South omo zone Prosperity Party - የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ

South omo zone Prosperity Party - የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ይህ የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ አገልግሎት የፌስቡክ ገጽ ነው ።

ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን!ጳጉሜን የአስራ ሶስት ወር ፀጋ የሆነችው ሀገራችን በረከቶች፣ ከዘመን ዘመን መሸጋገሪያ ድልድል፣ የአዲስ ዓመት መዳረሻ ብሩህ ተስፋ አብሳሪ ተጨማሪ ቀናት እና ወር...
07/09/2026

ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን!

ጳጉሜን የአስራ ሶስት ወር ፀጋ የሆነችው ሀገራችን በረከቶች፣ ከዘመን ዘመን መሸጋገሪያ ድልድል፣ የአዲስ ዓመት መዳረሻ ብሩህ ተስፋ አብሳሪ ተጨማሪ ቀናት እና ወር ናት።

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት ጥንታዊት ሀገር መሆኗን ጠቋሚ ምልክቶች፣ የአዲስ ዓመት መዳረሻ ብስራት ናቸው የጳጉሜን ቀናት።

የጳጉሜን ቀናት ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የህዝባችንን ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በሚያጎለብቱ፣ የመጪውን አዲስ ዓመት ተስፋዎች በሚያንፀባርቁ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበሩ ቆይተዋል።

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናትም እንደ ሀገርም ሆነ በመዲናችን ለአዲስ ዓመት የላቁ ድሎች ተነሳሽነትን ከፍ በሚያደርግ መልኩ ‹‹ የኢትዮጵያ ማንሰራራት!›› በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ህዝባዊ ሁነቶች እየተከበሩ ይገኛሉ።

በተለወጠ አዲስ እሳቤ፣ በዳበረ የስራ ባህል የብልፅግና ፓርቲን አሻጋሪ እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም ኢትዮጵያን ከነበረችበት ጥልቅ ጉስቁልና በማውጣት ወደ ማንሰራራት ማሸጋገር ተችሏል፡፡

ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን በመተለም፣ ለዓለም አቀፍ ጫናዎች ያልተበገረ ዲፕሎማሲያዊ ድል በማስመዝገብ፣ ባለፈው ዓመት በተባበሩ እጆቻችን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዕውን ማድረግ መቻላችን ይታወሳል፡፡

እየተገነባ የሚገኘው ግዙፉ የማዳበሪያ ፋብሪካም ለምርትና ምርታማነት ማደግ በሚኖረው ጉልህ ሚና የምግብ ዋስትናችንን እና የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ርብርብ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡

የተገነቡ ግዙፍ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ማፋጠን ችለዋል፡፡

ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው የተገነቡ ጥራታቸውን የጠበቁ ግዙፍ መንገዶችም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን አሳልጠዋል፡፡

ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን የጳጉሜን ቀናት ስናከብርም፣ የመጪውን ጊዜ ተስፋ የሚያለመልሙ፣ የህዝባችንን ማህበራዊ መስተጋብር የሚያጠናክሩ፣ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ፅኑ መሰረት የሚሆኑ ስራዎችን በማከናወን ሊሆን ይገባል፡፡

በአዲሱ ዓመት በግለሰብ ደረጃም ሆነ በሀገራችን ለሚከናወኑ ተግባራት እንዲሁም ለሚመዘገቡ ድሎች ሙሉ ዝግጅትን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባትም ከሁላችንም ይጠበቃል።

"በአዲሱ ዓመት በአዲስ አስተሳሰብ፣ በተግባር አንድነት እና ፅናት ክልላችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር በትጋት እንሰራለን" ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ...
07/09/2026

