Arada Sub City Prosperity Party -ብልጽግና

Arada Sub City Prosperity Party -ብልጽግና አዲስ እይታ ለተለወጠ አራዳ !!

01/09/2026
ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።  በውይይታችንም  እቅዶ...
31/08/2026

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።

በውይይታችንም እቅዶቹን ይበልጥ ተጨባጭ በማድረግ በቀጣይ አምስት ዓመታትም አልቀን በመፈፀም፣ የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት ሳንሸራርፍ ለመፈፀም፣ የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እጅግ ጠቃሚ እና ገንቢ ተግባቦት እና ዝግጁነት ፈጥረናል።

ከሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂያችን በመነሳት ህዝባችንም በድጋሚ ሲመርጠን “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር” ብለን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንደ አዲስ አበባ “አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት” ለማድረግ የጀመርነውን ጉዞ ዋና ርዕያችን አድርገናል።

ለእቅዳችን ስኬት መሰረቶች የሆኑት ባለፋት አምስት ዓመታት አቅደን አልቀን ያስመዘገብነው ውጤት፣ የህዝብና መንግሥት ከደህነት የመውጣት ፍላጎት፣ በከተማችን የተፈጠረው የስራ ትጋት፣ በታማኝነት ማገልገል፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በፍጥነትና በጥራት የመፈፀም ልምድ፣ በጀትን በመቆጠብ መጠቀም ትልቅ ስንቅ ናቸው።

በቀጣይ ትኩረታችንም ተቋማዊ ብቃትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ የዘመነ ቴክኖሎጂ በሚጠቀም የላቀ አገልግሎት መስጠት፣ የተቀናጀ ጥራት ያለው ሰፊ መሰረት ልማት በፍጥነት መገንባት፣ አዲስ መሰረተ ልማት መገንባት ብቻ ሳይሆን ነባሮቹን በሚገባ ማስተዳደር፣ የንፁህ መጠጥ ውኃና የቤት አቅርቦት ማሳደግ፣ የማህበራዊ ዘርፍ (ጤና፣ ትምህርት …) ተደራሽነትና ጥራት እንዲሁም ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ አልቀን መፈፀም፣ ዓለማቀፍ ስታንዳርድ ያሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት፣ የጤና ቱሪዝም ማዕከል መሆን፣ የከተማችንን የቱሪዝም መዳረሻ ከተማነት ማረጋገጥ፣ አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ ማድረግ፣ ለወጣቶች ተጠቃሚነት፣ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲሁም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ባህል በማድረግ ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማትን ማጠናከር፣ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ አምራችነትን ማሳደግ፣ ተረጂነትን መቀነስ፣ የስራ እድልን በሰፊው መፍጠር፣ የከተማ ግብርና፣ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን፣ ፅዳትና የቆሻሻ አወጋገድን ባህል ማድረግ … ወዘተ፤ በአጠቃላይ ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና ለሁሉም የምትመች ከተማ ማድረግ የእቅዳችን ትኩረቶች ናቸው።

የእቅዳችን ቅኝትም ስትራቴጂክ እይታ ያለው፤ ራዕያችንን ለማሳካት አቅዶ መተግበር፤ የተለጠጠ፣ አካታች፣ ፍትሃዊ እንዲሁም አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ይህ የእቅድ ውይይት አመራራችን በዋናነት እቅዱን በተሟላ ሁኔታ የተረዳ፣ ስትራቴጂክ አመራር የሚሰጥ፣ በአስተሳሰብ አንድነት የሚቆም፣ ከተለያየ የጥቅም ትስስር ነፃ የሆነ፣ የይቻላል መንፈስን የተላበሰ፣ በአፈፃፀም ተቀራራቢ የሆነ፣ ትጋት እና የአመራር ዲሲፒሊን ያለው፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት እያሰፈንን ህዝቡ የከተማችንን ራዕይና ግብ የተጋራ እንዲሆን በተለየ መንገድ የሄድንበት የውይይት መድረክ ነው።

ልማትን በመንግስት ብቻ ማሳካት እይቻልም። በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪዎች፣ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ የግሉን ዘርፍ ማበረታታት፣ በጊዜ የለንም መንፈስ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ አሳድገን በከተማችን ለማሳካት የተወጠነውን ትልቅ ራዕይ ለመፈፀም በላቀ እንተጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተ...
31/08/2026

ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!

የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተግባራት የህዝባችን ብዝሀ አብሮነት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል።

የህዝባችን በጎ እሳቤዎች በተገቢው መንገድ ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራር ስርዓቶች መዘርጋታቸውም ለዕድገታችን መፋጠን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በክረምቱ ወራት ተወስነው የነበሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት፣ በተፈጠረው የአስተሳሰብ ለውጥ፣ እንዲሁም በዳበረው ሁሉንም አቅሞች የማስተባበር ቁርጠኝነት ዓመቱን ሙሉ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ለወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰጠው ልዩ ትኩረትም ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሚያከናውኗቸው በገንዘብ የማይተኩ ተግባራት ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እያጠናክሩ ነው።

የህዝባችን ጥንታዊ እሴቶች በየጊዜው እየተሸረሸሩ ከመምጣታቸው ባሻገር አቀናጅቶ የሚያስተባብር ተቋም ስላልነበር በተለያዩ አግባብ የሚገለፁ የሀብት፣ የጊዜ እንዲሁም የጉልበት ብክነቶች ሲስተዋሉ ቆይተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲን ሰው ተኮር እሳቤዎች አልቆ ለመተግበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የተቀናጀና የተደራጀ ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽንን በማቋቋም አገልግሎቱን ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው ማድረጉ የበጎ ፈቃደኞችን የተደመረ አቅም ፈጥሯል።


በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤትም በተለይም በወጣቶች ክንፍ እና በሴቶች ክንፍ አባላት አስተባባሪነት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊነት እና ዘላቂነት በልዩ ትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የታመሙትን በመጎብኘት ተስፋና ሞራል የመስጠት የበጎነት በሆስፒታል መልካም ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው።

ለአቅመ ደካሞች ቤት ገንብቶ የማስረከብ የበጎነት ተግባርም የበርካታ የሀገር ባለውለታ ዜጎችን ህይወት ማፍካት ችሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ባለፀጎችን በማስተባበር ያስገነባቸው የበጎነት መንደሮች ለከተማችንም ተጨማሪ ድምቀት ሆነዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተለይም በበዓላት ወቅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የሚያከናውነው ማዕድ የማጋራት ተግባርም በከተማችን በተገነቡ የምገባ ማዕከላት ተቋማዊ መልክ ይዞ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማስተባበር ዓመቱን ሙሉ እየተከናወነ መሆኑን ልብ ይሏል።

ደም በመለገስ በደም እጥረት ምክንያት ሊጠፋ የሚችል ህይወትን የመታደግ የበጎነት ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መምህራን በማስተማር፣ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ህሙማንን በማከም፣ ሌሎችም በየተሰማሩበት የሚያከናውኗቸው ሙያዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትም የከተማችንን ዕድገት አፋጥነዋል::

የፓርቲያችንን ሰው ተኮር እሳቤዎች በተግባር ለመተርጎም የሚደረገው ርብርብ ዘላቂ ዕድገትን እያረጋገጠ መሆኑ ተጨባጭ ሲሆን ፤ ማህበራዊ አካታችነትን እንዲሁም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ከፍ ማድረግ አስችሏል።

መልካም የስራ ሳምንት!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት  መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል። በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የ...
30/08/2026

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል።

በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት መነሻ ያደረገ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፈን ቃላችንን በተግባር ቆጥረን ፈፅመን የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ከተማችን ደግሞ ተወዳዳሪ እንድትሆን አድርገናል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የከተማችን ነዋሪ እምነት አድሮበት ዳግም መርጦን ሀላፊነት ሰጥቶናል።
የዛሬው ውይይትም የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት መነሻ ያደረገ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ዝርዝር ግቦች ላይ ተወያይተን በማዳበር የባለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀምን በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ ነው።

