Lemi Kura Woreda 05 Communication

Lemi Kura Woreda 05 Communication ሚድያን ለበጎ ተግባር እናውል! ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን

የፅዳት መረሃ ግብር ተካሄደ ​በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 «ጳጉሜን 1 - የእምርታ ቀን»ን አስመልክቶ ታላቅ የአካባቢ ፅዳት ዘመቻ ተካሄደ። በመረሃ ግብሩ የከተማ ፅዳት ኤጀንሲ አመራሮ...
06/09/2026

የፅዳት መረሃ ግብር ተካሄደ

​በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 «ጳጉሜን 1 - የእምርታ ቀን»ን አስመልክቶ ታላቅ የአካባቢ ፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

በመረሃ ግብሩ የከተማ ፅዳት ኤጀንሲ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳው የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በንቃት ተሳታፊ ሆነዋል።

​ይህ ተግባር የአካባቢን ውበት ከማደስ ባለፈ ህብረተሰቡ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለፅዳትና ውበት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ለማስገንዘብ አልሞ የተከናወነ ነው። ተሳታፊዎቹ በአንድነት በመሆን የመኖሪያና የሥራ አካባቢያቸውን ፅዱ አድርገዋል።

​ህብረተሰቡ አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስና በፅዱ አካባቢ እንዲቀበል ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ነዋሪ የአካባቢውን ፅዳት እንደ ዘላቂ ባህል አድርጎ እንዲቀጥል መልዕክት ተላልፏል።

ለሚ ኩራ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ጳጉሜን 1 / 2018 ዓ.ም

05/09/2026

ለሚ ሁለገብ ገበያ ማዕከል የአዲስ አመት የገያ አቅርቦት ከአቅራቢዮች ጋር የተደረገ ቆይታ

ለሚ ኩራ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ነሃሴ 30 / 2018 ዓ.ም

05/09/2026
በለሚ ሁለገብ ገበያ ማዕከል የተሰማሩ ነጋዴዎች መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት በቂ አቅርቦት እያስገቡ መሆናቸውን ገለፁ​የለሚ ሁለገብ ገበያ ማዕከል መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክ...
04/09/2026

በለሚ ሁለገብ ገበያ ማዕከል የተሰማሩ ነጋዴዎች መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት በቂ አቅርቦት እያስገቡ መሆናቸውን ገለፁ

የለሚ ሁለገብ ገበያ ማዕከል መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ በቂ የሸቀጦችና የተለያዩ ግብዓቶችን አቅርቦት በሰፊው እያስገቡ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው አቅራቢዎች ገልጸዋል።

ማዕከሉ ከንግድ አቅራቢዎች፣ ከጅምላ ሻጮችና ከአምራቾች ጋር በሚያደርገው ትስስር በበዓሉ ወቅት የሚፈለጉ መሠረታዊ ግብዓቶች ያለ ምንም የእጥረት ስጋት በጥራትና በበቂ መጠን እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል።

​አቅራቢ ነጋዴዎች እንደገለፁት በበዓሉ ወቅት ከፍተኛ ፍላጎት የሚኖራቸው የምግብ ዘይት፣ ሩዝ፣ዱቄት፣
ስኳር፣ ሽንኩርት፣ ቅመማ ቅመሞችና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች በበቂ መጠን ወደ ማዕከሉ እያገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡን ከያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ለመጠበቅ ከምርት አቅራቢዎች የምርት ዋጋዎችን ለማስጠበቅ ከንግድ ጽ/ቤት ጋር የጋራ ስምምነት እንዳለቸው የተገለፀ ሲሆን በበዓል ሰሞን በሚፈጠሩ የሸቀጥ እጥረቶችና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሳይሰጉ የሚፈልጉትን ምርት በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ ሁሉንም አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቁ ተገልጿል።

ለሚ ኩራ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ነሀሴ 29 / 2018 ዓ.ም

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

02/09/2026

በ72 አካበቢ የተሰሩ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ ከነዋሪዎች ጋር የተደረገ ቆይታ‼

በወረዳው የተከናወነው የኮብልስቶን ንጣፋ ስራ የነዋሪዎችን ስጋት በመቅረፍ ለአካባቢው ፅዳትና ውበት መንገድ ከፈተ‼​ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር  በጥራት የተከናወነው የኮብ...
01/09/2026

በወረዳው የተከናወነው የኮብልስቶን ንጣፋ ስራ የነዋሪዎችን ስጋት በመቅረፍ ለአካባቢው ፅዳትና ውበት መንገድ ከፈተ‼

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በጥራት የተከናወነው የኮብልስቶን መንገድ ንጣፍ ስራ የአካባቢውን ገጽታ በመቀየር ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ አካባቢን መፍጠሩ ተገልጿል።

አካባቢው ከዚህ ቀደም በጭቃ፣ በአቧራ እና ባልተመቻቸ ሁኔታ ምክንያት ለህፃናት ደህንነት ትልቅ ስጋት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተሰራው ጥራት ያለው የኮብልስቶን ምንጣፍ ስራ ምክንያት ቦታው ፅዱ፣ ማራኪ እና ለእንቅስቃሴ ምቹ ማድረግ እንደተቻለ የወረዳው በጎ ፈቃድና ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይማኖት በላይ ገልጿል።

በመንግስት እና በነዋሪዎች መዋጮ የተሰራው ይህ መሰረተ ልማት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ደስታንና እርካታን ፈጥሯል።


የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ቀደም ሲል ልጆቻቸው ወደ ውጭ ወጥተው ሲጫወቱ ያሳድርባቸው የነበረው ስጋት አሁን ላይ በመቅረፉ እፎይታ እንደሰጣቸው የጠቆሙ ሲሆን መንገድ መሰራቱ የአካባቢውን ፅዳትና ውበት ከመጠበቁ ባሻገር የነዋሪዎችን እለታዊ እንቅስቃሴ እና የህፃናትን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሻሻላለቸው ገልጿል።

በወረዳው እንዲህ ያሉ የልማት ስራዎችን በመከናወናቸው የህብረተሰቡን የእለት ተእለት ችግር በመቅረፍ ረገድ የጎላ ሚና የተጫወተ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተጠቁሟል።

ለሚ ኩራ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ነሀሴ 26 / 2018 ዓ.ም

31/08/2026
ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት  መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል። በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የ...
30/08/2026

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል።

በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት መነሻ ያደረገ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፈን ቃላችንን በተግባር ቆጥረን ፈፅመን የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ከተማችን ደግሞ ተወዳዳሪ እንድትሆን አድርገናል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የከተማችን ነዋሪ እምነት አድሮበት ዳግም መርጦን ሀላፊነት ሰጥቶናል።
የዛሬው ውይይትም የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት መነሻ ያደረገ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ዝርዝር ግቦች ላይ ተወያይተን በማዳበር የባለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀምን በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ ነው።

እነዚህን ዝርዝር ውይይቶች ስናደርግ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ በማሳደግ፣ አመራራችን ከፊት ሆኖ የበለጠ እየሮጠ ህዝባችንንና የልማት አጋሮቻችንን በማስተባበርና ተሞክሮዎችን በማስፋት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሀገራዊ ማንሰራራት ውስጥ የአዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ እንተጋለን።

በተጨማሪም በክረምት የያዝናቸው የ90 ቀን ስራዎች ውስጥ የ60 ቀናት አፈፃፀማችንንም የምንገመግምበት የውይይት መድረክ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

29/08/2026

Address

Sammit Condumnim
Addis Ababa
1000

Telephone

+251969478157

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lemi Kura Woreda 05 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share