"በአዲሱ ዓመት በአዲስ አስተሳሰብ፣ በተግባር አንድነት እና ፅናት ክልላችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር በትጋት እንሰራለን" ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በክልሉ መንግስት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም፤ በ2019 መሪ ዕቅድ እንዲሁም የቀጣይ 5 ዓመት ጠቋሚ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር የአመራር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ማጠቃለያ የክልሉ መንግስት በሁሉም ዘርፍ ዘላቂነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሰው በተለይም የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተረጋጋና ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የፈጠራቸው ዕድሎችን ተጠቅሞ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ተግባራት በቀኝ እጅ ተይዘው መመራታቸው ፣ በክልሉ ያለው አንፃራዊ ሰላም ክልሉን የብልፅግና ምሳሌ፣ ለኢንቨስትመንት በእጅጉ ተመራጭ ክልል እያደረገው እንደሚገኝ ጠቅሰው ይሄንን እድል ለመጠቀም ተግተቶ በመስራት የአባራ ሳይሆን የአሻራ ፖለቲካችንን ለማሳረፍ መስራት አለብን ብለዋል።

አመራሩ የውስጥ አንድነቱን በማጠናከር ፣ ለፈተና የማይበገር ፣ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በመላበስ የሚናገረውን የሚንተገብር የበለጠ ውጤት ለማምጣት ተግቶ የሚሰራ ልንሆን ይገባል ብለዋል።

በአዲሱ ዓመት ተደራራቢ የቤት ስራዎቻችን በመስራት፣ የባከነ ግዜን በማካካስ በጋራ ብዙ በመሮጥ ፣ ተለዋዋጭ ከሆነ የአለም ነባራዊ ሁኔታ አብሮ መጓዞ መቻል እና አቅሞቻችን ለመጠቀም ችግሮቻችንን ለመፍታት ወትሮ ዝግጁ በመሆን ሀገራችንን ብሎም ክልላችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር መትጋት ይገባል።

ለዘመናት ሲንኳባለሉ የመጡ ችግርች ፣ አሁን የተፈጠሩ እና ወደፊት የሚያገጥሙን ችግር ውጤታማ እንዳንሆን ሊፈትነን ይችላሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በመፍጠን ፣ በመፍጠር እና በመዝለል ችግሩን ለመሻገር መስራት ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።

በቀጣይ የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ ከራሳችንን ነባራዊ ሁኔታ ከልሰን የሰው ሀይል ምርታማነትን በመጨመር መስራት ፣ ወጪን በመቀነስ የገቢ አቅምን ማላቅ፣ ችግሮችን መቋቋም የሚችል ግብርና መፍጠር ፣ አምስቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩን አጠቃለዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር ) ባለፉት ሶስት አመታት የቆሙ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና አዳዲሶች በመጀመር ፕሮጀክት የመጨረስ እና የማስፈፀም ልምድ ያሳደግንበት ፣ በሰላም ዘርፍ፣ በኮሪደር ልማት ፣ በቱሪዝም፣ በአብዛኛው ዘርፎች በፈተናዎችን መሃል ሆነን እንኳን ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ብለዋል።

የተመጣጠነ ማስፈፀም አቅም ከመፍጠር አኳያ በታችኛው መዋቅር ያሉ ክፍተቶችን ማረም በአገልግሎት፣ በኢንዱስትሪ በግብርና ዘርፍ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን በማውጣት በማልማት ክልሉን ክፍ ወዳለ ደረጃ ለማሻገር በትኩረ እየተሰራ መሆንን ገልፀል ክልሉ ካለው ፀጋ እና አቅም አንፃር ብዙ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በቀጣይ ክልሉን ወደ ብልፅግና ለማሻገር የፓርቲን አቅም አሟጦ መጠቀም ፣ የአመራር የተግባር ውጤታማነት እና በተግባሮች ላይ የጣራ አመለካከት መያዝ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

‎አምባሳደር ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊዝም ቲም እና ግሎባል ኮሚሽን ፌሎሽፕ (GCF) ለ74 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በስጦታ አበረከተ*********‎‎ዲመካ፣ ጷጉሜ  2/2018 ...
07/09/2026

‎አምባሳደር ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊዝም ቲም እና ግሎባል ኮሚሽን ፌሎሽፕ (GCF) ለ74 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በስጦታ አበረከተ
*********

‎ዲመካ፣ ጷጉሜ 2/2018 ዓ/ም

‎ለ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ በተደረገ የትብብር ሥራ፣ ለ74 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በስጦታ መልክ ተበርክቷል።

‎ስጦታውን ያበረከቱት አምባሳደር ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊዝም ቲም እና ግሎባል ኮሚሽን ፌሎሽፕ (GCF) ከደቡብ ኦሞ ዞን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጋር በመተባበር በዲመካ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን መሆኑ ተገልጿል ።