እነዚህን ዝርዝር ውይይቶች ስናደርግ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ በማሳደግ፣ አመራራችን ከፊት ሆኖ የበለጠ እየሮጠ ህዝባችንንና የልማት አጋሮቻችንን በማስተባበርና ተሞክሮዎችን በማስፋት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሀገራዊ ማንሰራራት ውስጥ የአዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ እንተጋለን።

በተጨማሪም በክረምት የያዝናቸው የ90 ቀን ስራዎች ውስጥ የ60 ቀናት አፈፃፀማችንንም የምንገመግምበት የውይይት መድረክ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የትምህርት ትራንስፎርሜሽን ለሀገራዊ ብልጽግና የነገዋን ኢትዮጵያ በዕውቀት፣ በጥራትና በምቹ የትምህርት አካባቢ የመገንባት ጉዞ!ከ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ ወዲህ፣ ብልጽግና ፓርቲ ሀገርን የ...
29/08/2026

የትምህርት ትራንስፎርሜሽን ለሀገራዊ ብልጽግና የነገዋን ኢትዮጵያ በዕውቀት፣ በጥራትና በምቹ የትምህርት አካባቢ የመገንባት ጉዞ!

ከ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ ወዲህ፣ ብልጽግና ፓርቲ ሀገርን የማዘመንና ሁለንተናዊ እድገትን የማረጋገጥ ራእዩን እውን ለማድረግ ለትምህርት ዘክተር ልዩና ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ትምህርት የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የፖለቲካዊ እድገታችን ዋና መሠረት ነው የሚለው የፓርቲያችን እሳቤ፣ ጥራቱን የጠበቀና ምቹ የትምህርት ሥርዓት መገንባት ላይ ያተኮሩ በርካታ ታሪካዊ እርምጃዎችን እንድንወስድ አድርጎናል።

ትምህርት ቁጥርን ብቻ ሳይሆን ዕውቀትን፣ ክህሎትንና በጎ ምግባርን ማስታጠቅ አለበት በሚለው የብልጽግና መርህ መሠረት፣ በትምህርት ጥራት ላይ መሠረታዊ የፖሊሲና የአሠራር ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

አዲስ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ካሪኩለም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ፣ የተማሪዎችን የፈጠራና የችግር ፈቺነት አቅም የሚያሳድግ አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት ተቀርፆ ሥራ ላይ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና የ12ኛ ክፍል ፈተና ማሻሻያ የትምህርት ስርቆትንና ኩረጃን በማስቀረት ተማሪዎች በገዛ ጥረታቸውና ዕውቀታቸው ብቻ የሚመዘኑበት፣ የትምህርት ጥራትን የሚያስከብር ቁርጠኛ አሠራር ተዘርግቷል።

የመምህራን አቅም ግንባታ መምህራን የትምህርት ጥራት ቁልፍ ማዕከል እንደመሆናቸው መጠን፣ የሙያ አቅማቸውንና ብቃታቸውን ለማሳደግ ተ தொடታታይ የስልጠናና የማብቃት ሥራዎች ተከናወነዋል።

ለተማሪዎቻችንና ለመምህራኖቻችን ሳቢ፣ ምቹና ዘመናዊ የትምህርት አካባቢን መፍጠር የመማር-ማስተማሩን ውጤታማነት በእጅጉ ያሳድገዋል።

የቅድመ-መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደረጃን ማሻሻል የህዝብንና የመንግስትን አቅም በማስተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉና ለህፃናት ምቹ የሆኑ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፤ ነባሮቹም ታድሰዋል።

የተማሪዎች ምገባ ተማሪዎች በረሃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ እንዲያደርጉ የታሰበው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናትን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል።

