ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክር ቤት

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክር ቤት Welcome to Ethiopia National House of Congress which engage knowledge based African Authority.

Welcome to Ethiopia National House of Congress that engage Knowledge Based Africans Authority.
የአፍሪካዉያን ስልጣን እዉቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ወደሚያበረታታ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክር ቤት እንኳን በሰላም መጣችሁ፡፡

ከ200 ሚሊዮን እስከ 800 ሚሊዮን የኢትዮጵያ የማይበገር የተስፋ ጉዞኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን ሀ ብላ ስት...
31/07/2026

ከ200 ሚሊዮን እስከ 800 ሚሊዮን የኢትዮጵያ የማይበገር የተስፋ ጉዞ

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን ሀ ብላ ስትጀምር ዓላማዋ አካባቢን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ታሪክ እና የዜጎችን አስተሳሰብ የመለወጥ ትልቅ ራዕይ ነበረው።

በ2011 ዓ.ም በየዓመቱ ከሚተከለው በርካታ ቢሊዮን ችግኞች በተጨማሪ "በአንድ ሰው 40 ችግኝ" እንዲሁም "በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኝ" ለመትከል እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር ሲገባ በርካቶች "ይህ አይሆንም፣ ቅዥት ነው" በማለት ተስፋ ለማስቆረጥ ጥረት አድርገው ነበር።

ሆኖም ኢትዮጵያውያን በነቃ ሕዝባዊ ንቅናቄ እና በተግባር በሰጡት ምላሽ በአንድ ጀምበር ዘመቻ ታቅዶ የነበረውን 200 ሚሊዮን አልፎ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በመላ ኢትዮጵያ 353 ሚሊዮን 633 ሺህ 660 ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡

ከ2011 እስከ 2018 ዓ.ም የተመዘገበው የጽናት እና የተስፋ ጉዞ ከስድስት ዓመታት በፊት የተዘራው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ዛሬ ላይ ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ የመላው ኢትዮጵያዊ ባህል እና መለያ መሆን ችሏል።

አይሆንም ላሉት አካላት በየዓመቱ በሥራ እና በውጤት እየመለሰች የመጣችው ኢትዮጵያ፣ በ2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል " በሚል ታላቅ ሀገራዊ መሪ ቃል ሂደቱን በይፋ ጀምራለች።

ይህ ከ2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ከ200 ሚሊዮን ዕቅድ የተነሳው ንቅናቄ ዛሬ በአንድ ጀምበር ወደ 800 ሚሊዮን ማደጉ በሀገራችን በየዓመቱ እያደገ የመጣውን አቅም በግልጽ ያሳያል።

የ2011 ዓ.ም ጅማሮ ትልቁ ስኬት "አይቻልም" የሚለውን የጠላት እና የተስፋ አስቆራጮችን ትርክት በመስበር በኅብረት ከተነሳን ማሳካት እንችላለን የሚል ፅኑ ሀገራዊ እምነት መፍጠሩ ነው።

በ2011 ዓ.ም የተጀመረው ሥራ አፈር ከመሸርሸር እና ከደን ጭፍጨፋ መከላከል ቢሆንም በ2018 ዓ.ም ግን እንደ ማካዴሚያ፣ ኮኮናት፣ ቡና እና የፍራፍሬ ተክሎችን በስፋት በማካተት የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ ገቢ የሚያሳድግ እና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ የልማት ምሰሶ ሆኗል።

"ተስፋን እንትከል" የሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል በፈተናዎች ውስጥ ያለችውን ሀገር በኅብረት እና በአረንጓዴ ልማት እርስ በእርስ በማስተሳሰር ለቀጣዩ ትውልድ የተረጋጋች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያመላክታል።

በ2011 ዓ.ም በ353 ሚሊዮን በላይ የአንድ ጀምበር ተከላ የተጀመረው የተስፋ ጉዞ ዛሬ በ2018 ዓ.ም በ800 ሚሊዮን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጽፍ ዝግጅቱን ጨርሷል።

