Tourism Training Institute

Tourism Training Institute It is established as an autonomous legal executive entity of the Federal Government Ethiopia. The institute shall have the following
objectives:
1.

Providing skill-based and up to the standard
pre and on job training both in terms of
theory and practice to foster the
development of the tourism and hotel
sector.
2. Offering short, medium, and long-term
professional development training to
employees, leaders, and service providers in
the hotel and tourism sector.
3. Supporting the overall socio-economic
development endeavor of the coun

try
through the provision of training,
conducting research, consultancy, and
technology transfer as a center of
excellence.

በመረጃ አያያዝ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተጎበኘ።ቱ ማ ኢ ግንቦት /2018 ዓ ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት...
21/05/2026

በመረጃ አያያዝ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተጎበኘ።
ቱ ማ ኢ
ግንቦት /2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ‎ ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው።
መረጃ የተዋሰ ወይም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ ሀገራዊ አጃንዳን ለማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ተብሏል።
በኤግዚብሺኑ ‎ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት መሰራቱ ለየት ያደርገዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን እንዳለበት በባለሙያዎቹ ተገልጿል።
ኤግዚቢሽኑን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ኤጄንሲ እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ናቸው።

ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

‘ንቁ የዲጂታል ብልህነት ለሥራ ፈጠራ’ በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።ቱ.ማ.ኢግንቦት 7/2018 ዓ.ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሸጋ ትውልድ ...
15/05/2026

‘ንቁ የዲጂታል ብልህነት ለሥራ ፈጠራ’ በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቱ.ማ.ኢ
ግንቦት 7/2018 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሸጋ ትውልድ ማህበር ጋር በመተባበር በተቋሙ ለሚገኙ ሠራተኞች፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ንቁ የዲጂታል ብልህነት ለሥራ ፈጠራ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ አምስት ሚለዮን ኮደሮች በማስመዝገብና በማሰልጠን ለዜጎች ሥራ ዕድል እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት በኢትዮጵያ መንግስት ተነሳሽነት ዓለም አቀፍ በሆኑ አራት ስልጠና አይነት ስልጠናዎችን ሁሉም ዜጋ እንዲሰለጥን ተመቻችቷል፡፡ስለሆነም የተቋሙ ሠራተኞችና ሰልጣኞች በዚህ የኢትዮጵያ አምስት ሚለዮን ኮደሮች ስልጠና ውስጥ እንዲያልፉ በሸጋ ትውልድ አስተባባሪነት ሁሉም ከምዝገባ እስከ ምስክር ወረቀት አወሳሰድ ያለው ግንዛቤ አግኝቶ ወደ ስልጠና እንዲገቡ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
የተቋሙ አመራር እና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው ሠራተኞች ይህን ስልጠና በመውሰድ ተጨማሪ የሥራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስልጠና መሆን እንደለበት ተናግረው ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ በዚሁ ልክ የሚራመድ ሰራተኛ፣አሰልጣኝ እና ሰልጣኝ እንደተቋም ለመፍጠር በፍጥነት የዚህ ስልጠና ተጠቃሚ ኢንዲሆኑ እድሉ እንደተመቻቸ ገልጿል።
የሸጋ ትውልድ ባለራዕይና መስራች አቶ ሳሙኤል ገረመው በዚህ ፕሮግራም ሦስት ነገሮች ለማድረግ እንደመጡ ጠቁመው እነሱም ለማስተማር ለማጽናትና ለማብቃት ነው በማለት ከምዝገባ እስከ ምስክር ወረቀት አወሳሰድ ያለውን በከፍተኛ የኮምፒውተር ባለሙያዎች ስልጠናው እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በስልጠናው ወቅት የሸጋ ትውልድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተው ስልጠናውን በተግባር አሰልጥነዋል። በስልጠናውም የተቋሙ ሰራተኞች፣አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በመሳተፍ ከዚህ በፊት በራሳቸው ተነሳሽነት ስልጠናውን ከወሰዱት ውጪ ያሉት ሁሉም እንዲመዘገቡና ስልጠናውን እንዲጀምሩ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

