አዲስ ጋራ/Addis Gara

አዲስ ጋራ/Addis Gara Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አዲስ ጋራ/Addis Gara, Government Official, Addis Ababa.

ራዕይ (Vision)

በ2022 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተለለፍ የቀነሰባት፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ሆና ማየት፡፡

ተልዕኮ (Mission)

በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ሕገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተልና በመቆጣጠር አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ እንድትሆን ማድረግ፡፡

04/08/2026
02/08/2026
የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በወረዳ 03 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በይፋ አስጀመረአዲስ አበባ | ሐምሌ 23/2018 ዓ.ምየየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ...
31/07/2026

የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በወረዳ 03 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በይፋ አስጀመረ

አዲስ አበባ | ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ከተሰጠው የከተማዋን ህግና ስርዓት የማስከበር ዋና ተግባር ጎን ለጎን፣ ህዝባዊና ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት በጎ ባህሉን በማጠናከር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎችን መኖሪያ ቤት የማደስ ሰፊ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምሯል።

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ደማቅ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እሱባለው መንደዶን ጨምሮ የክፍለ ከተማውና የወረዳው ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች፣ የጽሕፈት ቤቱ ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

መርሃ ግብሩን አስመልከተው ንግግር ያደረጉት የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ፣ ይህ የወገን ደራሽነትና የበጎ አድራጎት ስራ በስኬት እንዲጀመርና ግቡን እንዲመታ ቁሳቁሳዊ፣ የገንዘብና የሞራል አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኃላፊው አክለውም፦ «ጽሕፈት ቤታችን የከተማዋን ደንብና ስርዓት በማስከበር ረገድ የሚያከናውነው ዕለታዊ ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በችግር ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖቻችንን መደገፍና የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር የሁላችንም ሰብአዊና ማህበራዊ ኃላፊነት ነው። ይህ የቤት እድሳት መርሃ ግብርም የዚሁ ቃል ኪዳናችን ማረጋገጫ ነው፤ በቀጣይም ተመሳሳይ ማህበራዊ ድጋፎችን አጠናክረን እንቀጥላለን» ሲሉ ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙት የክፍለ ከተማውና የወረዳው አመራሮች በበኩላቸው፣ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ያሳየውን ህዝባዊ ወገንተኝነትና በጎ አነሳሽነት አደንቀው፤ የእድሳት ስራው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳና ጥራት ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች እንዲረከብ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

ይህ የመኖሪያ ቤት እድሳት መርሃ ግብር በተለይም ክረምቱን ምክንያት በማድረግ ዝናብና ቅዝቃዜ የሚፈታተናቸውን ወገኖች ችግር በመቅረፍ ረገድ ትልቅ እፎይታን እንደሚፈጥር የተገለፀ ሲሆን፣ እድሳቱ አጠቃላይ ስራው ተጠናቆ አቅመ ደካሞቹ ወገኖች ምቹና አስተማማኝ መጠለያ እስኪያገኙ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

📲 ማስታወሻ፦ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ይደውሉ። ስለ መልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን!

🌐 የጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የመረጃ ገፅ፦
https://linktr.ee/yekasubcitycodeenforcementoffi
📌 መረጃው፦ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀ ነው።

#የየካክፍለከተማ #ደንብማስከበርጽቤት #ወረዳ03 #የቤትእድሳት #የበጎአድራጎትስራ #ህዝባዊወገንተኝነት #አዲስአበባ

«ወርቃማ ሰኞ»፦ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበት የሚያደርገውን የልምድ ልውውጥ አጠናክሮ ቀጥሏል፤አዲስ አበባ | ሐምሌ 20/2018 ዓ.ምየየካ ክፍለ ...
31/07/2026

«ወርቃማ ሰኞ»፦ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበት የሚያደርገውን የልምድ ልውውጥ አጠናክሮ ቀጥሏል፤

አዲስ አበባ | ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የውስጥ አሰራሩን ለማዘመንና ህዝባዊ አገልግሎቱን በተሳለጠ መልኩ ለማቅረብ ያለመውን የ«ወርቃማ ሰኞ» የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት በፊት ማካሄዱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዕለቱ የደመቀውን መርሃ ግብር በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የጽሕፈት ቤቱ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከልና ስልጠና ስራዎች አስተባባሪ አቶ ከፈለኝ በልሁ፣ መድረኩ ሙሉ ሳምንቱን በላቀ የስራ መንፈስና በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል አቅም የሚገነባበት መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ከፈለኝ አክለውም፦ «ይህ መድረክ ሰራተኞቻችን እርስ በእርስ የሚማማሩበት፣ መልካም ተሞክሮዎችን የሚያካፍሉበት እና ህዝባዊ አገልግሎት አሰጣጣችንን ደረጃ በደረጃ ለማሻሻል የምንመካከርበት ወሳኝ መድረካችን ነው» ብለዋል።

በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ በጽሕፈት ቤቱ የሰው ሀብት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ ትምህርት ዜና «የደንበኛ አያያዝ» በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ ተገልጋይ ህብረተሰብን በቅንነት፣ በሙያዊ ስነ-ምግባርና በአክብሮት ማስተናገድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አስተማሪ ሀሳቦችን አቅርበዋል።

በተጨማሪም አቶ ከፈለኝ በልሁ ባደረጉት ተጨማሪ ገለፃ፣ በተቋሙ ውስጥ ልምድ ማጋራትና በቡድን መንፈስ መስራት ተቋማዊ ውጤታማነትን እንደሚያረጋግጥ ጠቁመው፤ በተለይም በከተማችን የሚገነቡ ህንፃዎችና የሚሰጡ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹና ተደራሽ መሆን እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመጨረሻም በተነሱት ነጥቦች ላይ ከአስተባባሪዎች፣ ከቡድን መሪዎችና ከባለሙያዎች ሰፊ አስተያየትና ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን፤ በአቶ ከፈለኝ በልሁ የቀጣይ አቅጣጫዎችና ማጠቃለያ ተሰጥቶበት ስብሰባው በስኬት ተጠናቋል።

📲 ማስታወሻ፦ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ይደውሉ። ስለ መልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን!

🌐 የጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የመረጃ ገፅ፦
https://linktr.ee/yekasubcitycodeenforcementoffi
📌 መረጃው፦ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀ ነው።

#የየካክፍለከተማ #ደንብማስከበር #ወርቃማሰኞ #የእውቀትሽግግር #የደንበኛአያያዝ #አዲስአበባ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ጋራ/Addis Gara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share