Yeka Woreda 09 Prosperity Party ብልጽግና

Yeka Woreda 09 Prosperity Party ብልጽግና This page is yeka woreda-09 prosperity party media and communication official face book page

ጳጉሜን 2የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን  ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ጉዞ!​በባለፉት ዓመታት የተተገበሩት እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የገበታ ለሀገርና አረንጓዴ አሻራ ያሉ ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶ...
07/09/2026

ጳጉሜን 2
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ጉዞ!

​በባለፉት ዓመታት የተተገበሩት እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የገበታ ለሀገርና አረንጓዴ አሻራ ያሉ ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በአዲሷ አዲስ አበባ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት፣ የሰው ተኮር ፕሮጀክቶችና የዲጂታል አገልግሎቶች መስፋፋት ተስፋችንን ወደ ተጨባጭ እውነታ የለወጡ የታሪክ ማዕዘናት ናቸው።
#የካ

07/09/2026
ጳጉሜ 2የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ  ጉዞ!    #የካ
07/09/2026

ጳጉሜ 2
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ጉዞ!


#የካ

ጷጉሜ _1 የእመርታ ቀንን በደግነት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09  የጷጉሜን ወር ጷጉሜ 1 «የእመርታ ቀን» ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካ...
06/09/2026

ጷጉሜ _1 የእመርታ ቀንን በደግነት

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የጷጉሜን ወር ጷጉሜ 1 «የእመርታ ቀን» ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሂዷል ።

በበጎ አድራጎት እና በጋራ የመደጋገፍ እሴት ላይ ተመስርቶ በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር የላምበረትና አካባቢው ለወገን ደራሽ ድርጅት ከሀገር ውጭ ከሀገር ውስጥ ካሉ በጎፍቃደኞች ሀብት በማሰባሰብ አቅመ-ደካሞች፣ አረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ነበተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ እንዲህ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በመርሀግብሩ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሱባለው መንደዶ፣የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቲ ታሪኩ አለማየሁና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ መገርሳ ተገኝተዋል።

06/09/2026
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሰንበት ገበያ የምርት አቅርቦት የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል በትኩረት እየሰራ ነው። በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የኅብረተሰቡን የእለት ተእለት የኑሮ ጫና ለማቃለል...
05/09/2026

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሰንበት ገበያ የምርት አቅርቦት የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል በትኩረት እየሰራ ነው።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የኅብረተሰቡን የእለት ተእለት የኑሮ ጫና ለማቃለልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለመ የሰንበት ገበያ የምርት አቅርቦት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው የሰንበት ገበያ ላይ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ እህልና የእንስሳት ተዋጽኦ ውጤቶች በስፋት ለህብረተሰቡ የቀረቡ ሲሆን፤ ምርቶቹ ከአምራቾችና ከዩኒየኖች በቀጥታ የቀረቡ በመሆናቸው ከነጻ ገበያው በወረደ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማች የቀረቡ ናቸው።

የወረዳው ነዋሪዎች የሚቀርቡት የምርት አይነቶችና የዋጋ ልዩነቶች እፎይታ እንደሰጧቸው ጠቅሰው፤ የሰንበት ገበያው በቋሚነት፣ በበቂ መጠንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

woreda9 prosperity

የኢትዮጵያ ማንሰራራት፤ ከጽናት ወደ ላቀ የልዕልና ምዕራፍ! ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሟትን በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች በጽናት አልፋ፣ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ...
04/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት፤ ከጽናት ወደ ላቀ የልዕልና ምዕራፍ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሟትን በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች በጽናት አልፋ፣ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማኅበራዊ ዘርፎች ተጨባጭ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችላለች። የትናንት ድሎቻችን የጽናታችን ማሳያ ሲሆኑ፣ የዛሬው ጥረታችን ደግሞ ነገን በጽኑ መሠረት ላይ የመገንባት አቅም ፈጥሮልናል።

ይህ የጳጉሜን ወቅት የነበሩንን ጉድለቶች በመገምገም፣ ያመጣናቸውን ስኬቶችና ያሉንን ሀብቶች ፈትሸን ወደ ላቀ የልዕልና ምዕራፍ የምንሸጋገርበት የቁርጠኝነት ጊዜ ነው።​የዘመኑ የጳጉሜን አከባበር ሀገራችን 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት አጠናቅቃ፣ በህዝብ ሙሉ ድምፅ እውቅና ያገኘው ፓርቲ የህዝቡን አደራ በታማኝነት ለመፈጸም በተዘጋጀበት እና ሀገራዊ የምክክር መድረኩ በተሳካ ሁኔታ በተጠናቀቀበት ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል።

ይህ ታሪካዊ ክስተት የዲሞክራሲ ስርዓታችንን ከማጠናከሩ ባሻገር፣ በህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት እና የጋራ ራዕይ ይበልጥ ያጠናከረ የምስራችና የአዲስ ተስፋ ማብሰሪያ ነው።​የዘመኑ የጳጉሜን በዓል የኢትዮጵያን የብልፅግና ራእይ በሚያበስርና በሽግግር ምዕራፉ ላይ ያለንን ሀገራዊ ልዕልና በሚያጎላ መልኩ "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ዋና መሪ ቃል ይከበራል።

በመሆኑም እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን ይህንኑ የማንሰራራትና ልዕልና መልእክት የሚያንጸባርቅ በመሆኑ፣ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዮጵያን ወደ ተመኘናት የከፍታ ማማ ከፍ ልናደርጋት ይገባል።

