04/02/2021
ቀረጥ ተመላሽ ጥያቄ ለማቅረብ ምን ሊሟላ ይገባል
የቀረጥና ታክስ ተመላሽ ጥያቄ ለቀረጥ ተመላሽ ቡድን ስታቀርቡ የሚከተሉትን ሠነዶችን/መረጃዎችን መሟላት አለባቸው
1. ለሁሉም አይነት የቀረጥ ተመላሽ ጥያቄዎች
ማመልከቻ ደብደቤ (በአስመጪው ሄዲንግ የተፃፈና ፍሬ ነገሩ በአጭሩ የሚገልፅ)
የተበተነ ዴክላራስዮን ኮፒ
ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ(removal)
ግብር ከሚከፍልበት ቅ/ፅ/ቤት በተጠቀሰው ሰነድ አለ/ማወራረዱ
2. በዋጋ፣ በታሪፍ፣ CPC በአገላለፅ እና በሌላ የሂሳብ አስራር ስህተት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች
በተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ
በትክክል ለእቃው ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ የያዘ ድራፍት ዴ/ን
በእቃው ዋጋ አተማመን፣ ታሪፍ እና cpc አመዳደብ በቂ ማስረጃ እና ውሳኔ
የአገላለፅ ልዩነት፣ የልኬት፣ በጉድለት እና የመሳሰሉ ከሆነ የፍተሻ ውጤት እና ከገቢ ዕቃ አወጣጥ ቡድን ማረጋገጫ
በጉድለት የሚጠየቁ የቀረጥ ተመላሽ ጥያቄዎች የውጭ ምንዛሪ ተመላሽ ስለመደረጉ የባንክ ማረጋገጫ፤ እንዲሁም በምትክነት አለመስተናገዳቸው ከገቢ ዕቃ አወጣጥ ቡድን ማረጋገጫ
3. በደረጃ፣ ጤና እና በሌሎች ምክንያቶች ተመልሰው የሚወጡ እቃዎች (re-export)
በተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ
Re-Export ዴ/ን ኮፒ፣
የCIF 5% ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ (removal) ፣
እቃው ተመልሶ መውጣቱ ማረጋገጫ፣
የውጭ ምንዛሪ ተመላሽ ስለመደረጉ የባንክ ማረጋገጫ፣
4. በተለያዩ ምክንያቶች ተወርሰው የተወገዱ እቃዎች
በተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩትበተጨማሪ
እቃው ውርስ የተደረገበት ሞዴል 265 ደረሰኝ ኮፒ፣
በተጓዳኝ መ/ቤት (ጤና ፣ ደረጃ…..) ውድቅ የተደረገ ከሆነ ማረጋገጫ፣
በመጓጓዝ እያለ ጉዳት የደረሰበት ከሆነ ጉዳት ስለመድረሱ የሚገልፁ ማስረጃዎች (የፓሊስ፣ ቃለጉባኤ፣ የኢንሹራንስ የመድን ካሳ ወዘተ)፣
የፀደቀ የአስወጋጅ ኮሚቴ ቃለ-ጉባኤ፣
ተወርሰው የተወገዱ እቃዎች በከፊል ከሆነ በትክክል ለእቃው ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ የያዘ ድራፍት ዴ/ን፣