Prosperity party yeka woreda 12 branch ብልፅግና

Prosperity party yeka woreda 12 branch ብልፅግና official page yeka woreda 12 prosperity party

07/09/2026
ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን!ከግምገማ ወደ ተግባር፣ ከተግባር ወደ ውጤት!የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን ከወረዳው ሰራተኞች ጋር የወርቃማ ሰኞ ተወያይተዋልጳጉሜ ቀናት የአ...
07/09/2026

ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን!

ከግምገማ ወደ ተግባር፣ ከተግባር ወደ ውጤት!

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን ከወረዳው ሰራተኞች ጋር የወርቃማ ሰኞ ተወያይተዋል

ጳጉሜ ቀናት የአንድ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን በመገምገም፣ የተሳካውን በማጠናከርና ያልተሳካውን በመለየት ለቀጣዩ ዓመት የተሻለ አቅጣጫ ለመያዝ የሚያገለግሉ የግምገማና የእርምት ጊዜያት ናቸው።

በዚህ መነሻ “የማንሰራራት” ውይይት ያለፈውን በመገምገም፣ ዛሬን በማሻሻልና ነገን በመገንባት ላይ ትኩረት አድርጓል።

ማንሰራራት ከድክመት መነሳት፣ አዲስ ኃይልና ተስፋ መፍጠር፣ የተሻለ አሠራር መጀመርና ከተገኘው ልምድ በመማር ለተሻለ ውጤት መዘጋጀት ነው።

የዓመቱን አፈጻጸም መገምገም፣ ድክመቶችን መለየት፣ የተሻሉ አሠራሮችን ማጠናከር፣ አዲስ አቅጣጫ መያዝና የሰው ኃይልና የተቋም አቅምን ማሳደግ ነው።

ስኬትን ማጠናከር፣ ድክመትን ማረም በመሆኑ ጥሩ አመራር፣ ተግባራዊ እቅድ፣ የቡድን ሥራ፣ ቁርጠኝነትና ተገልጋይ-ተኮር አሠራር ለስኬት መሠረቶች መሆናቸው ተመላክቷል በውይይቱ ተመላክቷል።

ለውጡ የሁሉም ሚና ነው፤በማንሰራራት ሂደት አመራር ራዕይን ይመራል፣ ሰራተኞችን ያነቃቃል፣ ሀብትን ያስተባብራል እና ውጤትን ይከታተላል። ሰራተኛው ደግሞ በተግባሩ፣ በባህሪውና በፈጠራ ሀሳቡ የለውጡ ተዋናይ ነው።

በተለይም ተገልጋይ-ተኮር አገልግሎት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሃዊነት፣ ተሳትፎና ውጤታማነት የተሻለ ተቋማዊ አሠራር መሠረቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ቅሬታ ችግር ብቻ ሳይሆን የማሻሻያ ግብዓት በመሆኑ
የተገልጋይ ቅሬታ የተቋሙን የአገልግሎት ክፍተት የሚያሳይ መረጃ በመሆኑ፣ ቅሬታን መስማትና ዋና ምክንያቱን ማስወገድ የማሻሻያ ሂደቱ አካል መሆኑ ታውቋል።

በመጨረሻም ከሰራተኞች ማንሰራራት የአንድ ቀን ውይይት ሳይሆን የአዲስ አስተሳሰብ፣ የተሻለ አሠራርና የተሻለ ውጤት ጉዞ መሆኑ ተገልጿል።

እንነሳ፣ እንለወጥ፣ እንሻሻል፣ እንሰራ!

ጳጉሜ 2 — የማንሰራራት ቀን! አብሮነትን በማጠናከር፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ለተሻለች ከተማ!የየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 ነዋሪዎች የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማትን በመጎብኘት፣ በጋራ መስራትና...
07/09/2026

ጳጉሜ 2 — የማንሰራራት ቀን!

አብሮነትን በማጠናከር፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ለተሻለች ከተማ!

የየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 ነዋሪዎች የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማትን በመጎብኘት፣ በጋራ መስራትና አካባቢያችንን መንከባከብ የከተማችንን ማንሰራራት እንደሚያፋጥን አሳይተዋል።

የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ለመዝናኛና ለአረንጓዴ ልማት ምቹ ስፍራ ከመፍጠር ባለፈ፣ ነዋሪዎች በጋራ እንዲሰሩ፣ እንዲተሳሰቡና የጋራ ከተማቸውን እንዲንከባከቡ የሚያጠናክር የአብሮነት መድረክ ሆኗል።



ጎቤና ሽኖዬ  ባህላችንን እንጠብቅ፣ እሴታችንን እናስቀጥል!
07/09/2026

ጎቤና ሽኖዬ ባህላችንን እንጠብቅ፣ እሴታችንን እናስቀጥል!


ጎቤና ሽኖዬ  ባህላችንን እንጠብቅ፣ እሴታችንን እናስቀጥል!የየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 ወጣቶችና ሴቶች በጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ ጨዋታ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።ወጣቶችና ሴቶች በባህላዊ አል...
07/09/2026

ጎቤና ሽኖዬ ባህላችንን እንጠብቅ፣ እሴታችንን እናስቀጥል!

የየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 ወጣቶችና ሴቶች በጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ ጨዋታ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ወጣቶችና ሴቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው በመሳተፍ ባህላችንን በተግባር እያስተዋወቁና እያስጠበቁ ይገኛሉ። ይህ ተሳትፎ የበዓል ድምቀት ብቻ ሳይሆን፣ ትውልድ ከትውልድ የሚተላለፉ ባህላዊ እሴቶቻችንን ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ነው።

ባህል የሕዝብ ማንነትና የታሪክ አሻራ ነው። እንደ ጎቤና ሽኖዬ ያሉ ባህላዊ ጨዋታዎች የቀድሞ ትውልዶችን ታሪክ፣ እሴትና የአብሮነት መንፈስ የሚያስተላልፉ ሕያው ቅርሶች ናቸው። በዚህም ወጣቶች ባህላዊ አልባሳትን፣ ጨዋታዎችንና ሥርዓቶችን በመለማመድ ራሳቸውን ከባህላቸው ጋር ያገናኛሉ፤ የባህል ቅርስንም ከመዘንጋትና ከመጥፋት ይከላከላሉ። በተለይም ሴቶችና ወጣቶች በንቃት መሳተፋቸው የባህል ቅብብሎሹን የሚያጠናክር ነው።

የኢትዮጵያ ጥንካሬ በብዝሃነቷ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮችና እሴቶች ውስጥ ይገኛል። እነዚህን የተለያዩ ባህላዊ ሀብቶች ማክበርና ማስጠበቅ የአንድ ማኅበረሰብ ብቻ ጉዳይ ሳይሆን የጋራ ሀገራዊ ኃላፊነት ነው። ባህሎቻችንን በመጠበቅ ልዩነታችንን እንደ ሀብት ተጠቅመን የመተሳሰብ፣ የመከባበርና የአብሮነት እሴቶችን ማጠናከር እንችላለን።



#ጎቤናሽኖዬ
#የኢትዮጵያእሴቶች

07/09/2026
የማንሠራራት ቀን ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ...
07/09/2026

የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።



Guyyaa Bayyanannaa

Itoophiyaa jecha bira darbuun milkaa'ina qabatamaadhaan dhaabbatte!

Kaleessa "Itoophiyaan Kaateetti" gaafa jennu hawwii utuu hin ta'iin dhugaa har'a qabatamaadhaan mirkaneessinedha! Ijaarsa Hidha Haaromsaa Guddicha irraa hanga misooma kooriidarii ammayyaatti, Buufata Xiyyaaraa Bishooftuu guddichaa hanga riifoormii dinagdee maakrootti dadammaqinsi biyya keenyaa gochaan dhugoomeera. Jijjiiramni kun sadarkaa jireenyaa lammiilee keenyaatiin, ammayyoomuu magaalotiifi carraa hojii uumuutiin ifa dhugaa ta'uurraayyuu, mul'ata guddaa abdii egeree ijoollee keenyatti horudha. Kana booda duubatti hin deebinu! Imala bayyanannaa seena-qabeessa eegalleen humna misoomaa keenya caalaatti saffisiisuudhaan olka'insa Itoophiyaa gara badhaadhina waaraatti ol ni kaafna.

ጳጉሜ 2የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ  ጉዞ!    #የካ
07/09/2026

ጳጉሜ 2
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ጉዞ!


#የካ

Address

Yeka
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity party yeka woreda 12 branch ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share