House of Peoples Representatives of FDRE

House of Peoples Representatives of FDRE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from House of Peoples Representatives of FDRE, Government Organization, House of peoples' representatives of FDRE, Addis Ababa.

"ባለፉት አምስት ዓመታት በምክር ቤቱ ለተከናወነው አበረታች ሥራ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ሚና የጎላ ነው” — የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ‎-------------------‎(ዜና ...
05/09/2026

"ባለፉት አምስት ዓመታት በምክር ቤቱ ለተከናወነው አበረታች ሥራ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ሚና የጎላ ነው” — የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
‎-------------------
‎(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 30፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በምክር ቤቱ ለተከናወኑ ውጤታማና አበረታች ተግባራት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ሠራተኞቹ ላሳዩት የላቀ የሥራ አፈጻጸም ምስጋናቸውን በማቅረብ፣ ሽልማት አበርክተዋል።

‎አፈ ጉባኤው ይህንን የገለጹት፣ በ2018 ዓ.ም. በሥራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በተዘጋጀው የዕውቅናና የምስጋና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።

‎በዕለቱ በተሰጠው ሽልማት ላይ ጥቂት ሠራተኞች ቢመረጡም፣ በተግባር ግን ሁሉም የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች ተሸላሚ መሆናቸውን አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

‎አክለውም፣ የምክር ቤቱ ሥራዎች በስኬት ሊጠናቀቁና ውጤታማ ሊሆኑ የቻሉት በመላው ሠራተኛ ያልተቆጠበ ጥረትና ድካም መሆኑንም አስረድተዋል።

‎የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እስከ አሁን ላደረጉት አበረታች አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም ተቋማዊ ስኬቱን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ትልቅ የሥራ አደራ ጥለውባቸዋል።

‎በቀጣይ የሚመጡ አዳዲስ የምክር ቤት አባላትን በተለመደው የምክር ቤቱ ደንብና አሠራር መሠረት ተቀብለው በብቃት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

‎የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ተወካይ እና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ከረዩ ባናታ በበኩላቸው፣ ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ሠራተኞች ዕውቅና መስጠት ለሌሎች አርአያ የሚሆንና ለተቋም ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የማበረታቻ ሽልማቱ ዋና ዓላማ የጽሕፈት ቤቱን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።

‎ይህ ሽልማት በጽሕፈት ቤቱ ሥር ያሉ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻነት የተዘጋጀ መሆኑን በመጠቆም፣ በቀጣይም ሌሎች ሠራተኞች ለተሻለ ውጤት እንዲነሳሱ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

‎የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ (የሙያዊ ዘርፍ ተወካይ) ወ/ሮ ቁስቋም ማሞ፣ ሽልማቱ ከቁሳዊ ዋጋው ባሻገር ለሌሎች ሠራተኞች መልካም ተሞክሮ የሚፈጥርና የጽሕፈት ቤቱን ሥራዎች በብቃት ለማከናወን የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎(በሀብታሙ አብርሃም)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

‎"የነፍስ ወከፍ ለውጥ ለቡድን እና ለተቋማዊ እምርታ" በሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ‎------------------‎(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 29፣ 20...
04/09/2026

‎"የነፍስ ወከፍ ለውጥ ለቡድን እና ለተቋማዊ እምርታ" በሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ
‎------------------
‎(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 29፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት "የነፍስ ወከፍ ለውጥ ለቡድን እና ለተቋማዊ እምርታ" በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሠራተኞች ያዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል።

‎ዶክተር ተአምራት ዘላለም ስልጠናው ላይ እንደገለጹት፤ የሥልጠናው ዋና ዓላማ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና የሥሜት ማሳያዎችን በመገንዘብ በጎ እና ቅን አስተሳሰቦችን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

‎አክለውም በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እየፈቱ በመሔድ፣ ራስን የማሻሻልና ለተሻለ ውጤት እንዲሁም ለምርታማነት የመብቃት አቅምን ማሳደግ የሥልጠናው ትኩረት መሆኑን ተናግረዋል።

‎የማንኛውም ተቋም ዕድገትና ስኬት መነሻው የግለሰብ ለውጥ በመሆኑ፣ የነፍስ ወከፍ ለውጥ ለቡድንና ለተቋም መሻሻል እንዲሁም ለበለጠ እምርታ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

‎በሥልጠናው ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ ተወካይ እና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸኃፊ አቶ ከረዩ ባናታ በበኩላቸው፤ ሠራተኞች ራሳቸውን በመመልከት ከዚህ ቀደም ከነበራቸው በተሻለ መልካም ምግባርና ዝግጁነት ውስጥ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

