ARADA Sub city Woreda five Communication

ARADA Sub city Woreda five Communication PROSPERITY PARTY is striving for ALL Ethiopians prosperity በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

21/07/2023
13/11/2022

 Messages from the main demonstrators of Addis Ababa  (Mesquel  Square)  TPLF is the Cause!  Respect Our Sovereignty!...
22/10/2022


Messages from the main demonstrators of Addis Ababa (Mesquel Square)
 TPLF is the Cause!
 Respect Our Sovereignty!
 For Sustainable Peace, Disarm TPLF!
 TPLF is a Trojan Horse!
 No two Parallel Armies in a Sovereign State!
ወዳጀ ኢትዮጵያ እስከሽበት ሽምግልና በሀላፊነት የምትጠበቅ በህይዎት መስዕዋትነት የፀናች የብዙሀን ሀገር ነች!!!!!
በማንም የአዳራሽ ድንፋታ አትፈርስም ልኡላዊ ክብሯም አይደፈርም::
🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️

16/10/2022

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም “ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ለሰንደቅ ዓላማ በሚሰጡት ክብር ይገልፃል፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ሰንደቅ ዓላማ ትልቅ ስፍራ ያለው ነው፤ ለሰንደቅ ዓላማ የምንሰጠው ክብርና ፍቅር ከእናት አባቶቻችን በክብር ወርሰን በክብር ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው በልባችን ውስጥ ታትሞ የሚቆይ የብዝሃነታችን፣ የአንድነታችንና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ እሴት ነው፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን የመስዋዕትነት፣ የሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት፣ የስነ-ልቦና፣ የፖለቲካ ታሪክ፣ የአብሮነትና የብሔራዊ መግባባት መገለጫ አርማ ምልክታችን በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት፤ የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ አለበት።

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል፡፡

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በተለያየ መልኩ በየዓመቱ እየተከበረ አስራ አራት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በያዝነው ዘንድሮ ዓመትም “ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!” በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በዋጀ ለ15ኛ ጊዜ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም በፌደራል፣ በክልሎችና በሁለቱም የከተማ አስተዳደር ከተሞች ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር ተገናዝቦና ሀገራዊ ሪፎርሙን በሚያስቀጥሉ ውይይቶች ታጅቦ በየተቋማቱ ይከበራል፡፡

የውስጥ ቅጥረኛ ተላላኪዎቻቸውን ይዘው በቅርብም ከሩቅም ያሉ የውጭ ጠላቶቻችን አቅደውና ተናበው ብሔራዊ አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ ለመጣል እየሰሩ ባሉበት በዚህ ወቅት የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበሩ ለሕብረብሄራዊ አንድነታችን መጠናከር፣ ለሉዓላዊነታችን መከበርና ይበልጥ ብሔራዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ትልቅ ትርጉም የሚኖረው ሲሆን ለሀገር ክብርና ጥቅም ሁላችንም እንደዜጋ የበኩላችንን ለመወጣት በሰንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ዕለት ይሆናል፡፡

ስለሆነም የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በዓሉ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት በመላው ሀገሪቱ የሚከበር ሲሆን በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ሰንደቅ ዓለማ በመስቀልና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም ስነ-ስርዓት እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ይሆናል፡፡

12/10/2022

ደማችን ለሉዓላዊነታችን፣ ላባችን ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን !!

አባት እናቶቻችን ክብር ይግባቸውና አንገታችንን ቀና አድርገን የምንራመድና ስሟን ስንጠራት ኩራት የሚሰማን ነፃና ኩሩ ሀገር በደም መስዋዕትነታቸው አውርሰውናል።

በጥቁሮችና በጭቁኖች ላይ የተቃጣውን ኢ-ፍትሀዊነትን ድል አድርገን ሰው የመሆንን እኩልነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያረጋገጥንበት አኩሪ ታሪካችን ዛሬም የተፈጥሮ ሀብታችንን እንዳንጠቀምና ሁሌም በድህነት እንድንኖር የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን በተላላኪ አሸባሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ የተከፈተብንን ጦርነት በመመከት ቀጥለናል።

