Arada Werda 7 Trade Office

Arada Werda 7 Trade Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arada Werda 7 Trade Office, Government Organization, Addis Ababa.

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት ለወረዳው ነጋዴዎች በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/06 ስልጠና እና በአዲስ መልክ የነጋዴ ፎርም ማደራጀት መድረክ በቀን 6/9/2011ዓ...
14/05/2019

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት ለወረዳው ነጋዴዎች በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/06 ስልጠና እና በአዲስ መልክ የነጋዴ ፎርም ማደራጀት መድረክ በቀን 6/9/2011ዓ.ም ተካሄደ።

ከእንግዲህ አትክልት ለማልማት ቦታ የለኝም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውምበእቃ ላይ አትክልትን ማልማት
10/01/2018

ከእንግዲህ አትክልት ለማልማት ቦታ የለኝም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም

በእቃ ላይ አትክልትን ማልማት

10/01/2018

ኑኑኑ… አብረን አንስራ!!!

ከእንግዲህ አትክልት ለማልማት ቦታ የለኝም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡

የወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት ከተማ ግብርና ቡድን መሪ
011-1-22-28-09

10/01/2018

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት ከተማ ግብርና ቡድን መሪ

ስለ እብድ ውሻ በሽታ ይህንን ያውቃሉ?

ውሻውን የሚያሳብድ በሽታ የእንሳሳትና የሰውን የመልዕክት ማስተላለፊያ ነርቮችን፤ አንጎልንነና ጡንቻዎችን በማደንዘዝ የሚያጠቃና ህልናን ሰውሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወትን ልያጠፋ የሚችል አደገኛና አሰቃቂ በሽታ ሲሆን የያዘውን ሁሉ መቶ ፐርሰንት የሚገድል በሽታ ነው፡፡ የበሽታው አምጪ ቫይረስ በንክሻ በመቧጠጥ ወይም ክፍት የሆነን ቆዳ በመላስና ባልተጎዳ ሚዩከስ መምብሬን ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ የሚራባው አካባቢው ባሉ የሰውነት ክፍሎች ጡንቻዎችና በነርቭ ሴሎች ውስጥ ሲሆን ከዚያም ወደ ነርቮች ውስጥ በመግባት ጉዞውን ወደ አንጎል በመቀጠል የአንጎልን ስር ያጠቃል፡፡ አንጎል ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ከተራባ በኋላ በነርቮች አማካኝነት ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨትና በተለይም በምራቅ እጥዎቸወ ውስጥ በመጠራቀም በንክሻ አማካኝነት በቀላሉ የሚተላለፍ አደገኛና ገዳይ በሽታ ነው፡፡

የአብድ ዉሻ በሽታ ከአደገኛነቱ ባሻር ለመቆጣጠር ብዙም የማይከብድ በሽታ ሆኖ በአፍሪካ መዲናቸን በምናሞካሻት በአዲስ አበባቸን ጭምር ዋነኛ የጢና ጠንቅ መሆኑ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ የተጠናከረ የበሽታ ቁጥጥረ ስራዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉዳዩ ትኩረት ስጥቶት እያረገ ያለወን እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በሽታዉን ከነአካቲዉ
ከከተማይቱ ለማጥፋት ይቻል ዘንድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርቦሽ ያስፈልጋል፡፡

በሽታዉን ለመቆጣጠር ምን መደረግ አለበት?

በሀገራችን ዉሻን የሚያሳብድ በሽታን ወደ ሰዉ በማስተላለፍ ከሚታወቁት 95 በመቶ የሚሆኑት ዉሾች ናቸዉ ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመፍትሂ ሀሳቦች ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ፡፡
1 የእብድ ዉሻ በሽታን ለመቆጣጠር ዉሾችን ለመመዝገብ የሚያስችል የተጠናከረ ደንብ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፤
2 ሰፊ የክትባት መርሀ ግብር በመዘርጋት የተመዘገቡት ዉሾችንና ድመቶች በሙሉ 80 በመቶ የሚሆኑትን እንዲከተቡ ማድረግ
3 ተልከስካሽ ዉሾችን ስርአት ባለዉ መልኩ ማስወገድ ፤
4 በቂ የበሽታ መመርመሪያ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፤
5 በበሽታዉ መለከፋቸዉ የተጠረጠሩ ዉሾችን ሊሎች እንሰሳት ለ10 ቀናት በማቆያ ክፍል ዉስጥ አስሮ መከታተልና የበሽታዉን ምልክት ባሳዩ እንሰሳት /ዉሾች/ የተነከሱትን ማስወገድ ፤
6 የተጠናከረ የበሽታ ቅኝትና አሰሳ በማከናወን
7 የዉሻ ባለቢቶች የባለቢትነት ግዲታቸዉን እንዲወጡ ማስተማር ፤
8 የሚመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች በሽታዉን መቆጣጠር ስለሚቻልባቸዉ ሁኔታወች የጋራምክክሮችን ማካሄድ ፤
9 ህብረተሰቡን በተለይም ደግሞ ታዳዲ ልጆችን በትምህርት ቤቶች አማካኝነት ስለ በሽታዉ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ማድረድ፡፡
10 በንክሻ ለሚጠቁ ሰዎችም አስቸኳይ የህክምና እርዳታ መስጠት የእንሰስት ጤና ጥበቃን በገጠርም በከተማም አጠናክሮ መተግበር ፤
11 ዉሾችን ማስከተብና ባለቤት አልባ ዉሾችን መቆጣጠር ፡፡\
12 በየክፍለ ከተማዉ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን በማማከርና የዉሾቻችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር በሽታዉ እንዳይከሰት ይረዳል ፤
13 የዱር ስጋ በል እንሰሳት የበሽታዉ ዋነኛ ምንጭ ስለሆኑ እነሱን ሊስቡ ከሚችሉ ድርጊቶች በተለይም ከጓሮ እርድ መቆጠብና ዉድቅዳቂ ተረፈ ስጋንም በአግባቡ መስወገድ ፡፡
14 የዱር እንሰሳትን ለሆቢ ለመዝናኛ ወዘተ በመኖሪያ ሰፈሮች ዉስጥ አለመያዥ ፡፡
15 በትምህረትቤቶች አካባቢም ሆነ በቤትዉስጥ ለህጻናት አስፈላጊዉን ትምህርት መስጠት ፡፡
16 የዉሾቻቸዉን ጤንነት በማይጠብቁ ግለሰቦች ላያ አግባብ ያለዉን ህጋዊ ሀላፊነትና ግዴታ መጣል ፡፡
17 የህክምና እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት፡፡

በአራዳ ክ/ከ  ወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት የHIV AIDS ሜኒስትሪሚንግ ኮሚቴ  ለ2ኛ ዙር ከሰራተኛው በሚሰበሰበው ገንዘብ መዋጮ ለወረዳው ተረጂ ህፃናት የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ እርዳ...
28/09/2017

በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 7 ንግድ ጽ/ቤት የHIV AIDS ሜኒስትሪሚንግ ኮሚቴ ለ2ኛ ዙር ከሰራተኛው በሚሰበሰበው ገንዘብ መዋጮ ለወረዳው ተረጂ ህፃናት የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ እርዳታ አደረገ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251111222809

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada Werda 7 Trade Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share