Bio and Emerging Technology Institute - BETin

Bio and Emerging Technology Institute - BETin Center of Excellence for Bio and Emerging Technology!!

Bio and Emerging Technology institute - BETin is a research and development institute under the ministry of innovation and technology of Ethiopia.

የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጫንጮ ወተት ምርት ማሻሻያ እና የሀገር በቀል ዕፅዋት መድኃኒት ምርምር ንዑስ ማዕከል በድምቀት ተመረቀ18/9/2018 ዓ.ም.................
26/05/2026

የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጫንጮ ወተት ምርት ማሻሻያ እና የሀገር በቀል ዕፅዋት መድኃኒት ምርምር ንዑስ ማዕከል በድምቀት ተመረቀ
18/9/2018 ዓ.ም................................
የአካባቢውን የእንስሳት፣ የወተት ምርታማነት እና የዕጽዋት ሀብትን በሳይንሳዊ ምርምር ለመደገፍና ለማሳደግ ታስቦ የተገነባው አዲስ የምርምር ንዑስ ማዕከል በሰሜን ሸዋ ዞን ጫንጮ ከተማ በይፋ ተመርቋል።
በዚሁ በድምቀት በተከናወነው የምረቃ ስነስርዓት ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በምረቃው ወቅት ማዕከሉ በአካባቢው ለሚስተዋሉ የምርትና የብዝሃ ሕይወት መመናመን ችግሮች ሳይንሳዊና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል።

የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ይህ ንዑስ ማዕከል ሁለት አበይትና ስትራቴጂካዊ ዓላማዎችን አንግቦ ወደ ሥራ መግባቱን አብራርተዋል። የመጀመሪያው ግብ የአካባቢውን የእንስሳት ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በሀገር በቀል ዕፅዋት ላይ ጥልቅ ምርምር በማካሄድ ለዘመናዊው መድኃኒት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሚሆን ጥራት ያለው የግብዓት አቅርቦት ማረጋገጥ ነው።

ፕሮፌሰር ካሳሁን አክለውም የማህበረሰቡን ጥያቄ በመያዝ ወደ ኢንስቲትዩቱ በመምጣት ለዛሬው ስኬት መሠረት ለሆኑት የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች እንዲሁም የመሬት አቅርቦትን ጨምሮ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ለጫንጮ ከተማና ለዞኑ አስተዳደሮች ምስጋናቸውን አቅርበው ተቋሙ ለፕሮጀክቱ ስኬት በልዩ ትኩረት እንደሚተጋ አረጋግጠዋል።

ሌላኛው ማዕከሉ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል የሀገር በቀል ዕፅዋት መድኃኒት ምርምር አንዱ ሲሆን ይህ ተግባር ሀገሪቱ ያላትን ሰፊ የብዝሃ ሕይወትና የባህላዊ ሕክምና ዕውቀት ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ለመቀየር ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ኢትዮጵያ እጅግ የበለፀገ የመድኃኒት ዕፅዋት ክምችት ቢኖራትም ባህላዊ ዕውቀቱ በሳይንሳዊ መንገድ ያልተሰነደና በቃል ብቻ የሚተላለፍ በመሆኑ የማህበረሰብ ሽማግሌዎችና አዋቂዎች ሲያልፉ አብሮ የመጥፋት ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