ነፃነታችንን በደማችን ተጎናፅፈን እኩል መሆናችንን ብናረጋግጥም የድህነትን ጦር ባለመስበራችን "ከዓለም ጭራ" ጎራ መመደባችን ደግሞ በተለይም የዚህ ትውልድ ትልቅ ቁጭት ነው። ታፍራና ተከብራ የኖረች ታላቅ ሀገር እንዳለችን ስንናገር በስንዴ እርዳታ እንደምትኖር በማስታወስ የሚያሸማቅቁን ብዙ ናቸው።

ይህ ትውልድ አስከፊውንና አሳፋሪውን ድህነት ታሪክ ለማድረግ በምንም በማንም ማሳበብ አይበጀውም፤ በተፈጥሮም ቢሆን፣ በዝናብ እጥረት ችግር በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸው አካባቢዎች ጭምር ለም መሬት ያለን በመሆኑ እና ወንዞቻችን በመጠቀም ከክረምቱ አልፎ በበጋም በስንዴና በሌሎች ሰብሎች ገፅታቸው እየተቀየረ እያየን ነውና።

ብልፅግና ነገ የምንደርስበት ብቻ ሳይሆን ዛሬም እውን እያደረግነው ያለ ሀቅ መሆኑን በስንዴ ምርታችን ብቻ እየታየ ያለውን እመርታ መመልከት በቂ ነው። ትናንት ስንዴ ለመግዛት አቅም አልነበረንም፤ ትናንት የስንዴ እርዳታ ለማግኘት ለጋሾች በሚያስቀምጡት ቅድመ ሁኔታ ተቸግረናል፤ ዛሬ ደግሞ ስንዴን ከእራሳችን አልፈን ለሌሎች ሀገሮችም ለማቅረብ እየተንደረደርን ነው።

በባለፈው በጀት አመት ከ60 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ አምርተን ዘንድሮ ደግሞ ከ100 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚገመት ምርት ለመሰብሰብ መዘጋጀታችን ከራሳችን አልፈን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የያዝነው የብልፅግና ውጥን መቃረቡን ሁሉም ይረዳዋል።

ለሀገሩ ሉአላዊነት ደሙን ከመስጠት ወደ ኋላ የማይል ህዝብ ካሳፋሪው ድህነት ለመውጣት ላቡን ጠብ አድርጎ ለመስራት የሚበግረው ፈተና ሊኖር አይገባም። ስለዚህ በደማችን ሉዓላዊነታችንን በማስከበር በላባችን ደግሞ ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ እንትጋ።

Addis Ababa Prosperity Party Youth's - ብልፅግና

 🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️
12/09/2022

🇪🇹❤️🇪🇹❤️🇪🇹❤️

20/02/2022
17/02/2022

የለውጥ አመራር ትርጉምን ጥርት ባለ ተግባር አሳይተውናል የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት የሆኑት ክቡር ሙስጠፌ ኡመር! ያለፉትን አመታት የሚያስተዳድሩትን ክልል 100% ሰላሙን ያረጋገጡ ጀግና የኢትዮጵያ ልጅ!

17/02/2022

"እጄ እንደተቆረጠ አላስብም፤ ሙሉ እንደሆንኩ ነው የማስበው!" - ኮሎኔል ሁሴን አህመድ

ኢትዮጵያን የሚመስል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ኢትዮጵያውያን የአብራካቸውን ክፋይ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የአንደኛ ደረጃ የምርጥ አዋጊ እና ተዋጊ የወርቅ ሜዳይ ተሸላሚ ኮለኔል ሁሴን አህመድ ገለፁ፡፡