ኢትዮጵያ ለሚነሱባት ጥርጣሬዎች በተግባር እየመለሰች የተተከሉ ችግኞች አድገው ፍሬ ማፍራት እንደጀመሩት ሁሉ የዕድገት እና የሰላሟ ተስፋም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ይሄዳል።

በሃና ምንዳሁን

መምከር ፣ መግባባት እና መወሰንኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው ምክክር እንደ ጅማሮ ብቻ ሳይሆን እንደ ተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ ነው። ነገር ግን መምከር ስሉት አይ እኔ መግባባትን ነው ያልኩት ፣ ...
29/07/2026

መምከር ፣ መግባባት እና መወሰን
ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው ምክክር እንደ ጅማሮ ብቻ ሳይሆን እንደ ተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ ነው። ነገር ግን መምከር ስሉት አይ እኔ መግባባትን ነው ያልኩት ፣ መግባባት ስሉ አይ እኔ መወሰንን ነው ያልኩት የሚሉ ዜጎች የምክክር ህደትን ያልተረዱ አልያም ለመቃዋም ምክንያት ያጡ ሰዎች ሊሆኑት ይችላሉ ። ይሁን እንጂ ምክክሩ በአግባቡ መመራት አለበት። እነኚህ 4000 ዜጎች አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት እና ጥቃቅን ሀሳቦች ላይ ለመካካር ሳይሆን ከህዝብ በተሰባሰባው ሀሳቦች ወይም አጀንዳዎች ላይ 130,000,000 ህዝብን ወክሎ ለመመካከር ፣ ለማሳላጥ እና ለመግባባት የሄዱ ናቸው። ይሁን እንጂ የ130 ሚሊዮን ህዝብ አዳዲስ ሀሳቦች እና አስተሳሰቦችን ወይም አጀንዳዎችን ፈጥረው ለመወያያት ግዜም የሚበቃቸው አይመስለኝም። ነገር ግን እነኚህ ሰዎች እንደ አማካሪዎች መካሪ መታያት እና በዚያ ደረጃ ማዘጋጃት ይገባቸዋል። እነሱ የመከሩበትን ጉዳዮች መልሰው ህዝብን በሰፊው ማማከር ወይም ማወያያት ይገባቸዋል። ይህ ማላት እነሱ የመከሩበትን ሀሳቦች እና የመንግስት ፍላጎት አንድ ላይ ተጨምቀው በማሳተም ሰፊውን ህዝብ መልሰው ማማከር ያስፈልጋል። እነሱ የመከሩበትን ደግሞ የህዝብ እንደ ራሴዎች "ፓርላማ" መርምረው ፣ተወያይተው ማፅደቅ ወይም መወሰን ይገባል። አለበለዚያ ህዝብም የየእራሳቸውን ፣ መንግስትም የእራሱን መንገድ ይዛው እንደ እብድ ከእራስ ጋር እያወሩ መሄድ ነው። የህዝብ ምርጫ ወይም የእራስን እድል የለ ማንም ጣልቃ ገብነት በእራስ መወሰንም ውሃ መተንፈስ ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በምክር ቤቱ ጽ/ቤት የ5 ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ‎--------------‎(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 18፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበ...
25/07/2026

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በምክር ቤቱ ጽ/ቤት የ5 ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
‎--------------
‎(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 18፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከተለያዩ የዓለም ሀገራትና ከሀገር ውስጥ ተቋማት የተወሰዱ መልካም ተሞክሮዎችን ያካተተውና ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።

‎በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎች ዕቅዱ ሳይንሳዊ አካሄድን የተከተለ፣ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ የዳሰሰና ቀድሞ ለውይይት መቅረቡ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።

‎በተጨማሪም ልምድ ከሚወሰድባቸው የዓለም ሀገራት እንዲሁም ከሀገር ውስጥ የፕላንና ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ተሞክሮ መወሰዱ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም የሠራተኞችን ማኅበራዊ ሁነት፣ የሥራ ክፍሎችን ቁርኝትና የሕዝብን ተሳትፎ የሚያጠናክሩ ነጥቦች ይበልጥ እንዲጎለብቱ አስተያየት ሰጥተዋል።