የስማርት ኤሌክትሮኒክስና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራእይን ታሳቢ በማድረግ፣ የኮምፒውተር ላቦራቶሪዎችን ማደራጀትና ዲጂታል የመማሪያ መሣሪያዎችን ወደ ትምህርት ቤቶች የማስገባት ሥራ በስፋት ተሰርቷል።

የትምህርት ተቋማት ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው እውነተኛ የዕውቀትና የጥናት ማዕከል እንዲሆኑ ተደርጓል። በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የራስ ገዝነት አሠራር እንዲሰፍን በማድረግ የምርምርና የትምህርት ጥራታቸውን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ የማሳደግ ጉዞ ተጀምሯል።

ብልጽግና ፓርቲ የጀመረውን የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ፣ የትምህርት ቤቶችን ምቹነት የማሳደግና የትውልድ ግንባታ ጉዞ በተጠናከረ ሁኔታ ያስቀጥላል። ነገ የተሻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሠረቱ ዛሬ በክፍል ውስጥ የምንቀርፀው እውቀትና መልካም ዜጋ ነው!

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ  ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት"  ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ...
27/08/2026

ዛሬ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለውን “የሜክሰድ ማርሻል አርት እና የንኪኪ ስፖርት በአንድ መድረክ የሚይዘው ዓድዋ ፋይት ናይት" ውድድር፣ በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ወጣቶችን አበረታተዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው፥ ውድድሩ በአደጉና በበለፀጉ ሀገራት እጅግ ተወዳጅ ስፓርት ሲሆን፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፓር መሰረተ ልመቶችን የሚፈልግ በመሆኑ እስከአሁን በአገራችን ሲካሄድ አይስተዋልም፥ ዛሬ ግን በከተማችን በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ምቹ የስፓርት መሰረተ-ልማቶች እውን በመሆናቸዉ አዳዲስ የፓርት አይነቶች እየተካሄዱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

በመቀጠልም፥ ውድድሩ ወጣቶች ልዩ ተሰጥኦና ችሎታቸዉን የሚዳብሩበት ፣ለስፖርት ቱሪዝም፥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት፣ የከተማችንን ገፅታ የሚቀይር እና ተወዳዳሪነታችን የሚጨምር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም እንዲህ አይነት ውድድሮች፥ ወጣቱን ታሳቢ ያደረጉ መሠረተ-ልማቶችን ይበልጥ አጠናክረን እንድንሰራ ያደርገናል፤ ወጣቱም አለማቀፍ የተወዳዳሪነት መንፈስ እንዲያሳድግ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል።

ክብርት ከንቲባ በመልእክታቸው አዘጋጆችን “በርቱ” ያሉ ሲሆን፤ ለተወዳዳሪዎችም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።


የመረጃ እና የትርክት የበላይነትን መጎናፀፍ ዋና ስትራቴጂካዊ ግባችን ነው ! ዶ/ር ሚኤሳ ኤለማበብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ በየደረጃው የሚገኙ አ...
27/08/2026

የመረጃ እና የትርክት የበላይነትን መጎናፀፍ ዋና ስትራቴጂካዊ ግባችን ነው ! ዶ/ር ሚኤሳ ኤለማ

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የዘርፉን የ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በውይይት አዳብረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኤሳ ኤለማ ሮቤ( ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳስገነዘቡት በበጀት ዓመቱ በሀሳብ ልህቀት፣ በተጨባጭ ስኬት የገዘፈውን ብልፅግና ፓርቲን፣ በሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን እና በፈጣን ለውጥ ላይ የምትገኘውን አዲስ አበባን የሚመጥኑ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎችን ለማከናወን ሁሉንም አቅሞች በማቀናጀት ብርቱ ርብርብ ይደረጋል።

አርቆ ማለም፣ አስፍቶ ማቀድ፣ አልቆ መተግበር እና የላቁ ድሎችን ማስመዝገብ የብልፅግና ፓርቲ መለያ መሆኑን ያወሱት ዶ/ር ሚኤሳ ዘርፉም አንድ ዕቅድ፣ አንድ ምዘና፣ አንድ ሪፖርት በሚል የተልዕኮ ስምሪት የተናበበና የተቀናጀ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