'መልካምነት ተመሰገነቱ.ማ.ኢ'ሚያዝያ 30/2018ዓ.ም  የቀድሞ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች  የቀለምና የስነምግባር መምህራችን ናቸው ያሏቸውን የኢንስቲትዩቱ  የቀድሞ የፈረንሳይ...
09/05/2026

'መልካምነት ተመሰገነ
ቱ.ማ.ኢ
'ሚያዝያ 30/2018ዓ.ም
የቀድሞ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የቀለምና የስነምግባር መምህራችን ናቸው ያሏቸውን የኢንስቲትዩቱ የቀድሞ የፈረንሳይኛ ቋንቋ መምህር አቶ ሳምሶን መንገሻ (መስዬ ሳምሶን) ለመልካምነታቸውና በህይወታቸው አርአያ ስለሆኗቸው የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጁ ።

የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በምስጋና ፕሮግራሙ ተገኝተው እንደገለጹት አቶ ሳምሶን የቀድሞ መምህራቸው በኋላም የሥራ ባልደረባ ሆነው አብረው መስራታቸውን ገልጸው ትውልድ ላይ የሠሩት ሥራ እንዲህ ለምስጋና መብቃቱ በጣም መደሰታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ሳምሶን የኢንስቲትዩቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሥራቸው ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የጡረታ ጊዜያቸው ከደረሰ በኋላም በራሳቸው ፍላጎት ተጨማሪ ክፍያ ሳይጠይቁ ከ10 ዓመታት በላይ በበጎ ፈቃዳቸው ለትውልድ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተዋል።

መስጠት መታደል ነው ፤ ከማስተማር ባሻገር ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ከማስቀጠል አኳያ ወሰንም መጠንም የሌለው መልካምነት ሰጥቶናል ብለዋል የቀድሞ ተማሪዎቻቸው።

ፕሮግራሙን ያስተባበሩ እና ያዘጋጁት የኢንስቲትዩቱ የቱር ጋይድና የቱር ኦፕሬሽን የቀድሞ ተማሪዎች ሲሆኑ በፕሮግራሙ ምስክርነት ከሰጡት አቶ ሳምሶን መምህር ብቻ ሳይሆን እንደ አባት የሚከታተል፣ የሚቆጣጠር ፣ምንቸገረህ የሚል እና እንደጓደኛ የሚቀርብ ነበር ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

የፈረንሳይኛ ቋንቋን ሲጀምሩት ፈርተው ሲጨርሱ ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንደ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ቋንቋ ሳይሆን እንደ አፍመፍቻ ቋንቋ እንዲወዱት እንዲነጋገሩበት እድል እንደፈጠራላቸው በአስጎብኚነት ሥራ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ አስጎብኚ የሆኑ በርካታ እንደሆኑም በምስጋና ፕሮግራሙ ተገልጿል።

በመጨረሻም የቀድሞ ተማሪዎቻቸው የማሰታዎሻ ስጦታ አበርክተዋል።
መልካምነት " ለራስ እንደሚቀቡት ሽቶ ነው ወደዱም ጠሉሙ ለሌሎች የሚሸት ፣ የሚጋባነው ብለውታል" እኛም መልካም ሥራ ለራስ ፣ ለውስጥ ሰላም ነው በማለት አቶ ሳምሶን ስለሰጡን መልካም ነገር ፕሮግራሙን ያዘጋጁትንም እናመሰግናለን።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

04/05/2026
በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ አቅሞችን አሟጦ ለመጠቀም ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ።ቱ.ማ.ኢሚያዚያ 25/218 ዓ.ም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር ...
03/05/2026

በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ አቅሞችን አሟጦ ለመጠቀም ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ።
ቱ.ማ.ኢ
ሚያዚያ 25/218 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የዩንቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በዘርፉ የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ታግዘው ሁለቱ ተቋማት ቢሰሩ እንደሀገር በዘርፉ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።

