10/07/2026
ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት፣ ለላቀ የህዝብ ተጠቃሚነት!
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት፣ ለላቀ የህዝብ ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የፓለቲካና የአደረጃጀት ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።
በግምገማ መድረኩ ላይ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ወይዘሪት ወይንሸት አስናቀን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማና የሁሉም ወረዳ ፓርቲ ኮሚቴዎች የተገኙ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የፖለቲካና የአደረጃጀት ሰራዎች ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ተካሂዷል።
የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ኃላፊ ወይዘሪት ወይንሸት አስናቀ በግምገማ መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ባለፈው በጀት ዓመት በተቀናጀና በተናበበ ሁኔታ ባስቀመጥናቸው ግቦች መሠረት ምርጫን ጨምሮ በርካታ ስኬታማ የሆኑ የፖለቲካና የፓርቲ ስራዎችን ሰርተናል ያሉ ሲሆን ከዕለት ወደዕለት እያደገና እየጎለበት እንዲሁም ተጨባጭ ለውጦች እያመጣ ያለውን የአመራራችንን ሁለንተናዊ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅምን ባገናዘበ የአመራር ስምሪት ክፍለ ከተማችንን የአዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌትና በሁሉም ዘርፍ ሞዴል ለማድረግ የሰራናቸው ተግባራት እጅግ አመርቂ ነበሩ ብለዋል።
በተለይ የሰባተኛው ዙር ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ ስራ ከተጀመረ በኋላ ሁሉንም አቅማችንን በማስተባበር በአንድ በኩል ምርጫው ፍትሐዊ፣ዴሞክራሲያዊና ቅቡልነት ያለው እንዲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ውድድር ፓርቲያችን አሸናፊ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ያስቀመጥናቸው መንትያ ግቦችን ለማሳካት የሰራናቸው ስራዎች ውጤት አስገኝቸውልናል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ አዳዲስ አባላትን ወደ ፓርቲው ከመቀላቀል፣በሰው ተኮር ተግባራትና በንቅናቄ ስራዎች እንዲሁም በየደረጃው ያለውን የአመራራችንና የአባላትን የአቅም በመገንባት ረገድ የሰራናቸው ጠንካራ ስራዎች ለውጤታማነታችን ጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው ሲሉም ኃላፊዋ አክለው ገልፀዋል።
የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ሳህሉ በበኩላቸው ባለፈው በጀት ዓመት በክፍለ ከተማችን አመራሩ ህዝባችንና መላ መዋቅራችንን ከጎኑ በማሰለፍ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው የብልፅግና ቤተሰብ ውይይቶችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ የሌብነትና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን የምንተጋገልበት መድረክ ከማድረግ አንፃር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል።
የሞዴል ተቋማትን ለመፍጠር ህብረቶች በጎ ተፅኖ ውድድሮች የጥያቄና መልስ ውድድሮች እና የፓርቲ ተቋማት አቅም ሆነው እንዲወጡ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ የተገኘባቸው ተግባራት መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል።
የግምገማው ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው ባለፈው በጀት ዓመት ለውጥ ባመጣንባቸው ተግባራትና የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጎልበት እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በማረም በ2019 በጀት ዓመት በልዩ ትኩረት እንሰራለን ብለዋል።
Nifas Silk Lafto Woreda 05 Prosperity Party