ከዚህ በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ የመጣው የደን መጨፍጨፍ፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የግብርና መሬት ፍላጎት መጨመርና ዕፅዋቱን ያለአግባብ መመንጠር ለአካባቢው ስነ-ምህዳር መመናመንና ለዝርያዎቹ መጥፋት ዋነኛ ተግዳሮቶች ሆነው በመቆየታቸው አዲሱ ማዕከል እነዚህን ዕፅዋት በላቦራቶሪ በመደገፍና በመንከባከብ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በምረቃው ላይ ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ተወካይ የተከበሩ አቶ ታገል ጌትነት በበኩላቸው ለማዕከሉ ግንባታ የሚሆን የመሬት አቅርቦትና ተያያዥ ድጋፎች ከጫንጮ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን በቅንጅት መከናወናቸውን ጠቅሰው በቀጣይም ማዕከሉ ለሚፈልጋቸው ማናቸውም ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። አቶ ታገል በተለይም የጫንጮ እና የአካባቢው የእንስሳት እና ወተት ልማት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን የወተት ኮሪደር ወደ ቀድሞ ህልውናውና ምርታማነቱ ለመመለስ ከአዲሱ የምርምር ማዕከል ፈጣንና ውጤታማ ምላሽ እንደሚጠበቅ በአጽንዖት አሳስበዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን በተለይም የጫንጮ አካባቢ ለአዲስ አበባና ለሌሎች ትላልቅ ከተሞች ባለው ቅርበት እንዲሁም ለእንስሳት እርባታ ምቹ በሆነው የአየር ንብረቱ ሳቢያ ከፍተኛ የወተት ምርት አቅም ያለው ቀጠና ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በርካታ ስር የሰደዱ ችግሮች እየተፈታተኑት ይገኛሉ። ጥራትና ብዛት ያለው የእንስሳት መኖ እጥረት፣ ለግጦሽ የሚሆን የመሬት ጥበት፣የነባር እንስሳት ዝርያ ደካማ የወተት ምርት አቅም፣ በቂ የእንስሳት ሕክምናና የሰው ሰራሽ ማባዣ አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን እንዲሁም የገበያ ትስስር ማነስ ዘርፉን ክፉኛ የጎዱት ዋነኛ ተግዳሮቶች ናቸው።

እነዚህ ችግሮች በአርሶ አደሩና በአርብቶ አደሩ ኢኮኖሚ ላይ የፈጠሩትን ጫና ለመቀረፍ አዲሱ ንዑስ ማዕከል የሚያቀርባቸው ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶችና የተሻሻሉ ዝርያዎች እንደ ትልቅ መፍትሔ ተወስደዋል።

የማጠቃለያ ንግግርና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ የሰጡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራና ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ለንጮ ኢንስቲትዩቱ በአካባቢው የገነባው ማዕከል ታሪክ የማይረሳውና ተቋሙ ለማህበረሰቡ ያለውን የላቀ ቅርበትና ፍቅር ያሳየበት ሰው ተኮር ተግባር መሆኑን ገልጸው አድንቀዋል።

የማህበረሰቡ ጥያቄዎችና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ዘላቂ ምላሽ ማግኘት የሚችሉት በሳይንሳዊ ምርምር ብቻ መሆኑን ያስገነዘቡት ዶ/ር ነገሪ ማዕከሉ በቀጣይ በልዩ ትኩረትና በዕቅድ በመመራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ የአካባቢውን ህዝብ ከእንስሳትና ከወተት ልማት ጋር ተያይዘው ካሉበት ስር የሰደዱ ችግሮች ማውጣት እንዳለበት የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በማዕከሉ መከፈት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በመግለፅ ማዕከሉ ለታለመለት ዓላማ እንዲበቃና ቀጣይነት ያለው ስኬት እንዲያስመዘግብ የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት ለቀጣይ ስራዎች የሚረዱ ጠቃሚ ሀሳቦችን በግብዓትነት አቅርበዋል።

18/9/2018 ዓ.ም (BETin)

upcoming...
26/05/2026

upcoming...

26/05/2026
🌙✨  ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል  አደረሳችሁ! መልካም በዓል ✨🌙
26/05/2026

🌙✨ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ! መልካም በዓል ✨🌙

25/05/2026

HAPPY AFRICA DAY TO ALL OUR AFRICAN BROTHERS AND SISTERS!

63 years ago, our forefathers gathered right here in Addis Ababa and dared to dream of a free, united Africa, and that dream still burns bright.

