Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና

Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና Building a brighter future for Kolfe through economic growth, social equity, and community development

07/09/2026

ጳጉሜ 2፡ የማንሰራራት ቀን
"አዲስ አበባ የትንሳኤና የማንሰራራት አብነት" !





!!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ የማንሰራራት ቀንን በተለያዩ አደባባዮች በድምቀት አከበረየኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ሀገራዊ ራዕዮችን በሚያሳዩ ስያሜዎች ...
07/09/2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ የማንሰራራት ቀንን በተለያዩ አደባባዮች በድምቀት አከበረ

የኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ሀገራዊ ራዕዮችን በሚያሳዩ ስያሜዎች እየተከበሩ የሚገኙ ሲሆን፤ የዛሬው የጳጉሜን 2 ቀንም “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” ቀን በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከብሯል፡፡

ይህንኑ ዕለት በተለዩ አውዶች ለማሰብና ለሕዝብ ለማድረስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በተለያዩ አደባባዮች በደምቀት አክብሯል፡፡

ጳጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን" ተብሎ መከበሩ በተጨባጭ እየታዩ ያሉ ሰፋፊ ሀገራዊ ስኬቶችን አመላካች መሆኑን ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተቋማት ግንባታ እና ሌሎች አጠቃላይ ሪፎርሞችን በማድረግ ጠንካራ መሠረት የጣለችበት፤ አሁን ደግሞ የዘላቂ ልማት ትሩፋቶችን ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሷን የማንሰራራት ጉዞዋ በግልጽ እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

በተለይም በታዳሽ ኃይል ልማት፣ በከተሞች ገጽታን የመቀየር ሥራዎች እና በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ውጤት ተኮር ተግባራት የተከናወኑበት ወቅት መሆኑ ለቀኑ መበሰር ዋና ምስክሮች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገራት ልዩ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ የጳጉሜን ቀናት ሲሆኑ፣ እነዚህ ቀናትም የተለያየ ትርጉምና ሀገራዊ ራዕይ ተሰጥቷቻ በመከበር ላይ ይገኛሉ፡፡





!!

07/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሠራራት





!!

አዲስ አበባ የትንሳኤና የማንሰራራት አብነት፦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ «የማንሰራራት ቀን» በልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት ተከበረጳጉሜ 2 «የማንሰራራት ቀን» በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስ...
07/09/2026

አዲስ አበባ የትንሳኤና የማንሰራራት አብነት፦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ «የማንሰራራት ቀን» በልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት ተከበረ

ጳጉሜ 2 «የማንሰራራት ቀን» በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ታላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ ከተማችን አዲስ አበባ እየመዘገበች ያለችውን የትንሳኤና የማንሰራራት ጉዞ በአካል ለመታዘብና የህብረተሰቡን የአብሮነት እሴት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።

በጉብኝቱ ወቅት ክፍለ ከተማው ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸው ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችና ያስመዘገባቸው ተጨባጭ ውጤቶች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በበጎ መልኩ የለወጡና ለከተማዋ አዲስ ገጽታ ያበሱ መሆናቸው ተገልጿል። በተለይም ህዝባዊ ትስስርን የሚያጎለብቱና የነዋሪዎችን ማህበራዊ አገልግሎት የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው ተጎብኝተዋል።

ከተጎበኙት በርካታ የልማት አውተሮች መካከል የነዋሪዎችን ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክሩ፣ ለአካባቢው ውበት የሚጨምሩና ለአእምሮ እረፍት የሚሰጡ የመዝናኛ አካባቢ ልማቶች ተስፋ ሰጪነታቸው ተረጋግጧል።

ይህ የማንሰራራት ቀን መርሃ ግብርም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማን ጥረትና የስኬት ጉዞ በግልጽ ያሳየ ህዝባዊ ሁነቶች አንዱ ሆኖ አልፏል።




!!

ጳጉሜ 2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ አውደርዕይ በ4 ኪሎ ፕላዛ ተከፈተ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ያዘጋጀው አውደርዕይ ተቋሙ ባለፉት ሁለት አ...
07/09/2026

ጳጉሜ 2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ አውደርዕይ በ4 ኪሎ ፕላዛ ተከፈተ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ያዘጋጀው አውደርዕይ ተቋሙ ባለፉት ሁለት አመታት የሰራቸውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማት የሚያሳይ ነው።

ከ41 ሺ በላይ ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማትን በGIS በማደራጀት ከአንድ ማዕከል መቆጣጠርና ማስተዳደር መቻሉን ገልፀዋል።

ይህም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ከፍታና ማንሰራራት ማረጋገጫ መሆኑን አስረድተዋል ።





!!

የማንሰራራት ቀን ስፖርታዊ ትርኢት በግዙፉ አራዳ ፓርክ!ህፃናት የሚቦርቁበት፣ ወጣቶች የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያከናውኑበት፣ አረጋውያን ንፁህ አየር የሚቀበሉበት አራዳ ፓርክ የከ...
07/09/2026

የማንሰራራት ቀን ስፖርታዊ ትርኢት በግዙፉ አራዳ ፓርክ!

ህፃናት የሚቦርቁበት፣ ወጣቶች የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያከናውኑበት፣ አረጋውያን ንፁህ አየር የሚቀበሉበት አራዳ ፓርክ የከተማችን ማንሰራራት አንዱ ምልክት ነው።

በዙሪያው ባሉት ዘመናዊ ሱቆች፣ ግዙፍ የመኪና ማቆሚያ ፓርኮች ለብዙዎች፣ ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች እና በሌሎችም በርካታ የስራ ዕድሎችን መፍጠር ያስቻለው አራዳ ፓርክ የሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን የውጭ ሀገር ጎብኝዎች የስዕበት ማዕከል ሆናል።

የተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች የሚካሄዱበት አራዳ ፓርክ በዛሬው ዕለትም ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀንን በተመለከተ በመቶዎች የሚቆጠሩ የብስክሌት ጋለቢዎች እና የተለያዩ ትርኢት አቅራቢዎች የተሳተፉበትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በድምቀት አስተናግዷል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት




!!

07/09/2026
07/09/2026
07/09/2026

ጳጉሜ 2፡ የማንሰራራት ቀን
"አዲስ አበባ የትንሳኤና የማንሰራራት አብነት" !

ኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞዋን በተግባራዊ ለውጦች፣ በዜጎች ንቁ ተሳትፎና በጸና የጋራ ጥረት በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች።




!!

"ትናንት 'ኢትዮጵያ ተነሥታለች' ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)       !!
07/09/2026

"ትናንት 'ኢትዮጵያ ተነሥታለች' ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)




!!

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share