‎አቶ ከረዩ አክለውም ለተገልጋዮች የሚሰጠው አገልግሎት የተቃና ይሆን ዘንድ፣ አገልግሎት በምንሰጣቸው አካላት አስተሳሰብ ውስጥ ሆኖ ነገሮችን በቀናነት መመልከትና ተቋሙን ለማሻገር እነዚህን መልካም አስተሳሰቦች ማጤን እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎ለማንኛውም ነገር መነሻው እኛ በመሆናችን ቀድመን ራሳችንን በመመልከት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ከረዩ፣ በየትኛውም መስክ ራስን እያሠለጠኑና እያስተማሩ ወደ ከፍታ ጫፍ መድረስ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

‎በተጨማሪም ዋናው ነገር ራስን ማሠልጠን መሆኑን እና ክህሎት በአንድ ጊዜ የሚመጣ ሳይሆን በጊዜ ሒደት የሚዳብር በመሆኑ፣ ሠራተኛው በትዕግሥትና በትጋት ራሱን ማነጽ እንዳለበት አስረድተዋል።

‎የሥልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች በበኩላቸው፤ የተሰጣቸው ሥልጠና ጠቃሚ፣ ተገቢና መንፈስን የሚያድስ ገንቢ ሥልጠና መሆኑን ገልጸዋል።

‎ሠራተኞቹ አክለውም ሥልጠናው ለሁሉም አካል ትልቅ የማንቂያ ደውል መሆኑን በመጥቀስ፣ በእኩል እንክብካቤና ያለ አድልኦ ተቋማዊ ሥራን ለማከናወን እንዲሁም እንግዶችንና ተገልጋዮችን በተቋማዊ አክብሮት ለመቀበል የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው አብራርተዋል።

‎(በ ሀብታሙ አብርሃም)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

ቋሚ ኮሚቴው በተቋማት ግንባታ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገለጸ-------------------(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 26፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕ...
01/09/2026

ቋሚ ኮሚቴው በተቋማት ግንባታ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገለጸ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 26፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት 5 ዓመታት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገምግሟል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በሰጡት አስተያየት ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት 5 አመታት ጥራታቸውንና አገራዊ ፋይዳቸውን የጠበቁ አዋጆችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመመርመርና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ የማቅረብ ተግባራትን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል።

በሂደቱም ለአገራዊ ሪፎርም፣ ለፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውን 28 አዋጆች እና 2 ደንቦችን በጥልቀት መርምሮ አጸድቋል ብለዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የፌዴራል ወንጀል ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ማስመለስ የሚያስችል አዋጅ እና ወንጀለኛን አሳልፎ መስጠትና የጋራ የሕግ ትብብርን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ አክለውም በተለይም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የተቋማትን አቅም በመገንባት የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በተቋማት መካከል ቅንጅት መፈጠሩና አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መደረጋቸው፣ በፍርድ ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች በተደረጉ የመስክ ምልከታዎች የታራሚዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ መሻሻሉ እና ለችግረኞች የሚሰጥ የነፃ ሕግ ድጋፍ አገልግሎት ቋሚ ኮሚቴው ካከናወናቸው ስኬታማ ተግባራት የሚጠቀሱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በሕግ አወጣጥና ጥናት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የሕግና የቴክኒክ ሙያተኞች እጥረት ማጋጠሙ፣ በተቋማት መካከል የዲጂታል መረጃ ልውውጥና የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት ሙሉ በሙሉ አለመዘመኑ፣ የሎጅስቲክስና የቅንጅት መጎደል ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩም ተጠቁሟል።

በተቋማት መካከል ያለውን የመረጃ መለዋወጫ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ማሸጋገር እና አሠራሮችን ማዘመን፣ የሕግና የሙያ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ የሕግ ምርመራ ጥራትንና ፍጥነትን የበለጠ ማጠናከር እንዲሁም ከክልል ምክር ቤቶችና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅት ማሳደግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይገባልም ተብሏል።

(በድረስ ገብሬ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

"ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ለቀጣዩ ጉዞ ታላቅ አርአያ ናቸው" — የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ------------(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 25፣ 2018 ዓ.ም...
31/08/2026

"ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ለቀጣዩ ጉዞ ታላቅ አርአያ ናቸው" — የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ
------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 25፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ውስጥ ባለፉት አምስት ዓመታት የነበሩት አባላት አገራዊ ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ የስራ ትጋት በመወጣት በርካታ አበረታች ሥራዎችን አከናውነው ማለፋቸውን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ገልጸዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በየዘርፉ ያከናወኗቸው ዘመናዊና የተቀናጁ ተግባራት የኮሚቴውን አቅም ከማሳደጋቸውም በላይ፣ ለቀጣይ የፓርላማ የሥራ ዘመናትና ለአዳዲስ አባላት ትልቅ ምሳሌና መማሪያ የሚሆን ጠንካራ መሠረት መጣላቸውን የተከበሩ ሰብሳቢዋ አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በነበረው የአምስት ዓመታት የሥራ ጉዞ ውስጥ ውጤታማ ሊሆን የቻለው አባላቱ በቅንነት፣ በታማኝነት፣ በትጋትና በመሥራታቸው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ የመከባበርና የጋራ ዓላማ ለተቋማዊ ስኬቱ ዋና ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴው በራሱ ጥረትና ልምድ ብቻ ሳይወሰን፣ በምክር ቤቱ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎች መልካም አሠራሮችንና ተሞክሮዎችን በየጊዜው እየቀሰመ አሠራሩን ሲያዘምን እንደነበር አስረድተዋል።

የቋሚ ኮሚቴውን ጉዞ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ በአምስቱም ዓመታት ያከናወናቸውን ሁኔታዎች፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች እንዲሁም የሕግ ማውጣት ሂደቶች እና የዲፕሎማሲ ተግባራት አንድም ሳያስታጎጉል በየዓመቱ በአጠቃላይ አምስት መጽሔቶችን አዘጋጅቶ ማቅረብ መቻሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

እነዚህ አምስት መጽሔቶች የቋሚ ኮሚቴውን አጠቃላይ ታሪካዊና ተቋማዊ እንቅስቃሴ በዝርዝር የሰነዱ በመሆናቸው፣ ለቀጣዮቹ የሥራ ዘመናት ተተኪዎች ተጨባጭ ማሳያና የመማሪያ ሕያው ሰነድ ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸውን ሰብሳቢዋ አፅንኦት ሰጥተውበታል።

የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ አክለውም፣ ይህንን ተምሳሌታዊ የሥራ ባህል አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይም ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝቧ የሚጠቅሙና የሚበጁ ታላላቅ ተግባራትን በቅንነትና በሙሉ አቅም ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለእነዚህ በርካታ ስኬቶች መመዝገብና ለተከናወኑት አበረታች ሥራዎች በልዩ ትጋት አስተዋፅኦ ላበረከቱ፣ ላገዙ፣ ለደገፉና በየደረጃው ከቋሚ ኮሚቴው ጎን ለቆሙ አካላት በሙሉ ሰብሳቢዋ ጥልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተለይም የቋሚ ኮሚቴው የክትትልና የቁጥጥር ሥራ፣ የህዝብ ውክልና ተግባራት፣ ሕግ የማውጣት እና የዲፕሎማሲ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ ሌተቀን ሙያዊ ድጋፍ ሲሰጡ ለነበሩት የምክር ቤቱ ፅ/ቤት ባለሙያዎችና ሀላፊዎች እውቅና በመስጠት ምስጋና አቅርበዋል።

በስተመጨረሻም፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች የተቀናጀ ጥረት ኢትዮጵያ በጤና፣ በማኅበራዊ ልማት፣ በባህልና በስፖርት ዘርፎች የያዘችውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ግብ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደፈጠረ አንስተዋል።

(በ ሀብታሙ አብርሃም)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

የህፃናት ማቆያዎች ለተቋማት ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሆነ ተገለጸ -------------------- (ዜና ፓርላማ)ነሐሴ 25 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በመንግስት ተቋማት የሚከፈቱ የህ...
31/08/2026

የህፃናት ማቆያዎች ለተቋማት ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሆነ ተገለጸ
--------------------
(ዜና ፓርላማ)ነሐሴ 25 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በመንግስት ተቋማት የሚከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች እናቶች ያለ ስጋት በስራ ገበታቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲሰጡ ከማስቻላቸውም ባለፈ ለተቋማት ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጭቴ ፍላቴ እንደገለጹት የህፃናት ማቆያ ቦታዎች የሰራተኛ መረጋጋትን ለመፍጠርና የተቋማትን ውጤታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፆ እያበረከቱ ነው፡፡