Today, as the proud home of the African Union, Ethiopia stands shoulder to shoulder with every African nation in that same spirit of unity.The work is far from over. Let us move from words to action, from promises to progress.

Africa's greatest resource has always been her people, and together, WE RISE!

የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአማራ ክልል ደቡቡ ወሎ ዞን ኮንበልቻ ከተማ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ !!----------------------------...
25/05/2026

የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአማራ ክልል ደቡቡ ወሎ ዞን ኮንበልቻ ከተማ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ !!
-----------------------------------------------------------------------------------------
የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ወሎ ዞን ኮንበልቻ ከተማ ግብርና መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የተፈጥሮ ማደበሪያ አዘገጃጀት ላይ ከግንቦት 3-4/2018 ዓ.ም በኮንበልቻ ከተማ በተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀት ላይ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የቆየ ዘርፉ ከሚመለከታቸው ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ የቢሮ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተግባርና የንድፍ ሃሳብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተስቷል፡፡

ስልጠና በዋናነት የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚሰራቸው ዋና ዋና ስራዎች እና የተቋሙ ስኬቶች፣ የኮንፖስት ቴክኖሎጂ ከላብ ወደ መስክ፣ የቨርሚን ኮንፖስት አዘገጃጀት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች፣ ባዮቻር የአፈር ለምነትን ለማሻሻል ፣ የቆሻሻ አወጋገድ፣ልየታና መልሶ መጠቀም፣ የተፈጥሮ ማደበሪያ እንዴት አማራጭ የቢዝነስ ሞዴል መሆን እንደሚችል በባዮና ኢመጅንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተማራማሪዎች በዘርፉ ከተገኙ ተጨባጭ የምርምር ውጤቶች ጋር በማስተሳሰር ጥልቅ የሆነ የንድፍ ሃሳብና የተግባር ስልጠን ያካተተ እንደነበር ተገልጻል፡፡
በስልጠው ሂደትም ከ25 ተቋማት ማለትም የደሴ እና ቃሉ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከከተማ ቆሻሻ አወጋገድ እና የግብርና ባለሙያዎችና የግብርና የኤክስቴሽን ባለሙያዎች ፣ ከኢንተርፕራይዞችና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስትና የግል ተቋማት የተሳተፉበት እንደነበር ታይቷል፡፡

በመጨረሻም የኮንበልቻ ከተማ ግብርና መምሪያ ሃላፊ በተገኚበት ሰልጣኞች በቀጣይ የሰለጠኑት ስልጠና እንዴት ማሰልጠንና ወደ መሬት አውርደው ለአርሶ አደሩ እንደሚደርሱ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የኮንበልቻ ግብርና መምሪያ በዋናነት ሃላፊነት ወስዶ ለተግባራዊነቱ እንደሚሰራ ለዚህም ኢንስቲትዩቱም አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ እንደሚደርግ መግባባት ላይ ተድርሶል፡፡

Strengthening Ethiopia–China collaboration in biotechnology and emerging technologies! The Bio and Emerging Technology I...
24/05/2026

Strengthening Ethiopia–China collaboration in biotechnology and emerging technologies!

The Bio and Emerging Technology Institute (BETin) was honored to host a productive discussion with the China National Center for Biotechnology Development (CNCBD) and delegates from China Medical City (CMC) on 22 May 2026. The engagement focused on expanding partnerships in biotechnology research, vaccine and diagnostic development, biotech innovation, joint laboratory establishment, and short and long term human capacity building. During the meeting, BETin highlighted its key achievements and ongoing initiatives, including:
· Vaccine and diagnostic development research
· Genomic sequencing capacity and bioinformatics trainings
· Cholera and Animal vaccine research
· COVID-19 testing and SARS-CoV-2 surveillance as well as the National Virus Research Center (NVRC) activities.
· Agricultural and industrial biotechnology innovations
· National and international research collaborations
CNCBD also shared its extensive experience in biotechnology program management, policy development, industrial biotechnology, and international scientific cooperation in China.
The discussion identified exciting opportunities for future collaboration, including:
· Joint research programs
· Scientist exchange and fellowship opportunities
· Technology transfer and innovation
· Capacity development and training
· Strengthening One Health research initiatives
Together, BETin and CNCBD are committed to advancing scientific innovation and contributing to global health and sustainable bioeconomy development.