‎የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የዋና ጸሐፊ ተወካይና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ከረዩ ባናታ እንደገለጹት፤ ዕቅዱ በአጭርና በረጅም ጊዜ ተከፋፍሎ የሚተገበርና አዳዲስ ሁነቶችን ታሳቢ እያደረገ የሚቀጥል ነው ብለዋል።

‎የፓርላማውን ሚዲያ የይዘት አማራጮች ማሻሻል፣ ከእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ጋር በስታንዳርድ ዙሪያ መመካከር እና በውስጥ አቅም በርካታ ሥልጠናዎችን መስጠት ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል።

‎በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ጸኀፊ (የሙያዊ ዘርፍ ተወካይ) ወ/ሮ ቁስቋም ማሞ በበኩላቸው ጽሕፈት ቤቱ የተቋቋመበትን ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ የማጠናከር ዓላማ መነሻ በማድረግ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ውጤታማ ሥልጠናዎች ለሠራተኞች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

‎የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፈለጉሽ ወርቁ እንደገለጹት የውጭና የሀገር ውስጥ ተሞክሮዎች ከፓርላማው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ የተወሰዱ ናቸው ብለዋል።

‎አክለውም ዕቅዱ ፈታኝ ሁኔታዎችን ለመቋቋምና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም የፓርላማ ራዲዮና ስቱዲዮ ለማቋቋም በስፋት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎(በ ሀብታሙ አብርሃም)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት  የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እያደረገ ነው--------------------(ዜና ፓርላማ)...
25/07/2026

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እያደረገ ነው
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 18 ፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከ2019 እስከ 2023 ዓ.ም የሚዘልቀውን የምክር ቤቱ ጽ/ቤትን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እየቀረበ ይገኛል።

በዕቅድ ውይይቱ መግቢያ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የዋና ጸሐፊ ተወካይና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ከረዩ ባናታ እንደገለጹት፤ የ2019 ዓ.ም ዕቅድ የ2018 ዓ.ም ዕቅድን መነሻ በማድረግና የሁሉም ሠራተኛ ግብዓት እንዲካተትበት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ከረዩ አክለውም አሁን ያለው ጊዜ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማቀድ ምቹ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቆ አሸናፊውን አካል በምክር ቤቱ ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት የሚከናወን በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዕቅዱ የሌሎች የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድ በተሻለ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፈለጉሽ ወርቁ ዕቅዱን ለምክር ቤቱ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በዝርዝር በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

በዚሁ መድረክ ላይ የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በዕቅዱ ይዘት፣ አፈጻጸምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያላቸውን ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች የሚጨምሩ ሐሳቦችን በስፋት ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህም አሳታፊ የውይይት ምህዳር በመፍጠር ዕቅዱ ይበልጥ እንዲጠናከርና አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በተነሱት መሠረታዊ ጥያቄዎችና ነጥቦች ላይም ከምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች በኩል አስፈላጊው ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጥበት ሲሆን፣ በቀጣይ የጋራ ትግበራ ላይም ግልጽ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።

(በ ሀብታሙ አብርሃም)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

"4 ሺህ ተመካካሪዎች በከፍተኛ መተማመን በነፃነት እየተወያዩ ነው" - ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር)ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮ...
23/07/2026

"4 ሺህ ተመካካሪዎች በከፍተኛ መተማመን በነፃነት እየተወያዩ ነው" - ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር)
ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ ለመገናኛ ብዙኃን ዕለታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በሰላማዊ፣ በነፃ እና በመተማመን መንፈስ እየተካሄደ መሆኑን ገለጸዋል።
እንደ ዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎች ከ10 እስከ 50 አባላት ባሉት ንዑሳን የውይይት ቡድኖች ተከፋፍለው ሀሳባቸውን በነፃነት እየተለዋወጡ ይገኛሉ።
በቀጣይም እነዚህ ቡድኖች 250 አባላት ወደሚያካትቱ ስብስቦች በማደግ ውይይታቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎች ያለምንም ፍርሃትና ገደብ ሀሳባቸውን እየገለጹ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ በሚያቀርቡት ማንኛውም ሀሳብ ምክንያት በሌላ አካል ተጠያቂ እንዳይሆኑ ኮሚሽኑ ሙሉ ኃላፊነትና ከለላ መስጠቱንም አስረድተዋል።
በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በታሪክ፣ በማንነት፣ በፌዴራሊዝም እና በግጭት አፈታት ዙሪያ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ምሁራን ለተሳታፊዎች ገለጻ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነር፤ በ500 አባላት በስምንት ቡድኖች የተከፋፈሉት ተሳታፊዎችም ከምሁራኑ ጋር ሰፊ ውይይት እያካሄዱ ነው ብለዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሕዝቡና የመገናኛ ብዙኃን በጥንቃቄ እንዲያዩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዜጎች በየዕለቱ የሚወጡ የኮሚሽኑን መረጃዎች እንዲከታተሉም አሳስበዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ ታሪካዊ በሆነው የሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በታሪክ ምዕራፍ ላይ ...
15/07/2026