በዚህም መሰረት፦

​ጳጉሜን 1፦ የእመርታ ቀን
​ጳጉሜን 2፦ የማንሰራራት ቀን
​ጳጉሜን 3፦ የጽናት ቀን
​ጳጉሜን 4፦ የኃብር ቀን
​ጳጉሜን 5፦ የነገ ቀን

​በማለት የተሰየሙ ሲሆን በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ይከበራሉ።
#የካ

ከተሜነት! የዘመናዊነት መገላጫ፣ የመልካም መስተጋብር ማሳያ ነው!የሀገራት ዕድገት ነፀብራቅ፣ የዘመናዊ ስልጣኔዎች ምልክት የሆኑት፣ ሰፊ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች የሚታዩባቸው ...
03/09/2026

ከተሜነት! የዘመናዊነት መገላጫ፣ የመልካም መስተጋብር ማሳያ ነው!

የሀገራት ዕድገት ነፀብራቅ፣ የዘመናዊ ስልጣኔዎች ምልክት የሆኑት፣ ሰፊ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች የሚታዩባቸው ከተሞች ዘመኑ በደረሰባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ውድድራቸውን አጠናክረዋል፡፡

ከተሞች ለሰው ልጅ አካላዊ፣ አእምሯዊና መንፈሳዊ ጤንነቱ ተጠብቆ አምራችነቱ እንዲያድግ ማኅበራዊ መስተጋብሩን ያጠብቃሉ፡፡ ከተሜነት የሰው ልጅ የብልጽግና መዳረሻ ነው ብንል ገሀዳዊውን ዓለም ምስክራችን አድርገን ነው።

የሰው ልጅን ድካም ለሚቀንሱ፣ ምርታማነትን ለሚያሳድጉ የግብአትና የክሂሎት አቅርቦትና ተደጋጋፊነት ከተሞች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዴሞክራሲያዊ ለውጦችን ለማሳካትም ከተሞች ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተሰጠውን የመመራመርና የመጠየቅ ስጦታ ተጠቅሞ አዳዲስ ፈጠራዎችንና ሐሳቦችን ለማፍለቅ ከተሞች አስቻይ ሁኔታፈጥረዋል፡፡

ከተማ ማኅበረሰባዊ፣ አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እርስ በእርስ ያላቸውን መስተጋብር የሚያቅፍ በመሆኑ ብዝሀ መልክ ያለው ነው፡፡ በዲፕሎማሲውም ቢሆን የከተሞች ሚና ቀላል አይደለም፡፡ አንዳንዴ ሞስኮ እንዲህ አለች፣ ዋሽንግተን እንዲህ አለች ወዘተ የሚባለው በተለይም ዋና ከተሞች ሀገራቱን ለመግለፅ ጭምር አቅም ስላላቸው ነው፡፡

የአፍሪካ መዲና፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መናኸሪያ የሆነችው አዲስ አበባም በተለይም ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የስዕበት ማዕከል በመሆን የተፅዕኖ አድማሷን አሳድጋለች፡፡

ከተማ የሰው ልጅ ዘመናዊነት መነሻም፤ መገለጫም ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የከተሞች ጉስቁልና የሀገራትን ገፅታ በእጅጉ ይጎዳዋል፡፡ ለአብነትም በድህነት ማጣቀሻነት ስሟ ሲነሳ ለነበረው ኢትዮጵያ በከተማችን የነበረው አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ጥልቅ ጉስቁልና ትልቅ ሚና ነበረው፡፡

በተለወጠ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ አበባን ውብ አበባ ለማድረግ እየተደረገ ባለው ርብርብ የመጣው አንፀባራቂ ስኬት የኢትዮጵያን ተምሳሌታዊ ጊዞ በማጠናከር ገፅታዋንም እየገነባ ይገኛል፡፡ የህዝባችን መስተጋብር እየተጠናከረ መምጣቱም ለጋራ ነጋችን ምቹ መደላድል ፈጥሯል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት


መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተ።በየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ  "መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ...
03/09/2026

መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተ።

በየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ "መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ የበዓል ባዛር ተከፍቷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ግዛው ባዛሩ ሻጮችንና ሸማቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ የግብይት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ውጤታማና አጥጋቢ የግብይት ሥርዓት እንዲሰፍን የሁሉም አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ዶ/ር ኤፍሬም ባዛሩ በሰላማዊና ሥርዓት በተሞላበት መልኩ እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው፣ ባዛሩ ለነዋሪዎችና ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት የሚያግዝ፣ የግብይት ሥርዓቱን የሚያሻሽልና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

የባዛሩ ዓላማ በሸማቾች እና በአምራቾች መካከል ቀጥተኛ የግብይት ሥርዓትን በማጠናከር የምርት አቅርቦትን ማሳደግና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰቡ ማቅረብ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንዳልካቸው፣ ለባዛሩ ስኬታማ አፈጻጸም የተረባረቡ አካላትን በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

ባዛሩ በቀጣይም በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር እንዲጠናከር አስፈላጊው ሥራ በየደረጃው መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የተከፈተው የበዓል ባዛር እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማው ንግድ፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ህብረት ሥራ፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና እንዲሁም ሥራና ክህሎት ተቋማት በጋራ በመሆን የባዛሩን አገልግሎት እያስተባበሩ ይገኛሉ።
#የካ

Address

Asmera Street
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka Woreda 09 Prosperity Party ብልጽግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share