‎በመርሃግብሩ የአምባሳደር ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊዝም ቲም ፕሬዚዳንት መጋቢ ቢንያም አበራ ከባለቤታቸው ጋር፣ የግሎባል ኮሚሽን ፌሎሽፕ (GCF) ፕሬዚዳንት መጋቢ ዶ/ር ወንድማገኝ አስፋው፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሰብሳቢ መጋቢ ታምሩ፣ እንዲሁም የዲመካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ ተገኝተዋል።

‎በስጦታ ርክክቡ ወቅት የአምባሳደር ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊዝም ቲም ፕሬዚዳንት መጋቢ ቢንያም አበራ ንግግር በማድረግ፣ ትምህርት የሕይወት ቁልፍ መሆኑንና ለተማሪዎች የሚደረግ ድጋፍ ለወደፊቱ ትውልድ ተስፋ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል።

‎“ዛሬ እዚህ የተገኘነው ቁሳቁስ ለማስረከብ ብቻ አይደለም፤ ተስፋን፣ ፍቅርንና ለነገ ትውልድ ያለንን እምነት ለመግለጽ ነው” ብለዋል።

‎የግሎባል ኮሚሽን ፌሎሽፕ (GCF) ፕሬዚዳንት መጋቢ ዶ/ር ወንድማገኝ አስፋውም በሰጡት ንግግር፣ ለተማሪዎች የሚደረግ ድጋፍ በነገው ትውልድ ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎“አንድ ተማሪን ስንደግፍ፣ አንድ ሕይወትን እናበረታታለን፤ አንድ ትውልድን ስናስተምር፣ የአገርን ወደፊት እንገነባለን!” በማለት ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎በተጨማሪም ተማሪዎች የዛሬ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የነገው የአገሪቱ መሪዎችና የማኅበረሰቡ ተስፋዎች መሆናቸውን በመግለጽ፣ በትጋት እንዲማሩ፣ ትልቅ ሕልም እንዲያልሙና ለማኅበረሰባቸው በረከት እንዲሆኑ አበረታተዋል።

‎ይህ የትብብር ተግባር ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረሰብ እና የአካባቢ አስተዳደር በጋራ በመሥራት ለሕጻናትና ለወጣቶች የተሻለ የትምህርት ዕድል ለመፍጠር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

‎“ለተማሪዎች የሚደረግ ድጋፍ ለነገ ትውልድ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው!”

ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕ...
07/09/2026

ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጳጉሜ 2  ... የማንሰራራት ቀን !! ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!
07/09/2026

ጳጉሜ 2 ... የማንሰራራት ቀን !!

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

07/09/2026
ሀገራዊ አቅም እና የኢትዮጵያ ከፍታየኢትዮጵያ ማንሰራራት ከውድቀት መነሳት ብቻ አይደለም፤ ለዘመናት ተጭኖ የነበረውን የተስፋ መቁረጥ እና የጥገኝነት ሥነልቦና ሰብሮ፣ የራስን እውነተኛ ብሔራዊ...
07/09/2026

ሀገራዊ አቅም እና የኢትዮጵያ ከፍታ

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ከውድቀት መነሳት ብቻ አይደለም፤ ለዘመናት ተጭኖ የነበረውን የተስፋ መቁረጥ እና የጥገኝነት ሥነልቦና ሰብሮ፣ የራስን እውነተኛ ብሔራዊ አቅም እና ከፍታ ማብሰር ነው።

ለዘመናት በዘለቀው የስጋት እና የእርዳታ ጥገኝነት አሠራር ምክንያት፣ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ታላቅ ተፈጥሯዊ ጸጋ አውጥተው ለመጠቀም እንዳይደፍሩ “አንችልም” በሚል ሥነልቦናዊ ሰንሰለት ታስረው ቆይተዋል።

የመደመር እሳቤ ግን ይህንን የተሳሳተ የታሪክ ትርክት በመቀየር ሀገር በቀል አቅምን ወደ ሁለንተናዊ ዕድገት ያሸጋገረ አዲስ የልማት እና የሉዓላዊነት ምዕራፍ ከፍቷል።