በመንግስት ተቋማት የህጻናት ማቆያ ቦታዎች የተከፈቱበት ዋና ዓላማ ሴት የመንግስት ሰራተኞች የሚኖርባቸውን የቤት ውስጥና የስራ ጫና በመቀነስ በስራቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ሲሉም ወይዘሮ ነጭቴ አስገንዝበዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ለዓራት ዓመታት ያህል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው የቆዩ ስምንት ህፃናት ወደ መደበኛ የቅድመ - መደበኛ ትምህርት (KG) የመሸጋገሪያ ምረቃቸውን በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።

በዚህ ወቅት በተቋሙ የህፃናት ማቆያ ቦታው መከፈቱ እናቶች ልጆቻቸውን በቅርበት ጡት የማጥባት፣ የመንከባከብና የጤና ሁኔታቸውን የመከታተል እድል ከማግኘታቸው ባለፈ የመንግስት የስራ ሰዓት ብክነትን እንደቀነሰውና በስራቸው ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማገዙን አስረድተዋል።

ወ/ሮ ነጭቴ አክለውም፣ ፅ/ቤቱ ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በግንባር ቀደምትነት የጀመረውን ይህን አርአያነት ያለው ተግባር ሌሎች የፌደራልና የክልል ተቋማትም በስፋት እያስፈጸሙት እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ህፃናቱ በማቆያው በሚቆዩበት ጊዜ ስለሚያገኙት ሁለንተናዊ እንክብካቤ ያብራሩት የህፃናት ጤና ባለሙያዋ ሲስተር የየሽወርቅ ስለሺ በበኩላቸው፣ ህፃናት ከ 6 ወር ዕድሜያቸው ጀምሮ እስከ 4 ዓመት በሚቆዩበት ወቅት የንጽህና፣ የምግብና የጤና ሁኔታቸው በየዕለቱ ክትትል እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

ህፃናቱ አእምሯዊና አካላዊ ንቃታቸውን የሚያሳድጉ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችንና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በመደረጉ፣ አሁን ላይ በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ምግባቸውንና ልብሳቸውን በራሳቸው ማስተካከል የሚችሉ ንቁ ልጆች መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ማቆያው የእናቶችን ብቻ ሳይሆን የወላጅ አባቶችንም የስራ ጫና ያቀለለ ተግባራዊ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ልጃቸውን ከ 8 ወሯ ጀምሮ በማቆያው ሲያሳድጉ የቆዩት ወላጅ እናት ወ/ሮ ሶስና አሰፋ በስራ ቦታ ማቆያው የስነ-ልቦናና የቤተሰብ መረጋጋት ፋይዳ በገለጹበት ወቅት ልጄን እዚህ በማቆየቴ የቤት ሰራተኛ ወይም የእንክብካቤ ስጋት ሳይኖረኝ ስራዬን በሰላምና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንድሰራ አስችሎኛል ብለዋል። በስራ መሃል ልጃቸውን በቅርበት ማየትና በደስታ ማሳደግ መቻላቸው ለስራ አፈፃፀማቸውና ለቤተሰባቸው ሰላም ትልቅ አቅም እንደሆናቸውም አክለው ገልጸዋል።

በስራ ቦታዎች የሚከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች የቅንጦት ሳይሆኑ፣ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እና የነገዋን ሀገር የሚረከቡ ጤናማ ህፃናትን ለማፈራት ቁልፍ የልማት መሳሪያዎች መሆናቸውን የምክር ቤቱ ተሞክሮ ያሳያል። በምረቃው ወቅት ለ 8ቱ ህፃናት ወደ መደበኛ ትምህርት ሲገቡ የሚያገለግሏቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ አርአያነት ያለው ይህ ተግባር በሌሎች ተቋማትም በስፋት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላክቷል።

(በሚፍታህ ኪያር)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት አምስት ዓመታት  የፋይናንስ ሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲቶች ህጎችን መሠረት አድርገው መተግበራቸውን ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገለፀ--------------------(...
28/08/2026

ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት አምስት ዓመታት የፋይናንስ ሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲቶች ህጎችን መሠረት አድርገው መተግበራቸውን ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገለፀ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 22 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት አምስት ዓመታት የፋይናንስ ሕጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ህጎችን መሠረት አድርገው መተግበራቸውን ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ቋሚ ኮሚቴው ይህን የገለፀው የአምስት ዓመታት ዓበይት ተግባራት አፈፃፀምን በተመለከተ ከቴሌቪዥን ጣቢያችን ጋር ባደረገው ቆይታ ነው።

የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት አምስት ዓመታት ቆይታው የምክር ቤቱን ተልዕኮ መሠረት በማድረግ ተግባሩን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀው፣ የወጡ ህጎች ተግባራዊ መሆናቸውን እንዲሁም አግባብነት ያላቸው መመሪያ እና ደንቦች መውጣታቸውን በመቆጣጠር ለፌዴራል መስሪያቤቶች የተመደበ በጀት ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት መሠረት አድርጎ ተልዕኮውን ሲወጣ መቆየቱን አብራርተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ፣ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለቋሚ ኮሚቴው የተመሩ ረቂቅ ህጎች ባይኖሩም በሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው የወጡ አዋጆችን ተከትለው ደንቦች እና መመሪያዎች እንዲወጡ ቁጥጥር በማድረግ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው በጀት ህግን ተከትሎ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን በፌደራል ዋና ኦዲተር ተመርምረው የቀረቡ የፋይናንስ ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መሠረት አድርጎ በመመርመር አስፈላጊው እርምት እንዲወሰድ ሲሰራ መቆየቱንም ገልፀዋል።

(በ-ሣራ ዮሐንስ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት እየሰጠ ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ-------------------(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 21፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕ...
27/08/2026

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት እየሰጠ ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 21፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት እየሰጠ ያለው ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት የሪፎርም ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢው ይህን ያሳሰቡት፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና እና የቀጣይ ዓመት እቅድ ዝግጅት በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የምክር ቤት ጽህፈት ቤት አግልግሎት እየተሻሻለ የመጣ መሆኑን የተከበሩ አቶ መለሰ መና ጠቁመው፤ የምክር ቤቱ በሕገ መንግስቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት የጽህፈት ቤቱ ደጋፍ የሚይተካ ሚና እንደበረው እና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ተጨባጭ ውጤት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የጽህፈት ቤቱ የስራ ኃላፊዎችን አስተዋፅኦ የጎላ እንደነበረ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ገልጸው፤ ለሀገር እድገት የተቋማት ግንባታ መሰረት የሚጥል እና አቅም የሚፈጥር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ምክር ቤቱ ሀገራዊ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የተጀመሩ የዲጂታል አስራሮችን ፈጥኖ ወደ ሥራ በማስገባት 2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የተከበሩ አቶ መለሰ መና አመላክተዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ሀጂ ከማል ሃሺ ከምክር ቤቱ የሚሰራጩ መረጃዎች በታቀደ እና በተቀናጀ መልኩ መሆን እንዳለበት እና ለሀገርና ተቋማት ገጽታ ግንባታ መሰረት የሚጥሉ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የተከበሩ አብርሃም በርታ (ዶ /ር) በጽ/ቤቱ በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ዘመኑን ያዋጁ ለሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥሉ በመሆናቸው የሰራተኛውን አቅም በማጠናከር በይበልጥ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ፀሀፊ ተወካይ እና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸኃፊ አቶ ከረዩ ባናታ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና እና የቀጣይ ዓመት እቅድን ዝግጅትን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት በበጅት ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም እና የአገልግሎት አሰጣጡ እየተሻሻለ መምጣቱን አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ አቶ ከረዩ ባናታ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም የምክር ቤቱን አሳራሮች ለማዘመን እና ለማሻሻል ዲጂታል አሰራሮችን ለመከተል በእቅድ ተይዞ እንደሚሰራ እና (IPU) የምክር ቤቱ ስታንዳርድ ጥናት ተጠናቆ ተግባር ላይ ሲውል ብዙ ስራዎችን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ አቶ ከረዩ ባናታ አያይዘው ጠቁመዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የመግስት ተጠሪ ጽህፈት ቤት ም/ዋና ጸኃፊ አቶ አንድነት አድነው በበኩላቸው፤ የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተሻሻለ የመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በተያዘም የሪፎርም ኮሚቴው በምክር ቤቱ እየተሰሩ ያሉ የግንባታ ፕሮጃክቶችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

( በመኩሪያ ፈንታ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

የንግድና ቱሪዝም ዘርፎች ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋፅዖ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ‎--------------------‎(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 20 ፣ 2018 ዓ.ም.፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር...
26/08/2026

የንግድና ቱሪዝም ዘርፎች ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋፅዖ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ
‎--------------------
‎(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 20 ፣ 2018 ዓ.ም.፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ባለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ከኢቲቪ ፓርላማ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የንግድና ቱሪዝም ዘርፎች ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋፅዖ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።

‎የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አሻ ያህያ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በንግድ፣ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ዘርፎች አዳዲስ ለውጦችና እድገቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።

