋል። በባዛርና ኤግዚቢሽኑ በርካታ ኢንተርፕራይዞች፣ አርሶ አደሮችና አምራቾች የተሳተፉ ሲሆን፣ በቂ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ቀርበው ሸማቹን ማኅበረሰብ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። አያይዘውም ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ፣ ምርት ማከማቸት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ እና ለጤና ጎጂ የሆኑ ምርቶችን የመቆጣጠር ሥራ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ ነዋሪዎች በተዘጋጀው ባዛር ተገኝተው እንዲገበያዩ ጥሪ አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሰይፉ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በበዓላት ወቅት የሚከሰተውን የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት ለመከላከል ከአምራቾች ጋር በማገናኘት የደላሎችን ሰንሰለት ለመበጠስ በ19 የእሁድ ገበያዎች ምርቶችን በስፋት እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል። በዛሬው ዕለትም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከእሁድ ገበያዎች በተጨማሪ ይህ ደማቅ ኤግዚቢሽንና ባዛር መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው!!!ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸው...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው!!!

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

02/09/2026
በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃግብር በ90 ቀናት እቅድ መካከል በርካታ መርሃ-ግብር  ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።         ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳       ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም    ...
01/09/2026

በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃግብር በ90 ቀናት እቅድ መካከል በርካታ መርሃ-ግብር ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን
በወረዳችን በርካታ በጎ ፍቃደኞች፣የግልና የመንግስት ድርጅቶች፣ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ባለሃብቶች በበጎ ፈቃድ ተግባራት እየተሳተፉ ሲሆን በርካታ አረጋውያን፣ አቅመ-ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብም ነዉ ።
የ2018 የክረምቱ "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ከተከናወኑ ተግባራት መካከልም የጉድጓድ ቁፋሮና ችግኝ ተከላ እንዲሁም እንክብካቤ፣በጎነት በሆስፒታል፣የደም ልገሳ፣የትራፊክ ደህንነት፣የክረምት ትምህርት.....በዋናነት የክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ይገኛል።
በተጨማሪም ከዉበትና ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የቅድመ ጎርፍ መከላከል የቦይ ጠረጋ ተከናዉኗል።

እንዲሁም በክረምቱ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በጎ ፈቃደኞችን በየደረጃው በማሳተፍ ህዝባዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
በተለያዩ ዘርፎች በተደረጉ ሁለገብ እንቅስቃሴዎች ብዙዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። በወረዳዉ አካባቢ ጽዳትና አረንጓዴነት ተረጋግጧል፤ እንዲሁም ማህበራዊ ትስስሩ ይበልጥ እንዲጠናከር ተደርጓል።
ይህ ዉጤት የተገኘዉ በጎ ፈቃደኞች፣ በባለሙያዎች፣ በባለሃብቶችና ድጋፍ አድራጊ ተቋማት ቅንጅታዊ ጥረት ነው። ይህ የተቀደሰ የወገን አለኝታነት ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ይህ ነዉ የማይባል አስተዋጽኦ ያበረክታል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912413563

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki Kality Woreda 9 communication-አቃቂ ቃሊቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Akaki Kality Woreda 9 communication-አቃቂ ቃሊቲ:

Shortcuts

Share