በታቀደላቸው ጊዜ ፕሮጀክቶችን አለማጠናቀቅ በቀደሙት ጊዜያት ብሔራዊ ስጋት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ይህ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተሰብሮ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ የታሪክ አዲስ ምዕራፍ መጻፍ ጀምራለች።

የዓለም አቀፍ ተቋማትን እጅ ሳትጠብቅ በዜጎቿ ወዝ እና የጋራ አስተዋጽኦ የተገነባው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እና የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ ብሔራዊ የኃይል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የትልቅ ማንሰራራት ህያው ምልክቶች ሆነዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍላጎትን ማሟላት ብቻ ሳይሆን፣ የቀጣናውን ሀገራት በኃይል በማስሳሰር የጋራ እድገትን እውን የሚያደርጉ ስትራቴጂካዊ ሀብቶች ናቸው።

ከኃይል ማመንጨት ጎን ለጎን፣ የአፍሪካ ትልቁ የመንገደኞች እና የካርጎ ማዕከል የሚሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እና የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማቶች መስፋፋት የኢትዮጵያን አህጉራዊ የትራንስፖርት የበላይነት ወደ አዲስ የልዕልና ማህተም ያሸጋገሩ ናቸው።

በተጨማሪም ለዘመናት በመሬት ስር ተቀብሮ የነበረውን ተፈጥሯዊ ሀብት አውጥቶ ማቀነባበር፣ የምግብ ዋስትናን በሀገር ውስጥ ምርት ማረጋገጥ እና የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን በሀገር ውስጥ የመገንባት ጥረት የውጭ ጥገኝነትን በማስቀረት ብሔራዊ የኢኮኖሚ ነፃነትን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው።

እነዚህ ግዙፍ ሥራዎች ሲከናወኑ ትልቁ የማንሰራራት ማረጋገጫ የግንባታዎቹ መጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎች እና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የተፈጠረው ጥልቅ እይታ ነው።

ኢትዮጵያ በገዛ ሀብቷ፣ በዕውቀቷ እና በሕዝቧ አስተዋጽኦ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ እንደምትችል በተግባር በማሳየት የጸና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር አድርጋለች።

ኢትዮጵያ የእርዳታ እጅ ዘርጊ ምሳሌ ከመሆን ወጥታ የራሷን የልማት እጣ ፈንታ በራሷ የምትወሰን የማይበገር የቀጣናው የኢኮኖሚ ሞተር መሆኗን አስመስክራለች።

"አይደፈርም" የሚለውን የተረጂነት እና የእንቅፋት አጥር መስበር ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ትልቁ ሀገራዊ የማንሰራራት ውርስ ነው።

የዛሬው ትውልድ ከትናንቱ የተስፋ መቁረጥ ጥላ ወጥቶ፣ በማንኛውም የልማት መስክ ላይ "እንችላለን" የሚል የጸና ሥነልቦናዊ እምነት እንዲላበስ ተደርጓል።

ይህ አዲስ አካሄድ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ከፍታ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያበስር ወርቃማ የማንሰራራት ምዕራፍ መሆኑን ያረጋገጠ ነው።


07/09/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የ 2018 ዕቅድ አፈፃፀምና የ 2019 ዕቅድ ክልላዊ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የ 2...
07/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የ 2018 ዕቅድ አፈፃፀምና የ 2019 ዕቅድ ክልላዊ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ 2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ ክልላዊ የአመራር ዉይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክልሉ መንግስት የ 2018 ዕቅድ አፈፃፀምና የ 2019 ጠቋሚ ዕቅድ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ በበጀት ዓመቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን በመፈተሽ ጥንካሬዎች የሚቀጥሉበት እንዲሁም የ 2019 የትኩረት አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በመድረኩ የ 2019 ዕቅድ ግብ ስምምነት፣ የዞኖችና ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች የምዘና ዉጤትና ዕዉቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

በመድረኩ የክልሉ መንግስት አስተባባሪ አካላት፣ የክልል ማዕከል አመራሮች፣ የዞኖችና ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች አስተባባሪ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

Address

Dimeka
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South omo zone Prosperity Party - የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share