‎ሀገሪቱ ያላትን ሰፊ እምቅ ሀብት በተለያዩ ዘርፎች ለማልማት የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፣በተለይም በንግድና በኤክስፖርት ዘርፍ የተሻለ እድገት መመዝገቡን ገልፀዋል።

‎የቱሪዝም ዘርፍም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከት የሚችል ሰፊ አቅም እንዳለው በመግለጽ፣ የሀገሪቱ የቱሪስት መስህቦች በሚገባ ከለሙና ከተጠቀምንባቸው የኢኮኖሚ ዕድገትን ማፋጠን እንደሚቻል የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አመላክተዋል።

‎የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የግሉን ዘርፍ ማሳደግ፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና ኤክስፖርትን ማሳደግ የሀገሪቱ የዕድገት እቅድ ቁልፍ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ መስፍን በበኩላቸው፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ቋሚ ኮሚቴው በሚከታተላቸው ተቋማት በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውንና የተሻለ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።

‎የቀጣይ ሥራዎች በተገኙ ውጤቶች ላይ በመመስረት በትኩረት መሰራት አለባቸው። ይህም ተቋማቱ ለሀገርና ለህዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል።

‎(በ አገሪቱ ጌቴ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

በሀገራችንና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለ1ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል አደረሣችሁ! አደረሠን!-------------------...
24/08/2026

በሀገራችንና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤
እንኳን ለ1ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል አደረሣችሁ! አደረሠን!
-----------------------
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነብዩ መሐመድ የልደት በዓልን በማስመልከት ለሕዝበ ሙስሊሙ እንኳን አደረሣችሁ ሲል የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋል።

ነብዩ መሐመድ ህይወታቸውን በሙሉ ለሰው ልጆች ምሳሌ ሆነው ያለፉ ነብይ እንደመሆናቸው መጠን ሕዝበ ሙስሊሙ ከነብዩ መሐመድ ህይወት በመማርና የእሳቸውን የእምነት አስተምህሮ በመከተልና ተምሳሌት በማድረግ ለሰው ልጆች ፍቅርና ሠላም እንዲኖር ሊተጉ ይገባል፡፡

ታላቁ ነብዩ መሀመድ በነበራቸው የላቀ ስብዕና እና በአስተምህሯቸው ይመክሯቸው ከነበሩት ዕሴቶች፤ በሰዎች መካከል ፍጹም ፍቅር፣ መቻቻል፣ ሠላም፣ ደግነት፣ መተሳሰብና መረዳዳት እንዲኖር ነው፤ እሳቸውም በፍጹም ፍቅር ሰዎችን ያለመከፋፈል የሚወዱ ነበሩ፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ይህን ታላቅ ስፍራ የሚሰጠውን የመውሊድ በዓል ሲያከብር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቻቻል፣ በመከባበር፣ በመግባባትና በሠላም አብሮ የመኖር እሴቶችን መሠረት በማድረግ ሊሆን ይገባል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ሁለንተናዊ ዕድገትና የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የዜጎች አንድነት፣ መከባበርና በጋራ መቆም ወሳኝ ሚና አላቸው። በመሆኑም ይህ ታላቅ 1ሺህ 501ኛው የመውሊድ በዓል የሚከበርበት ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊና ሁለንተናዊውን ሀገራዊ ምክክር በተሳካ ሁኔታ በአካሄደችበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመሆኑ ለበዓሉ ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል። ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩት የሰላም፣ የዕርቅ፣ የውይይት እና የጋራ መግባባት እሴቶች ለሀገራዊ ውይይቶቻችንና መግባባቶቻችን ጠቃሚ ግብዓቶች ናቸው።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና በመተሳሰብ ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና አንድነት በጋራ ለመቆም ቃል በመግባት መሆን ይኖርበታል። በመሆኑም ምክር ቤቱ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የደስታና የሰላም በዓል እንዲሆንላቸው እየተመኘ፣ ይህ በዓል የሀገራችንን ሰላም ይበልጥ የምናጠናክርበት፣ ለአብሮነትና ለልማት በጋራ የምንቆምበት እንዲሆን ጥሪውን ያስተላልፋል።
በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የመውሊድ በዓል እንዲሆን ምክር ቤቱ ከልብ ይመኛል!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

https://youtu.be/ASXPfrk-wM8
24/08/2026

https://youtu.be/ASXPfrk-wM8

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Address

House Of Peoples' Representatives Of FDRE
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251111241000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when House of Peoples Representatives of FDRE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to House of Peoples Representatives of FDRE:

Shortcuts

Share