ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!
(2)

ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሠላም ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገለፁ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
09/09/2026

ዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሠላም ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገለፁ ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮ/ር ሀብታሙ አሠፋ እንደገለጹት፣ አዲሱ ዓመት ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም እንዲከበር ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ገልጿል ።

ህብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት የበኩሉን ጥንቃቄና ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ ምክንያት የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ባዕድ ነገር ቀላቅለው በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዉ ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በገበያ አካባቢዎች ከፍተኛ የሰው ፍሰት ስለሚኖር ማህበረሰቡ ራሱን ከሌቦችና ኪስ አውላቂዎች እንድሁም ሎተሪ ደርሰውኛል ግን ለከተማው አድስ ነኝ እያሉ ከሚያታለሉ ግለሰቦች እንዲጠብቁ አሳስበዋል ።

የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት የጸጥታ አካላትና ትራፊክ ፖሊሶች ከወትሮው በተለየ መልኩ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋሉ ተብለዋል ።

በበዓሉ አከባበር ወቅት የእሳት አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ መደረግ አለበት ተብሏል ።

ኮ/ር ሀብታሙ አሠፋ የ2019 አዲስ ዓመት ለመላው የከተማ ህዝብ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ማንኛውንም ዓይነት የጸጥታ ስጋትና ጥቆማ ሲኖር በከተማዉ ፖሊስ መረጃ ስልክ ቁጥር 0465510146 እና በነፃ ስልክ ቁጥር 6793 ላይ በመደወል ማሳወቅ ይቻላል።

🌼 እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🌼

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 3 ቀን "የጽናት ቀን" በተለያዩ ሀገራዊና አካባቢያዊ መፈክሮች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ።
08/09/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 3 ቀን "የጽናት ቀን" በተለያዩ ሀገራዊና አካባቢያዊ መፈክሮች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ።

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።(ወላይ...
05/09/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
(ወላይታ ሶዶ ፖሊስ መምሪያ፤ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም)

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እና በክፍለ ከተማ ፖሊስ አባላትና አመራሮች ደረጃ ለተከታታይ ቀናት በስፋትና በጥልቀት ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በዚህ የማጠቃለያ መድረክ ላይ የሕዝብ አመኔታን ይበልጥ ለማሳደግና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚያስችሉ አበይት ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን፥ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ጉራማይሌን ጨምሮ የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።

በማጠቃለያ መድረክ ላይ የፖሊስ መምሪያው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ በተግባር የተመዘገቡ ውጤቶች፣ በሂደት ላይ የታዩ ተግዳሮቶችና ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ አንኳር ሥራዎች ዙሪያ ሰፊና ግልጽ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የተካሄደው ግምገማ በተለይም ከአመለካከትና ከተግባር አኳያ፣ ከሥራ አፈጻጸምና ከሙያዊ ሥነ-ምግባር አንፃር እንዲሁም የዜጎችን ሰብዓዊ መብት በአግባቡ ከማክበርና ከማስከበር አኳያ በጥልቀት ተፈትሿል።

በዚህም የተሻለና ቀልጣፋ የፖሊስ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠትና የሕዝብ አመኔታን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ጠንካራ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በንግግራቸው የፖሊስ ተቋም የሕግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ ግንባር ቀደም ተዋናይ እንደመሆኑ መጠን ለሕዝብ የሚሰጠው አገልግሎት ምንጊዜም ከከፍተኛ ሥነ-ምግባር፣ ከተጠያቂነትና ከላቀ ሙያዊ ግዴታ ጋር የተቆራኘ መሆን እንዳለበት በፅኑ አሳስበዋል።