በጥናትና ምርምር ጉባኤው ከቀረቡ የጥናት ወረቀቶች አንዱ በሲዳማ ክልል ያለውን የምግብ ቱሪዝም ሀብት የሚያሳይ ሲሆን በሚገባ ማስተዋወቅና ክልሉም ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ የሚዳስስ ነው።
አጥኚው የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኝ ጌትሽ ገደፋው ሲሆኑ በገለፃቸው በዓለም ላይ በምግብ ቱሪዝም የሚታወቁ ከተሞችን እንደምሳሌ አቅርበዋል።
ሌላው የጥናት ጽሑፍ አቅራቢ ከወልዲያ ዩንቨርስቲ አቶ ጌታቸው ከበደ 'Reimagining Tourism as Catalysts for Ethiopia 's Multi_Sectoral Transformation in the Digital Era' በሚል ርዕስ እና ሌሎች ሁለት የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል።
በመጨረሻም ለጥናቱ ተሳታፊዎች እና አስተባባሪዎች የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና የዩንቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንት የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት'ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት' መቀናጀት አለባቸው ተባለ።ቱ.ማ.ኢ ሚያዝያ 25/2018  ዓ ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ...
03/05/2026

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት'ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት' መቀናጀት አለባቸው ተባለ።
ቱ.ማ.ኢ
ሚያዝያ 25/2018 ዓ ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው 15ኛው የጥናትና የምርምር ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራ እና ዘላቂነት"/Innovations and Sustainability in Modern Tourism Development"/" በሚል መሪ ሀሳብ በርካታ የምርምር ሥራዎችና ቁልፍ መልዕክት ቀርቧል።
የምርምር ኮንፈረንሱ ቁልፍ መልዕክት አቅራቢ የሆኑት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደ ገለጹት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ቱሪዝምን ከአካባቢ ጥበቃ እና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት ጋር
በማጣመር ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጤት ማስመዝገብ እና ፈጠራን ማስፋፋት እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላም በኩል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የከተማ ዲዛይኖችን በመጠቀም የጎብኝት ልምድ ማሳደግ እና ሀገራዊ ገጽታን መገንባት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ፈጠራ እና ቱሪዝም በኢትዮጵያ የማይነጣጠሉ በመሆኑ አዳዲስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የቅርሶች ገለጻ (AR/VR) ፣ ቀልጣፋ የዲጂታል ክፍያ እና የቦታ ማስያዣ (Reservation) የመሳሰሉ ዘዴዎችን መጠቀም ዋናዎች ናቸው ብለዋል።

በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት አቀናጅቶ መሰራት እንዳለበት በመልዕክቱ ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ መሆኑ ተገለጸ።ቱ ማ ኢ ሚያዝያ 24/2018  ዓ ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ...
02/05/2026

የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ መሆኑ ተገለጸ።
ቱ ማ ኢ
ሚያዝያ 24/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር "የፈጠራና ኢኖቬሽን ቀጣይነት ላለው የቱሪዝም ልማት"በሚል መሪ ሀሳብ የተለያዩ ምርምር ሥራዎች ቀርቦ ወይይት ተደርጓል።
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመክፈቻ ፕሮግራሙ እንደገለፁት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው ተጨባጭ እድገት በማስመዝብ ላይ የሚገኝ ዘርፍ ነው፡፡
በርካታ ጥናቶች እንደያሚያረጋግጡት፣ ዘርፉ ለበለፀጉትም ሆነ ለታዳጊም አገራት ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እና የውጪ ምንዛሪ ገቢን በማስገኘት ሁነኛ የሀገራዊ ሀብት ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም፣ አሁን በደረስንበት፣ ዘመን የቱሪዝም ዘርፉ፣ ከማህበራዊ ወደ ኢኮኖሚ ሴክተር ብሎም ወደ ዲጂታል ቱሪዝም በመሸጋገር ላይ የሚገኝ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሆኖ እየመጣ በመሆኑን ዘርፉ ለሰዎች በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን ከማስገኘት በዘለለ በሕዝቦች መካከል መልካም የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ግንኙነት እንዲሁም የባህል ትስስር እንዲጠናከርና እንዲጎለብት ለማድረግ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተናግረዋል ፡፡
የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ዋና ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በበኩላቸው እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት እንደዚህ አይነት የምርምር ሥራዎች አብሮ መስራት ለሀገር እድገት ወሳኝ ለተቋማትም ጠቃሚ መሆኑን እና ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገትና ለሥራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
በመሪ ቃሉ መነሻነት በዘርርፉ ምሁራን አራት የጥናት ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

' በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራ እና ዘላቂነት"/በሚል መሪ ቃል የምርምር ኮንፈረንስ ተጀመረ።ቱ ማ ኢ ሚያዝያ 24/2018 ዓ ም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋ...
02/05/2026

' በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራ እና ዘላቂነት"/በሚል መሪ ቃል የምርምር ኮንፈረንስ ተጀመረ።
ቱ ማ ኢ
ሚያዝያ 24/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 15ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ 'በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራ እና ዘላቂነት"/ Innovations and "Sustainability in Modern Tourism Development በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ እያተካሄደ ነው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

ስልጠና ከወሰዱት 139 የልምድ ባለሙያዎች 124 ያህሉ በጥሩ ውጤት አለፉ  ቱ. ማ. ኢ ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሲቪል ሰርቪስ  ዩንቨርሲቲ ጋር በ...
28/04/2026

ስልጠና ከወሰዱት 139 የልምድ ባለሙያዎች 124 ያህሉ በጥሩ ውጤት አለፉ
ቱ. ማ. ኢ
ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር በምግብ ዝግጅት፣ በእንግዳ አቀባበልና በመስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በዳቦና ኬክ ዝግጅቶች ለአንድ ወር ያህል ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ ምዘና በመስጠት አጠናቋል።
የአጫጭር ስልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ ስልጠናው በሥራ የተገኘን ዕውቀት አጫጭር ስልጠና ሰጥቶ በመመዘን ወደ ደረጃ ለመቀየር የሚያስችል ሲሆን ከ139 ሰልጣኞች መካከል 124 የሚሆኑት ተመዝነው በጥሩ ብቃት አልፈዋል ብለዋል፡፡ ምዘናውን ያላላፉ 15 የሚሆኑት ሰልጣኞች በቀጣይ ራሳቸውን በማብቃት ድጋሚ መመዘን የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን ሲወስዱ የነበሩ ሰልጣኞች በልምድ ሲሰሩ ከነበረው በዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና እጅግ እንደጠቀማቸው፤ ጉልበት ከሚያደክም ሥራ የተሻለ፣ ጊዜና ገንዘብ ሊቆጥብ የሚችል አሰራር እንደሰለጠኑም ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

ኢንስቲትዩቱ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ   ጋር   የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ሚያዝያ 2018 ዓ.ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስ...
25/04/2026

ኢንስቲትዩቱ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ሚያዝያ 2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ኢንስቲትዩቱ እና ዩንቨርሲቲው አብረው ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰው
በቱሪዝም እና በሆቴል ዘርፍ በስልጠና በጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ አንጋፋ ተቋም መሆኑን እና
ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተደረገው ስምምነት የተቋሙን ተልዕኮ በማከናወን ሂደት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ በበኩላቸው የአማራ ክልልና በተለይም ባሕር ዳር ከተማና አካባቢው ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ለማልማትና ለመጠቀም ይህ ስምምነት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው ፣ ለትግበራውም ዩኒቨርሲቲው ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ፊርማውን የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩምና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ፈርመውታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/

Address

Near Guenet Hotel
Addis Ababa
4350

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tourism Training Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share