21/05/2026

21/05/2026

📸 Family photo of the Member State representatives at the ongoing 32nd session of the ICGEB Board of Governors - taking place in Cape Town, South Africa.🇿🇦
Celebrating 20 years of ICGEB Cape Town and of long-standing partnerships driving scientific excellence, international cooperation, and tangible impact across the continent.🌍

Article in the comment section👇

Department of Science,Technology and Innovation SA Ambasciata d'Italia a Pretoria Ministero degli Affari Esteri e della Cooperazione Internazionale Department of Biotechnology, India ICGEB New Delhi

The Bio and Emerging Technology Institute (BETin) has successfully concluded a intensive, two-day Training of Trainers (...
19/05/2026

The Bio and Emerging Technology Institute (BETin) has successfully concluded a intensive, two-day Training of Trainers (ToT) program dedicated to advancing composting technologies, biochar production, and organic soil fertility management.
Held from May 8-9, 2026, at the Addis Amba Hotel in Bahirdar, the initiative marks a critical step forward in addressing Ethiopia’s current fertilizer shortages while accelerating the transition toward environmentally sustainable farming practices.

The high impact program convened a diverse cohort of experts, researchers, educators, and agricultural practitioners who are tasked with cascading these advanced methodologies and leading practical field demonstrations across the Amhara region.

Key participating institutions included the Amhara Region Agricultural Research Institute, the Amhara Region Bureau of Agriculture, the Bahir Dar City Administration Agriculture Office, and the Bahir Dar City Administration Cleaning, Beautification and Parks Office. The event also drew critical stakeholders from the Amhara Region Environmental Protection Authority, Bahir Dar Polytechnic College, the Bahir Dar Soil Research and Fertility Improvement Center, and Bahir Dar University, alongside various local enterprises and development partners.

Demonstrating strong institutional backing, the training featured active participation from prominent academic and regional leaders, including Dr. Amare Bitew, Director of the Bahirdar University Beautification Office, and Dr. Silesh Andualem, Deputy Director of the Bahirdar University Biotechnology Institute.

The comprehensive curriculum balanced rigorous theoretical coursework with immersive, hands-on field applications. Participants engaged in specialized modules covering windrow composting, vermicomposting, biochar-based organic fertilizer production, and the technical operation of composting machinery. Additionally, the sessions focused on the downstream commercialization process, including compost processing, packaging, and marketing, integrated within a broader framework of urban waste management systems.

To ground the theoretical concepts, practical demonstrations and field visits were conducted at several strategic locations throughout the city.

These included the Bahirdar University School of Law, the Institute of Soil Administration, and the Bahir Dar Soil Research and Fertility Improvement Center. Participants also visited an active composting site near the Bahirdar textile factory, currently managed by the Bahirdar University Biotechnology Institute.

The core mission of the program rests on three strategic pillars: accelerating the adoption of affordable, locally adaptable composting technologies; restoring soil health through organic resources; and significantly reducing national reliance on costly imported chemical fertilizers.

Building on the success of this initial program, BETin has announced plans to roll out cluster based regional trainings, localized field demonstrations, and extensive community awareness campaigns.

By equipping farmers, extension workers, and local communities with the practical skills needed to manufacture high-quality organic fertilizers locally, the initiative is poised to foster a more resilient, self-reliant, and productive agricultural ecosystem in Ethiopia.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bio and Emerging Technology Institute - BETin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bio and Emerging Technology Institute - BETin:

Share