ወ/ሮ እታገኝ አክለውም፣ እስካሁን የተገኙ በጎ ውጤቶችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው፥ በግምገማው ላይ በግልጽ የወጡ ክፍተቶችን በቀጣይ በተግባራዊ ዕቅድ በመሙላት ለሕዝብ የሚሰጠውን የፖሊስ አገልግሎት ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሻሻልና መለወጥ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ጉራማይሌ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የወንጀል መከላከል ሥራ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ጠንካራ የሕዝብ መሠረትና ተሳትፎ እንዲኖረው ማድረግ ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከርና የሕዝብን ሰላም በዘላቂነት በማረጋገጥ ረገድ እያንዳንዱ የፖሊስ አባልና አመራር የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም ቀጥሏል!በመምሪያው እና በክፍለ ከተማው አባላትና አመራሮች የሥራ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደ...
04/09/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም ቀጥሏል!

በመምሪያው እና በክፍለ ከተማው አባላትና አመራሮች የሥራ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ፣ ግልጽና ጠንካራ የውስጥ ህስ-ግል ህስ ግምገማ እየተደረገ ይገኛል።

ይህ መድረክ ባለፉት የሥራ ጊዜያት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር በመለየት፣ በቀጣይ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ ነው።

ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ይህ ግምገማ፣ የፖሊስን ወቅታዊ ዝግጁነትና ቁመና ለመለካት እንዲሁም ለሕዝብ አገልግሎት ያለውን ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ እገዛ ያደረጋል ተብሎ ይገመታ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏል።የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላ...
03/09/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ፣ የመምሪያው እና የክፍለ ከተማዉ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር በመለየት ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት የሁለተኛ ቀን ያደረገው መድረኩ፣ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት ያለበትን ዝግጁነትና ቁመና ለመለካት ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል።

በህብረተሰቡ ዘንድ በፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በመልካም አስተዳደርና ፍትህን በማስፈን ረገድ የሚነሱ ቅሬታዎችን በዝርዝር በመለየት የነበሩ ክፍተቶችን ለማረም ውይይት ተደርጓል።

መድረኩ የነበሩ ደካማ ጎኖችን በማረም፣ በአዲሱ በጀት ዓመት የማህበረሰቡን የአገልግሎት እርካታ ለማሳደግና የፖሊስን ስራ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ፨፥፥፥፥፥፥፦፦፦፦፦፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፨ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ  ማህበራዊ ሳይንስ ቤተ...
03/09/2026

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
፨፥፥፥፥፥፥፦፦፦፦፦፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፨
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ማህበራዊ ሳይንስ ቤተ-መጽሐፍት ሕንጻ ላይ ዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የእሳት አደጋው ከተከሰተበት ሰዓት ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሶዶ ከተማና የዞን አስተዳደር አካላት እንዲሁም የግል ድርጅቶች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብና ብርቱ ትግል እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር እንዲውል አጋርነታቸውን ላሳዩና ሁለንተናዊ ትብብር ላደረጉ መላው አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን አቅርቧል።

እስካሁን የአደጋው መንስዔና የደረሰው የጉዳት መጠን በትክክል ያልታወቀ ሲሆን፣ በሚመለከተው አካል ተጣርተው ሲጠናቀቅ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስተዳደሩ አስታውቋል።

ዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ወላይታ ሶዶ  ፖሊስ መምሪያ (ነሐሴ 27/2018...
02/09/2026

ዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወላይታ ሶዶ ፖሊስ መምሪያ (ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም)

የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስ/ር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ግምገማ በሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ የዎላይታ ከተማ አስ/ር ም/ካንቲባ መንግስቱ ትግሮ ፣የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽኔር እና የምርመራ ዘርፍ ኮ/ር ጉራማይለ ጉርኦ፣ ኢንስፔክተር ጣሰዉ ጥላሁን ፣ የከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሠፋ እንዲሁም የከተማና የክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦች እና የማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የከተማዉ ምክትል ከንቲባ እና ሥራ እና ክሎት መምሪያ ሀላፊ መንግስቱ ትግሮ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው ፣ የፖሊስ አባላት በቁርጠኝነትና በትጋት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመወጣት ውጤታማ ሥራ ማከናወናቸውን ገልፀው ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መድረኩ ደካማ ጎን ላይ ትኩረት የምናደርግበት ነው አሉ