ኮለኔል ሁሴን አህመድ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለማጠናከር ወላጆች ልጆቻቸውን መርቀው ወደ ሀገር መከላከያ ሰራዊት መላክ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያን የሚመስል ሰራዊት ለመገንባት ብሄር ብሄረሰቦች የአብራካቸውን ክፋይ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ የማድረግ ሀገራዊ ግዴታ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አለኝ ያሉት ኮሎኔሉ፤ ‹‹ውትድርና ቅብብሎሽ ሥራ ነው፡፡ እኔ በግሌ 31 ዓመት ለሀገሬ ኢትዮጵያ በውትድርና አገልግዬ ቦርድ እየወጣሁ ነው፡፡ የእኛ ተተኪ ያስፈልጋል፡፡ ሰራዊታችን ተተኪ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ ህዝቡ ልጆቹን መርቆ መላክ አለበት›› ብለዋል፡፡

እንደ ኮሎኔሉ ገለፃ፤ ውትድርና በግዳጅ ሊሆን የማይሆንና ይልቁንም ለሀገር ሠላምና አንድነት ሲባል የሚገባበት ክብር ያለው ሙያ ነው፡፡ በዚህ ክቡር ሙያ ላይ መሰማራት ደግሞ ለሀገርም ለወገንም የሚያኮራ ነው።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሀገርና ወግንን የሚያኮራ ጠንካራ ሰራዊት እየገነባች ነው፡፡ እየተገነባ ያለው ሰራዊት ህዝቡ የሚተማመንበትና የሚኮራበት እንዲሆን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለው ኢትዮጵያዊ መከላከያ ሰራዊትን ሊቀላቀል ይገባል፡፡

ልማት የሚቀጥለው ሠላም ሲኖር ነው ያሉት ኮሎኔሉ፤ ‹‹ሠላም ባለመኖሩ የተፈጠረውን ክፍተት እየተመለከትን ነው፤ ከተሞችም ወድመዋል፤ የልማት ስራዎች ተቋርጠዋል፡፡ ስለዚህ የደፈረሰው ስላማችንን ለመመለስ ህዝቡ ሰራዊቱን በመደገፍ እና አካባቢውን በማልማት ንቁ ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል›› ብለዋል።

አሸባሪውን ህወሓት በመፋለም ላይ ሳሉ እጃቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ኮለኔል ሁሴን፤ ‹‹እጄ እንደተቆረጠ አላስብም፤ ሙሉ እንደሆንኩ ነው የማስበው፡፡ የሰው ልጅ እግሩ ወይንም እጁ አሊያም ዓይኑ ሊጠፋ ይችላል።

ነገር ግን ከእኛ መጥፋት የሌለበት ህሊናችን ነው፡፡ የምናስብበት አዕምሮ ነው መኖር ያለበት፡፡ አዕምሯችን እስከሠራ ድረስ ማንኛውንም ነገር መሥራት እንችላለን፡፡ በሕይወት መትረፌ በራሱ ዕድለኝነት ነው፡፡

ሊያቆስለኝ ሳይሆን ሊገለኝ የመጣ መሳሪያ ነበር፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ተረፍኩኝ፡፡ እጄ ስለተቆረጠ ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር አይሰማኝም፡፡ ውስጤ እጅግ ደስተኛ ነው፡፡ አዕምሮዬ የሚያስበውና ይከፋኝ የነበረው ለሀገሬ አስተዋፅኦ ባላደርግ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ባልሳተፍ ኖሮ መኖር አልችልም፡፡ ያመኛል፡፡ አሁን ግን የምችለውን አድርጌ ስለሆነ ውስጤ ደስተኛ ነው›› ብለዋል፡፡

ኮለኔል ሁሴን አህመድ ለፈጸሙት ጀብድ፤ የደቡብ ዕዝ ‹‹ጥሩ አዋጊ እና ተዋጊ አንደኛ ደረጃ የወርቅ ሜዳሊያ›› እንዳበረከተላቸው ይታወቃል፡፡

#ኢፕድ

Address

Piasa
Addis Ababa

Telephone

+251918721879

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ARADA Sub city Woreda five Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ARADA Sub city Woreda five Communication:

Share