22/01/2025
በከተማ አስተዳዳሩ የተቋቋመ የሱፐርቪዥን ኮሚቴ በክ/ከተማው ምልከታ ማድረግ ጀመረ
ላፍቶ፣ ታህሳስ 24(2017)፦በከተማ አስተዳዳሩ የተቋቋመ የሱፐርቪዥን ኮሚቴ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምልከታ ማድረግ ጀምሯል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ኦረንቴሽን በመስጠት ስራውን የጀመረ ሲሆን የውስጠ ፓርቲ ስራዎችን አስመልክቶ በተመረጡ የመንግስት ሴክተሮች እና በ3 ወረዳዎች ላይ ሱፐርቪዥኑን ያካሂዳል።
የትኩረት መስኮችም ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ ፣ በቅሬታ አፈታትና በመረጃ አያያዝ እንዲሁም በሰው ተኮር ተግባራት፣ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ስራዎች የሚታዩ ናቸው።
በተጨማሪም በሪፖርት አቀራረብ ስራ በአግባቡ ከመገምገምና የግንኙነት ጊዜን አስጠብቅ ተቋም ፈጥሮ ከመሄድ አንጻር በ6 ወራት አፈጻጸም ላይ ምልከታ ይደረጋል።