የመረጃና የትርክት የበላይነትን መጎናፀፍ የዘርፉ ዋና ስትራቴጂካዊ ግብ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ሚኤሳ በሰው ሀይል፣ በአሰራር እና በግብዓት የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማላቅ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የህዝባችንን የአብሮነት እሴት የሚያጠናክሩ፣ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብቱ፣ ስኬቶቻችንን የሚያሰፉ፣ የፓርቲያችንን እና የመንግስትን ቅቡልነት የሚያሳድጉ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎችን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ዶ/ር ሚኤሳ በአፅንዖት ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዱ አሰፋ በበኩላቸው ተቋማዊ አቅምን በማሳደግ፣ የመረጃና የአጀንዳ የበላይነትን በማጠናከር ፣የብልፅግና ፓርቲ እሳቤን ማስረፅ እና የትርክት የበላይነትን ማረጋገጥ የ 2019 ዋነኛ የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ባቀረቡት ሪፖርት አስረድተዋል።

አዲስ አበባ በፈጣን ለውጥ ላይ የምትገኝ ፣ አዳጊ የህዝብ ፍላጎት ፣ ለቴክኖሎጂ የቀረበ ህዝብ ያላት፣ ከጉስቁልና ወደ ተምሳሌትነት የተሸጋገረች፣ ተፈጥሮ በህብር የሽመናት ዓለም አቀፍ መዲና መሆኗን ታሳቢ ያደረጉ የዘርፉ ግቦች የቀረቡ ሲሆን የበሰለ ውይይትም ተደርጎባቸዋል።

ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ቁርጠኝነትን በመላበስ የዘርፉን ስትራቴጅካዊ ግቦች አልቆ ለመፈፀም ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም፣ ሁሉንም አቅሞች በማስተባበር ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚደረግ ተመላክቷል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የዘርፉ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ የከተማ፣ የክ/ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ዕቅዱን የሚያዳብሩ፣ የጋራ ግልፅነት የሚሹ ሀሳቦች ላይ የበሰለ ውይይት በማድረግ የጋራ ተግባቦት ፈጥረዋል።

የላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ሀሰን እና የላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀም በውይይቱ መጀመሪያ ላይ በመገኘት ለዘርፉ ስኬት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ...
27/08/2026

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፣ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ዳግም «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ተኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq



የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ! ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና)   መርቀን ...
26/08/2026

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ!

ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና) መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የትራፊክ መጨናነቅን የሚያቃልሉ፣ የትራንስፖርት ሥርዓትን የሚያሻሽሉ፣ ህዝባችንን ከዝናብና ፀሐይ እንግልት የሚከላከሉ፣ በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ ምቹ ፣ ንፁህ እና የሰውን ክብር የሚመጥኑ የዘመነ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

መሰረተ ልማቶቹ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች፣ ሰፊ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች፣ ካፍቴሪያና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻና ማረፊያ ስፍራዎች፣ ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የአስተዳደር እና የትኬት መቁረጫ ቴክኖሎጂዎች፣ አሳንሰሮች እና ንፁህ መፀዳጃ ቤቶች እንዲሁም የደህንነትና የአደጋ ቅድመ መከላከል ሥርዓቶች የተሟሉላቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም እና ምንም ያልነበረንን ተርሚናል በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል ።
ለከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ቃላችንን በተግባር ስራዎችን እየፈጸምን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እንገኛለን። አዲስ አበባ ከዚህ በላይ ይገባታል ቀጣይም ከሰራነው በላይ እንተጋለን!

የዛሬዎቹ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ለተጋችሁ፣ ላስተባበራችሁ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች በዚህ ስራ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
-prosperity

Address

4 Kilo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada Sub City Prosperity Party -ብልጽግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Arada Sub City Prosperity Party -ብልጽግና:

Shortcuts

Share