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር እና የምርመራ ዘርፍ ሀላፊ ኮማንደር ጉራማይለ በበኩላቸው ግምገማው ለህብረተሰቡ የሚሰጥ አገልግሎት አሰጣጥ ፣የተቋሙ እሴት እና ገጽታ የሚያበላሹ ጉዳዮች ትኩረት እንደምደረግ ገልጸዋል።

‎‎‎በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ኪዳነ ምህረት ቀበሌ (ልዩ ስሙ 30) በተባለው አካባቢ በሕዝብ መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የነበረው ተጠርጣሪ ከተሰረቀው ንብረት ...
31/08/2026



‎በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ኪዳነ ምህረት ቀበሌ (ልዩ ስሙ 30) በተባለው አካባቢ በሕዝብ መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የነበረው ተጠርጣሪ ከተሰረቀው ንብረት ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

‎ተጠርጣሪ ጌታሁን በየኔ ዳኜ የተባለዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ንብረት የሆነውን፣ መንግሥት በከፍተኛ ወጪ ያስገባቸውን ወደ መኖሪያ ቤቶች የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን (ኬብሎችን) ቆርጦ በመስረቅ ያከማቸውን የአካባቢው ማኅበረሰብ በሰጠው ጥቆማ መሠረት፣ ተጠርጣሪው ከተከማቸው ንብረት ጋር መያዙን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ደርጉ አሣለ ገለፁ ።

‎አዛዡ አክለውም ተጠርጣሪው ከተከማቸው ንብረት ጋር የተያዘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ምርመራ ተጀምሮበታል ብሏል።

‎በመጨረሻ የሕዝብና የሀገር ሀብት የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የአካባቢው ማኅበረሰብ ያደረገውን ተሳትፎ አድንቀዋል።

‎መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በጋራ ለማስቆም፣ መላው ሕዝብ ምንጊዜም ከፀጥታ አካላት ጎን እንዲቆም ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል!

‎የሕዝብ ንብረት የጋራችን ነው!
‎በጋራ እንጠብቀው!

‎መረጃው ፦የክ/ከተማ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው

29/08/2026
በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በወቅታዊ የጸጥታ ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት አካሄደ!፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨በዛሬው ዕለት (ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም) ...
28/08/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በወቅታዊ የጸጥታ ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት አካሄደ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዛሬው ዕለት (ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም) በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 4 ቀበሌያት ከነዋሪው ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የክፍለ ከተማዉ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ ወ/ል መከላከል ማስተባበሪያ ሀላፊ ም/ኢንስፔክር አስታረቀኝ ቆርጋ እንደገለጹት ውይይት የተካሄደው በጉልጉላ ቀበሌ፣በማዮ ቆቴ ቀበሌ ፣ በፋና ኦፋሴሬ ቀበሌ (ቀጠና 3) እና በኦፋሴሬ (ቀጠና 5) ነው።

የውይይቱ ዋና ትኩረት በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከአከባቢ ማህበረሰብ በጋራ መስራት እና በአካባቢያቸው የተገነቡ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በባለቤትነት ስሜት መጠበቅ ዙሪያ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም የአካባቢያቸውን ሰላምና መሠረተ ልማት በንቃት ለመጠበቅ ያላቸውን ዝግጁነት በስፋት አንጸባርቀዋል።

በጋራ በመተባበር ወንጀልን አሰቀድሞ መከላከል እንደሚቻል የገለፁት ነዋሪዎቹ አካባቢያቸውን ከማንኛውም ዓይነት ወንጀል እና ፀረ ሠላም እንቅስቃሴ ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል ።

( ሰላማችን በእጃችን ነው)!!!

መረጃዉ ፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው ።

Address

Wolayta Sodo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share