የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2

የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2, Government Organization, Road From Mexico to Kera Street Kassa Grand Mall, Addis Ababa.

ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ሁለተኛ ዙር ድጋፍ ተደረገ!************************************(ጷጉሜን 2/2018 ዓ.ም መካከለኛ ግብር ከፋዮች ...
07/09/2026

ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ሁለተኛ ዙር ድጋፍ ተደረገ!
************************************
(ጷጉሜን 2/2018 ዓ.ም መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጨፍ ጽ/ቤት)

የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገቢ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ ያደረገ ቢሆንም፣ በአካል በተደረገ ምልከታ ያደረገው ድጋፍ በቂ እንዳልነበር በመገንዘብ በድጋሚ ድጋፍ አድርጓል።

የተቋማዊ አቅም ድጋፍ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዑዳ አሊ ቃል በተገባው መሠረት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱን ሰራተኞች በማስተባበር ድጋፉ መደረጉን ያወሱ ሲሆን፣ የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል በበኩላቸው ማዕከሉ እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ነጻነት ጥጋቤ እንደገለጹት፤ በአካል ተገኝተው ማዕከሉን በጎበኙበት ወቅት የነበረውን አሳሳቢ ሁኔታ በመመልከት ለሠራተኞች ማብራሪያ ተሰጥቷል። በዚህም መሠረት ከሠራተኛው በፈቃደኝነት የተሰበሰቡ የታሸገ ውሃ ፣ ፍራሽ ፣ የሕክምና መድኃኒቶች እና የጽዳት ዕቃዎች ለማዕከሉ ማስረከብ ተችሏል ብለዋል።

የማዕከሉ ኃላፊዎችም "እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለእናንተ ትንሽ ቢመስልም ለማዕከሉ ግን ወሳኝ እና ትልቅ አስተዋፅኦ አለው" በማለት ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።ማዕከሉ በችግር ምክንያት ጎዳና ላይ የወደቁ ወገኖቻችንን በማንሳት እያገገሙ እንዲቋቋሙ እያደረገ ይገኛል። እንደ ዝክር፣ የሙት ዓመት፣ ልደት፣ ሠርግ፣ ኒካህ እና ሌሎች ዝግጅቶችን በማዕከሉ ውስጥ በማዘጋጀት ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) 6860 ላይ OK ብለው በመላክ ለማዕከሉ ደጋፊ አባል በመሆን አጋርነትን ማሳየት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
የበጎ አድራጎት ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ግብር÷ ለሃገር ክብር!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-MTO2
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል ላይ እንገኛለን

የማንሠራራት ቀንጷግሜን 2/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)ጷግሜን 2 የማንሠራራት ቀንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስተላለፉት መልእክት ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስ...
07/09/2026

የማንሠራራት ቀን

ጷግሜን 2/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ጷግሜን 2 የማንሠራራት ቀንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስተላለፉት መልእክት

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።

07/09/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀን መልዕክት ***ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 1 ቀን የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት አባቶቻችን ...
06/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀን መልዕክት
***

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 1 ቀን የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል ብለዋል።

ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንደምንገኝ አስታውሰዋል።

ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን።

እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

02/09/2026
የኦዲት አሰራር ግልጽነትን ለማሳደግ ያለመ የስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ****************************************************************(ነሐሴ 26...
01/09/2026

የኦዲት አሰራር ግልጽነትን ለማሳደግ ያለመ የስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ
****************************************************************
(ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመካከለኛ ግብ ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)

በስጋት መስፈርት ደረጃ ተመርጠው ኦዲት ለሚደረጉ ድርጅቶች የታክስ ህግ ተገዥነትን ለማሳደግ፣ የኦዲት ሂደቱን ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲሁም የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠናዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ ላይ የመነሻ ሰነድ ያቀረቡት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል እንደገለጹት፤ የኦዲት አሰራር ዋና ዓላማ ግብር ከፋዮች ህግን ጠብቀው እንዲሰሩ ለማስቻልና ክፍተቶችን በጋራ ለማረም እንጂ ጫና ለመፍጠር አይደለም ያሉ ሲሆን፤ በመነሻ ሰነዱ የኦዲት አሰራር ስርዓት እና ደረጃዎች፣ኦዲት የሚከናወንበት ግልጽ አሰራር፣ ቅድመ-ኦዲት ዝግጅት ፣ድርጅቶች ኦዲት ከመጀመሩ በፊት ማድረግ የሚገቧቸው ቅድመ ዝግጅቶች፣ መቅረብ የሚገባቸው ሰነዶች ፣የደረሰኝ ህጋዊነት እና ተያያዥ ማስረጃዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረብ ያለባቸው ሰለመሆኑ ፣የኦዲት ግኝት (Audit Findings) እና ምላሽ፡ በኦዲት ሂደት የሚወጡ ግኝቶች ለግብር ከፋዩ የሚገለጽበትና ድርጅቶችም የራሳቸውን ማብራሪያና ማስረጃ የሚያቀርቡበት ህጋዊ አሰራር የሚሉት በቀረበው ሰነድ በስፋት ከተዳሰሱ ነጥቦች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የውይይት መድረኩን በጋራ የመሩት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሮዛ ጀማል እና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ በላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለይም ከተሳታፊዎች ከኦዲት ግኝቶች አወሳሰን፣ ከሰነድ አቀራረብ፣ ከውሳኔ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፤ ከአመራሮቹ ለአሰራር ግልጽነት ቅድሚያ እንደሚሰጥና የሚነሱ ክፍተቶች በመሙላት ለግብር ከፋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ በትኩረት እየተሰራ ያለ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጻል።

በመጨረሻም ወ/ሮ ሮዛ ጀማል ባቀረቡት የማጠቃለያ ሀሳብ፤ ግብር ከፋዮች አስፈላጊውን ሰነድ በወቅቱ በማቅረብና ግልጽ አሰራርን በመከተል ለኦዲት ስራው ስኬት ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ግብር÷ ለሃገር ክብር!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-MTO2
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል ላይ እንገኛለን

Address

Road From Mexico To Kera Street Kassa Grand Mall
Addis Ababa
5:00PM

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share