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ ታሪካዊ በሆነው የሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በታሪክ ምዕራፍ ላይ ታላቅ ስፍራን የሚይዝ ነው ብለዋል።

‎ ይህ አይነቱ ሀገራዊ ምክክር የሀገራችንን ማህበራዊና የፖለቲካ ጉዞ የሚያቀና እንዲሁም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የሀሳብ ልዩነቶች ውበት ቢሆኑም፤ ነገር ግን እነዚህን ልዩነቶች በሀይልና በግጭት ለመፍታት የተሄደበት ሁኔታ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንደማይችል የኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ ምስክር ነው።

‎በመሆኑም ለዘላቂ መፍትሔ እንዲሁም የወደፊት እጣ ፈንታችን ላይ በጋራ እንድንስማማ የሚያስችለንና ለሀገራችን ፈውስ የሚሆነው ብቸኛ መድኃኒት ታማኝ፣ ግልጽና አካታች ሀገራዊ ምክክር መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

"በዚህ ሀገራዊ ምክክር የሚከሰር የለም፤ ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
14/07/2026

"በዚህ ሀገራዊ ምክክር የሚከሰር የለም፤ ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያን ባህል ​ለፓርላማ የመረጃና ደህንነት መድረክ ፎረም ተሳታፊዎች የማስተዋወቅ ስራ ተከናወነ------------------(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 04 ቀን፣ 2018  ዓ.ም.፤​በኢፌዴሪ ...
11/07/2026

የኢትዮጵያን ባህል ​ለፓርላማ የመረጃና ደህንነት መድረክ ፎረም ተሳታፊዎች የማስተዋወቅ ስራ ተከናወነ
------------------
(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 04 ቀን፣ 2018 ዓ.ም.፤
​በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የፓርላማ የመረጃና ደህንነት ፎረም ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የኢትዮጵያን ባህልና የማስተዋወቅ ስራ ተካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) ለፎረሙ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተከበሩ ዲማ (ዶ/ር) በንግግራቸው ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የዲፕሎማሲ ታሪክ ፣ የሰላም እሴት ያላት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ጽኑ አቋም ያላት መሆኑን በማንሳት እንግዶቹ በቆይታቸው የኢትዮጵያን እውነተኛ ገጽታ ፣ ባህል እና እንግዳ ተቀባይነት እንዲመለከቱ በአክብሮት ጋብዘዋል።

የፎረሙ ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያውያን ባህል በሚያስተዋውቅ ምሽት ላይ በቀረቡት ባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ ሙዚቃዎች እና የባህል አልባሳት መደነቃቸውን ገልፀዋል።

ይህ ዝግጅት ኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የደህንነት ማዕከል ከመሆን አልፋ፣ የቱሪዝም እና የባህል መዳረሻ መሆኗን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር ያረጋገጠችበት ምሽትም ነበር።

(በሚፍታህ ኪያር)

“ኢትዮጵያ በቀጠናው እያሳየች ያለው አስደናቂ የመሪነት ሚና ለዓለም አብነት የሚሆን ነው”-- የፓርላማ የመረጃና ደህንነት መስራች እና ሊቀመንበር ሮበርት ፒተንጀር --(ዜና ፓርላማ)፤ ሐምሌ ...
10/07/2026

“ኢትዮጵያ በቀጠናው እያሳየች ያለው አስደናቂ የመሪነት ሚና ለዓለም አብነት የሚሆን ነው”

-- የፓርላማ የመረጃና ደህንነት መስራች እና ሊቀመንበር ሮበርት ፒተንጀር --

(ዜና ፓርላማ)፤ ሐምሌ 03 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እያሳየች ያለው አስደናቂ የመሪነት ሚና ለዓለም አብነት የሚሆን ነው ሲሉ የፓርላማ የመረጃና ደህንነት መስራች እና ሊቀመንበር ሮበርት ፒተንጀር ገለፁ።

ሊቀመንበሩ ይህንን የተናገሩት በአዲስ አበባ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የደህንነት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ በገቡበት ወቅት ሲሆን፥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የፓርላማ አባላትን ለማስተናገድ ላሳዩት የላቀ አመራር ጥልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ ታሪካዊ መድረክ ኢትዮጵያ ገጽታዋን እና እምቅ አቅሟን ለዓለም የምታሳይበት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም አብራርተዋል።

በቴክኖሎጂ ደህንነት እና ድንበር ዘለል ወንጀሎች ዙሪያ አለም አቀፍ ባለሙያዎች በሚመክሩበት በዚህ መድረክ የኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው አዲስ የመሪነት እና የዕድል ምዕራፍ እንደሚከፍት ያላቸውን ጽኑ እምነት አረጋግጠዋል።

(በ ሚፍታህ ኪያር)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ------------------------(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 27፣ 2018 ዓ.ም፤ ቢሾፍቱ ፤በሕዝብ ተወ...
05/07/2026

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ
------------------------
(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 27፣ 2018 ዓ.ም፤ ቢሾፍቱ ፤በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ አርሰዴ ሀይቅ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡

በዚህ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እና የተመራጭ ሴቶች ኮከስ የበላይ ጠባቂ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ ተግባር የመሬት ደህንነትን በመጠበቅ የኢኮኖሚ እድገትን እና ዘላቂ ልማትን በማጠናከር ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም፤ የአረንጓዴ አሻራ ለግብርና ምርታማነት ያግዛል፡፡ የአፈር ጥበቃን በማሻሻልና እርጥበትን በማስጠበቅ የሰብል ምርታማነትን ለመጨመር እንደሚያግዝ የገለፁ ሲሆን በዘርፉ እየተፈጠረ ያለው የስራ ዕድል ሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያስቻለ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

እንዲሁም አረንጓዴ አሻራን የማኖር ተግባር እጽዋትን ከመትከል ባለፈ ለዱር እንስሳት ጥበቃ ዘርፉ ትኩረት መስጠት ጭምር መሆኑን አንስተዋል፡፡ ይህም ተግባር የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን በማብዛትና በመጠበቅ ገቢ ማመንጨት እንደሚያስችል የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አመላክተዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ የአካባቢ ጥበቃን፣ የኢኮኖሚ እድገትን፣ የምግብ ዋስትናን፣ የሕዝብ ጤናን እና ዘላቂ ልማትን በማጠናከር ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ሴት የምክርቤት አባላት እንደ ሀገር እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ከምንጊዜውም በላይ በማጠናከር ያላቸውን ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ የአረንጓዴ አሻራ ስራን ወደ ባህልነት የመቀየር ተግባርን ትኩረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ምክትል አፈ ጉባኤ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በተያያዘም የቱሪዝም ልማትን በተመለከተ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ መንግሥት ትኩረት ከሰጣቸው ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚዎች ቱሪዝም አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ ከዘርፉ ኢኮኖሚ በማመንጨት የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

ቱሪዝም ለሀገር እና ለትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥል ለህዝቦች አብሮነት በመጠናከርም ፋይዳው የጎላ መሆኑን አያይዘው አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ፀጋ ያላት ሀገር መሆኗ በመረዳት በዘርፉም የሚጠበቀውን ገቢ ለማግኘት በሁሉም አካባቢ የተመዘገቡ አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አሳስበዋል፡፡

(በመኩሪያ ፈንታ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Address

Areda
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክር ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share